Telegram Web Link
👉አልናፈቃችሁም በአሏህ⁉️
👍88
.....እስኪ አትነካኩኝ.....⁉️

👉#እሸት__
--------------------------
ማኛና ሰርገኛ ነጭ ጤፍ ምስሩ፡
ሽንብራና ጓያ ባቄላና አተሩ፡
አረንጓደ ለብሶ ሲታዩት ማማሩ፡
ገጠር ሁሉም አለ ቀፎ ሞልቷል ማሩ፡
----------------------------------
ከዘንጋዳው መሀል ይመረጣል ጥንቅሽ፡
የትውልድ መንደሬ እስኪ ላስተዋውቅሽ፡
ገጠር ነሽ እያለ ማንም እንዳይንቅሽ፡
አዝመራሽን አይቶ ማንም እንዳልቅሽ፡
ሁሌ እሸት እንደሆንሽ ፈጣሪ ያዝልቅሽ፡
ከደግነትሽ ጋር ሰላም ላይ ያፅድቅሽ፡
------------------------------------
ከማሽሎች መሀል ጥንቅሽ ይመረጣል፡
ልጦ ለማላመጥ ሁሉም ይቋምጣል፡
ከገጠሩ ህዝቤ እሸት መች ይታጣል ፡
ባህሉ ነውና ሳትጠይቅ ይሰጣል፡

.....ገጠሬ ነኝ እሽ...

እናቴ ''ባለ አገር'' አባቴ ገበሬ፡
አንሸምትም እኛ ሽሮና በርበሬ፡
ሁሉም ከጓሮው ነው ፀጋ አለው ገጠሬ፡
እኔም ደስ ይለኛል እዚያ መፈጠሬ፡
---------------------------------

ተራራና ሜዳው አልባብ አልባብ ሲሸት፡
ገጠር ደስ ይለኛል ያለ ምንም ውሸት፡
መስከረም ጥቅምትን ይቀጠፋል እሸት፡
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
#በኑረዲን_አል_አረብ
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍83
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማሻአሏህ ተጋበዙ በትዝታ ሰፈር ሆናችሁ
👍87
የሶሪያው ንጉስ

አላሁ አክበር
አላሁ አክበር

ሺዓዎችና ኢኽዋኖች የሚፈሩት ጀግናውና ወጣቱ የሶሪያ መሪ..
ከኺሊፋዎች በኋላ የመጀመሪያዉ የሙስሊም ንጉስ በሆነው በሙዓዊያህ ቢን አቢ ሱፍያን(ረዲየላሂ አንሁ) ስም
በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ መንገድ ተሰይሞለታል።

ይህ ዛሬ በይፋ የተቀየረው መንገድ የቀድሞው ስሙ «የኢራቆች ጎዳና» ሲሆን

አሁን ደግሞ

ወደ ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን ተቀይሯል ይህ እጂግ የሚበረታታ ነው።

አላህ አዲሱ የሶሪያ መሪንም ለዑማዉ የሚጠቅም መሪ ያድርገዉ።አሚን።
👍193
(⓮)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =⓮

«ሶሀቦችን መውደድ»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍25
➥ንግግር እንምረጥ እባካችሁ⁉️

.....ቃላት ሰው ያጠፋል....

በቃላታችን ቀስት ስንቱ እንደተወጋ፡
ስንቱ እንደታመመ ተጋልጦ ለአደጋ፡
ከሰላም ኑሮው ላይ ስንቱ እንደተናጋ፡

አይገባንም እንጂ ብዙ ግፍ ሰርተናል፡
ማስታመም ስንችል ጨቅጭቀን ገድለናል፡
ዛሬም አልተውነውም ግን ምን ይሻለናል⁉️

ምላስ እንደሆነ ከነገር አይቦዝን፡
በምሰማው ሁሉ አለሁ እኔም ሳዝን፡
ሳስብ ሳሰላስል ስሰፍር ስመዝን፡

ችግርን በተስፋ ጎራደን በጋሻ፡
ሀዘንን በምክር ፅናትን በዋሻ፡
ህመምን በክኒን መርዝን በማርከሻ፡

ስመክት ከርሜ ሰበረኝ ንግግር፡
ሀሜት ጆሮን አልፎ በቅፅበት ሽግግር፡
እስከ ነፍስ ይጓዛል ባይኖረውም እግር፡

....አወ...

እግር ባይኖረውም ሁሉን ነገር ያልፋል፡
ደግሞ እንደ ፈንጅ ነው እያደር ይሰፋል፡
ከተቀጣጠለ ሁሉንም ይጠልፋል፡
እንደ ጂረትም ነው ውስጥ ላይ ይጎርፋል፡
እንጠንቀቅ እንጂ ቃላት ሰው ያጠፋል፡

....ኑረዲን አል-ዓረብ....

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍49
«ክፉ ቃል ክፉ ነው»
ኑረዲን አል-ዓረብ
ለቃላታችን እንጠንቀቅ‼️

«ቃላት ሰው ያጠፋል»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍32
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
Photo
የኦሮሚያ ክልል መጂሊስ ስራውስ⁉️
--------------------------
በእምነታችንና በእምነት ቦታወቻችን ከሚደርሰው በደልና ግፍ በላይ እኛ በዘር ቅርቃር ውስጥ ገብተን አማራ ቢሆን ኖሮ ኦሮሚያ ቢሆን ኖሮ እያልን መሸራኮታችን በኢስላም ዘረኝነት የተወገዘ ከመሆኑም በላይ ለጠላቶቻችን ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላቸው አታውቁምን⁉️

.....ዘረኝነት የሚባል ወጥመድ ጠላቶች አዘጋጅተው ሙስሊሙን ከዚህ ወጥመድ ውስጥ ካስገቡት በኋላ ሙስሊሙ በዘረኝነት ልክፍት ተለክፎ መርጦ ባልተፈጠረበት ዘሩ ከሙስሊም ወገኑ ጋር ሲናከስና ሲጠላላ...‼️

እነሱ እንደ ኳስ እየተቀባበሉ አንዴ #በአማራ ሌላ ጊዜ ደግሞ #በኦሮሚያ እያፈራረቁ እቅዳቸውን በሚገባ ይፈፅሙብናል።

ሙስሊሙም ገና የዘረኝነት ወጥመዱ ስላለቀቀው  አማራ ክልል መስጂዱ ሲደፈርና ኢማሜው ሲረሸን ከመስጂዱ መደፈር ከኢማሜው መረ*ሸን ይልቅ ዘሩን አስቀድሞ #ስስልጤ.....#ኦሮሞ...እያለ ያስተባብላል።

ይህን ያስተዋሉት ጠላቶቻችንም ተመቻቸውና ኦሮሚያ ላይም ድንገት ብድግ ብለው መስጂዱን በ➌ ቀን ውስጥ አፍርሱ ምንም አታመጡም አይነት #ትዕዛዝ ይሰጣሉ።

...እውነታቸውን ነው በዘረኝነት ሱስ የተያዘ የእምነቱ መደፈር የማይቆረቁረው ትውልድ ምን ያመጣል⁉️

ባለፉት ጥቂት አመታት መስጅድ ክብሩ ተገፎ በጅምላ የፈረሰበት ክልል ቢኖር #ኦሮሚያ ክልል ዋነኛው ነው።
ከፍተኛ የሙስሊም ቁጥር ባለው በዚህ ክልል መስጂዶችን እንደ ልብ ለማፍረስ ኢምንት ያክል ህዝቡን አላፈሩትም..ለምን⁉️

...የክልሉ መጅሊስ ደግሞ የበለጠ ያሳዝናል። ከጥቂት የተቋሙ አመራሮች ውጭ በተደጋጋሚ ከነሱ በሚሰማው ሽንገላ በመታለል ጠንካራ ተቃውሞ እንኳን እንደ ተቋም ሲያደርግ አይስተዋልም።
....እመኑኝ #ኢስላም አለም ቢዘምትበት አይጠፋም ግን እንደዚህ የምትሽለጠለጡና የምትጉደፈደፉ ሰወች ካላችሁ ነገ አሏህም ፊት ከታሪክም ፊት እንፋረዳችኋለን።

አማራ ክልል በጽንፈኞች ለደረሱ የሙስሊም በደሎች፣ ትግራይ ክልል በአክሱም ተማሪዎች ላይ ለደረሰው እንግልት፣ በጉራጌ ዞን በጉንችሬ በደረሰው የመብት ጥሰት ሁሉ የአካባቢው መጅሊሶች በቻሉት ልክ ጠንክረው ሲታገሉ እንጅ አመራሩ ጋር በመለሳለስ ጉዳዩን ችላ ሲሉ አላስተዋልንም።

ውጤቱ ምንም ይሁን ምን የተቀያየሩ መሪዎች በዚህ ረገድ የሙስሊሙ ህመም ሲጋባባቸው አስተውለናል።

➥የኦሮሚያ መጅሊስ ለሚፈርሱ ቦታዎች ልመና ከሚመስል ተደጋጋሚ ተማጽኖ በዘለለ የክልሉን ሙስሊም መብት ለማስከበር የሄደበት ርቀት ግን #የተልፈሰፈሰ እንጂ ጠንካራ የሚባል አይደለም።

ምን አይነት ሀላፊነት ጫንቃቸው ላይ እንዳለ እንኳን ሳያስተውሉና ሳያስተነትኑት #የዞን_መጂሊስ_አመራሩ ጥቂት ጥረት እንኳን ሳያደርግ ለበላዩ "ከአቅሜ በላይ ነው" የሚል ደብዳቤ ለመጻፍ ሲሮጥና ሲሽቀዳደም ይስተዋላል።

➥የኦሮሚያ ክልል መጅሊስም ቢሆን በተለይ ሸገር ላይ ሲፈርስ ጠብቆ ሌላ ቦታ ትክ ከመቀበል የዘለለ መስጅዱን ላለማስፈረስ ይህ ነው የሚባል ህጋዊ አካሔድ ሲሄድና ሲታገል አይታይም።

ይህ ባለፉት አመታት ያስተዋልነው እውነታ ነው። ይህንን ደካማነት የሚያውቁ በአስተዳደሩ ውስጥ ያሉ መስጅድ ጠሎች እያረፉ እየመጡ ማፍረሳቸውን ቀጥለዋል።

#የኮዬ_ፈጬና #ቱሉዲምቱ አካባቢ ከስፋቱ አንጻር ከፍተኛ የመስጅድ እጥረት ያለበት እንደመሆኑ ተጨማሪ መስጅድ የሚሰጥበት እንጅ ያሉት የሚፈርሱበት ቦታ አልነበረም።

ይህ እየሆነ ያለው የኦሮሚያ ክልል መጂሊስ በሚያሳየው ለዘብተኝነቴና ግደለሽነት ነው።
......ግን ምን ዋጋ አለው፣ እንደፈለጉ ቢያፈርሱ ማን ይጠይቃቸዋል⁉️
ማንስ "ለምን" ብሎ ይታገላቸዋል⁉️

በጣም ያሳፍራል⁉️
እጂግ በጣም ያሳዝናል⁉️

.....ኑረዲን አል_ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍35
በ➌ቀን ውስጥ ይፍረስ የተባለው መስጂድ ይህ ነው

እስኪ ምን ተሰማችሁ
እስከመቼስ ነው በዚህ መልኩ የምንቀጥለው⁉️
👍57
«ለመስጂዳችን ዘብ»

በኦሮሚያ ሁሌ መስጂድን ሲያፈርሱ፡
ከመኖሪያ ቀዬ ሙስሊሞች ሲፈልሱ፡
በጂምላ ስንሞት በኦሮሚያ ክልል፡
ግፍን ስንቋደስ ጠፍቶ የሚያስጠልል፡

...አልበቃቸው ብሎ ያፈረሱት ቦታ፡
ያሁሉ መከራ መስሏቸው ስጦታ፡
አሁንም ድጋሜ ከተዘጋጁልን፡
እስኪ መጂሊሶቹ መግለጫ ያውጡልን⁉️

በአማራ ኢማሜው በመስጂድ ሲረ*ሸን፡
በኢስላም ጥላቻ #ፋኖ ሲረብሸን፡
ውስጣችን ሲታወክ ስቃይ ሲያቀረሸን፡
ግፍ ሞልቶ ፈሶብን እያንገሸገሸን፡
አንድ እንሁን እንጂ ለስንቱ እንሸንሸን⁉️

የሙስሊሞች ብቻ ሲመረጥ ሰፈሩ፡
ዘወትር ከመኖር እየተደፈሩ፡
ምናል ብንሰዋ ቢቀለን አፈሩ፡

ነገ እንዳይጠይቀን ሀያሉ አምላካችን፡
ለመስጂዱ ክብር እንጩህ ሁላችን፡
በታሪክ ገፅ ላይ እንዳንተዛዘብ፡
ሳይፈርስ አለን እንበል ለመስጂዳችን ዘብ፡

.....ኑር....

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍51
ልጆችን ከሳዑድ ወደ ኢትዮ

ከሳዑድ አረቢያ ወደ ኢትዮጲያ ህፃናት ይዞ መግባት ተፈቅዷል።
በሳዑዲ የኢትዮጲያ ኢንባሲ በዛሬው ለት እንዳስተላለፈው ከሆነ የሳዑድ ኢሜግሬሽን ለብዙ ጊዜ አግደውት የነበረውን የህፃናት የጉዞ ክልከላ እንደተነሳና እንደተፈቀደ ገልፀው...ልጆቻቸውን መውሰድ የሚፈልጉ ሰወች ከወዲሁ ቅድመ ሁኔታውን አሟልተው ፕሮሰስ እንድጀምሩ ሲል አብስሯል።

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍74
2025/10/19 18:29:22
Back to Top
HTML Embed Code: