Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
*[ماحكم تارك الصلاة ]*

*🎙لنخبة من العلماء*
*الشيخ محمد بن صالح العثيمين رحمه اللّٰه*•
*الشيخ صالح الفوزان الفوزان حفظه الله*•
*الشيخ صالح اللحيدان رحمه الله*•
*الشيخ عبد الله القصير رحمه الله*•

https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
https://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍44
«ርካሽ አትሁን!»

ብዙ ሲያገኙህ
ብዙ ያወቁህ ይመስላቸው!

ብዙ ሲያውቁህ
ብዙ ይንቁሃል!

ብዙ ሲንቁህ
ዋጋ የሌለህ ያደርጉሃል!

ዋጋ የሌለህ ሲመስላቸው
ይተዉሃል!!

ስለዚህ ብዙ አትገኛቸው

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍100
«➐» «خذ عقيدتك»
አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ኹዝ-አቂደተክ

ክፍል «➐»

👉ስራችንን አሏህ እንድቀበለን መስፈርቱ ምንድን ነው⁉️

🎙አቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
«❽» «خذ عقيدتك»
አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ኹዝ አቂደተክ

👉ክፍል ❽

ሙታንን መጣራት ይችላልን
ሙታኖች ጥሪን ይሰማሉ።
ኢብኑ ተይምያ‼️
ኢብኑል-ቀይም‼️
ኢማሙ ነወውይ⁉️
መልስ ግን አይሰጡም።

🎙አቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍23
መተናል መተናል ቤተሰብ!!

«ያሙኛል አትበል»
----------------

ሰው ልማደኛ ነው፤
ፍርስራሽ ስር ቆሞ ለሽንቁር ያመሀል፡
ሰው ልማደኛ ነው፤
አዝለኸው ብትዞር ለእግሩ ይወቅስሀል፡
ታዲያ ይሔ ፍጡር፤
ምንስ ነገር ቢልህ ለምን ይገርምሀል⁉️

.....ሰውኮ....

ነጥብ ቀዳዳህን ይውላል ሲመትር፡
አያስተውለውም የጉያውን ትርትር፡
ኸይር ለዋለለት ያዘጋጃል ብትር፡
ነፍስያና ስሜት ልሶ የጨረሰው፡
እንደዚህ ነው ገፁ ፀባዩ አንዳንዱ ሰው፡

ጆሮ አይሞላም ስማ ግን ደግሞ አትቀበል፡
በአቋምህ ላይ ፅና ያሙኛል አትበል፡
ከወንጀል ብትገባ ቢሻህ ተጨማልቀህ፡
ሐቅ ላይ ብትፀናም በሱና ላይ ፀድቀህ፡
የስኬትን ህይወት ብትኖርም ባትኖርም፡
ነውርህን ፈላጊ አፉ ፆም አያድርም፡

ብቻ በእቅድ ተጓዝ አንተ ዝም በላቸው፡
ያሉትን ይበሉ እንደፈለጋቸው፡
ከላይ ታች ይበሉ ይሙህ ይመቻቸው፡
የታች ሰፈር ሰዎች ሐሜት ነው ስራቸው፡

ኑር እንደመሻትህ ኑር ከነፍስህ ጋራ፡
ከልቡ ይጠፋል ምላስ የሚፈራ፡
ሐሳብህን ግለፅ በቀን በጠራራ፡
ለሀሜት አትቅለጥ ፅና እንደ ተራራ፡

ውሳኔህን ፈፅም ከአቋም አትዘንበል፡
ውስጥህን አዳምጠው ከውጭ አትቀበል፡
ላንተ ከተስማማህ ያሙኛል አትበል፡

...ኑር ነኝ.....✍️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍88
«➒» «خذ عقيدتك»
አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ኹዝ አቂደተክ

ክፍል =➒

ታላቁ ሽርክ አይነቶች

🎙አቡ-ፋሩቅ
«❿» «خذ عقيدتك»
አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ኹዝ አቂደተክ

ክፍል ❿

በህያዋን መረዳት ይቻላልን⁉️

🎙አቡ-ፋሩቅ
👍20
{➍}الركيزة في العقيدة السلفية
🎙አቡ ፋሩቅ حفظه الله
الركيزة في العقيدة السلفية

👉ክፍል =➍

«የአልለ-ሱናወች መለያ ምልክቶች»

🎙በአቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍14
አትታለል ... አተታላይ ... አትታለሉ ... አንታላል !

ኑሮህን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚታየው የሰዎች ሳቅና መፍለቅለቅ አትለካ ... ከሚዲያው ሳቅ ጀርባ በቤቶቻቸው የማይቋረጥ ጭንቀትና የማይነጥፍ እምባ አለ .... ገንዘብንና ታዋቂነትን ፍለጋ የሚስቁና የሚደንሱ " እንቅልፍ አልባ " አመፀኞች ቁጥር ስፍር የላቸውም ... እናም በነሱ የውሸትና የንግድ መፍለቅለቅ አትታለል !

ትዳራችሁን በየሚዲያ ተፈብርኮ ከሚቀርበው ትዳር ጋር አታናጽፅሩ ... እንከን አልባ እያስመሰሉ ከሚሰብኩለት ትዳር ጀርባ 1000 ሽምግልና አልፏል .... ብዙ ድብደባና ስብራት ታይቷል .. አንዳንዴ 30 ዓመት ዘለቀ እያሉ ታዋቂ የሚባሉ ሰዎች ከሚሰብኩለት ትዳራቸው ጀርባ ከ30 የበዙ ዝሙቶች አሉ !

የኛን ከአንድ በላይ ማግባት ከሚፃረሩ እና ከሚያነውሩ " ባለ ትዳሮች " ጀርባ ተቆጥረው የማይዘለቁ የትዳር ክህደቶችና ብልግናዎች አሉ !

ባለህ ነገር ጌታህን አመስግን ... ትዳርሽ እንከኖች ቢኖሩበትም ታላቅ ፀጋ ላይ እንደሆን ሽ አትርሽ !

ካስተዋልን - እኛ ትልቅ ፀጋ ላይ ነን! እንደኛም የለም !! የአለማት ጌታ አሏህ ምስጋና ይገባዋል !

መጨረሻችንን አሏህ ያሳምረው !

https://www.tg-me.com/msirage4
👍63
★ ሁሌም አስታውስ....

★ ምንም ነውር የሌለበት ጓደኛ የፈለገ ሰው ብቻውን ይኖራል፣
★ ምንም አይነት ችግር የሌለበት ትዳር የፈለገ ላጤ ሆኖ ይኖራል፣
★ ሙሉ የሆነ ዘመድ የፈለገ ሰው ዝምድናውን ቆራጭ ይሆናል።
                          
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍95
«እነሱ እንደዚህ ነበሩ እኛስ⁉️»

     ሐፍስ ቢን ሑመይድ
ለዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ
  "የሆነ ሰው ሰው ሲገል አየሁኝ።
ከዝያም በነፍሴ ከገዳዩ የተሻልኩ እንደሆንኩ ተሰማኝ"
አልኩት‼️

👉#ዐብዱላህ 
"ነፍስህ ላይ መተማመንህ እሱ ከሰራው ወንጀል የከፋ ነው" አለኝ ይላል።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍33
«መጓዝ ይከብዳል»

ሰው ባልሔደበት ሰው ባልመጣበት፡
መኖር ይጨንቃል ሰው በታጣበት፡
ከመናገርም እጂግ ይልቃል፡
ሁሉንም ሀሳብ አይገልፀውም ቃል፡
ሰው በሌለበት መኖር ይጨንቃል፡

ህይወት ጉዞዋ ምንም ቢያታክት፡
ምንም ታግሰን ሁሉን ብንመክት፡
መጥፋት ያስፈራል ያለ ምልክት፡

ከሆነው አንፃር ቃላት ይገዳል፡
አማረ ሲሉት ይወላገዳል፡
ለካ ሰው ሆኖ መጓዝ ይከብዳል‼️

...እህህህህ...ሲደክም⁉️

.....ኑር...

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍42
«አቀብለኝ ወንጭፍ»
-------------------
ና ጥንቅፍ እንብላ ወደ ቆላ ወርደን፡
ና ሰተር እንበል በማማው ተጋርደን፡
ወደ ቆላ እንውረድ ከሰው ተለይተን፡
ሐሜቱ እስኪረሳ አረዳ እስኪበተን፡

ከዚህ እንሰወር፤
ከሽማግሌ ጋር ነገር አትለቃቅም፡
ካሰብከው እስክትደርስ፤
ሁሉን ነገር መቻል መታገስ አታውቅም!?

ጉዳዩ እስኪረሳ፤
ከማሽላው መሀል ገብተን እንደበቅ፡
ደግሞ እናመልጣለን፤
ከእማዬ ቁንጥጫ ከአባታችን ለበቅ፡

ወይ ፍየል ተመልከት ወይ በሮቹን ፍታ፡
ወይ ክላሹን አንግት ተጠባበቅ ሽፍታ፡
ይሄ ነው ጂማሮው የነገህ ከፍታ፡
ሰበህለላ አትሁን ሁሌ ስራ አትፍታ፡

አንገትክን አትድፋ ነገር አታንቀራጭ፡
ከካሜራ በላይ አዕምሮ ነው ቀራጭ፡
ወንድ ሀሜት ፈርቶ አይሆንም ተመራጭ፡

ስሜን እየጠራህ በቃ አታንቀራጨኝ፡
እንደ ወንድ አቋም ያዝ አቦ አታበሳጨኝ⁉️
ማርና ወተቱ ካላደነደነህ፡
ወንድነቱን ልቀቅ የገጠር ልጅ ማነህ‼️

ስም እንዳታጠፋ እንዳታሰድበን፡
ገጠሬ ጀግና ነው ሀያዕ ካልገደበን፡
ከመንገድ ዳር ቆመህ አትክልት አትጨፍጭፍ፡
ወፎቼን ልጠብቅ አቀብለኝ ወንጭፍ፡

...ኑረዲን አል-ዓረብ...✍️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍70
👉ኡስታዝ ምን ሆኖ ነው የጠፋው⁉️

የጠና ነገር ካልገጠመው ደርስ አያቆምም
ከባድ ሁኔታ ውስጥ ካልሆነ ከነ አካቴው አይጠፋም።

ታዲያ ምን ሆኖ ነው⁉️

ሰሞኑን👉ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከሚዲያ የለም እና ምን እንደሆነ አጣርታችሁ አኽባር ንገሩን⁉️

ኡስታዝ የከበደ ነገር ካልገጠመው መረጃ ከመስጠት አይቆጠብም እባካችሁ አሞትም ከሆነ የቻልነውን አድርገን እናሳክመው⁉️
ስንጠፋም እንጠያየቅ⁉️
በህይወት እያለን እንተሳሰብ⁉️
እንረዳዳ እንተጋገዝ⁉️

👉#ሰለፍዮች እባካችሁ ይህን የመተሳሰብና የመጠያየቅ ድክመታችንን እናስተካክል ወላሒ በጣም ያማል።

በአቅራቢያው ያላችሁ ወንድም እህቶች ምን እንደሆነና ምን ላይ እንዳለ አሳውቁን በአሏህ ‼️

ባለህበት አላህ ከክፉ ነገር ይጠብቅህ ህመምህንም አሏህ ያሽርህ ‼️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍219
:
:
አስባችሁታል⁉️
:


እንደ ሰው ክፋት እንደ እኛ መፍጨርጨር፡
እንደ እነሱ በደል ደግሞ እንደ መቀንጨር፡
እንደ ወንጀላችን እንደጣስነው ድንበር፡
አሏህ ባያዝንልን ምን ይውጠን ነበር⁉️
:
:

ህፀፅ እየሰራን በደርዘን በኩንታል፡
አሏህ አዛኝ ባይሆን አስባችሁታል⁉️

በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍79
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍68
«ሳንማር አለቁ!!»

እያጠፉ ማረም እያረሙ ማጥፋት፡
እየሳቁ ማልቀስ ሲደሱ መከፋት፡
ትልቅ ሆኖ ማነስ ጠባብ ሆኖ መስፋት፡
ሲርቁ መጠራት ሲጠጉ መገፋት፡

ወገን በጭካኔ በህፀፅ ሲከበብ፡
የተገላቢጦሽ ሰውነት ሲነበብ፡
አዋቂ ሰው ሲናቅ መሀይም ሲጠበብ፡
አሁን በኛ ዘመን እንድህ ሆኖ ጥበብ፡

ክስተት በተቃርኖ በመፈራረቁ፡
የጎበጠው ሁሉ ባለመታረቁ፡
መልካምነት ጠፍቶ ክፋት በመፍለቁ፡
ላጲሱም እርሳሱም ሳንማር አለቁ፡

.....ኑር...✍️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍50
«⓫» «خذ عقيدتك»
አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
ኹዝ አቂደተክ

ክፍል=⓫

👉መቃብር መዞር ይቻላልን⁉️
👉ጠንቋይና ተንባይን ማመንስ ይቻላልን⁉️

🎙አቡ-ፋሩቅ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍21
አሰራጩት መረጃውን

ምናልባት ቤተሰብም ተጨንቆ መፍትሔ ጠፍቷቸው ይሆናል #ተጣብቀው የተወለዱ መንታ ልጆች ካሉ በቤት ውስጥ ተደብቀው ከሆነ መፍትሔ አለው።
ወደ ሳውዲ አረቢያ በነፃ ህክምና ያገኛሉ አለም አቀፍ መሊክ አብደላ በጎ ፈቃድ ድርጂት አብሽሩ ብሏል።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍120
2025/11/13 17:26:58
Back to Top
HTML Embed Code: