በጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ነዉ ያለዉ
የኬንቼው ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የንግድ ባንክ
አካውንት ➯
1000261754987
ሁላችሁም እኅት ወንድሞች የተጀመረውን ቤተክርስቲያን ከፍጻሜ እናደርስ ዘንድ እናት ቤተክርስቲያን እኛን ልጆቿን ትጠይቃለች።
ለተጨማሪ መረጃ ዲያቆን በሀይሉ በማለት መደውል በተጨማሪም እቃ መግዛት የምትችሉ ለሱ መስጠት ትችላላችሁ
091 070 8770

👍5
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - 🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽 🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ) Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
"ነቢያትን ተመልከቱ"
https://youtu.be/6onvBNTa0gs
"ወንድሞች ሆይ፥ የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ" 【ያዕ 5:10】

❤4👍3
"#ዕለተ_ባርኮ #ወሕርመተ_ተርኪ (Days of Thanksgiving and Prohibition of turkey)
┄–┉┉✽»✧†✧«✽┉┉–┄
ዶ/ር ጽጌ ማርያም በሰይፉ ኢቢኤስ እንግድነታቸው "ኢትዮጵያ የአፍሪካ አክሊል የዐለም መቅደስ ናት ሀብቷ በተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነው" ብለዋል። እውነት ነው ኢትዮጵያውያን የትም ቢሄዱ የኢትዮጵያዊነት መገለጫቸውን ባይሸጡት፣ መልክአ ኢትዮጵያን ባይለውጡ ትውልዱን ይታደጋሉ ዐለምን ለድኅነት ያበቃሉ!
ጉዳይ ፩ #የምስጋና_ቀን ( ዕለተ ባርኮ ⇥ Thanksgiving day)
በወርኃ ሕዳር አራተኛው ሐሙስ የሚታሰብ ምንም እንኳ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ መነሻ እንዳለው ቢታመንም በሀገረ አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በካሪቢያን ደስያት እና በላይቤሪያ ዐለማዊ ብሔራዊ በዓል (secular national holiday) ዕለተ ባርኮ Thanksgiving day በመባል ታስቦ የሚውል ቀን አለ!
በ James W. Baker የተጻፈው "Thanksgiving: The Biography of an American Holiday"
የሚለው መጽሐፍ በታሪክ የመታሰቢያውን የትመጣ ሲነግረን በእ.አ.አ. ከ1536 በፊት «በካቶሊካዊት» ቤተ እምነት በዐመት ውስጥ 95 የሚሆኑ የ«ቤተክርስቲያኗ» በዓላትና 52 ሰንበታት ይከሩ እንደነበር … ከ1536 አንስቶ ግን በተሃድሷውያኑ ጫና በዓላቱን ወደ 27 አውርደዋቸዋል
ኋላ ላይ የተነሱት ከካተሊካዊ ባህል ፕሮቴስታንቱን እናነፃለን የሚሉ ወገኖች (The Puritans) በአላቶችን በሙሉ (ገናና ፋሲካን ሳይቀር) በመሻር ዝክረ ዕለታትን ከሁለት ወገን ይከፍላሉ
ችግር ጉዳትና አደጋ ከላይ የወረደ ቁጣ ተብለው የሚዘከሩባቸው ቀናት «ዕለታተ ፆም» ( Days of Fasting) ሲባሉ ልዩ በረከት ከአምላክ የሚሰጡባቸው ቀናት ዕለታተ ባርኮ (Days of Thanksgiving) ብለዋቸዋል። በ1620ዎቹ እና በ1630ዎቹ ይህን ባህል ይዘው ወደሰሜን አሜሪካ በመጓዝ ከነጆርጅ ዋሺንግተን (አሜሪካን ያገኙ አሳሾች) አንስቶ እስከ 1863 (አብርሃም ሊንከን ዘመን) ድረስ እውቅና ባይሰጠውም ሲዘከር ቆይቷል። በዚያም ዘመን በርእሰ ብሔሩ አዋጅ (presidential proclamation) የሕዳር የመጨረሻው ሐሙስ እንዲከበር ታዟል። ኋላ ግን የአሜሪካን አብዮታዊ ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዞች ከአሜሪካ ለቀው የወጡበትን ቀን (Evacuation Day) ያጣመረ በዓል ሆኖ ከዘመናችን ደርሷል።
የዚህን በዐል የትመጣነት ሳያውቁ መተባበር፣ አብሮ መዘከርን ከእነርሱ መደመር እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?
የሥርዓት መጽሐፍ ይህን ይላል "ወኢይደደልዎ ለክርስቲያናዊ ከመ ይዝክር አስማቲሆሙ ለጣዖታት ወለሰይጣናት #በቃለ_ስባሔ ዘኢመፍትው ⇋↴
በክርስቶስ ክርስቲያናዊ የተባለ ምእመን በማይገባ ምስጋና ቃል የጣዖታትን የሰይጣናት ስም መጥራት (ቅዱስ ዲያብሎስ ስቡሕ አጵሎስ ብሎ ማመስገን) አይገባውም!
ጉዳይ ፪. #የተርኪ_መከልከል (ሕርመተ ተርኪ ⇥ prohibition of turkey)
በቅድሚያ መባልዕት ሀዲስ ኪዳንን ተሻግረው በቤተክርስቲያናችን የተፈቀዱና የተከለከሉ ተብለው የተለዩበት ምክንያትበጥቂቱ እንመልከት ፦
በዘሌዋውያን ፲፩ ላይ ከቁጥር ፲፫ አንስቶ እንደተቀመጠው "ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው አይበሉም የተጸየፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥ ጭላት፥ ጭልፊት በየወገኑ፥ ቁራ ሁሉ በየወገኑ፥ ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥ ጕጕት፥ እርኩም፥ ጋጋኖ፥ የውኀ ዶሮ፥ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥ ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ። የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሔድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።" ይላል።
በምሥጢር አስቀድሞ ክንፍ ገለፈት የሌለውን አትብሉ ብሎ ሃይማኖት የሌለውን ሰው ቀድሞ በረድኤት ዛሬ በልጅነት አልቀበለውም ጸሎቱም ግዱፍ ነው ይለናል። ቃሉ በቁም ከተነገረበት ፍቺ በላቀ ልዩ ምሥጢር ይዞ መብራራቱን መጋቤ ጥበብ መምህር ብርሃኑ አድማስ
☞ ያስተማሩትን https://www.youtube.com/watch?v=Dgvonk351us&app=desktop እና
☞ በጽሑፍ ያጋሩትን https://m.facebook.com/notes/birhanu-admass-anleye/ሰኮናቸው-ያልተሰነጠቀና-የማያመሰኩ-እንስሳት-የዘመናችን-ተሐድሶዎች/694338210580697/ መከታተል በቂ ይሆናል። (Birhanu Admass Anleye)
ከአመክንዮ ዘሐዋርያት በቅዳሴአችን ላይ እንዲህ የሚል የሃይማኖት ምስክርነት ይገኛል
"ንብል እንከ ከመ ኵሉ ሠናይ ፍጥረተ እግዚአብሔር ወአልቦ ግዱፍ … የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ በጎ እንደሆነና የሚጣልም እንደሌለው እንናገራለን"
ይሔን መርኅ በማድረግ የምትመራው ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ዛሬ በሕርመት ለመብልዕነት ስለማትፈቅዳቸው ፍጥረታት የምታስረዳበት የተብራራ ትምህርት በፍትሐ ነገሥቱ አላት!
ፍትሐ ነገሥት ሀያ ሁለት መንፈሳዊ ና ሀያ ዘጠኝ ሥጋዊ ፍትሕ ያለበት የቤተክርስቲያን የሥርዓት መጽሐፍ ነው! «በእንተ ይፈልጥዋ ወበእንተ ይከልኡ ኪያሃ» ሥሩ ተብለው የታዘዙና አትሥሩ ተብለው የተከለከሉ ሕግና ሥርዓት ተቀምጠውበታል! ፍትሕ ሥጋዊ የሚጀምረው በአንቀጽ ፳ወ፫ «በእንተ መብልዕ …ስለ ምግበ ሥጋ» በማተት ነው!
"ወመብልዕሰ በውስተ ሕግ መሲሓዊት አልቦ ውስቴቱ ሕርመት (ዘእንበለ ዘከልኡ ሐዋርያት) … በክርስቶስ ሕግ የሚከለከል መብል የለም (ሐዋርያት ከከለከሉት በቀር) " ይለናል በመጽሐፍ ኩሉ ዘፈጠረ ሰናይ ባለበት ያለምክንያት ርኩስ በፍጥረቱ ተብሎ እርም የሆነ የለም!
በሐዋርያት ሲኖዶስ ① ደምን ታንቆት የሞተውን፣ ② ከአውሬ የተረፈውን(ብላዐ አውሬ) ③ ለጣኦት የተሰዋውን እንዳንበላ ተከልክሏል። ይሕም ፦
✧ ነፍስንም ሥጋንም የሚጎዳ ሕማም በውስጡ ያለ ሆኖ ☞ አእምሮን ወደማጥፋት (ሙስና ሕሊና) ☞ የሥጋን ባሕሪ ስምምነት ወደማናወጽ (አማስኖ ጠባይዕ) ☞ አካልን ወደማጉደል (ሀጒለ አባል ወሙሥና ሥጋ) የሚያደርሱ በመሆኑና
✧ ጣኦትን ከሚያመልኩ ጋር አንድ አድርጎ ስለሚስብ ተከልክሏል።
ከዚህ ውጪ ያሉትን ግን በሁለት መልክ እንድንከለከላቸው ያዘናል!
፩. ለምግብነትና ለመድኃኒትነት የማይጠቅሙ ሆነው ከጎዱን (ዘኢይሤኒ ለሲሳይ ወኢለመድኃኒት) ይኽም እንሰሳትን ብቻ ሳይሆን ጎጂ አትክልትንም ይጨምራል "አኮ እምነ እንሰሳ ባሕቲቱ አላ እምነ በቊላትኒ ካዕበ" ይላል። …
፪. እየተጠራጠረ የሚበላውን ወይም እርሱ በልቶ ሌላውን እንዲጠራጠር የሚያደርገውን (ዘይናፍቅ በመብልዕ ወዘያናፍቅ ቢጾ)
በጥርጣሬ መብላት ማለት " ወኩሉ ይትቄደስ በቃለ እግዚአብሔር ወበጸሎት… ሁሉም በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ይቀደሳል" የተባለውን ከድካመ ሕሊና የተነሳ ባለማመን ቢፈጽሙት በደል ይሆናል "ወኩሉ ዘኢኮነ በሃይማኖት ኃጢኣት ውእቱ …በሃይማኖት ያልተደረገ ሁሉ ኃጢኣት ነው " እንዲል
በልቶ ሌላውን ማጠራጠር
ድካመ ሕሊና ሳይሰለጥንብን በእምነት ብናደርገው እንኳ "ዳሩ ግን ይህ መብታችሁ ለደካሞች ዕንቅፋት እንዳይሆንባቸው ተጠንቀቁ።" (፩ ቆሮ ፰፥፱)ይለናል!

YouTube
የማይበሉ Yemayebelu - በመ/ር ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ (Memeher Dn. Birehanu Admas)
ኦሪት ዘሌዋውያን ፲፩ ÷ ፩
Leviticus 11 ÷ 1
የሐዋርያት ሥራ ፲ ÷ ፲
Acts 10 ÷ 10
ማቴዎስ ወንጌል ፲ ÷ ፲፮
Matthew 10 ÷ 16
ሉቃስ ወንጌል ፳፫ ÷ ፬
Luke 23 ÷ 4
የሐዋርያት ሥራ ፲ ÷ ፲
Acts 10 ÷ 10
ማቴዎስ ወንጌል ፳፫ ÷ ፬
Matthew 23 ÷ 4
መዝሙረ ዳዊት ፲፩ ÷ ፩
Psalms 11 ÷ 1
በደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ…
Leviticus 11 ÷ 1
የሐዋርያት ሥራ ፲ ÷ ፲
Acts 10 ÷ 10
ማቴዎስ ወንጌል ፲ ÷ ፲፮
Matthew 10 ÷ 16
ሉቃስ ወንጌል ፳፫ ÷ ፬
Luke 23 ÷ 4
የሐዋርያት ሥራ ፲ ÷ ፲
Acts 10 ÷ 10
ማቴዎስ ወንጌል ፳፫ ÷ ፬
Matthew 23 ÷ 4
መዝሙረ ዳዊት ፲፩ ÷ ፩
Psalms 11 ÷ 1
በደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ…
👍4👏1
ጽኑእ ቁስል ሲድን ጠባሳን በምልክትነት እንዲተው ነገር ግን እንደማያም እንዲሁ የኦሪቱ የከበደ ሸክም ጽኑእ ሕመም ያለ ተረፈ ደዌ በክርስቶስ የተወገደላት ተዋህዶ ቤታችን የኦሪቱን ጥላ እንደጠባሳ እያየች ውለታውን ሳትዘነጋ የቀደመውን ሸክም ስትዘክር ያለተጠጓትና ያልተከተሏት ሲያሟት ይደመጣሉ!
"ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።" (፩ቆሮ ፱፥፳፪)
turkey (ተርኪ) ለሚለው ቃል አቻ አገርኛ ፍቺ ባይቀመጥለትም (እኔ ባልደርስበትም) የአሜሪካ ዶሮ፣ የቱርክ ዶሮ … የሚሉ አቀራረቦችን በመዛግብተ ቃላት ተጠቁመዋል።
በቡዙኃን ባህል የምስጋና ቀን «ድራር» ላይ የገበታው ፊትአውራሪ ( main course of Thanksgiving dinner) ተርኪ ነው!
ተርኪ ከአእዋፍ ዝርያ (avian species) የሚመደብ
የቤተ አይሁድ የማዕድ ሕግ (Kashrut) ውስጥ ዶርሆ (chickens) , ዳክዬ (ducks), "ዝዬ" ( geese) , and ተርኪ (turkeys) ተብሎ ለመብላት የተፈቀደ በሚል ዝርዝር ውስት ተካቷል። (https://www.jewishvirtuallibrary.org/overview-of-jewish-dietary-laws-and-regulations)
በእኛ ቤተክርስቲያን በኩል ስለሚገኙ ምልከታዎች
በመልአከ ኤዶም ኤፍሬም እሸቴ በኩል ያገኘሁት «በእንተ ተርኪ» በሚል ርእስ የተሰነደ የመልአከ አርያም ቀሲስ ብርሃኑ ጎበናን ጽሑፍ ተመልክቻለሁ
☞ Ephrem Ephrem https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=10155996128938063&id=735343062
☞Berhanu Gobena https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2739713209387068&id=100000452473097
ከተገለጠው ሀሳብ የሚቃረን ምንም ዐይነት የማቀርበው ዝርዝር ባይኖረኝም ስለጽድቅ ብለው ስለሚራቡና ስለሚጠሙ ብፅዕናን የሰጠ ዋጋቸውንም መንግሥተ ሰማይ ያደረገ አባት እያለን በሰው ባሕል (እኛን ፈጽሞ እንደማይመለከተን በማምነው ቀን) እንብላ አንብላ መከራከሪያ ሲሆን መብል ሆድን ያጸናል ሆድ መብልን ይሸከማል ሁለቱንም ግን አምላክ ያጠፋቸዋል መባሉን ላስታውስ ፈለኩ (፩ቆሮ . ፮፥፲፫)
በተጨማሪም "ዘፈተወ ይስተይ…" ዐይነት መፍትሔም ሲጠቆም ባይ በደረጃችን ጉዳዩን ብናይ ሠናይ ነው አልኩ!
#መፍትሔ ፦
የዛሬ ዐመት በብርዱ ወራት በእስካንዲኔቪያን አውራጃ በሀገረ ኖርዌይ አንድ እንግዳ ነገር ዐየሁ ወቅቱ የገና ጾም ነው አብዛኛው የአሳ ዘይት
በተፈጥሮ የአንድ አልያም የሁለት ሠዓት የፀሐይ ብርሃን ብቻ ይለገሳቸዋል። ፀሐይን የሚራበው (sun-starved) ዜጋ ለአጥንት ጉዳት እንዳይዳረግ በሀኪሞቹ የተሰጠውን መፍትሔ ይዞ ወደ አባቶች ይሔዳል፤
«ይህን በሚተካ የቫይታሚን ዲ (vitamin D) ምንጭ የአሳ ዘይት [cod liver oil] ለመጠቀም እንገደዳለን… የዘይቱ መገኛ የዐሣ ጉበት ነውና በአጽዋማት ወር እንደምን እንሁን?»
በወቅቱ ሊቁ ክቡር መጋቤ ምሥጢር አባ ቴዎድሮስ አንድ መፍትሔ አበጁ እኔ ካሕን ነኝ እንዲህ ዐይነቱን የሕርመት ቀኖና በቤተክርስቲያን ውክልና የማቅናት ሥልጣን ያላቸው ሊቃነ ጳጳሳቱ ናቸው ብለው ከሚመለከታቸው አባቶች መክረው ቦታውን ብቻ ያማከለ አባታዊ ብያኔ አስተላልፈዋል።
በዚህ መነሻ የተርኪ ጉዳይ ያልተከለከለ ነገር ግን ያልተፈቀደ ቢሆን በኤጲስ ቆጶሱ ከሚሰጥ ብያኔ ውጪ መከልከልና መፍቀዱ የቀደመውን መንገድ ሳይጠብቁ ሳያስጠብቁም ማለፍ ነው ባይ ነኝ! ኤጲስ ቆጶሱን "ወበውስተ እዴሁ ይደሉ ከመ ይኩን ግብረ ቤተ ክርስቲያን ኵሉ… የቤተ ክርስቲያን ሥራ ሁሉ በጁ ሊሠራ በቃሉ ሊታዘዝ ይገባልና " ይለዋልና።
እኛ ምእመናንም መጽሐፍ "ወይደልወነ ከመ ንኅረይ እመባልዕት ወአልባሳት ዘየአክል ወይሤኒ ⇋↴
ከምግብ ከልብስ ወገን ለቁመት ሥጋ ያህል ምግብ ለከዲነ ዕርቃን ያህል ልብስ መሻት ይገባልና" ይለናልና ለሚያልፍ መብልዕ ከመጨነቅ ለመንግሥቱ ጽድቅ ያትጋን።
~~~> (በቴዎድሮስ በለጠ ☞ ሕዳር ሚካኤል ፳፻፲፩ ዐ.ም.)

www.jewishvirtuallibrary.org
Overview of Jewish Dietary Laws & Regulations
Encyclopedia of Jewish and Israeli history, politics and culture, with biographies, statistics, articles and documents on topics from anti-Semitism to Zionism.
👍13❤2
Forwarded from ጠቢቡ መርጌታ ዘረያቆብ መድሀኒት ቀማሚ
እውነት ነው የምላችሁ አንብብ እና የሰላም እንቅልፍ ተኙው
አስታዋሽ አምላኬ ሆይ
የሥነልቦና ባለሞያ Bini Girmachew እንደፃፈው
በተደነቀ ዝምታ የምትኖር አስታዋሽ ፈጣሪ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ በዝምታህ ውስጥ መልስ አለህና አከብርሃለሁ፡፡
እንደማይሰማ ዝም ብትልም፣ እንደማይሰጥ ብትዘገይም፣ እንደማይገደው ብታልፍም ዓላማ አለህና ተመስገን፡፡ የቀኑን ምልክት በማየት አለባበሴን ባስተካክልም፣ የዘመኑ ምልክት ግን ሳይገባኝ በአንደበቴ ጠፍቻለሁና አድነኝ፡፡ ዓለም ስትንጫጫ ዝም ማለትን አስተምረኝ፡፡
እውነት ስናገር ሰዎች ይከፋቸዋል፣ ሐሰት ስናገር ፍቅርህ ያዝንብኛል፡፡ እባክህ የአንተ ወገንተኛ አድርገኝ፡፡ ያንተ ወገን በሁለት ወገን እንደተሳለው ቃልህ ለማንም አይመችም፡፡
መተማመን በጠፋበትና ቋንቋ በተደባለቀበት ዘመን የልቤና የአንደበቴ ጠባቂ ሁን፡፡ በሰነፎች ዘመን ጠቢብ አድርገኝ፡፡
ውዴ ሆይ፡ የሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ንግግር እንዳያናግረኝ እባክህ ተቆጣጠረኝ፡፡
ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ ከሚሉ ግትሮች ጠብቀኝ፣ እኔም ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ በሚል የሕይወት ጠንቅ ውስጥ እንዳልገባ ያዘኝ፡፡
ሥጋዬን አላምነውምና መንፈስህ ይምራኝ፡፡ የገዛ ፍቅሬ እንጂ ሌሎችን መጥላት ከማንም ጋር እንዳያፋቅረኝ ተጠንቀቅልኝ፡፡ ያምራል ብዬ ከተናገርኩት ይከፋል ብዬ የተውኩት እንደሚሻል አሳየኝ፡፡
ዘላለም የሚጸናው የአሁኑ ሳይሆን ያንተ ሥርዓት መሆኑን ግለጥልኝ፡፡ ለስሜቴ የሚስማማኝን እየመረጥኩ ቃልህን እንዳልታዘዝ እማጸንሃለሁ፡፡
ተስፋህ ተስፋ ያደረኳቸውን ነገሮች ሁሉ ይውረሰው፡፡ ሰዎች እንዲያምኑኝና ፍትሐዊ ነው እንዲሉኝ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፡፡
አንተ ትበቃኛለህና ልቤን በጥላህ አኑረው፡፡ በማስፈልግበት ሰዓት እንዳልተኛ እርዳኝ፡፡ ሰው ሁሉ የመፍራት ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሲፈራ እኔን በዓለት ላይ አቁመኝ፡፡
ሰዎች ሲያዘምሙ ሳይ ነቢይ እንዳልሆን ጠብ ቀኝ፡፡ ካንተም ይልቅ ቸር እንዳልሆንኩ አስረ ዳኝ፡፡ እገሌ በደለ እንጂ እኔ በደልኩ የማይልን አገርና ትውልድ ፈውስ፡፡ የመካሰስ ወራትን በይቅር ነፋስ ለውጥ፡፡
በአገራችን ሁሉም ሊቅ ነውና የሚማር መንፈስን ስጠኝ፡፡ የሰዎች ርእስ ያልሆኑትን የተረሱትን አንተ አስታውስ፡፡
ኃያላን ሲጣሉ እኛ እንዳንደቅ አውጣን፡፡ በደግ ቀን ያልጸለዩት በክፉ ቀን አይረዳምና በጸሎት አትጋኝ፡፡
አስቤ እንድናገር ሊቃውንት ነግረውኛል፡፡ ነገር ግን አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ለሰውዬው የምትናገረውን እንድናገር እርዳኝ፡፡
የጥያቄዎች ሁሉ መልስ «አምላኬ በእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?» የሚለው መሆኑን አብራልኝ፡፡
ጣዕም ባለው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።
የማይሾሙህ ንጉሤ
ከከበሩት በላይ ከብረህ የምትኖር የማይ ሾሙህ ንጉሤ፣ የማያበድሩህ ብልጥግናዬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ ዓመታት ዘመናት ብዙ ወዳጆቼን ሲለውጡ እኔም በብዙዎች ስለወጥ አንተ ግን ያው አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ፡፡
ልብስ የሸፈነውን ጓዳዬን፣ ጥርስ የሸፈነውን ልቤን ላንተ እገልጣለሁ፡፡ ልትረዳኝ አቅምና ፈቃድ ላለህ ላንተ መሸነፌን አወራለሁ፡፡ አንተ እንደ ሰው አልፎ ሂያጅ አይደለህምና እመካብሃለሁ፡፡
ሰው ሁሉ ራሱንና አካባቢውን በሚያ ዳምጥበት ዘመን ቃሌ አይሰማምና እባክህ አንተ ስማኝ፡፡
ፍቅርና መልካምነት የራቀኝ የትዝታ ሰው ሆኛለሁና ዘመኔን እንደ ቀድሞው አድስ፡፡ ሰው በተሰለቻቸበት ዘመን የማይጠገብ ፍቅር ስጠኝ፡፡ ክፉን በክፉ ሳልመልስ በመልካም ማሸነፍን አድለኝ፡፡
በፀፀት የትላንትናውን፣ በንዴት የዛሬን ከመመልከት በእምነት የወደፊቱን እንዳይ እባክህ እርዳኝ፡፡ በማየው ተወስኛለሁና የተስፋ አገሬን አጉላልኝ፡፡
ሰው በሰው ሆኖ ሲጠቃቀም እኔ ግን ካንተ በቀር የምጠራው የለምና ድረስልኝ፡፡ ሰዎችን በፍጹም ልቤ እንድወዳቸው እርዳኝ፡፡ ሰዎችም እኔን በመውደድ እንዳይፈተኑ አግዛቸው፡፡ ቃላት ቆርጣሚ አማርኛ ሰንጣቂ ከመሆን እውነት ቀማሽ አድርገኝ፡፡ ሰዎች ቋንቋን ያዳምጣሉ፣ አንተ ግን አሳቤን ተረዳልኝ፡፡
ሁሉም ወደ ራሱ አሳብ ሲያዘነብል እኔን ግን በአሳብህ ማርከኝ፡፡ ባልንጀርነትና ትዳር ባቢሎን ሲሆን ለእኔ ግን ቋንቋዬ ሁንልኝ፡፡ የሰው አንደበት ያቆስላል፣ የሚያዩት የሚሰሙት አያስደስትምና ለእኔስ ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል፡፡
ንጹሕ ምንጭ እንደሚደፈርስ የብዙ በጎ ሰዎች አእምሮ ደፍርሷልና እባክህ አድነኝ፡፡
ከልብ የሚያመልኩህ ሳይበላሹብህ ውሰዳቸው፡፡ የሃይማኖት ቃላችንን ማንም ሊሰማው ጠልቷልና ደግ ዘመን አምጣልን፡፡ ራሴን በቃልህ እንጂ በደከመው ወንድሜ እንዳልመዝን እርዳኝ፡፡ በሚያስጠጋው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።
በምስጋና ተውበህ
በክብር ደምቀህ፣ በምስጋና ተውበህ፣ በአእላፋት ተከበህ፣ በኪሩቤል ጀርባ ነግሠህ የምትኖር የማትወሰን፣ ለሁሉ ወሰን የሰጠኸው አምላኬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡
ለዚህ ሁሉ ፍጥረተ ዓለም ምክንያቱ አንተ ነህ፣ አንተ ግን ምክንያት ሳትሻ ትኖራለህና አከብርሃለሁ፡፡
እንደ ወደድኸኝ ልወድህ አልችልም፣ እንዴት እንደወደድከኝ እንኳ የፍቅርህን ልክ ማወቅ ተስኖኛልና እባክህ አግዘኝ፡፡
ባምነው መንግሥተ ሰማያት እገባለሁ፣ ብክደው ገሀነመ እሳት እወርዳለሁ ብዬ ሳይሆን ወዶኛል ሞቶልኛል ብዬ እንድከተልህ እርዳኝ፡፡
አቅሜን አላውቅምና በፍቅር አቅሜን አሳውቀኝ፡፡ በመሰበር መማር አይረሳም፣ እኔን ግን በመውደድህ አስተምረኝ፡፡
ሰው ሁሉ ለመከራው አያቅድም፡፡ መከራ ግን በሰው ላይ ያቅዳልና ይሆናል ብዬ መጠበቅንም አስተምረኝ፡፡
የምወዳቸው ያለ ችግር እንዲሆኑ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፣ አይሳካምና፡፡ ለማንም ካንተ በላይ ደግ እንዳልሆንኩ አሳውቀኝ፡፡ የማልፍበትን የኑሮ ገጽ ሁሉ «ይህም ሕይወት ነው» እንድል አሰልጥነኝ፡፡
ፀጥታ ረብሻ ሲሆን አጽናኝ፡፡ ማንም እንዳይደርስብኝ የከለልኩት የፀጥታ ሰዓቴን ለተጨነቁት ማዋልን አድለኝ፡፡
ራስን በማዳመጥ ሳይሆን ሌሎችን በመርዳት ያለውን ደስታ ግለጥልኝ፡፡
የማላደርገውን እንዳልናገር፣ የተናገርኩትን እንድፈጽም፣ ከሁሉ በላይ ተስፋ ሰጪ ሰው እንድሆን እለምንሃለሁ፡፡ ሰውን የሚያህል ፍጡር በማይፈጸም «እሽ» እንደ ዶሮ እንዳላባርር ማስተዋል ስጠኝ፡፡
«አይሆንም» በጊዜው ጥሩ መልስ መሆኑንም ግለጥልኝ፡፡
ጌታዬ ሆይ ምንም ባስቸግርህ ለፍላጎቴ አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡ ከሚያፀፅት ሕሊና አድነኝ፡፡
ሥጋዬ የበላይ ሆኖብኛልና አንተ ግዛኝ፡፡ ላንተ ከመገዛት ውጪ ሌላ አሳብ የለኝም፡፡ ለመታዘዝ ግን ፍላጎት እንጂ አቅም የለኝምና ጸጋህንና የጸጋ ስጦታህን ላክልኝ፡፡
አውቄህ እንዳላወቀህ ከመሆን አድነኝ፡፡ ለዚህ የእንግድነት ኑሮ እንዳልረሳህ ከራሴ ጠብቀኝ፡፡ ምናልባት ነገ ብትመጣ ከነኃጢአቴ እንዳታገኘኝ ነጩን ሸማህን አልብሰኝ፡፡
ወደ ፍጡራን ብጠጋም ጽድቃቸው ለራሳቸውም አልበቃቸውም፣ አንተው በሚተርፈው ጽድቅህ አጽድቀኝ፡፡
በማይታበለው እውነትህ ለዘላለሙ አሜን፡፡
Bini Girmachew ( ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን)
YouTube ሰብስክራይብ ለማድረግ ይሄን ሊንክ
ይጠቀሙ!! 🔔
👉
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
@Bini_Girmachewbot @BiniGirmachew
የነገ ሰው ይበለን

👍22❤21👏1
╔ ✞═ ●═ ◉ ❖ ◉═ ● ═ ✞ ╗
✥ይለብስ አጽርቅተ ወይሴሰይ ፍርፋራተ✥
╚ ✞═ ●═ ◉ ❖ ◉═ ● ═ ✞ ╝
"ዮሐንስ ፍቁሩ ይለብስ አጽርቅተ፣ ወይሴሰይ ፍርፋራተ "
ከሐዋርያት አንዱ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ የወደቀውን ጨርቅ አንሥቶ ሰፍቶ ወሰዶ ከነዳያን ደጅ ይጥለዋል ያን አንሥተው የለበሱት እንደ ሆነ "ይህን ለብሼ ፈጣሪዬን ላሳዝነው ኑሯልን?" ብሎ እንደ ገና ለዓይን የሚከፋውን ለአፍንጫ የሚከረፋውን አንሥቶ ሰፍቶ ወስዶ ከነዳያን ደጅ ይጥለዋል "ይህን ማን አምጥቶ ጣለብን" ብለው አንሥተው የጣሉት ከራሳቸው ያራቁት እንደሆነ ደስ እያለው ያን ይለብስ ነበር!

👍23❤11👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - 🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽 🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ) Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
❤3

ቅዱስ ድርጣድስ ንጉሠ አርማንያ
○።።።።።።༒ ♚ ༒።።።።።።○
መጻሕፍቶቻችን የድርጣድስን ማንነት ሲገልጡት ዕብነ አዕቅፎ (የመሰናክል ድንጋይ) ፣ ከሀዲ፣ ርኩስ ፣ አረማዊ… ይሉታል የቀደመ ግብሩን ይዘው፤ ይሁንና በተቀሩት ጽባሐውያን (other Orientals) ዘንድ ለብዙዎች አስተማሪ የሆነ የኋላ ታሪኩም ጭምር ጎልቶ ይነገራል በቅድስናውም ጭምር ይዘከራል።
ይህም በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ውስጥ ልክ እንደ ጲላጦስ ማለት ነው። የጰንጤናዊ ጲላጦስን ቅዱስና ሰማዕት ሆኖ በክብር ማለፍ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
በቅዱስ ኤጲፋንዮስ የተጠቀሰውና በግእዝ በቁብጥና በልሳነ ዐረቢ ቅጂው እንደተገኘ አጥኚዎች የሚገልጡት በውስጡ ላሃ ድንግል ‘ማርያም’ና የጲላጦስ ነገረ ሰማዕትነት (LAMENT OF THE VIRGIN & MARTYRDOM OF PILATE) የተካተተበት የገማልያል ድርሳን እንደሚተርከው መስፍኑ ጲላጦስ ከክርስቶስ የስቅላት ፍርድ እጁን ቢያናጻም ሔሮድስ ግን እንዲገደል እንደፈረደ ጲላጦስም ኋላ ሰማዕት ሆኖ በቅድስና ማለፉ ተጽፏል። (በዚሁም ላይ የባለቤቱና የሁለቱ ልጆቹም ተጋድሎና ክብር አብሮ ይነገራል)
በሱርስት ተጽፎ የሚገኘው የ፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅጂ በ‘ገድለ’ ጲላጦስ (Acts of Pilate ) እንደተመሰከረው ጲላጦስ ስለ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት አይሁድን በመቃወምና በጢባርዮስ ቄሳር ፊት ምስክርነት በመስጠት ጭምር በሰማዕትነት ማለፉ ተጽፎ እናገኛለን።
በእኛም ዘንድ "ማኅበረ መላእክት ወሰብእ" የተባለው መርገፈ ስንክሳር (#ዐርኬ) በበዐተ ክረምት ሰኔ ፳፭ መታሰቢያ በቅድስና የደመቁትን ሰማዕቱ ጲላጦስን እና ባለቤቱ #አብሮቅላን ( ክላውዲያ ፕሩስኩላ በተለምዶ ቬሮኒካ የምትባል) እያመሰገነ እንዲህ ይዘክራቸዋል።
ሰላም ለጲላጦስ ዘተኀፅበ እዴሁ ።
እምደመ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ንጹሕ ለሊሁ
ለአብሮቅላ ሰላም ብእሲተ ዚአሁ ።
ዘለአከት እንዘ ትብል ኢታሕስም ላዕሌሁ ።
እስመ ውእቱ ጻድቅ ወኄር ብእሲሁ።
(ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም ራሱን ንጹሕ ለማድረግ እጁን ለታጠበ ለጲላጦስ ሰላም እላለሁ።
እውነተኛና ቸር ሰው ነውና በላዩ ላይ ምንም መጥፎ ነገር አታድርግበት ብላ መልእክት ለላከችበት ለባለቤቱ አብሮቅላም ሰላም እላለሁ)
እንደ ሰማዕቱ #ቅዱስ_ጲላጦስ የአርመን ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጠባቂ ቅዱስ በመሆን ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ፣ ከሐዋርያቱ ቅዱስ በርተሎሜዎስና ቅዱስ ታዴዎስ ፣ ከቅድስት አርሴማ ቀጥሎ የሚጠቀሰው ቅዱስ ድርጣድስ ሣልሳዊ ንጉሠ አርማንያ 【Saint King Tiridates III of Armenia】ነው።
መጽሐፈ ስንክሳራችንም በሁለት ወራት (መስከረምና ታኅሳስ)፣ በ፬ የተለያዩ ቀናት (መስከረም ፲፱፣ መስከረም ፳፱ ፣ ታኅሳስ ፮ እና ታኅሳስ ፲፭) ፣ ከሁለት ታላላቅ ቅዱሳን (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያና ቅድስት አርሴማ ሰማዒት) ጋር እያገናኘ ስለንጉሡ የሚነግረን ድንቅ ታሪክ አለ።
፩】 መስከረም ፲፱ ፦ ታላቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ ከአዘቅት (ጉድጓድ) በወጣበት መታሰቢያ ቀን።
የድርጣድስን ከሀዲና ለጣኦት የሚያጥን እንደነበረ ቅዱሱን አባት (ጎርጎርዮስን) እንዳስጨነቀው በእሳት አቃጥሎ ከአዘቅት እንደወረወረውና ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ሌሎች ቅዱሳት ደናግልን አስገድሎ ሥጋቸውን በተራራ ላይ በማስጣሉ የሰይጣን መጫወቻ እንደሆነ አርአያውም "ከመ ሐራውያ" የበረሓ ዐሣማ ወደ መሆን እንደተለወጠ ከእርሱ ውጪ የቤተመንግሥቱም ሰዎች በታላቅ ኀዘንና ጭንቀት እንዲኖሩ ጸላዔ ሰናያት እንደተጫናቸው ተነግሯል።
የንጉሡም እኅት ባየችው ራእይ ጎርጎርዮስን ከተጣለበት ጉድጓድ አውጥታው እርሱ የቅዱሳት ደናግሉን ሥጋ ገንዞ በመልካም ቦታ ካኖረ በኋላ " ወእምዝ ፈወሶሙ ለንጉሥ ወለኩሎሙ ሰብአ ቤቱ ⇨ ከዚህም በኋላ ንጉሡንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም ፈወሳቸው (he healed the king
forthwith and all those who were in his house)" ይላል።
፪】መስከረም ፳፱ ፦ ቅድስት አርሴማ እመምኔቷ አጋታና ሌሎች ደናግላን በሰማዕትነት ያረፉበት ቀን።
፸፭ ወንዶችና ፴፱ ሴቶች ከእነርሱ (ቅድስት አርሴማና ቅድስት አጋታ) ጋር ከሀገረ ሮሜ ከዲዮቅልጥያኖስ ፊት ሸሽተው ወደ አርማንያ እንደተሸሸጉ፤ ያቺም ግዛት “ሀገረ መንግሥቱ ለድርጣድስ” (የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት) እንደነበረች ይነግረናል። ንጉሥ ድርጣድስ ቅድስት አርሴማን ከድንግልናዋ ሊያረክሳት መታገሉን፤ ነገር ግን "እንዘ ጽኑእ ፈድፋደ በውስተ ጸብእ፡ ተሞዓ በነዓስ ወለት ⇨ በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ሆኖ ሳለ በታናሽ ሴት ብላቴና ተሸነፈ (for he was well known in battle, exceedingly strong valiant warrior but vanquished by the young Virgin girl)" ቢያፍር እርሷንና የቀሩ ደናግላን ሴቶችን ከእመምኔት አጋታ ጋር አንገታቸውን በሰይፍ አስቀላቸው፤ አብረዋቸው የመጡ ወንዶቹንም ጭምር አስገድሎ ሥጋቸው በተራራ ላይ የተጣለ ሆኖ ቀረ። ይህን ካደረገ በኋላ ንጉሡ ድርጣድስን አጋንንት እንዳደሩበት መልኩም እንደ ሐራውያ (የበረሓ ዕርያ) ተለውጦ እንደተሰቃየ ይነግረናል።
በፍጻሜውም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደ እርሱ መጥቶ "ወጸለየ ላእሌሁ ወሐይወ ወበእንተዝ አምነ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት ⇨ ጸለየለትና አዳነው ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ (prayed over him, and he was healed of
his pain immediately, and he believed in Christ) " የሚል ታሪክ ተጽፏል።
፫】ታኅሳስ ፮ ፦ የቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤትና ከ፳፯ቱ ደናግላን ሰማዕታት ጋር ፍልሰተ ሥጋዋ የተከናወነበት ቀን።
ንጉሥ ድርጣድስ ሥጋዊ በሆነ ምድራዊና ጊዜአዊ ክብር አብራው እንድትኖር ሲሸነግላት እምቢኝ ብትለው ወደ ጎን ወስደው ልብሷን ገፍፈው አንገቷን በሠይፍ እንዲቆርጡ የደናግሉም አንገት እንዲቆረጥ በማዘዙ በዚህ መንገድ በሰማዕትነት ማለፋቸው ተነግሯል። ስለእርሱ ፍጻሜ (የኋላ ታሪክ) ግን የሚያስረዳ ሐተታ አልተካተተም።
፬】 ታኅሳስ ፲፭ ፦ ሰማዕት ዘእንበለ ክዕወተ ደም (ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ) የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍቱ ቀን።
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ የንጉሡ ድርጣድስን ትዕዛዝ በመተላለፍ ለጣኦት አልሰዋም በማለቱ ወደ ደረቅና ጥልቅ ጉድጓድ ተጥሎ ለ፲፭ ዓመታት ያኽል እንደኖረና ፤ ንጉሡም ቅድስት አርሴማንና ሌሎቹንም ደናግላን አስገድሎ የሚያዝንና የሚተክዝ ይልቁንም የቅድስት አርሴማ ውበቷ እየታወሰው የሚጸጸት ሆኖ መኖሩ ተጽፎ እናነባለን።
የሠመረ ፍጻሜውን በሚመለከት ቀጣዩን ተጨማሪ ታሪክም ስንክሳሩ ያክልልናል ፦
ያን ለመርሳት በፈረስ ተቀምጦ ወደ ዱር ለአደን ሲወጣ አጋንንት አድሮበት ራሱንና ሌሎችንም የሚነክስ ሆነ በእርሱ በደል ምክንያት አጋንንት በሌሎቹም የቤተመንግሥት ሰዎች ላይ አድሮ ያሰቃያቸው ጀመረ።

👍7
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - 🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽 🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ) Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
የንጉሡ እኅት ባየቸው ራዕይ መሠረት ለድኅነታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስን አስፈለገች፤ ምግቡን ሁል ጊዜ በምታመጣለት አሮጊት ምክንያት ለ፲፭ በጉድጓድ የኖረውን ጎርጎርዮስን አውጥተው የሰማዕታቱን ሥጋ በከበረ ሥፍራ አኑሮ ድርጣድስ ወዳለበት ዱር ሔደ። እንዲህም አለው "ትትመየጥኑ እምግብርከ እኩይ ወተአመንሁ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት ⇨ ከክፉ ሥራህ ትመለሳለህ? ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህ? " ብሎ ጠየቀው "ወአመረ በርእሱ ከመ እወ ዘይብል ⇨ አዎ እንደሚል በራሱ አመለከተ (made a sign of consent with his head) " እንዳይታበይ በእግሩ ላይ የእርያ ጥፍር በምልክትነት አስቀርቶ ፈወሰው።
ሕዝቡንም ሰብስቦ ለ፰ ቀናት እንዲጾሙ አዘዛቸውና ሥርዓት እያስተማራቸው ኖሩ። ካህን ስላልነበር ሊያጠምቃቸው ባይችል የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ጎርጎርዮስን የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመውት ሕዝቡን አጥምቆ የእመቤታችንን መቅደስ አሳንጾ በሃይማኖት እንዲጸኑ አስተምሯቸው በሰላምና በፍቅር አርፏል።
ስለ ንጉሡ ዜና መዋዕል በሚያትቱ ድርሳናት ከንጉሥ ድርጣድስ ታሪክ ጋር ተያይዘው የሚጠቀሱ ሌሎች ሰፊና አስተማሪ ታሪክ ያላቸው በአርሜንያ ሐዋርያዊቷ እምነት (የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን) ውስጥ የሚወሱ ቅዱሳን አሉ። ከእነዚህም
🍁 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ
🍁 ቅድስት አርሴማ ሰማዒት
🍁 ራሱ ቅዱስ ድርጣድስ
🍁 ቅድስት አጋታ እመምኔት
🍁 የቅዱስ ድርጣድስ እኅት
🍁 የቅዱስ ድርጣድስ ባለቤት (ሚስት)
🍁 ቅዱስ ጎርጎርዮስን በጉድጓድ ለ፲፭ ዓመት የመገበች በእርግና ያለች እናት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በተለይም ደግሞ በሌሎች ሀገራት ሦስቱ ቅዱሳን ቤተሰቦች ንጉሥ ድርጣድስ ሣልሳዊ ፣ ባለቤቱ(አሽኸን) እና እኅቱ (ኹስሮቪዱት) አንድነት ሰኔ ፳፫ ቀን በዓመታዊ ክብረ በዓል ይዘከራሉ። 【Tiridates III with his wife Ashkhen and sister Khosrovidukht are Saints in the Armenian Apostolic Church. Their feast day is usually around June 30.】
በእኛው ሀገር ታሪክ ለከሣቴ ብርሃን ቅዱስ ፍሬምናጦስ ያለን ቦታ በአርመን ሐዋርያዊቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ለጎርጎርዮስ የሚሰጥ ሆኖ እናገኘዋለን። ሁለቱም በሁለቱ ጽባሐውያት አብያተክርስቲያናት ዘንድ ሁለቱም (ፍሬምናጦስና ጎርጎርዮስ) የሀገራቱ ቅዱሳን ቀዳምያን ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን ነገሥታቱን ጭምር ያሳመኑና ያጠመቁ ሆነው ተመሳሳይ ታሪክ ሲጋሩ እናያለን።
ከዚህ አልፎ በከወኗቸር ተመሳሳይ ተግባራትም ቅዱስ ድርጣድስ ሣልሳዊ ንጉሠ አርማንያም በነገሥታቱ ኢዛናና ሳይዛና (ቅዱሳኑ አብርሃ ወአጽብሃ) አንጻር የሚታይ ነው።
ንጉሥ ድርጣድስ ሣልሳዊ በክርስትናው ታሪክ በዓለም ደረጃ በቀዳሚነት የሚወሳባቸውን ተከታዮቹን ታላላቅ ተግባራት አከናውኖ አልፏል።
☞ በ፴፻፩ ዓ.ም. ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን በመደንገግ ክርስትናን በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንድ ሀገር የመንግሥት ሃይማኖት በማድረግ ውሳኔን ያስተላለፈ ቀዳሚው ንጉሥ ነው። (In 301, Tiridates proclaimed Christianity as the state religion of Armenia, making the Armenian kingdom the first state to embrace Christianity officially.) የሚደንቀው ዛሬም ከ፱ ሚሊየን በላይ ምእመናን ተከታዮች (> 9,000,000) ያላት የአርመን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሀገሩ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆና በሕገ መንግስቱ ጭምር የላቀ ሥፍራና እውቅና የተሰጣት የዜጎች ብሔራዊ ሃይማኖት (National church of the Armenian people) ተብላ የምትጠቀስ ባለውለታ እናት ናት።
☞ በምድራችን ላይ ቀዳሚ ካቴድራል እንደሆነ የሚነገርለትን ሕንጻ በማሳነጽ ለክርስትናው በዓለም መስፋፋት ከቤተመንግሥት በመሪነት በመደገፍ ከነቤተሰቡ የላቀ ድርሻ ያበረከተው ይኸው ንጉሥ ቅዱስ ድርጣድስ ሣልሳዊ ነው። (They participated in the construction of the Etchmiadzin Cathedral (often considered the oldest cathedral in the world) , Saint Gayane Church, Saint Hripsime Church and the Shoghakat Church.)
የታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ድርጣድስ በረከቱ በሁላችን ላይ ይደር።
✍ በቴዎድሮስ በለጠ መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፬ ዓ·መ· ተጻፈ

👍19
Forwarded from Tere
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነፃነትና የአንድነት ትዕምርት እንጂ የድህነትና የጉስቁልና ምክንያት አይደለችም! - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best And Reliable News Source In Ethiopia
https://www.ethiopianreporter.com/114103/

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነፃነትና የአንድነት ትዕምርት እንጂ የድህነትና የጉስቁልና ምክንያት አይደለችም! - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best And Reliable…
በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)
👍3