ሀለዉ ዝየ ይቀውሙ እለ ኢይጥእምዋ ለሞት
. በዚህ ከቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አሉ
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥
ይኽን ቃል የትህትና አባት ከሆነውና የራሱን ክብር ከመግለጥ ከተቆጠበው ቅዱስ ዮሐንስ በቀር ቀሪዎቹ የከበሩ ወንጌላውያን በክታባቸው አኑረውልናል።
ቅዱስ ማቴዎስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።” 【ማቴ. ፲፮፥፳፰】
ቅዱስ ማርቆስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው።” 【ማር. ፱፥፩】
ቅዱስ ሉቃስ
“እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከሚቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።” 【ሉቃ. ፱፥፳፯ 】
ቅዱስ ዮሐንስ በምድር ላይ የነበረውን የዘመኑን ፍፃሜ በሁለት የታሪክ ዘውጎች የሚተርኩ መዛግብትና ሊቃውንት አሉ።
① አንዳንዶች ሞቷል በሥጋና ነፍስ መለያየት በሚመጣ ሞት ዐረፍተ ዘመን ገቷቸው ነፍሳቸው በገነት እስከ ትንሳኤ ዘጉባኤ ከምትጠበቅ ጻድቃን ተደምሯል ይላሉ
② ሌሎች ደግሞ ‘የለም’ ቅዱስ ዮሐንስ እንደነ ኤልያስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነቀ በመሆኑ አርጓል ተሠውሯል ይላሉ።
አርፏል ለማለት እንደ ስንክሳር ያሉ መጻሕፍት ድርሳነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ከውጪ መዛግብት የተገኙ ቀደምት ምስክሮች በአስረጂነት ይቀርባሉ።
«ወበዛቲ ዕለት ዐዕረፈ …» ስንክሳር
«እስመ መብዝኅተ አዕፅምቲሆሙ ለሐዋርያት ኢነአምር አይቴ ውእቱ ወዘያሌቡሰ ላዕለ ዝንቱ ከመ መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ ወቶማስ እሙራን ወክሡታን እሙንቱ» የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ፳፮ ንባብ ይዘው ሞቷል ተቀብሯል ይላሉ።
አለመሞቱን ለመሞገት «ዐዕረፈ» ፣ «እሙር መቃብሩ» … ያለውን ለማስታረቅ ብዙ አስረጂ የሚያቀርቡ ሊቃውንት እንዲህ ያለ በመጻሕፍት የታሪክ ክፍተት የዘይቤ አለመስማማት ሲገኝ ሁለት መፍትሔ እንዲወሰድ ይመክራሉ።
፩ኛ) ቅድሚያ ለአብያተ ጉባኤ ትርጓሜ የወንበር ትምህርቶች ቦታ መስጠት ብሉያት ሐዲሳት ሊቃውንትና መነኮሳት የምንላቸውን ፬ቱን ትርጓሜ መጻሕፍት ሌሎች የዜማ ቤት የቅዱስ ያሬድ ገጸ በረከቶች እና በቅኔ ቤት የሚነገሩ ታሪኮች ከየቤተ ጉባኤ መምህራን ቀለማት ጋር ማሳተት
፪ኛ) የዘይቤና የታሪክ ክፍተቶችን በምሥጢር አስታርቆ ማስማማት
ለምሳሌ አንድ ታሪክ ቅድሚያ ቦታ ይሰጣቸው ብለን በጠቀስናቸው መጻሕፍት ላይ ቢገኝና እንደአሁኑ ዓይነት ከስንክሳሩ ታሪክ ጋር የተስማማ ባይመስል ሊቃውንት ይኽን ይላሉ
«ስንክሳር ምን ቁም ነገር ነው? ነገር እንደ ጉባኤ ቤቱ መጻሕፍት ነው እንጂ! የለም ይህስ ስንክሳርን መንቀፍ እንደ ሃይማኖተ አበው ያሉ ደገኛ መጻሕፍትን መንቀፍ ነው ምክንያቱም መላሻቸው አንድ ነው ብሎ ማስታረቅ ይገባል እንጂ!» ስለዚህ ያ በዚህ ምክንያት ይህ ደግሞ በዚህ ምክንያት ትክክል ነው ብሎ መጽሐፍ በመጽሐፍና በተጠያቂ ሊቅ ይዳኛል።
✧ በቅድሚያ ሐሳቦችን በአስረጂ ወደመሞገት እንለፍ
ሀ】ከወንጌል የተገኘ ምስክርነት ፩
ተከታዩን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል ልብ ብለን እናንብብ
"ጴጥሮስም ዘወር ብሎ ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ እርሱም ደግሞ በእራት ጊዜ በደረቱ ተጠግቶ፦ ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው? ያለው ነበረ። ጴጥሮስም ይህን አይቶ ኢየሱስን፦ ጌታ ሆይ፥ ይህስ እንዴት ይሆናል? አለው። ኢየሱስም፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ፥ ምን አግዶህ? አንተ ተከተለኝ አለው። ስለዚህ፦ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚለው ይህ ነገር ወደ ወንድሞች ወጣ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? አለው እንጂ አይሞትም አላለውም"
【የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩ ከቁጥር ፳ እስከ ፳፫ 】
ከዚህ ክፍል "እመኬ ፈቀድኩ የሀሉ እስከ ሶበ እመጽእ ሚላዕሌከ⇨ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ" የሚለውን ሲተረጉም አልሞተም አንድም ሞቷል የሚል መልስ እንደሚከተለው አብራርቶ ያኖርልናል
«እኔ ከወደድኩ እስክመጣ ቢኖር ምን አግዶህ አለው እንጂ አትሞትም አላለም። ዮሐንስ ሞቷልን አልሞተም ቢሉ አልሞተም። ይህ እንዳይሆን ሊቁ «መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ እሙራን ወክሡታን እሙንቱ» ይላል ብሎ ሞቷል። ይህም ሊታወቅ መላእክት መቃብሩን ቆፍረዋል ከመቃብሩ ገብቶ ሲጸልይ ደቀ መዝሙሩን ፋጊርን (አብሮኮሮስን?) የኤፌሶንን ሰዎች በተማራችሁት ትምህርት ጸንታችሁ ኑሩ ብለህ ንገራቸው ብሎ ላከው ነግሮ ቢመለስ መቃብሩ የለፋ መስክ ሁኖ አጽፉን መቋሚያውን መነሣንሡን ከዳሩ አግኝቶታል።»
መደረቢያው በትሩና ጭራው መገኘቱ መቃብር ሳትይዘው ለመውጣቱ በአስረጂነት ይቀርባል። በንባቡም ጌታው እስኪመጣ ድረስ እንዲኖር ወዷል ለሞቷል ባይ "ቢኖር ምን አግዶህ?» የሚል መልስ በባለቤቱ መሠጠቱን ማስተዋል ይገባል። ተሰውሯል የሚሉቱም ቢሆኑ አይሞትም ሳይሆን አልሞተም ባዮች መሆናቸውን መረዳት ይገባል።
ለ) ሁለተኛው ከላይ በመነሻነት የተቀመጡ የሦስቱን ወንጌላውያን መልእክት ስናነብ በመጽሐፍ ቤት የሐዲሳቱ ሊቃውንት ደብረ ታቦር አልፎ በተናገረበት አውድ ሲፈቱ ትርጓሜውን ለዮሐንስ ሰጥተው «የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች» የተባለው እርሱን የሚወክል እንደሆነ ነግረዋል
አንዳንዶች ብሎ ማብዛቱ መጽሐፍ ስም ካልጠራ ማብዛት ልማዱ ነውና
ለምሳሌ ፦ በተአምኖ አመ ነገርዎ ለኖኅ (የነገረው አንድ መልአክ ሆኖ ሳለ) ፣ ብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ዘነገሩኪ (ያበሠረው አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ሆኖ ሳለ)
በሌላ መልኩ በሁሉ ወንጌላውያን ተጠቅሶ በእርሱ አለመጻፉ ራሱን የሚመለከት ቢሆን ነው። ክብሬ ይገለጥልኝ መወደዴ ይነገርልኝ ብሎ ጉዳዩ ባለበት መነገሩን ሳያኖርልን የቀረው ስለትህትና እንደሚሆን ይታመናል።
ሐ) ደብረታቦርን ካነሳን እግረ መንገድ ቅዱሱ አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ምሥጢረ ታቦርን ደጋግሞ ከአማናዊት የሐዲስ ኪዳን መርጡል ጋር እያዛመደ አስተምሮበታል። በሥፍራው የተገኘውን አልያስን አንስቶ ወደብሔረ ሕያዋን እንዴት እንደተነጠቀ ሲነግረን «ወከበቶሙ እግዚአብሔር ውስተ ምድር ኅብእት እንተ ተሠወረት በጥበበ ዚኣሁ ወአልቦ ሥልጣነ ሞት» ይላል።
ታዲያ መሰሉን አብነት ይዘው መምህራን በቦታው የተገኘውን ኤልያስ ከዮሐንስ እንድናነፃፅር ያመለክቱናል። አምላካችን ክርስቶስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ጴጥሮስ በመስቀል ተሰቅለው ቢያልፉ ፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴና የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ ዕረፍተ ሰላም ይኽን ዓለም ተሰናብተዋል፤ ታላቁ ነቢይ ኤልያስና ተወዳጁ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተጠርተዋልና… በፍጻሜ መገናኛቸው እንደሚገናኙ ሊያሳይ አወዳጅቶ አገናኛቸው ተገናኛቸውም ይላሉ።

St. John the Evangelist Orthodox Church
Our Patron Saint - St. John the Evangelist Orthodox Church
The Holy, Glorious All-laudable Apostle and Evangelist, Virgin, and Beloved Friend of Christ, John the Theologian was the son of Zebedee and Salome, a daughter of St Joseph the Betrothed. He was called by our Lord Jesus Christ to be one of His Apostles at…
መ) ከዜማ ቤቱ ደግሞ ዮሐንስን በብሔረ ሕያዋን አየሁት የሚለን የኘቅዱስ ያሬድ ነው። በድጓው ደጋግሞ ምስክርነቱን ሠጥቶናል
«ይኔጽር ዓየራተ
ይነግር ኅቡዓተ
እንዘ ይጽሐፍ በእደዊሑ ዘወንጌል ቃላተ
በቅናተ እግዚኡ ሐቌሁ ቀነተ
ዮሐንስ ድንግል ዘኢጥዕመ ሞተ »
【በድጓ በግእዝ አርያሙ ክፍል ለጥር ፬ቱ ቁመት መነሻ እንዲሆን የጻፈልን ነው። ብራና ገጽ ፻፺፩】
በንጽሕና በድንግልና የኖረው ዮሐንስ ሞትን አልቀመሰም ይልና በሌላም ሥፍራ ከሞት ተለይቶ እንደመላእክቱ በሕይወት አለ ሲል ዳግመኛ ምስክርነቱን እንዲህ እያለ ያጸናዋል «በንጽሕ ከመ መላእክት ተሠርገወ ወእመዊት ከማሆሙ ሐይወ»
ሠ) በመልኩ ክፍልና በገድለ ሐዋርያት ማጠቃለያ የመሰወሩ ምስክርነት ተቀምጦ እናገኛለን
« ሰላም ለልብስከ ወለአሣእኒከ ደርገ፤
ተዝካረ ሕይወትከ ያዑቅ ለአብሮኮሮስ ዘተኃድገ፤
ዮሐንስ ዘኮንከ ምስለ መላእክት ዘውገ፤
ምሉዓ ወድግዱገ ዘሰላምከ ፈለገ፤
በውሣጤ ከርሥየ ኢይኩን ንቱገ፡፡ »
【የመኖርህን ነገር ያስረዳ ዘንድ ለተተወ ፤ ለልብስህ ከጫማህ ጋር ክብር ይገባል፤ ከመላእክት ጋር ወዳጅ የሆንክ ዮሐንስ ሆይ! ሞልቶ የተትረፈረፈ የፍቅር አንድነትህ ወንዝ በሆዴ ውስጥ የጎደለ አይሁን /ይሙላ/።】
ረ) የሊቃውንት ቅኔ ለጊዜው በዝክረ ሊቃውንት ከተዘገቡት ሁለቱን ልጠቁም
« ወልደ ነጐድጓድ ተሰደ እንዘ የኀድግ ሀገረ፤
እምኅበ አጥፍአ ሞተ ሰብእ ሦረ፤
ገራህቱ መቅበርት አምጣነ አብቈለት ሣዕረ»
«ዘማ መቅበርት ለወልደ ነጎድጓድ ትቤሎ፤
እመ ትጸልአኒ አንተ ዘያፈቅረኒ ሀሎ»
ሰ) ከውጭ የተገኙ ቀደምት ምንጮች
በውጭ ሀገራት ቀደምት ድርሳናትና ሊቃውንትም ዘንድ ቢሆን ከላይ ያነሳነውን ጭብጥ የሚደግፍ ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
https://www.stjohnaz.org/about-us/our-patron-saint/#:~:text=He%20bade%20them%20prepare%20for,disobedient%2C%20they%20fulfilled%20his%20bidding.
በሌላ ሥፍራ የተገኘው ደግሞ ይህን ይላል ቅዱስ ዮሐንስ የሚነጠቅበት ሠዓት እንደደረሰ ሲያውቅ በመስቀል ቅርጽ የተሰናዳ መቃብር እንዲያዘጋጁለት አርድእቱን አዟል እነርሱም በበዛ እንባ መምህራቸውን እየሳሙ ካለመታዘዝ እንዳይቆጠርባቸው ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ወደ መቃብሩ ሥፍራ አኑረውት ሄደዋል። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ( ቅዱስ አብሮኮሮስ) ወደቦታው ተመልሶ ቢመጣ መቃብሩን ቢከፍተው ባዶ ሆኖ አግኝቶታል።
«He bade them prepare for him a cross-shaped grave, in which he lay, telling his disciples that they should cover him over with the soil. The disciples tearfully kissed their beloved teacher, but not wanting to be disobedient, they fulfilled his bidding. They covered the face of the saint with a cloth and filled in the grave. Learning of this, other disciples of Saint John came to the place of his burial. #When_they_opened_the_grave, they found it empty.»
በአብሮኮሮስ ስለተሠጠው ምስክርነት (testimony of St. Prochorus) ደግሞ ተከታዩት አስረጂ በሊንኩ ታግዘው ቢያዩ የበከጠ ሐሳባችንን ያግዛል።
https://www.johnsanidopoulos.com/2009/09/repose-of-st-john-theologian-according.html?m=1
✧ ለማስማማት በሚነሳው የማስታረቂያ ሐሳብ
በኤፌሶን/ ቱርክ የመቃብሩ ሥፍራ ይህ ነው እየተባለ ዛሬም ለጎብኚዎች ይታያል።
ይሁንና ግን ☞ገራህቱ መቅበርት አምጣነ አብቈለት ሣዕረ ፣
☞ልብሱ ለዮሐንስ ወአሣእኑ ዘተኃድገ ለአብሮኮሮስ ከመ ያዑቅ ሕይወቱ ፣
☞ When they opened the grave, they found it empty ከሚሉቱ ሳይስማማ ሞቷል ለሚሉቱ ድጋፍ መስሎ ቀርቧል። በመላእክት ቢሎ በደቀመዛሙርቱ መቃብሩ መዘጋጀቱ እውነት ቢሆንም ሥጋው ከዚያ መታጣቱና የአብሮኮሮስ ምስክርነት ተሰውሯል ወደሚለው ያደርሰናል።
የስንክሳሩን አገላለጥ በሚመለከት ደግሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጥቀዋል ብላ ቤ/ክርስቲያን የምትናገርላቸውን ቅዱሳንን ዐዕረፈ ብሎ ማስቀመጥ በአያሌው የተለመደ ነው። ዐረፈ የሚለው በአገባቡ ሞትን ብቻ አይገልጥም ከዚህ ዐለም ድካም መለየትን ካለንበት ዓለመ መሬት (ምድር) በሕይወት ወደ ብሔረ ብፁዓን አልያም ብሔረ ሕያዋን መሻገር ዕረፍት ተብሎ ይነገራል
የሌሎቹን አበው ወደብሔረ ሕያዋን መሔድ ዕረፍት ይለዋል
ለአብነት ግንቦት ፲፩ ስለ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር «በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው ኢትዮጵያዊው ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ» ይላል።
እንደመውጫ ቅዱስ ዳዊት “ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?” ይላል【መዝ ፹፱ ፥፵፰ 】ከሰው ወገን ሕያው ሆኖ ለዘለዓለም ነዋሪ ሞትንም ሳያይ በምድር ላይ ቀሪ የሆነ ማንም የለም። የሐዋርያው ክብርና ቅድስናም ከመሞቱ አልያም ወደ ብሔረ ሕያዋን ከመነጠቁ ጋር በቀጥታ የሚያያዝበት ልኬት የለውም። ባለመሞቱ የሚከብርበት በመሞቱ የሚቀርበት መንገድ ስለሌለ ክርስቶስ አይሞትም አላለም እስክመጣ ቢኖር… አለ እንጂ።
ሰው ሕያዊት ነፍሱበ በሞት ከተለየችው እንደፈሰሰ ውኃ ነው
ፈሶ የታፈሰ ውኃ 【ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ】
የቅዱሱ መጽሐፍ ብሂል እንዲህ ይላል "ዘእምከመ ተክዕወ ማይ ውስተ ምድር ኢይትገባእ" እኛም እንጂ ይህን ይዘን «የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም» እንል የለ!?
【፪ኛ ሳሙ፲፬፥፲፬ 】
ዮሐንስ ግን ሞቶ ተቀበረ ሲሉት ተነስቶ የተነጠቀ ነውና የታፈሰ ውኃ ነውና "ማይ ዘገብኣ እምድኅረ ተክዕወ" አልነው።
ሞተ የተባለ በሰዎች ኅሊና የተቀበረውን ማንነታችን ወደልዕልናው በቸርነቱ ይንጠቅልን
ሎቱ ስብሐት ለዘበስብሐተ አቡሁ ይሴባሕ፤ ወሎቱ ቅድሳት
ለዘበቅድሳተ መንፈ ሱይትቄደስ 🙏
በቴዎድሮስ በለጠ ጥር ፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ከደብረ ነጎድጓድ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Gwrw5N6DhSGtkzJqWWYwogjSJc9eyKA8fzp21g7zPCexn89qRvApZNRbfypLLyTpl&id=100001155652281&mibextid=Nif5oz

"ወቀዊሞ ማዕከለ ሕያዋን ወሙታን ከተረ መዓተ"
【መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፰ ቁጥር ፳፫】
°✞°°°°°°°°°°°°°°°✥°°°°°°°°°°°°°°°°†°(#ነገረ_ከተራ)
«አሁንስ አበዛችሁት!» ይላሉ ዳታንና አቤሮን እንዲሁም ሐሳባቸውን የገዙ ቆሬና ልጆቹ【ዘኁ. ፲፮፥፫】 የዛሬዎቹን ‘ሁላችን የሀዲስ ኪዳን ካህናት ነን’ ባዮቹን መስለውና በሙሴ ፊት በመቆም
‘አሮንን ብቻ ማን ካህን አደረገው እኛስ ካህን ለመሆን ምን ያንሰናል?’ እያሉ
ጨምረው እንዲህ ይላሉ «ማኅበሩ ሁላቸውም እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸው» ወይ መመሳሰል እንዴት ይደንቃል! ራሳችሁን ቅዱሳን ቅዱሳን እያላችሁ የምትጠራሩና የምትንጠራሩ ደቂቀ ዳታን ውሉደ አቤሮን ኧረ አድቡ። በእግዚአብሔር ምርጫ ላይ አፍ የሚከፍቱትን መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች እኮ!
ዛሬ በውሥጥ በውጪ የቸገረ ነገር የሆነው እንዲህ ዐይነቱ ግብረ ዕቡያን ነው።
⇄ በውሥጥ «አሁንስ እጅግ አበዛችሁት!» እያሉ ከመንበረ ፓትርያርክ ውጪ <መንበረ ሃሮ ዘኦሮሚያ> እና <መንበረ አክሱም ዘትግራይ> እያሉ ራሳቸውን በየሰፈራቸው የቀባቡና የተቀባቡ በሥልጣነ መለኮት ላይ የተሳለቁ የጥምቀት ማግሥት ጉዶች አየን።
⇆ በውጭ ክርስቲያን ነን የሚሉ ደፍረው ራሳቸውን ቅዱስ እያሉ የጠሩ ባለክህነት ለመሆንስ ማን ከልክሎን ብለው በዘፈቀደ የሚሿሿሙ!
ውጤቱ ምን ነበር?
ሙሴ ለቆሬ ልጆች «እጅግ ያበዛችሁትስ እናንተ ናችሁ» 【ዘኁ ፲፮፥፯】እኛ አልከለከልናችሁ ተፈቀደልን ካላችሁ በሉ ከእግዚአብሔር ጠይቃችሁ አግኙት አላቸው ፤ እነ ሙሴ እነ አሮነን ተሰበሰቡ በጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር አመለከቱ ከዚያ ጠሯቸው « አንመጣም! በእኛ ላይ ራስህን አለቃ ታደርጋለህ?" አሉ 【ዘኁ ፲፮፥፲፪/፲፫】
አወይ መመሳሰላችን እናንተዬ። ዛሬም አስኬማውን ከማጀት እንደተገኘ የቤታቸው ድስት አጥልቀው በየጎሳቸው የሚሮጡ ሲጠሩ እምቢኝ ብለው በየጓዳው የሚቀላውጡ አቤሮናውያን አየን።
ብቻ ተክህነናል ያሉቱ መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው 250ዎቹን አጣኝ ነን ባዮች ደቂቀ ቆሬና 14,700 ተከታዮቻቸውን መቅሰፍት እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታቸዋለች።
ያን ጊዜ ካህኑ አሮን ወደቀሩት ሕያዋን መቅሰፍት እሳቱ እዳይሻገር ከሙታኑ መንደር እንዲቀር በመካከል ቆሞ ያጥን ጀመር ያን ጊዜ #ከተራ_ሆነ። ‘ወበማዕከሎሙ ቀዊሞ ከተረ መዓተ’ ይለዋል።
“በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።” 【ዘኁ ፲፮፥፵፰】
ጠቢቡ ሰሎሞን ላለፈው የካህኑ አሮንን ለሚመጣው የሊቀ ካህናቱ የክርሰቶስን አይቶ ነገሩን እንዲህ እያለ በጥበብ መጽሐፍ ያስተምርበታል።
"ወቀዊሞ ማዕከለ ሕያዋን ወሙታን ከተረ መዓተ
አኮ በኃይለ ሥጋ ወኢበግብረ ንዋየ ሐቅል አላ በቃለ ዚአከ በዘአዘከረ ሎቱ መሐላ አበው ወኪዳኖሙ ☞ በሥጋዊ ኃይልና ለጦርነት በሚሆን መሣርያ አይደለም በራስህ ቃል ለቅዱሳን አበው የማለውን መሐላ የገባላቸውን ቃልኪዳን አስቦ በሞታንና በሕያዋን መካከል ቆሞ መዓቱን ከተረ/አቆመ " 【ጥበ. ፲፰፥፳፫】
የቀደመው አሮን በሙታኑና በሕያዋኑ መካከል ቆሞ "ተዘከር አብርሃምሃ ወይስሐቅሃ ወያዕቆብሃ ዘመሐልከ በርእስከ ☞ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በራስህ የማልከውን መሐላ አስብ" እያለ መዓቱን ከለከለ መቅሰፍቱን አቆመ። ከተራ ይለዋል እንዲህ ያለውን የመዓቱን መቆም የምሕረቱን መምጣት!
ቀዳማዊና ደኃራዊ ፊተኛውና ኋላኛው ዘልዓለማዊው የሐዲሱ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ "የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል" ተብሎ በበረኛው በዮሐንስ መጥምቅ የተመሰከረለት የነፍሳችን እረኛ በጥምቀቱ በኦሪታውያኑ ምውታንና በሀዲስ ኪዳኑ ሕያዋን መካከል ቆሞ በቁጣው እሳት በአዳም ዘር ላይ የነደደውን መርገማችንን ደምስሶ መዓቱን በምሕረት መልሶ ባርነቱን አቆመልን። ይህ #በጥምቀቱ_የተገኘ_ከተራ ነው።
① የበጉ እናት የሊቀ ካህናቱ ወላዲት እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለዚህ ከተራ መዓቱን አርቆ ምሕረቱን ልኮ ድኅነቱ ስለተሠጠበት ምሥጢር ይህን ትሰብክልናለች
“እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ”
【ሉቃስ ፩፥፸፪-፸፫】
② ይህን ከተራ ከድግል እመቤታችን ቀጥላ የሰበከችው አንቀጽ የተባለች ዮርዳኖስ ናት፤ ራሷ ቆማና ሸሽታ ከተራውን በተግባር እየመሰከረች
“አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ምን ሆናችኋል?” 【መዝ ፻፲፬፥፭】
③ በጥምቀቱ የተፈጸመልንን የነገረ ከተራውን ምስክርነት ዐጻዌ ኆኅት፣ ጺያሔ ፍኖት የተባለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሦስተኛ ጊዜ አጽንቶታል “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ (የሚከትር) የእግዚአብሔር በግ።”
【ዮሐ ፩፥፳፱】
ከተራ የሚለው ቃል በቁሙ ከመነሻው ከተረ ብሎ ዘጋ አቆመ አገደ ከለከለ ማለት ነው በቀረበ አውድ ደግሞ ከበበ ዐጠረ ዙሪያውን ያዘ ማለትም ይሆናል በተከበበ ገንዳ በታጠረ ሥፍራ ጥምቀቱን ከከተራ አንስተን ማክበራችን ለዚሁ ነው።
ከወንጌሉ ክፍል ለማጠቃለያ የሚሆነንን አንድ ምንባብ እናንሳና ነገረ ከተራችንን እንቋጭ
"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና"
የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ከቁጥር ፩―፲
በበሩ የማይገቡ «ቅዱሳን ነን ካህናት ነን» ባዮች ብዙ ወንበዴዎች አሉ። እነዚህ መዓት የማይከተርላቸው እሳተ ሲዖል የሚበላቸው የገሃነም አፍ የሚውጣቸው ናቸው። ሊቃውንቱ በሩን ወደእርሱ መግባትን ያገኘንባት እረኛችን ክርስቶስ እኛን ያገኘባት የምሥጢራቱ መግቢያ ቅድስት ጥምቀት ናት ይሉናል።
☞ ኖላዊ ኄር ዘይቤ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ (‹‹ቸር ጠባቂ›› ያለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።)
☞ ወአንቀጽኒ ፈለገ ዮርዳኖስ ውእቱ (‹‹በርም›› የዮርዳኖስ ወንዝ(ጥምቀት) ነው።)
☞ ወዐጻዊሰ ዮሐንስ መጥምቅ ውእቱ (‹‹በረኛውም›› ዮሐንስ መጥምቅ ነው፡፡)
☞ ወዐጸድ መንግሥተ ሰማያት ይእቲ ( ‹‹ስፍራም›› መንግሥተ ሰማያት ናት፡፡ )
አበው ሲተርቱ «ባጤ ሞት የተከተረ በስለት የተመተረ አንድ ነው» ይላሉ። ለእኛ የሕይወታችን ዐጤ የነፍሳችን ንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ከሥፍራችን እንዳንታጣ ከቤቱ እንዳንወጣ በሞት ሳይሆን በሕይወት እንዲከትረን ከዘልዓለማዊ ዐጸድ ከሰማይ ቤቱ እንዳንጎድልና በፍርዱ ሠይፍ እንዳንመተር ከሥላሴ ልጅነታችን ከተዋህዶ ሃይማኖታችን አያናውጸን።
✍️ በቴዎድሮስ በለጠ ከተራ ፳፻፲፮ ዓ.ም. ከደቡብ ሱዳን ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን

ውእቱሰ ከመ መርዓዊ ዘይወጽእ እምጽርሑ
#አርሱም_ከእልፍኙ_እንደሚወጣ_ሙሽራ_ነው
°°°°°°°°°°[መዝሙር ፲፰(፲፱)፥ ፭ ]°°°°°°°°
ቅዱስ ዳዊት ነገሩን የሚያነሳው "ወውስተ ፀሐይ ሴመ ጽላሎቶ ☞ በፀሐይ ክበብ ውሥጥ ጸዳሉን አደረገ (በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ)" በማለት ነው።
መልሶም ያ ፀሓይ ከጫጉላ የወጣ ሙሽራን ይመስላል [ውእቱሰ ከመ መርዓዊ ዘይወጽእ እምጽርሑ] በማለት ፀሐዩን በሙሽራ እየመሰለ በማሕጸነ ድንግል የተደረገውን ድንቅ ምሥጢረ ሥጋዌና ነገረ ተዋህዶ ወደእኛ እያቀረበ የበተስፋ ይተነብያ አራቅቆ ይተነትናል።
መተርጉማኑ ምሳሌስ ከተመሰለለት ነገር ቢያንስ እንጂ እንደምን ይበልጥ ብለው (ምሳሌ ዘየሐጽጽ ባለው) መምሰልስ ሙሽራው ነው ፀሐይን የሚመስለው እንጂ እንዴት ፀሐይ ሙሽራን ይመስላል ይላል ? ብለው ወደዘመኑ ተመልሰው ራሱን ዳዊትን ይጠይቁታል! ይመልስላቸዋል እንዲህ ብለው ይታረቁታል «መመሳሰል የጋራ ነው ብሎ እንዲህ አለ» ፤ ከዚህ አለፍ ብለው ደግሞ ሙሽራው ፀሐይን የፈጠረ መርዓዊ ሰማያዊ ክርስቶስ ሆኖ ፀሐይም ራሱ ፀሐየ ጽድቅ አማኑኤል ብለው አንዱን በአንዱ እያወዳጁ ምሥጢሩን በነገረ ምሳሌ ያስማሙታል።
ቅዱሱ ነቢይ የትንቢቱ ማረፊያ የሚያደርገው በፀሐይነቱ ውሳጣዊ ዓይናችን ብሩህ ያደረገልንንና የሕሊናችንን ጨለማ አርቆ ከእርሱ በሚገኝ እውቀት ያከበረንን እውነተኛ ብርሃን ቅዱሳኑን በጸጋ ብርሃናት የሚያሰኛቸውን አምላካችን ክርስቶስን ነው እንደሙሽራ ከጫጉላ ቤቱ ከሰርግ አዳራሹ ከድንግል እናቱ የወጣ ነውና ።
#ክርስቶስ_ፀሐይ
°°°°°°🌞°°°°°°
እርሱ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ ምሥራቅና ጽባህ ከተባለች እናቱ ድንግል ሲወጣ ከቆጥ ተሰቅሎ ከማገር ተንጠልጥሎ ያለ ሁሉ እንደሚገለጥ በእርሱም ፊት አንዳች የማይሠወር ፀሐይ [አልቦ ዘይትኀባእ እምላኅቡ] የተባለ፤
እርሱ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በዙፋኑ ከተቀመጠ ንጉሥ አንስቶ በአደባባይ እስከወደቀ ጽኑስ ሁሉ ሊያየው የሚመኝ የሚረባ የሚጠቅም በመንገዱም ለመሮጥ ደስ የሚሰኝ አርበኛ ፀሐይ [ይትፌሳሕ ከመ ይርባሕ ዘይሜርድ ፎኖቶ] የተባለ፤
እርሱ ፀሐየ ዘጽድቅ ክርስቶስ ከባህሪው በሚገኘው ብርሃን የምድርን ጨለማ ያራቀ በጽድቁ ኃጢኣትን በእውቀቱ ድንቁርናን በንጽሕናው ርኩስን ያስወገደ ፀሐይ [ንጹሕ ወይሜይጣ ለነፍስ] የተባለ፤
የከበረች ቤተክርስቲያንን ለራሱ ሙሽሪት ያደረገና እንደሰርግ ቤት (ጫጉላ) የእናቱ ድንግል ማርያምን ማሕጸን ንጽሕት አዳራሽ አድርጎ ሥጋችንን ነስቶ የተዋሐደን የማይጠልቅ ፀሐይ የተባለው ሙሽራው ክርስቶስ በቅዱሳኑ ላይ አድሮባቸው የሚኖርና የዓለም ብርሃን ያደረጋቸው
☀️ #ጊዮርጊስ_ጸሐይ☀️
ፀሐይን የሚገልጥ ፀሐይ ጊዮርጊስ ፀሐየ ልዳ
ፀሐይም ቁምነገር ሁኖ ቅዱሳንን በዚህ መመሰላችን የሚነደው መብዛቱ ያሳዝናል፤ እንኳን በምግባር በሃይማኖት የተገለጠ ቅድስና ብቻውን የሰውነት ተፈጥሮ ከፀሐይ የላቀ ነበር። መጽሐፍ እንዲህ ይላል
"ከፀሐይ የሚነጻ ምን አለ? እርሱስ እንኳ ያልፋል፤ እንዲህ መሆን ሳለ ደማዊና ስጋዊ (ሰው) ክፉ ነገር ያስባል" 【ሲራ ፲፯፥፴፩】
ፀሐይ ይደንቃችኋል? ቅድስናን የባህሪ ገንዘቡ ያደረገ የበጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ምንጭ የተለዩ ፣ የከበሩ ፣ የነጹና የጸኑ ቅዱሳኑን መርጦ በፀጋው ቅድስና ከፍ የሚያደርግ አምላካችን ክርስቶስ ፦ በኑሯቸው እርሱን የመሰሉት እርሱ በእነርሱ ሕይት ቢገለጥ የተገለና አድሮባቸው ቢኖር ቅዱሳንን ክብራቸው ከፀሓይ እጥፍ ድርብ (Resplendently) የሚያበራ እንደሆነ በወንጌል ነግሮናል!
“በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ።” 【ማቴ ፲፫፥፵፫】
ሊያውም በሃይማኖታቸው ጽናትና በምግባራቸው ተጋድሎ የጽድቃቸው መገለጫ የሆነው ብርሃን ጉድለት ሳይኖርበት የሚጨምር እንደሆነ ጠቢቡ ሰሎሞን ይመሰክራል
“የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።” 【ምሳ ፬፥፲፰】
በልዳ ምሥራቅነነት ለክርስትናው አርበኝነት ሲወጣና ሲያበራ የታየው ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው ፀሐይ ነው!
🌟 #ጊዮርጊስ_ኮከብ 🌟
ወደ ኮከብ የሚመራ ኮከብ ጊዮርጊስ ኮከበ ፋርስ
መክብበ ሰማዕታት ኮከበ ክብር ወመስተጋድል ቅዱሱ መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ ጨለማ በነገሠበት ሥቃይና መከራ በሠለጠነበት ምድራችን በሃይማኖቱ ጽናት በተጋድሎውም ትጋት በላይኛው ሰማይ በከበረች ነፍሱ እንደ ኮከብ ብሩህ ነው። "ወለነፍሰ ጻድቃንሰ ከመ ከዋክብት ብሩሃት በመልዕልተ ሰማያት" እንዲል【፩መቃ ፴፮፥፵】
በተለይም ደግሞ በዛሬዋ ኢራን የቀድሞዋ ፋርስ (persia) ለብዙዎች ከስሑታን ፍኖት መመለስና በእውነተኛው ሃይማኖት መጽናት አብነት ሆኖ በማለፉ ኮከበ ፋርስ ተብሏል።
“ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።” ይላልና【ዳንኤል ፲፪፥፫】
ክርስቶስ ያደመቃቸው ከዋክብት ከእርሱ የተገኙ የእርሱ ስለሆኑ መርተው ወደ እርሱ ያደርሳሉ፤ በዚኽች ጥንት ምሥራቃዊት (ጽባሓዊቷ) ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በኩል ያየነው ይህ ፍጡነ ረድኤት የተባለው ኮከብ እንደ ሰብአ ሰገል ፈጥኖ እየመራ ከቅድስናው አዳራሽ እያስገባን ለአምላካችን እንድንገዛለት ያደርገናል።
"ርኢነ ኮከበ ዚአሁ በምሥራቅ ወመጻእነ ከመ ንስግድ ሎቱ ☞ የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ ዐይተን ልንሰግድለት መጥተናል" 【ማቴ. ፪፥፪】
ደብረ ይድራስ ጽርሐ መርዓሁ ለጊዮርጊስ
#ጊዮርጊስ_የክርስቶስ_ሙሽራ #እልፍኙ_የይድራስ_ተራራ
°°°🏔°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°⛰️°°°
#ይድራስ የሚለው ቃል ምድረ በዳ ማለት እንደሆነ የገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሐፊ የእንቆራው ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ (Saint Theodotus of Ancyra) ይነግረናል።
☞ ወአዲ አዘዘ ይንሥኡ እምድር ከመ ይጹሩ ሐመደ ሥጋሁ ለቅዱስ ወይሰድዎ በከበሮ ወያዕርግዎ ኀበ #ደብር_ልዑል_ዘስሙ_ይድራስ ዘውእቱ መካነ በድው ብሂል ወይዘርዉ በነፋስ መልዕልተ ደብር ከመ ኢይርከብዎ ክርስቲያን ሐመደ ሥጋሁ ወወዓልትሂ ዘረዉ ሐመደ ሥጋሁ ውስተ ደብር ወተመይጡ
ዳግመኛም የቅዱሱን የሥጋውን አመድ አፍሰው በመውሰድ በቀፎ አድርገው ትርጓሜው #ምድረ_በዳ የሆነ ስሙ ይድራስ ተብሎ ወደ ሚጠራ ታላቅ ተራራ ላይ ክርስቲያኖች የሥጋውን አመድ እዳያገኙት በነፋስ እንዲያዘሩት አዘዘ፤ ጭፍሮቹም የሥጋውን አመድ በተራራ ላይ በትነው ተመለሱ።
የተራራውን ትክክለኛ መጠሪያ ስም በሚመለከት በገላትያ ላለችው እንቆራ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ብፁዕ ቴዎዶጦስ [The blessed Abba Theodotus, Bishop of Ancyra in Galatija] #የእውነት_ፀሐይ #የንጋት_ኮከብ (The sun of the truth☀️, the star of the morning🌟) እያለ ጠርቶ ያከብረውና በዱድያኖስ በኩል ከደረሰበት ጸዋትወ መከራ አንዱ ሥጋውን አቃጥለው አመድ አድርገው ከፍ ወዳለ ተራራ ይዘውት እንደወጡና በዚያም እንደበተኑት አመልክቶ የተራራውንም ስም #ደብረ_አሱርዮን ብሎ አስቀምጧል።
Then Dadianus made them take his ashes up to a high mountain called #Asurion, and they scattered them on the mountain to the winds.

ለበለጠ መረጃ ተከታዮቹን የውጪ ምንጮች ከገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለተጨማሪ ማስረጃ ያገናዝቡ ( በአስተያየት መስጫው በተቀመጠው አስፈንጣሪ ማውረድ ይችላሉ)
✧ THE ENCOMIUM OE BISHOP ABBA THEODOTUS [THE MARTYRDOM AND MIRACLES OF SAINT GEORGE OF CAPPADOCIA. THE COPTIC TEXTS EDITED WITH AN ENGLISH TRANSLATION
ERNEST A. WALLIS BUDGE, M. A] Pp. 307
✧ The Passion of St. George Translated by E. A. W Budge Written by Abba Theodotus, Bishop of Ancyra in Glaatia in 431 AD. Pp. 18
በተራራው ላይ ጥር ፲፰ ቀን ስለተደረው ገቢረ ተአምራት ገድሉ በተጨማሪነት ከላይ በርእስነት ያነሳነውን ቃል በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕይወት ውሥጥ እያየ እንዲህ ይነግረናል
☞ ወጸውኦ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ በቃሉ አምላካዊ … ወሶቤሐ ተንስአ ከመ መርዓዊ ዘይወጽእ እምጽርሑ እንዘ አልቦ ሕማም ለግሙራ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን በአምላካዊ ቃሉ ጠራውና "የመረጥኩህ ወዳጄ ጊዮርጊስ ሆይ አሁን ከእንቅልፍህ ተነሥ አትፍራ፡፡ የማዝህ በመከራህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያለሁት አምላክህ እኔ ክርስቶስ ነኝ" አለው፡፡ ያን ጊዜም #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሙሽራ_ከጫጉላው_እንደሚወጣ ምንም ሕማም ሳያገኘው ተነሣ፡፡
#ደብረ_አሱርዮን የክርስቶስ ሙሽራ ሰማዕተ ጽድቅ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመጨረሻው መከራ ለሦስተኛው ሞት የወለደች የሰርግ አዳራሹ ናት። ምንም ሕማም ሳያገኘው በክብር ላይ ክብር እንዲጨመርለት ለበለጠው ተጋድሎ ጥር ፲፰ ሥጋው አጥንቱ ተቃጥሎ አመድ ሆኖ ተዘርቶ ሙሽራ ሲያገባ ተሰበሰበ እንደሚባለው እርሱም የሰርግ አዳራሹ የሙሽርነት እልፍኙ ከተባለችው ከፍ ያለችና ምድረ በዳ ከሆነች/ይድራስ ተራራ በክብር ተሰብስቦ ተነሳ «#ደብረ_ይድራስ_ጽርሐ_መርዓሁ_ለጊዮርጊስ»
የቀደሙቱ በፈተና ሲጨነቁ በጸሎታቸው እንዲህ የምትል «አርኬ» የልብ ለልብ ተማጽኖ ለሰማዕቱ ያደርሳሉ።
«ተማኅጸንኩ በዝርወተ አጽምከ በደብረ ይድራስ በድው
በአምሳለ ጸበል ወሐመድ በእደ ሠገራት እደው
ጊዮርጊስ ኄር ጊዮርጊስ አፈው
ምርሐኒ ለፍቁርከ እምፆታ ፈቃድ ምንትው
በኀበ አስተርአየ ወፈቀደ መለኮት ሕያው»
በግጥም ወደኛው ስንመልሰው ይኽን ሐሳብ ይዟል
በአጥንቶችህ ተማጽኛለሁ
በተራራው የይድራስ አጸድ
በጠባቂዎች እጅ በተበተነው
እንደ ትቢያና እንደ አመድ
ቸር የምትባል ጊዮርጊስ
ምግባርህም የሚያውድ
ወዳጅህን አንተው ምራኝ
ከሥጋ ፈቃድ መንታ መንገድ
በሚገለጥበት ጎዳና
ሕያው የመለኮት ፈቃድ
🙏አሜን 🙏
መልካም በዓል
✍️ በቴዎድሮስ በለጠ ጥር ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፳፻፲፮ ዓ.ም. [📍ከደብረ ወርቅ አትርፎ ቅዱስ ጊዮርጊስ]

Forwarded from Amanuel Ayalew
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ
የህንጻ ቤተክርስቲያን ምርቃት ጥሪ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።።።።።።።፡፡።።።።።።።።።
ኑ" የእግዚአብሔርንም ሥራ አዩ
(መዝ66÷5)
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በአ/አ/ሀ/ስ/በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ቤ/ክ/የምስራቀ ፀሐይ ለቡ መርጡለ አርሴማ ገዳም ቀደም ሲል ክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ወደዚህ ደብር በዋና አስተዳዳሪነት ተመድበው በመጡበት ሰዓት በሚያደርጉት የጉብኝት ወቅት ቦታው መሀል ከተማ ተቀምጦ እንዴት የቅድስት አርሴማ ጽላት ቆርቆሮ በቆርቆሮ በሆነ መቃኞ ውስጥ ይቀመጣል በማለት መንፈሳዊ ቁጭት አድሮባቸው የአካባቢው ምዕመናንም ህንጻ ቤ/ክ እንዲሰራ ፍላጎት ስላላቸው ዋና አስተዳዳሪው ሳይውሉ ሳያድሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈው
እግዚአብሔርን ይዘው የንስሐ ልጆቻቸው የሆኑትን አክሊለ ስማዕትና ወለተ ሐና የተባሉ እግዚአብሔር የመረጣቸው ባልና ሚስቶች የቅድስት አርሴማን ህንጻ ቤተክርስቲያን እንዲሰሩ በማሳመን በራሳቸው ወጪ ብቻ ውሃ አንኳን ከቤተክርስቲያን ሳይጠቀሙ በገንዘብ እየገዙ ማንም ሳይጨመር በደብሩ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ የየዕለት ክትትል በ1 ዓመት ከ4 ወር
ህንጻ ቤተክርስቲያኑ በፈቃደ እግዚአብሔር እጀግ ዘመኑን በዋጀና ባማረ ሁኔታ ተሠርቶ ተጠናቆ የካቲት 9 ቀን2016 ዓ/ም እና የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም
.ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ለቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
.ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ጠቅላይ ዋና ስራአስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
.ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት እጅግ ባማረና በደመቀ ሁኔታ የህንጻ ቤተክርስቲያኑ ምርቃት ይከናወናል ።
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
በመሆኑም አርስዎም በዕለቱ ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ላልሰሙት ያሰሙ ዘንድ በሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ሰም መንፈሳዊ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን ።
የደብሩ ሰ/ጉ/አ/ጽ/ቤት
Mewi Events
Our passion is your perfect event.
For Bookings ☎️ 0979338787
0910611517

✧ ቃለ እግዚአብሔር ዘይትኀባእ በግእዘ ሕጻናት ✧
【በሕጻናት ባህሪ የተሰወረ የእግዚአብሔር ቃል】
ሰው ምኞቱን በተስፋ እየጠበቀ ፣ ነገውን በእቅድ እየናፈቀ … ገና ብላቴና ሳለ «ወደፊት ሳድግ እንዲህ ብሆን» ይላል ።
ያ በምናባችን የሳልነው ነገ በከንቱ አልፎ የምንቆጭበት ትናንት እየሆነብን እናዝናለን።
የዚህች ሕጻን ንግግር ግን ወደኋላ ልጅ ሳለን እንዲህ ሆነን ቢሆን ኖሮ ያስብለናል።
በዚህ መንገድ የቀረጻችሁ ቤተሰቦች ብድር ይግባችሁ!
ልጃችሁን ባልተለወጠ አንደበት በተመጠነ እድገት በቤቱ ያሰንብትላችሁ🙏
https://youtu.be/bRKiuAEcqOs?si=2CRRVXaQz_ImeLlv

YouTube
ለመጠየቅ ፈራሁ!! እጹብ ድንቅ ልጆች የሃረገወይን #etsubdinklijoch #comedianeshetu #ethiopia
ማን እንደ ሀገር አዲስ እስታንዳፕ ኮሜዲ ለማየት ይመዝገቡ
https://tally.so/r/nr6ljL
የወጌሻ ዩትዩብ ስልጠና | እስታንዳፕ ኮሜዲ | የእየሩሳሌም ጉዞ እና እጹብ ድንቅ ልጆች ጠቁሞ ለመመዝገብ ከታች ይምረጡ 👇
https://tally.so/r/3ldYl5
ውድ የዶንኪትዩብ ቤተሰቦቻችን የእጹብ ድንቅ ልጆች ፕሮግራማችንን በድጋሜ እነሆ!!!
የዛሬ ፕሮግራም እንግዳችን ህጻን ሃረገወይን ቀለሙ…

እግዚአብሔርን መውደድ የእ’ሱ የሆነውን ሁሉ በመውደድ ይገለጣል! ይልቁንም የእርሱ ከሆነው ሁሉ እርሱ የወደደውንና የሞተለትን ክቡር የሰው ልጅ መውደድ እርሱን ወደ መውደድ ያደርሳል!
ሰውን መግፋት እግዚአብሔርን መርሳት ነው። አበው «ተዘክሮተ እግዚአብሔር እና ተዛውኦተ አኃው ካለው ሰው በላይ እግዚአብሔርን ከቶ ማን ይመስለዋል?» ይላሉ!
ለዐቢይ ጾም ዐቢይ ትዕዛዝ የሚያስተምር ዐበይት ሕግጋቱን የሚናገር ዝማሬ እነሆ "የሕግ ፍጻሜ"
ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) ዝማሬ መላእክት ያሰማልን 🙏
#ሕግጋተ_ወንጌል
ከፍቅረ ቢጽ ጋራ ፍቅረ እግዚአብሔር አጽና
ኦሪትና ወንጌል በሁለቱ ትዕዛዛት ተሰቅለዋልና
በባልንጀራህ ላይ በከንቱ አትቆጣ
የእግዚአብሔር ሰላም ከቤትህ እንዳይወጣ
አድመኝነት ቁጣ ጠብና ክርክር
ፀሐይዋ ሳትገባ ትተህ በፍቅር ኑር
አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ)
ወደሴቲቱ አይቶ ልቡ ‘ሚያመነዝር
ምኞቱ ኃጢዓት ወልዳ ከሞት ጋር የሚኖር
ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ
ከሰማዩ መንግሥት የለው እድል ፈንታ
አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ)
እውነት ከሆነ አዎን ፡ ካልሆነ አይደለም በል
በሰማይም በምድር ፡ ፈጽሞ አትማል
ክፉውን በክፉ ፡ ተቃውመህ አትመልስ
መልካም የሆነውን በሰው ሁሉ ፊት ያዝ
አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ)
እግዚአብሔርን መምሰል ራስህን አስለምድ
ላሳዳጆች ጸልይ ጠላትህን ውደድ
የሚረግሙህንም መርቅ እንጂ አትርገም
ይህ ነው ሕገ ወንጌል ፡ ልዝብ ቀሊል ሸክም
አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ)
https://youtu.be/ERbbNT-RkOE?si=6GS0X04qOY15ikcO

🔴 "ሕግጋተ ወንጌል" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame | Hegegate wongel D Zelalem Takele
#like #share #subscribe
ሕግጋተ ወንጌል
ከፍቅረ ቢጽ ጋራ ፍቅረ እግዚአብሔር አጽና
ኦሪትና ወንጌል በሁለቱ ትዕዛዛት ተሰቅለዋልና
በባልንጀራህ ላይ በከንቱ አትቆጣ
የእግዚአብሔር ሰላም ከቤትህ እንዳይወጣ
አድመኝነት ቁጣ ጠብና ክርክር
ፀሐይዋ ሳትገባ ትተህ በፍቅር ኑር
ወደሴቲቱ አይቶ ልቡ ‘ሚያመነዝር
ምኞቱ ኃጢዓት ወልዳ ከሞት ጋር የሚኖር
ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ…
ሕግጋተ ወንጌል
ከፍቅረ ቢጽ ጋራ ፍቅረ እግዚአብሔር አጽና
ኦሪትና ወንጌል በሁለቱ ትዕዛዛት ተሰቅለዋልና
በባልንጀራህ ላይ በከንቱ አትቆጣ
የእግዚአብሔር ሰላም ከቤትህ እንዳይወጣ
አድመኝነት ቁጣ ጠብና ክርክር
ፀሐይዋ ሳትገባ ትተህ በፍቅር ኑር
ወደሴቲቱ አይቶ ልቡ ‘ሚያመነዝር
ምኞቱ ኃጢዓት ወልዳ ከሞት ጋር የሚኖር
ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ…
«ወኢትምጻእ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክከ ዕራቀከ»
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትህን አትምጣ
【ዘዳ ፲፮፥፲፮】
በዚህ መጻሕፍት ይተባበሩበታል
✧ "ወኢታስተርኢ ቅድሜየ ዕራቀከ ☞ በፊቴም አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ" 【ዘጸ ፴፬፥፳】
✧ "ወኢትትረአይ በቅድሜየ ዕራቀከ ☞ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። 【ዘጸ ፳፫ ፥፲፭ / ፳፬፥፲፩】
✧ ሲራክም "ኢትባእ ቅድመ እግዚአብሔር ዕራቀከ ☞ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ባዶህን አትግባ" 【ሲራ ፴፪፥፮】
በቅድሜየ ወይም በፊቴ ማለቱ ለእግዚአብሔርስ ሁሉ ቅድሙ ወይም ፊቱ ነው፤ በሁሉ ያለና ከፊቱ የሚሸሸግ የሌለ ሆኖ ሳለ መገለጫ መክበሪያውን ሲያይ ፊቴ ይላል።
☞ በዘመነ ብሉይ በደብተራ ኦሪትና በቤተ መቅደስ በረድኤት ያድር ነበርና
☞ ዛሬም በዘመነ ሐዲስ በሥጋውና ደሙ በቤተክርስቲያን ይገለጽባታልና ከሁሉ አብልጦ ማደርያ ቤቱን ቅድሜየ አላት።
ይህን ራሱ ሙሴ ሲገልጠው «ቅድመ እግዚአብሔር ፥ ውስተ መካን ዘኀርየ እግዚአብሔር አምላክከ ☞ በእግዚአብሔር ፊት ፥ እርሱ አምላክህ በመረጠው ስፍራ» ሲል አስረድቷል፤
ለሰው አካሉን ገልጦና ሰውነቱን አራቁቶ ለመታየት የታወቀ (በቂ) ምክንያት ያስፈልጋል፤ ሠለስቱ ምዕት ለመታከም «የሚተኮስ» «የሚታገም» አካል ቢኖር አልያም ከጸበል ሊነከሩና ሊታጠቡ እንጂ በሌላውስ መንገድ በማንም ፊት እርቃን መታየት ክልክል ነው ብለዋል።
"ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ። ☞ ዳግመኛም በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ፤ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ" 【ሃይ አበው ፳፥፲፪】
ራቁትነት በውጭ ያለ (አፍኣዊ) ገላን መክደኛ ነውርን መሸፈኛ ከሆነው ጨርቅ ከመራቆት በላይ በሦስት መንገድ ውሳጣዊ እርቃንን የሚያስረዱ ሦስት መንገዶችን እናስቀምጥ
፩ኛ] ራቁት የሚለው #በኃጢዓት_መመላለስ በበደል መጽናትን ነው። ያንን በንሰሐ ሳያጠሩ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚገባ አይደለምና።
በኃጢዓት ከመውደቃቸው አስቀድሞ የማይተፋፈሩ የነበሩ አዳምና ሴቲቱ ከሕግ ሲወጡ ራቁትነትን አወቁ፤
“የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።” 【ዘፍ ፫፥፯】
ቅዱስ ዳዊት ይህን ድርጊት «እንሰሳትን መምሰል» ብሎታል
【መዝ ፵፰፥፲፪/፳】
አባ ጊዮርጊስም በመጽሐፈ ምሥጢር እርቃን ከመቅረት በላይ እንሰሳትን መምሰል ወዴት አለ? ብሏል
“ምንት ውእቱ ተመስሎ እንስሳ ዘእንበለ ተከሥቶ ዕርቃኑ ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ሶበ ነፍጸ አጽፈ ብርሃን ዘላዕሌሁ ኀደጎ አጽፈ ብርሃን ⇨ በገነት ዛፎች መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ከመተየት በስተቀር እንስሳን መምሰል ምንድ ነው? የብርሃን ልብስ ከበላዩ ላይ በተገፈፈ ጊዜ የብርሃን መጐናጸፊየው ተለየው”
ክዶ ከአምላኩ ተለይቶ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታው በፊቱ በቆመ ሠዓት ለጊዜ እርቃኑን በልብስ ደብቆ ከባህር ጠልቆ መታየቱ ነውን በንሰሐ አርቆ ሥጋን በቅጣት አስጨንቆ ድኅነት እንደሚገኝ ማሳያ ነው።
“ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን፦ ጌታ እኮ ነው አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ።” 【ዮሐ ፳፩፥፯】
እንደ ወርቅ የተፈተነ ቃሉን በመያዝ ፣ እንደ ነጭ ልብስ የከበረውን ጸጋ ልጅነት ለማጽናት… ከፊቱ ቀርቦ በንሰሐ መመላለስ ይገባል
“ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።” 【ራእ ፫፥፲፰】
፪ኛ) ራቁት ማለት ራስን መግለጥ #ተርእዮን_መሻት እግዚአብሔርን መርሳት አምላከ ቅዱሳንን ማስረሳት ማለት ነው። ራስን ለመስበክና ስለራስ ለማውራት እግዚአብሔር ፊት መቆም ተገቢ አይደለም።
በሰማይ ያሉ አገልጋዮቹ ከመንበሩ ፊት የቆሙ መላእክቱ ፊት እግራቸውን መሸፈናቸው ለዚህ መማርያ ይሆነናል
“ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።” 【ኢሳ ፮፥፪】
ራሱን ሲሰብክ ለዋለው
"ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት” (ዮሐ 12፥2) የሚል መልእክት ልከው
ኋላ ተመልሶ ራሱን ሰውሮ ክብረ ክርስቶስን ቢሰብክላቸው
“ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።” (ዮሐ20፥20) ብለው አመስግነውታል።
፫ኛ) ራቁት ማለት ባዶ እጅ #ምንም_ሳይዙ_መምጣት ማለት ነው፤ መባዕ፣ ስእለት ፣ ምጽዋት ፣ ዐሥራት፣ በኩራት፣ ቀዳምያት እና መስዋእት ሳይይዙ ወደመቅደሱ መምጣት የሚገባ አይደለምና።
“ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።” 【ሉቃ ፮፥፴፰】
የእግዚአብሔር መልስ
መስፈርተ ሠናየ ☞ Good measure
ንሕኑሕ ☞ pressed down/deeper
ምሉዕ ☞ shaken together
ዝሕዙኅ ☞ Running over
በስብከት መልእክቱን በተከታዩ አስፈንጣሪ ያድምጡ
https://youtu.be/cTghI5q7d20?si=KbkRNZ2IdRq366aI

ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ በእግዚአብሔር ፊት ዕራቁትህን አትምጣ ዘዳ16፥16
✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን::
ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCol_BHX6I…

Forwarded from mikiyas danail
✝️ኑ! ቸርነትን እናድርግ ✝️
መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣
+++
ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል።
የመግቢያ ትኬቱን፡-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች
ለበለጠ መረጃ
• 09 44 71 82 82
• 09 42 40 76 60
ማኅበረ ቅዱሳን

መድኃኒታችን
የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት
ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት
⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
ትጉህ ኖላዊ ነው ፤ ነቅቶ የሚጠብቅ
ከተራራው ወርዶ፣
ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ
ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን
በመስቀል መንበር ላይ፣
አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም
⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
ጸጋችን ተገ’ፎ ፣ ተራቁተን ብንርቅ
በቁም ሞትን ለብሰን ፣
በለስ አገልድመን –በኃጢዓት ብንደርቅ
በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን
ከሸማኔ ጎድጓድ ፣
ከድንግል ተገኝቶ – ራሱን አለበሰን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም
⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
ከንቱ ቃል በመስማት ፣ ማረፊያ ስናጣ
ከገነት ተሰ’ደን ፣
ከሰማዩ መንግሥት–ወደ ምድር ብንመጣ
ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር
መንግስተ ሰማያት፣
ወንጌልና ተስፋ –እርሱ ነው እግዚአብሔር።
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማይፈርስ ጽኑ ቤት ለፈላሲው ዓለም
⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
https://youtube.com/watch?v=uHyymObqHQ0&si=VkH5pu91GUt0g8ki

🔴 "መድኃኒታችን" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame | Medhanitachen l D Zelalem Takele
#like #share #subscribe
መድኃኒታችን
የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት
ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት
ትጉህ ኖላዊ ነው ፤ ነቅቶ የሚጠብቅ
ከተራራው ወርዶ፣ ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ
ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን
በመስቀል መንበር ላይ፣ አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም …
መድኃኒታችን
የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት
ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት
ትጉህ ኖላዊ ነው ፤ ነቅቶ የሚጠብቅ
ከተራራው ወርዶ፣ ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ
ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን
በመስቀል መንበር ላይ፣ አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም …
Forwarded from Amanuel Ayalew
የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ሥርዓተ ቀብርን በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ
መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ክቡር አስከሬንም ከሀገረ አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ስርዓተ ቀብራቸው እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም በፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው ገነተ ኢየሱ ቤ/ክ ከ4- 6 ሰዓት ይፈፀማል::
ይህንንም በማስመልከት ለመልዐከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ መታሰቢያ ለማስቀመጥ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቃቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምራል::
በዚህም መሰረት ይህንን የተቀደሰ አላማ ለመደገፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አካውንቶች ገቢ እንድታደርጉ እንጠይቃለን::
1000614508497 ንግድ ባንክ
179465639 አቢሲኒያ ባንክ
መልአከብርሃንሙላት ክበቤ
መልአከብርሃን ቄሰ ገበዝ ተቋመ ማህቶት
መምህር በላይ ወርቁ
የመልዐከ ጸሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ የቀብር አስፈጻሚ አብይ ኮሚቴ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌾 አንተን ማሳዘኔ በደሌ ቢበዛ
ባታገኝም ከእኔ የጽድቅ መዓዛ
🌾 በምሕረትህ ብዛት አንተ ይቅር በለኝ
ሥራዬን አትይ እኔ ደካማ ነኝ።
🌾 ዘወትር አለቅሳለሁ ድካሜን አውቄ
መኖሬ ሲሰማኝ ከቃልህ ርቄ
🌾 በመንገድህ ምራኝ ፊትህን እንዳይ
ስለ እናት ብለህ ከኔ አትለይ
በዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
ባታገኝም ከእኔ የጽድቅ መዓዛ
🌾 በምሕረትህ ብዛት አንተ ይቅር በለኝ
ሥራዬን አትይ እኔ ደካማ ነኝ።
🌾 ዘወትር አለቅሳለሁ ድካሜን አውቄ
መኖሬ ሲሰማኝ ከቃልህ ርቄ
🌾 በመንገድህ ምራኝ ፊትህን እንዳይ
ስለ እናት ብለህ ከኔ አትለይ
በዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
« ይህን ዝማሬ በነፍሳችን እናኑረው »
°°°°°•°°°°°°•°°°°°°°°°°°°°°°°°
"ወዘያስተጋብዖ ለዝንቱ ዝማሬ ውስተ ነፍሱ ናሁ ረከበ ጸጋሁ ለእግዚብሔር ልዑል ዘይጸንዕ እምኵሉ ምግባራት እንተ ትረክቦ ☞ ይህን ዝማሬ በነፍሱ ያኖረ (በልቡ የያዘ) ሰው እነሆ ከተሰጠው ጸጋ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋን ከክቡር እግዚአብሔር ዘንድ አገኘ"
ከመጽሐፈ መነኮሳት ክፍል ማር ይስሐቅ በ፳፱ኛው አንቀጽ ላይ ስለ አእምሮ መንፈሳዊ የተነገረ መልእክት ነው።
☞ ናስተጋብእ ለዝንቱ ዝማሬ በውስተ ነፍሰነ
የበገና መዝሙር በመምህር አቤል ተስፋዬ
Abel Begena አቤል በገና
#ላንዴ_እስከወዲያኛው
#ያንን_ሰው_ባረገኝ ፣ #ያቺንም_ሴት_በሆንኩ [፩]
🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባ’ረገኝ ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ
~~~
ምነው እሱን በሆንኩ
ያን የቀኝ ወንበዴ
ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ
ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት
አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት
በዚያ መንገድማ
ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና
እኔን ታውቀኝ የለ …
የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች ዋና
ያ … ጸጸት ያዘለ
በዚያች የጭንቅ ሠዓት «አስበኝ» እያለ
ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ
ካ’ዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ
እኔም እንደ ጥጦስ : ማታዬ እንዲያምር
ብትለኝ ምን አለ? …
«ከገነት ተጠለል: ዛሬን ከእኔ እደር»
🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባ’ረገኝ ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ
~~~
ደ’ሞ ይህን ተመኘሁ
ለንጊኖስን በሆንኩ
ያቺን ዕለተ ዓርብ : ቀራንዮ በዋልኩ
ለአመጽ አይደለም : ከከአይሁድ ለማበር
አልያም ለመውጋት : ያንተን ጎን በጦር
በዚያ መንገድማ
አንተን ለማሳመም: ማን እኔን መሰለ
ስንቴ እንዳቆሰልኩህ …
ስንቴ እንደወጋሁህ : እኔን ታወቀኝ የለ!
ያ …የጲላጦስ ጭፍራ
በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ
በጦሩ ቢወጋህ ሳያዝን ሳይራራ
ከቀኝ ጎን አፍስሰህ ውኃው ከደም ጋራ
በፍቅርህ ስታስረው ዐይኑን ስታበራ
ትዕግስትህን ጎትቶት ባንተ እንደ ተጠራ
ምናለ እንደው ’ኔንም …
ላንተ ብቻ እንዲያድር : ልቤን ብታበራ
🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባ’ረገኝ ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ
~~~
ላንዴ እስከወዲያኛዉ
https://youtu.be/GjZf3fPaeDs

የበገና መዝሙር ዲ/ን አቤል ተስፋዬ ላንዴ እስከወዲያኛዉ ግጥም መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ቴዎድሮስ በለጠ ዜማ ዲ/ን ዘላለም ታከለ (ዘጎላ)
🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባ’ረገኝ ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ
~~~~~~~~~~~~~~~
ምነው እሱን በሆንኩ
ያን የቀኝ ወንበዴ
ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ
ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት
አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት
በዚያ መንገድማ
ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና
እኔን ታውቀኝ የለ …
የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች…
ያንን ሰው ባ’ረገኝ ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ
~~~~~~~~~~~~~~~
ምነው እሱን በሆንኩ
ያን የቀኝ ወንበዴ
ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ
ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት
አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት
በዚያ መንገድማ
ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና
እኔን ታውቀኝ የለ …
የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች…
╔✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╗
❀. #የማያሳፍር_ራቁትነት .❀
╚✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╝
ትናንት ሚያዝያ ፬ የመፈጠራቸው ነገ ሚያዝያ ፮ ደግሞ የዕረፍታቸውን መታሰቢያ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የምትዘክርላቸው አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በረከታቸው ይደርብን።
★ "ሀለዉ አዳም ወብእሲቱ (ሔዋን) እራቃኒሆሙ ወኢይትኃፈሩ ☞ አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።" 【ዘፍ ፪ ፥ ፳፭】
ሁለት ዐይነት እርቃን አለ የሚያሳፍር እና የማያሳፍር የማያሳፍረው ራቁትነት ደግሞ የተፈቀደ እና ያለተፈቀደ ሊሆን ይችላል
ዛሬ ላይ ትውልዱ ባልተፈቀደ መንገድ መራቆቱን ሳያፍርበት እንደፋሽንም እንደ ክብርም ይቆጥረዋል በቀደመው ታሪክ የቃየል ልጆች ባልተፈቀደ መራቆት አምላካቸውን ሲያሳዝኑ እንደታዩ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ገልጧል
"ርእዩ አዋልዲሁ ለቃየል በዘይሴኒ ሥነ ራእይ እንዘ የሐውራ ዕራቆን ዘእንበለ ሐፍረት ☞ የቃየን ሴቶች ልጆች ተውበው እርቃናቸውን በመሆን ሳያፍሩ ሲንቀሳቀሱ እዩዋቸው" 【ቀሌ. ፫፥፵፱】
ታዲያ እንዲህ ባለው መንገድ ነውርን እንደ ክብር መራቆትንም እንደ መሰልጠን ገላ መግለጥ እንደፋሽን እያዩ የሚኖሩ መጨረሻቸው ኩነኔ እንደሆነ መጽሐፋችን ይመሰክራል
“መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” 【ፊል ፫፥፲፱ 】
ለሰው ልጅ አካሉን ገልጦና ሰውነቱን አራቁቶ ለመታየት የታወቀ (በቂ) ምክንያት ያስፈልጋል፤ ሠለስቱ ምዕት ለመታከም «የሚተኮስ» «የሚታገም» አካል ቢኖር አልያም ከጸበል ሊነከሩና ሊታጠቡ እንጂ በሌላውስ መንገድ በማንም ፊት እርቃን መታየት ክልክል ነው ብለዋል።
"ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ። ☞ ዳግመኛም በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ፤ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ" 【 ሃይ አበው ፳፥፲፪ 】
መራቆት አለመዘጋጀት እፍረት ማሳየት የመዘናጋት በበጎ ምግባር ሳይተጉ የመኖር መገለጫ ነው። “እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” 【ራእ ፲፮፥፲፭】
አካልን ራቁቶ መታየት ቀርቶ የተራቆተ አካልም ማየት ራሱ ሲያስነቅፍ ፣ ሲያስቀጣና ሲያስረግም እናያለን
በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ ፱ እንደተገለጸው በኖኅ ልጅ በካም ላይ የደረሰው የዚህ ማሳያ ነው
" ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። " 【ዘፍ ፱፥ ፳ - ፳፯】
እንግዲህ የተራቆተን ማየት በዚህ መጠን የሚያስነቅፍ ከሆነ ተራቁቶ የመታየት ቅጣቱ የከፋ ስለመሆኑ አያጠራጥርም መራቆት የዲያቢሎስ የክብር ልጅ መሆን ነውና ፤ ሰይጣን ማለት በትርጉሙ እሩቅ እም ስብሐተ እግዚአብሔር 【ከእግዚአብሔር ክብር የተራቆተ】ማለት ነውና።
የተፈቀደ የማያሳፍርም ዕርቃን የተባለውና በጥንተ ተፈጥሮ በአዳምና በሴቲቱ ኑሮ የተገለጠው የትኛው ራቁትነት ነው?
① ራቁትነታቸው ከዚህ ዓለም ልብስ ነው አለማፈራቸው ብርሃን ለብሰው ስለነበር ነው
ዓለማችን የሚያለብሰን ምድራዊና ቁሳዊ ጊዜአዊና ኃላፊ ትጥቅ ነው መንፈሳዊ ትጥቃችን ግን ኅልፈትና ውላጤ ከሌለው ሰማያዊ አባታችን የምንቀበለው ነውና “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” 【ኤፌ ፮፥፲፩】
“እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤ … በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ” 【ቆላ ፫፥፲፪- ፲፬】
የዓለሙ ልብስ ንፍገት ጭካኔ ቅሚያ ትዕቢት ብልጣብልጥነት ችኩልነትና ጸብእን ነው። ይህን ለብሰው የሚዋጉንን ሥጋውያኑን በሥጋ ጦር ድል መንሳት እንዴት ይቻለናል?
የሳውልን የጦር ዕቃ የታጠቀ ካባ የለበሰና በአመጽ ወደተመላው እግዚአብሔርን ወደተገዳደረው ጎልያድ በሥጋዊ መሳርያ ውጣ የተባለው ብላቴናው ዳዊት መታመኛ ትምክህቱ መከታ ጉልበቱ እግዚአብሔር ስለበር በበትርና በኮሮጆው ጠጠር ዘምቶ አመጸኛውን ሰልፈኛ ሰው ድል ነስቶታል።
“ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ።” 【፩ኛ ሳሙ. ፲፯፥ ፴፱】
② አእምሮ ጠባያቸው ያላደፈ በተፈጥሮ እንደ ሕፃን ስለነበሩ በዕርቃናቸው አይተፋፈሩም
ሕጻናት በንጽሕና እንደ መላእክቱ ናቸው የእነርሱ አእምሮ ጠባይ ማደፍ ስላላገኘው ሊቁም «ንጽሖሙ ለሕፃናት በሥጋሆሙ ወነፍሶሙኒ ዘእንበለ ሕማም» ይላል።
በዘመነ ሥጋዌው ክርስቶስ አምላካችንም እንደ ሕፃናት መሆን ለክብረ መንግሥቱ እንደሚያበቃ ነግሮናል
“ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” 【ማቴ ፲፰፥፫】
መልሶም እንደነርሱ ላሉቱ ስለምትሠጥነና እነርሱኑ ለመሰሉት ስለምትገባዋ ዘልዓለማዊ ርስት ይህን ደግሟል
“ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤” 【ማቴ ፲፱፥፲፬】
ያለቂም ያለበቀል የሚኖሩ ክፋትንና ተንኮልን አልመው አስበው ሌላው ይጎዳበት ብለው የማይፈጽሙ እንደወረቀት የሠጧቸውን የሚቀበሉ እንደውኃም ቅርጻቸው ያረፉበትን ሥፍራ የሚመስሉ ልጆች ሕጻናትን መስሎ መኖር የሚማሩትን መያዝ በበጎ አርያነት የሚመሩትን መምሰል በእጅጉ ይገባል ፤
“ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”【፩ኛ ጴጥ ፪፥፪-፫】
እንዲህ ያለው የሕጻናት ንጹሕ አይምሮ መያዝ አያሳፍርም።
③ ከልብሰ ኃጢዓት ተራቁተው ኃፍረተ ነፍስ ሳይኖርባቸው ይኖሩ ነበር
ሰው ኃጢዓትን ለብሶ በደል ደርቦ ከመኖር በንሰሐ ቢራቆት ተኮንና የምታፍር ነፍስ የለችውም፤ ይልቁንም የልብ ንጽሕና ማጣት የሕሊና ሞት እንደሚያመጣበት አውቆ በኃጢዓቱ ምክንያት ያገኘውን ቁስለት የልቡናው ሰንኮፍ በንሰሐ ከከከበረች ነፍሱ ቢያርቅ መንገዱን በጥንቃቄ ቢመራና በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ለአምላኩ ቢገዛ በግራ ከሚቆምና ተኮንነው ከሚያፍሩ በመለየት መክበር ይቻለዋል።
“እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፥ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፥ ተንቀጥቀጡ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።”
【ኢሳ ፴፪፥፲፩】