"ብእሲት ዘኃደገት ቀሱታ ⇨ መቅጃዋን የተወችው ሴት"
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°•◇•°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከሰማርያ መንደር ከወጡ ደገኛ የቅዱስ መጽሐፍ ባለ ታሪኮች ደጉ ሳምራዊ እና ደጓ ሳምራዊት ጎልተው ይጠቀሳሉ። በመጽሐፈ ስንክሳራችንም መጋቢት ፭ ቀን የስሟ ትርጓሜ ሰላምና ሥምረት የሆነ ቅድስት አውዶክስያ የምትባል አንዲት ሳምራዊት ሴት በታላቅ ተጋድሎ ማረፏን ይነግረናል።
የደጉ ሳምራዊ ታሪክ ለትምህርት ምሳሌ ነው [የሉቃስ ወንጌል 10:33] ፤ የእርሷ ግን በአምላካችን ዘመነ ሥጋዌ የተፈጸመ አስተማሪ ኩነት አዝሏል። መኖርያዋ ሲካር ነው ታላቋ «ሳምራዊት» ሴት [የዮሐንስ ወንጌል 4:7]
ይህች ሴት መድኃኔዓለም የሚለውን ስም በወንጌል ቀድሞ በሰው አፍ እንዲጠራ በስብከቷ ምክንያት የሆነች የከበረች ምስክር ናት።
ሰማዕነ ወጠየቅነ ከመ ዝንቱ ውእቱ ክርስቶስ በአማን #መድኅነ_ዓለም
↳ ይህ በእውነት የዓለሙ መድኅን ክርስቶስ እንደሆነ ሰምተናል ተረድተናል
ወንጌል ስለመጨረሻው ተልእኮዋ ሲነግረን እንዲህ ይተርከዋል፦
☞ "ወኃደገት ቀሱታ ይእቲ ብእሲት ወአተወት ሀገረ ወነገረት ለሰብአ ቤታ ። ወትቤ ንዑ ትርአዩ ብእሲ ዘነገረኒ ኵሎ ዘገበርኩ እንዳዒ ለእመኑ ውእቱ ክርስቶስ "
↳ ሴቲቱም ማድጋዋን ትታ ወደ ሀገር ገብታ ለቤተሰቦቿ ነገረች ። የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፡ ክርስቶስም እንደሆነ እንጃ አለች ።
መምህረ ዓለም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሐዋርያዊ ሥራዋን በላቀ መንገድ ሲነግረን "ሌሎቹ ሐዋርያት መረባቸውን ጥለው ሲከተሉት እርሷም በሐዋርያነቷ መቅጃዋን ጥላ ተከተለችው ከእነርሱ እነ ፊልጶስ እነ እንድርያስ ሌላውንም እንዲከተለው በአንድ በሁለቱ ፊት ሲመሰክሩ እርሷ ግን መንደሩ ሁሉ እንዲከተለው ሰበከች" አለን ፤ አቤት መታደሏ!
ሳምራዊቷ ሴት ማናት?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከ፹፩ዱ ቅዱስ መጽሐፋችን በተጨማሪ በሌሎች የትውፊት መጻሕፍት አዋልድም ጭምር በተለያዩ መጠሪያዎች ተጠርታ ከተጨማሪ ታሪኮች ጋር እናገኛታለን።
ቀደምት የግሪክ ክታቦች አምስት እኅቶችና ሁለት ልጆች የነበሯት በሰማዕትነት ክብር ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትላ የጽድቅ ምስክር ሆና ያረፈች እንደሆነች አስረድተው ስሟ የከበረ ታላቋ ሰማዒት (ምስክር) ሳምራዊቷ ቅድስት #ፎጢን (holy and glorious Great-martyr #Photine of Samaria) እያሉ ገልጠዋታል።
የ’ኛውም ተአምረ ኢየሱስ ደግሞ ስሟን በመጥቀስ የታሪኳን ፍጻሜ እንዲህ አስቀምጦልናል ፦
☞ "ወሶበ ሰምአት ብእሲት ሳምራዊት ዘስማ #ብርፍሴንያ ነገሮ ለእግዚእ ኢየሱስ ሖረት ወዜነወት ለሰብእ እንዘ ትብል ንዑ ኀቤየ አርእየክሙ ብእሴ ዘየአምር ኅቡአተ እስመ ውእቱ ዜነወኒ ግብርየ ዘአኀብኦ እም ሰብእ"
↳ ይህችም ብርፍሴንያ የምትባል ሳምራዊት ሴት የጌታ ኢየሱስን ነገር በሰማች ጊዜ ወደሀገር ገብታ ለሰዎቹ ሁሉ በሆዴ ውስጥ ያለውን ምሥጢር ሁሉ የሚናገር ሰው አሳያችሁ ዘንድ ኑ እኔ ከሰው ደብቄ የያዝኩትን ምሥጢር ነግሮኛልና አለቻቸው ።
ሳምራዊቷ ሴት ቅድስት ብርፍሴንያ መቅጃዋን ጥላ ወደ መንደር ተመልሳ በሀገሩ ያሉትን ሁሉ ወደ ድኅነት ወደ ሕይወት ውኃ ጠራች የበረከት ቃል ከአንደበቷ እየተቀዳ አፏ የሕይወት ውኃ ምንጭ ሆነ። "ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ" ትላለች። ጠቢቡ “የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ናት፤ የኀጥኣንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።” 【ምሳሌ 10፥11】
ለሲካር መንደር ሕዝብ ቅድስት ብርፍሴንያ ለሕይወት ውኃ ክርስቶስ "መቅጃቸው" ናት። እነርሱ ግን የሴት ደቀ መዝሙር ለመባል አፍረው በእርሷ ስብከት ተከትለው ቢያምኑበትም የእርሷን ድርሻ ግን እንዲህ እያሉ ካዱ ፦
☞ "ወይቤልዋ ለይእቲ ብእሲት አኮ እንከ በነገረ ዚአኪ ዘአመነ ቦቱ አላ ለሊነ ሰማዕነ ወጠየቅነ ከመ ዝንቱ ውእቱ ክርስቶስ በአማን መድኅነ ዓለም ።"
↳ ሴትዮዋንም አሁን በእርሱ ያመን ፡ አንቺ በተናገርሽው አይደለም እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለሙ መድኅን ክርስቶስ እንደሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ አሏት።
የሳምራዊቷን ሴት የቅድስት ብርፍሴንያ [Great-martyr St. Photine]
✧ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር! ✧

❤13👍13🙏1
"The woman who left her water jar: The Samaritan Woman"
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°•◇•°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
[A theological discourse on a woman from Samaria, often referred to as the Samaritan woman. It delves into her encounter with Jesus Christ as described in the Gospel of John, chapter 4. The text highlights her significance in Christian theology and her role as an evangelist.]
From the Samaritan village, the noble stories of the good Samaritan and the good Samaritan woman stand out. In our Book of Synaxarium , on the 5th of Megabit, we read about Saint Eudoxia, a Samaritan woman whose name means 'peace and tranquility,' who achieved great martyrdom.
The story of the good Samaritan is a lesson [Luke 10:33], but hers is real story. Her dwelling place was Sychar, the great "Samaritan" woman [John 4:7].
This woman was a precious witness, causing the name 'Savior of the World' to be first spoken by human lips in the Gospel through her preaching.
"Martyrs testify to us that this is truly Christ, the Savior of the world."
The Gospel narrates her final mission thus: "And the woman left her water jar and went into the city and told the people, saying, ‘Come, see a man who told me all that I ever did. Could this be the Christ?’
The golden-mouthed preacher, Saint John Chrysostom, elaborates on her apostolic work: "While the other apostles left their nets to follow Him, she too, as an apostle, left her water jar and followed Him. While they witnessed to Philip, Andrew, and others to follow Him, she preached to the whole village to follow Him."
Who is the Samaritan woman?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
Beside our 81 books of the Holy Bible , other 'holy' traditions also mention her with various names and additional stories.
Early Greek texts describe her as having five sisters and two children, martyred for her faith, and a follower of Saints Paul and Peter. She is revered as the great martyr, Saint Photine of Samaria.
Our Teamre Iyesus (Miracle of Lord Jesus) also mentions her name and narrates her story as follows : "And when the Samaritan woman, named #BERFISENIYA, heard the word of the Lord Jesus, she went into the city and told the people, saying, ‘Come, see a man who told me all that I ever did. Could this be the Christ?’"
Saint Berfiseniya, the Samaritan woman, left her water jar and returned to the village, calling all to the living water, to salvation. Her mouth became a fountain of life. "The mouth of the righteous is a fountain of life, but the mouth of the wicked conceals violence." [Proverbs 10:11]
For the people of Sychar, Saint Photinia served as a "water jar" leading them to the living water, Christ. Though they followed her preaching, they denied her role, saying: "And they said to the woman, ‘It is no longer because of your words that we believe, for we have heard ourselves and know that this is indeed the Christ, the Savior of the world."
May the blessing of the Samaritan woman Saint Berfiseniya (Photinia) be upon us all!

👍36❤9
«ተውኔተ ጵጵስና ☞ የጵጵስና ጨዋታ»
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥
የኩላዊት ቤተክርስቲያናችንን ትውፊት [παραδοσις] ትምህርት [διδασκαλια] እና እምነት [πιστις] ከመነሻው ስንመለከት በክርስቶስ የተሠጠ በሐዋርያት የተሰበከና በአበው የተጠበቀ መንገድ ነው። በዚህም ቤተክርስቲያን ተመሠረተች!【ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ】
በቀደመው ዘመንማ የገሃዱ ሢመት ቀርቶ የሕጻናቱ ተውኔት እንኳ ደርዝ ነበረው!
በክርስትና ማኅተም ያልከበርክ
እንዴት ለጵጵስና ተመረጥክ? 【አባ ጊዮርጊስ】
ዛሬ ግንቦት ፯ ቀን በሃይማኖት የተዋቀረ ፦ የማይናወጥ መሠረት፣ የማይፈርስ ግድግዳ ፣ የማያዘነብል ምሰሶ የተባለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፳ኛው የኢትዮጵያና የግብፅ ፓትርያርክ በ፫፻፸፬ ዓ.ም. ከሥጋ ድካም ያረፈበትን ቀን ቤተክርስቲያናችን ትዘክራለች። ይህ የምሥጢር ምንጭ የጉባኤ ኒቅያ አፈ ጉባኤ ደገኛው መምህር ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ለ፵፯ ዓመት በፕትርክና ሲቆይ ሢሦውን 【፲፭ ዓመት】በስደት ነበር ያሳለፈው።
ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን ጳጳስ ቅዱስ ፍሬምናጦስን【አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን】የሾመልን ባለውለታችንና በመንበረ ማርቆስ የተቀመጠ ፳ኛው ፓትርያርካችን ነው። («ወማርቆስ ወንጌላዊ ‘ወኮነ ሰባኬ ወመጥምቀ ወሠያሜ ካህናት’ በእስክንድርያ ወግብፅ ወኖባ ወምድረ ኢትዮጵያ እስከ ጽንፋ» እንዲል መጽሐፈ ግጽው ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፩ )
ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ክርስትናው የመጣበትና ለጵጵስና የበቃበት መንገድ እጅጉን የሚደንቅና አስተማሪ ነው። ስንክሳራችን በቀደመ ሕይወቱ ከአረማውያን ቤተሰብ የተገኘ አረማዊ እንደነበርና ለመጠራቱ ምክንያት ስለሆነች «የጵጵስና ጨዋታ» እንዲህ እያለ ይነግረናል
ውእቱ ይነብር ምስለ ሕፃናት እለ ይትሜህሩ ኀበ መምህር ርእዮሙ ለእሙንቱ ውሉደ ክርስቲያን እንዘ ይገብሩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ወይትዋነዩ በበይናቲሆሙ ወይረስዩ እምኔሆሙ ዲያቆናተ ወኤጲስ ቆጶሳተ አደሞ ተላህዮቶሙ። ሰአሎሙ ዝንቱ አብ ለውሉደ ክርስቲያን ከመ ይሳተፍ ምስሌሆሙ በተላህዮቶሙ። ወከልእዎ ወይቤልዎ እስመ አንተ አረማዊ ኢንዴመር ምስሌከ ወይቤሎሙ ውእቱ አነ እከውን ክርስቲያናዌ ወተፈሥሑ ቦቱ።
【 እርሱም ከመምህር ከሚማሩ ሕፃናት ጋራ እያለ እርስ በርሳቸው በመጫወት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየሠሩ ከእነርሱ ውስጥ ዲያቆናትን ኤጲስ ቆጶሳትንም ሲያደርጉ እሊያን የክርስቲ ያንን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእሳቸው ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እነርሱም አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት እርሱም ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው እነርሱም ደስ ተሰኙበት።】
ወነሥእዎ አሜሃ ወረሰይዎ አምሳለ ሊቀ ጳጳሳት ወመትሕቲሁ አምሳለ መንበር። ወእኀዙ ይስግዱ ሎቱ ወበውእቱ ጊዜ ኀለፈ አባ እለእስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት። ወሶበ ርእዮሙ ለውሉደ ክርስቲያን እንዘ ይትዋነዩ ይቤሎሙ ለእለ ሀለዉ ምስሌሁ ወለዎ ለዝንቱ ሕፃን ይሠየም ሢመተ ክብርተ ወልዕልተ።
【ያን ጊዜም ወስደው በሊቀ ጳጳሳት አምሳል አደረጉት ከበታቹም ወንበር አድርገው ይሰግዱለት ጀመር። በዚያን ጊዜም ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ በዚያ አለፈ የክርስቲያን ልጆች ሲጫወቱ በአያቸው ጊዜ አብረውት ላሉ ይህ ሕፃን ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች ሹመትን ይሾም ዘንድ አለው አላቸው።】
ወንድማለም እንግዲህ ስማ መሾም ስለምትፈልግ ብቻ አትሾምም! እንኳን ሢመቱ ጭውውቱም ቢሆን ሥርዓት አለው። እንዳየኸው ጥንቱን የገሃዱ ሢመት ቀርቶ የሕጻናቱ ተውኔት እንኳ ደርዝ ነበረው! መጽሐፉም ቢሆን እንኳን ራስህን በቦታው ልታስቀምጥ በቦታው ተቀመጥ እንኳ ቢሉህ እምቢኝ በል ነው የሚል።
【"ኢመፍትው ለመኑሂ እምሰብእ ይምሥጥ ሢመተ ክህነት ለርእሱ አላ ለእመ ተውህበ እምእግዚአብሔር ☞ #የክህነትን_ሹመት ከእግዚአብሔር ካልተሠጠው በቀር ከሰው ወገን ማንም ለራሱ ይገባኛል ብሎ ቀምቶ እጅ አያድርጋት" መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ ፩፥፷፩】
ዛሬ የሕጻናቱን ያኽል ድፍረት አጥተን መሰል እምነት የሌለው ኢጥሙቅ ልብሰ ጵጵስና ለብሶ ሲተውን አይተን ዝም ከማለት አለፍንና በበር ያልገቡ «መስኮተኞች» አይደለም ጵጵስናው ፕትርክናውም ሳይቀር ይገባናል ሲሉ እየሰማን «ሃይ–ባይ» አለመገኘቱ በእጅጉ ያሳዝናል። «ኧረ ተዉ» የሚል መገስጽ ብቅ ሲል ተቆጪውን መቆጣት ከመንገድ ማጥፋት ሥራችን ሆኖ አረፍነው።
ኧረ ጉድ የዚያ ዘመን የእስክንድርያ ሕጻናት እንዴት አድርገው እንደሚበልጡን እዩልኝማ
«ሰአሎሙ ዝንቱ አብ ለውሉደ ክርስቲያን ከመ ይሳተፍ ምስሌሆሙ በተላህዮቶሙ። ወከልእዎ ወይቤልዎ እስመ አንተ አረማዊ ኢንዴመር ምስሌከ ☞ #እሊያን_የክርስቲያን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእነርሱ ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እነርሱም አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት »
እንዲህ ያለውን ጨዋታ ወዳጅ ፡ አልፎ ሂያጅ «ና ግባና ጰጵስ» ለሚሉ ድንበር አፍራሾች እንዲህ ባለው የሌባ መንገድ እንዳልመጣ የምናውቀው ራሱ ቅዱስ አትናቴዎስ በድርሳኑ "ንሕነሰ ኢንኌልቆ ምስለ ክርስቲያን አላ ምስለ አረሚ ወዐላውያን ☞ እኛ ግን እንዲህ ያለውን ከማያምኑና ከሚያምጹት እንጂ ከክርስቲያን ወገን እንኳ አንቆጥረውም!” እያለ ይዘልፋል 【ሃይ አበው ፳፱፥፲፭】
አባ ጊዮርጊስ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታና የእግዚአብሔር ምርጫ የሆነውን ሹመት በራሱ ጳጳስ ነኝ ይገባኛል ለሚል ንሥጥሮሳዊ በላከው ተግሳጽ ይህን ይላል ፦
እፎ ተኀረይከ ለጵጵስና ?
ዘኢተቀደስከ በማኅተመ ክርስትና
እፎ ተኀረይከ ለተክህኖ ?
ዘኢተሠርጎከ በተአምኖ
【በክርስትና ማኅተም ያልከበርህ ለጵጵስና እንዴት ተመረጥህ፡ በመታመን ያልተሸለምህ ሆይ እንደ ምን ለክህነት አገልግሎት ተመረጥህ ?】
【መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፮】
«ወአንተሰ ተመሰልከ ተክለ ዘእንበለ ፍሬ: ወዖመ ዘእንበለ ቈጽል: ፈለገ ዘእንበለ ውሒዝ : ወዐዘቅተ ዘእንበለ ማይ፡ ንጉሠ ዘእንበለ ጌራ መንግሥት : ሐራዌ ዘእንበለ ንዋየ ሐቅል : ደመና ዘእንበለ ዝናም : ወሰዊተ ዘእንበለ መስበልት : አበ ዘእንበለ ሀብተ ሲሳይ : ወእመ ዘእንበለ አጥባት : ንድቀ ዘእንበለ ተድባብ : ወኆኅተ ዘእንበለ ማዕፆ : መርዓዌ ዘእንበለ አክሊል : ወመርዓተ ዘእንበለ ባዝግና : ካህነ ዘእንበለ ኤፉድ : ምሥዋዐ ዘእንበለ ቊርባን : ኖትያዌ ዘእንበለ ሥርዐተ ሐመር : ወምሥያጣዌ ዘእንበለ ንዋይ : ሠረገላዌ ዘእንበለ ድርዐ ሐጺን : ወፈረሳዌ ዘእንበለ ኲያንው! እፎ ተኀረይከ ለጵጵስና ? ዘኢተቀደስከ በማኅተመ ክርስትና ፣ እፎ ተኀረይከ ለተክህኖ ? ዘኢተሠርጎከ በተአምኖ »

❤19👍12
☞ አንተ ግን ፍሬ በሌለው ተክል ፣ ቅጠል በሌለውም ዛፍ ፣ ፈሳሽ በሌለው ወንዝ ፣ ውኃ በሌለው ጉድጓድ ፣ የመንግሥት ዘውድ በሌለው ንጉሥ ፣ የጦር መሣሪያ በሌለው ወታደር ፣ ዝናም በሌለው ደመና ፣ ፍሬ በሌለው እሸት ፣ ለምግብ የሚሆን ሀብት በሌለው አባት ፣ ጡቶች በሌላት እናት ፣ ጣሪያ በሌለው ሕንፃ፡ መዝጊያ በሌለው ደጃፍ፡ አክሊል ባልደፋ ሙሽራ ፣ ጌጥ በሌላት ሙሽሪት፣ ልብሰ ተክህኖ በሌለው ካህን ፣ ቁርባን በሌለው መሠዊያ ፣ የመርከብ ሥርዓት በማያውቅ ዋናተኛ ፣ ገንዘብ በሌለው ገበያተኛ ፣ የብረት ጥሩር በሌለው ባለሠረገላ፣ ጦሮች በሌሉት ፈረሰኛ ትመሰላለህ ! በክርስትና ማኅተም ያልከበርህ ለጵጵስና እንዴት ተመረጥህ? በመታመን ያልተሸለምህ ሆይ እንደ ምን ለክህነት አገልግሎት ተመረጥህ?
Let us look from the beginning at that very tradition, teaching, and faith of the «Orthodox Church» which the Lord gave (εδωκεν), the apostles preached (εκηρυςαν) and the Fathers preserved (εφυλαςαν). Upon this the Church is founded. 【Athanasius of Alexandria (First Letter to Serapion, 28)】
በቃን ማለት አልቻልንበትምና ሥሉስ ቅዱስ ራሱ በቃችሁ ይበለን!
✍☞ ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ. ም. የተጻፈ
📍ከሀረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል

👍20❤16