Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተሰጠውን መግለጫ ከሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ደርሶናል እንደሚከተለው ይቀርባል።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ቤተክርስቲያን ህገና ሥርዓትን ለማስከበርና አሰራሯን ዘመኑን በማመጥን መልኩ ለማስተካከል የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች::
************
ጥንታዊት ፣ታሪካዊት፣ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የህግ፣የሥርዓት፣የእውቀት፣የጥበብና የሥልጣኔ መሰረት እንደሆነች የማያውቅ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም።

ይህች ጥንታዊት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከማንም ቀድማ ህግና ሥርዓትን ተክላ፣አሰራሮችና የማስፈጸሚያ ደንቦችን ደንግጋጋ፣ለአሰሯሯ የሚጠቅሟትን መዋቅሮች አደራጅታ ሥራዎቿን የምታከናውን ስንዱ ተቋም እንደሆነችም ይታወቃል።

ይህንን ህጋዊና ተቋማዊ አሰራር አክብሮና አስከብሮ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷ እንዲሳለጥ በማድረግ በመልካም አርአያነታቸው የሚጠቀሱና የሚመሰገኑ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ ህግና ሥርዓትን ከለላ በማድረግ ከቤተክርስቲያናችን ጥንታዊና ታሪካዊነት ጋር በፍጹም የሚጻረሩ መንፈሳዊ ተቋምነቷን የማይመጥኑ ተግባራትን በመፈጸም ቤተክርስቲያንን የማይመጥኑ ምዕመናንን የሚያሸማቅቁና መንጋዎቻችንን የሚበትኑ ተግባራትን በመፈጸም ቤተክርስቲያን አንገቷን እንድትደፋ የሚያደርጉ ኢ- ቤተክስቲያናዊና ኢ-ቀኖናዊ ሥራዎች በአንዳንድ የቤተክርስቲያናችን መዋቅሮች እየተሰሩ እንደሆነም የአደባባይ ምስጢር ነው።

ይህን አይነቱን ተግባር ማውገዝ፣መኮነንና መጠየፍ ካልተቻልን ለተቋማዊ ህልውናችን ቀጣይነት ብቻ ሳይሆን ለአገራዊ ሰላምና ልማት በተቋም ደረጃ የምናበረክተው በጎ አስተዋጽኦ ስለማይኖር በአዲሱ ትውልዱ ዘንድ የቤተክርስቲያን ቀጣይነት አደጋ እንደሚገጥመው ምንም ጥርጥር የለውም።

ስለሆነም ቋሚ ሲኖዶስና የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ቤተክርስቲያናችንን የማይመጥኑ፣
በመንፈሳዊም ሆነ በማኅበራዊ አገልሎታችን ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አሰራሮችን ሁሉ በመመርመርና ከሥሩ ነቅሎ በመጣል የቤተክርስቲያናችንን ክብርና ልዕልና በሚመጥኑ ህገዊ አሰራሮች በመተካት ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀትን ለመፍጠር የሚያስችሉ በጥናት ላይ የተመሰረቱ ርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችለውን ስልት በመቀየስ ወደ ተግባር ገብቷል።

ይህንን ተከትሎ በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተቃረበ ቁጥር ከህጋዊና ተቋማዊ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ የሚደረጉ ሰልፎችና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፊርማዎች የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ ከማወካቸውም በላይ ለከተማችን የጸጥታ መዋቅሮች ተጨማሪ ችግር እየሆኑ የሚቀጥሉበት ሁኔታ ማብቃት ይኖርበታል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት እገሌ እንዳይነሳብን በሚል የክፍለ ከተማ ቤተክህነትን፣የአድባራትና ገዳማት ማኅተሞችንና በቤተክርስቲያን ኃላፊነት የተቀረጹ የስም ቲተሮችን ጭምር በመጠቀም ሲከናወኑ የነበሩ ቤተክርስቲያናችንን የሚይመጥኑ የድጋፍ ማሰባሰብ ተግባራት በከተማችን የጸጥታ ችግርን የሚፈጥሩ ጭምር በመሆናቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም።ይህን ድርጊት የፈጸሙና የሚያስፈጸሙ ሁሉ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ከመግለጽ ጋርም ቋሚ ሲኖዶስና የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያካተተ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ሁሉም ነገር በሕግና በሥርዓት የሚፈጸም በመሆኑ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት እየተካሄዱ ያሉ አላስፈላጊ ግርግሮችና የፊርማ ማሰባሰቦች ከቃለ ዓዋዲውና ከቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኖናና መንፈሳዊ ድንጋጌ ውጭ ስለሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆሙ፤

ተለዋጭ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ምንም ዓይነት የቅጥር፣የዝውውር እና የዕድገት ሥራዎች የታገዱ መሆናቸውን፤

የጥቅምት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የሚካሔዱት ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት ተጠናቀው ተለዋጭ መመሪያ አሰስከሚተላለፍ ድረስ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ አድባራትና ገዳማት የሰበካ ጉባኤ ምርጫን አስመልክቶ በቃለ ዓዋዲው ድንጋጌ መሰረት ማከናወን የሚቻልበትን የቅድመ ዝግጅት ሥራን ብቻ እያከናወኑ እንዲቆዩ፤

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አለአግባብ የተፈጸሙ ብልሹ አሰራሮችን ማለትም የቅጥር፣የእድገት እና የዝውውር አፈጻጸሞችን ፣የፋይናንስና የሀብት ብክነቶችን እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ በሚገባ ተጣርተው እንዲቀርቡ፤ይህንንም የሚያከናውኑ ሦስት የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችን ያቀፈ አጣሪ ልዑክ መድቧል።

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጥቅምትና ግንቦት ወራት የሚከናወነውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያትን ተከትሎ የቤተክርስቲያናችንን ሕግ በሚጻረር መልኩ አድማ በማድረግ ፊርማ በማሰባሰብ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ቤተ ክርስቲያንና አገርን በሚያውክ መልኩ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ፤ይህ ካልሆነ ግን የጠቅላይ ቤተክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ እንዲሰራ፤

በዚህ የግል ፍላጎትን ለሟሟላት ሲባል እየተካሔደ ባለው አድማ በሕጋዊ መንገድ ለቤተክርስቲያን መገልገያነት የተቀረጹ ክብ ማኅተሞችንና የስም ቲተሮችን ለአድማ ሥራ ማዋል ፍጹም የተሳሳተና ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ የቤተ ክርስቲያን ማኅተሞችና የስም ቲተሮችን ለህውከትና አድማ ሥራ መጠቀም በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ማንኛውም አካል ከእንዲህ ዓይነት ተግባር እንዲታቀብ። ይህንን መመሪያ ተላልፈው በተገኘት ላይም አስፈላጊው የሕግ ክትትል እንዲደረግ ሲል ቋሚ ሲኖዶስ ወስኗል።

ህዝበ ክርስቲያኑም ይህ ውሳኔ የተላለፈው የቤ ተክርስቲያንን ክብር ለማስጠበቅ፣ሕግና ሥርዓትን ለማስፈን፣ የቤተ ክርስቲያንን አሰራር በማስተካከል ልዕልናዋን ለማረጋገጥ መሆኑን በመገንዘብ ለቋሚ ሲኖዶስና ለጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ ተግባራዊነት ከጸሎት ጀምሮ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ቋሚ ሲኖዶስም ሆነ የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው ግለሰቦችን ለማጥቃትና ለማሳደድ ሳይሆን ሕግና ሥርዓትን በማስፈን የቤተ ክርስቲያናችንን አሰራርን ለማስተካከል መሆኑን ያልተረዱ አንዳንድ ወገኖች በጎጥ በመደራጀት የሚያደርጉት አፍራሽ እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያናችንን የማይመጥንና ቤተ ክርስቲያናችን ድንበር የሌላት ብሔራዊትና ጥንታዊት ተቋም መሆኗን ካለመረዳት የሚመነጭ ነው።በዚህ ድርጊት የተሰማሩ ወገኖችም ከጎጥና ከጎሳ እሳቤ በመውጣትና ታላቋን ቤተክርስቲያናችንን ማዕከል በማድረግ ቤተክርስቲያንን ለመታደግ የሚደረገው ተቋማዊ ጥረት ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ቢያመላክቱ የተሻለ ይሆን ነበር።
👍14
በተለይም በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የሚካሄደውን የማጣራት ሥራን ተከትሎ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚዘገቡ ግለ ሰብ ተኮር ድጋፍና የስም ማጥፋት ዘመቻዎችም የቤተክርስቲያናችንን ልዕልና፣ሕግ ማስከበርና መልካም አሰራር መስፈንን በመቃወም ሕገ ወጥና ጥቅም ተኮር አሰራር እንዲቀጥል ከመፈለግ የሚመነጭ በመሆኑ በእጅጉ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። ይልቁኑም ማዕከል መደረግ ያለባት ቤተክርስቲያን መሆኗን በመገንዘብ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የሚደረገው ተቋማዊና ሕጋዊ ጥረት ፍሬ የሚያፈራበትን መንገድ በማመላከት መንቀሳቀስ በተገባቸው ነበር።

በመጨረሻም መላው ኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናንና ምዕመናት ሕግና ሥርዓት እንዲከበር፣የቤተክርስቲያናችን ልዕልናና ክብር እንዲጠበቅ በተለያዩ መንገዶች የምታነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት መጀመራቸውን በመረዳት ቤተክርስቲያናችን ለምታደርገው አሰራርን የማስተካከል ተቋማዊ እንቅስቃሴ ስኬታማነት በመጸለይ የልጅነት ሚናችሁን እንድትወጡ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን እያስተላለፈች ማንኛውም አይነት ሕጋዊ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሕጋዊውን የቤተክርስቲያን መዋቅርና አሰራርን በጠበቀና ፍጹም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን በተላበሰ መንገድ ጥያቄአችሁን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ
ተቢገቢና ትክክለኛ ምላሽ የምታገኙበት አሰራር የተዘረጋ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
መስከረም ፴ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
• አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
👍1
'ከወቀሳ በፊት ምክር ይቅደም፦'

"ለክርስትና መቆርቆርና በክርስትና ስም መነቆር ይለያያል። የተሳሳተን መመለስ የተጣመመን ማቅናት የወንድምን ድካም መሸፈን የክርስቲያኖች ባህሪ ነው ፤ መጀመሪያ ምክር ነው የሚቀድመው ከወቀሳው ።

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ፤የቤተክርስቲያን ለዛ ያሬዳዊው ውበት ጠፍቷል ፤ አዳራሽ እንድንለማመድ ከዓውደ ምሕረት እንድንርቅ መሳለም መስገድ መዳበስ እንድንተው አደጋ አለው ብሎ አሳብ ማቅረብ ይቻላል።

አሳብ ሰጥቶ አስተያየት አቅርቦ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ እርምት እንዲደረግባቸው አካሄዱን በመለየት በጥበብ ሴራም ካለው አክሽፎ ተንኮል ካለው በቅንነት አሸንፎ እሺ ካለ በፈሊጥ እንቢ ካለ በፍልጥ ልኩን ማሲያዝ ይቻላል።

አዋቂ መሳይ የእምነት ተቆርቋሪ፣ ሆኖ ከአዋቂዎች በላይ ተሟጋች ሆኖ መቅረብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው ፤ በስሜት ሳይሆን በስሌት መሄዱ የተሻለም ነው ባይ ነኝ።..."
-
👍231
✥ . ✥ . ይመስገን "ፈጣሪ" . ✥ . ✥
. ¯\_(ツ)_/¯
. [)(]
. _| \_

ዛሬ ከአንዲት ትዝብት ጋር ነው ብቅ ያልኩት። መቼም አዲስ ነገር ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ጉዳይ እንደሌላቸው የአቴና ነዋሪዎች " ምንተ ይፈቅድ ዝዘራዔ ነቢብ … ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? " እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ! 【ሐዋ ፲፯፥፲፰】 እነርሱስ ‘የማይታወቅ አምላክ’ ተከታዮች ናቸው፤ እኛ ግን በከበረ ሥልጣን በተለየ ስም የምናውቀውና የምናመልከው ታላቅ ፈጣሪ የከበረ አምላክ "ሥሉስ ቅዱስ" ያለን ነን።

በሰዎች ዘንድ አንገት ከሚያስደፉን ፣ "በማንነታችን" እንዳንኮራ ከሚያሸማቅቁን ተግባራት መኻል ፦
🍂 ስመ እግዚአብሔርን በክብርና በልዩነት ደፍሮ ለመጥራት መጨነቅ፣
🍂 ከመቅደሱ ደጃፍ ቆመን አልያም በአንጻረ ቤተክርስቲያን ስናልፍ ፣ ማዕድ ፊት ስንቀርብ ፣ ስንደነግጥ … ለማማተብ መሳቀቅ
🍂 በአንገታችን ያሠርነውን ማዕተብ መደበቅ አልያም ማውለቅ…

ዛሬ (ጥቅምት ፫) ቤተክርስቲያን ጽንሰቱን የምታከብርለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በረከቱ ይደርብንና በመጽሐፈ ምሥጢር ይህን " ሥርወ መሪረ ዘኀደገ ለነ ክርስቶስ ☞ ክርስቶስ የተወልን መራራ ሥር" ይለዋል።

"ኀደገ ለነ ሥርወ መሪረ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ምንት ውእቱ ሥርው መሪር ዘእንበለ ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ በኀበ ሰይጣን እምዝክረ ስሙ ይርዕድ ወእምዑታቤ መስቀሉ ይነፍጽ [ዝ ውእቱ መሪር ብሂል]"

"ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመር ሥርን ተወልን፤ ቅዱስ ስሙን ከመጥራት በሰይጣን ላይ በመስቀል ከማማተብ ሌላ የሚመር ሥር ምንድር ነው። ከስሙ መጠራት የተነሣ ይንቀጠቀጣል በመስቀሉ ከማማተብም የተነሣ ይሸሻልና [መሪር ማለት ይህ ነው! ]" 【መጽሐፈ ምሥጢር ፳፪፥፱】

ታድያ ለሰይጣን የሚመረው "ጽዋዔ ስሙ ቅዱስ ወዑታቤ መስቀሉ ☞ ቅዱስ ስሙን መጥራትና በቅዱስ መስቀሉ ማማተብ" ለእኛም እንዴት መረረን? የዛሬው መነሻዬ የስሙ ጉዳይ ብቻ ነው (ሌላው ሌላ ጊዜ እናሰንብተው) ፤

አምላክ / ፈጣሪ ማነው? የእኛ አምላካችን ፣ ፈጣሪያች ፣ ጌታችን የከበረ ስም የለውም ይሆን? ስሙን መጥራትስ ለምን እያሳፈረን መጣ?

ለእኔ አስማተ መለኮትን (የመለኮትን ስሞች) እንዳንጠራ የቃናዎቹ ቱርክ ፊልም ተርጓሚዎች ያለማመዱን ከፖለቲከኞች (በተለይም "ከአበልጻጊዎቻችን") ና ከ "ሁሉን እናስደስታለን" ባዮች የወረስነው ክብር የማንሰጥበት ስሁት መንገድ መስሎ ታይቶኛል።

☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ይመስገን ፣
☆ ፈጣሪ/ አምላክ / ጌታ ኢትዮጵያን ይባርክ ፣
☆ እንደ ፈጣሪ / እንደ አምላክ / እንደ ጌታ ፈቃድ ፣
☆ አምልኮተ ፈጣሪ / ፈሪሃ አምላክ … የሚሉቱ መገለጫዎቻችንን በመደበቅ ፣ ስለሌሎች በመጨነቅ ፣ አብሮነትን በማድነቅ ፣ ለምስክርነት በመሳቀቅ ዋጋ እያሳጡን ያሉ አካኼዶች መሆናቸውን አጢነነው ይሆን? እንጃ!

« ምንችግር አለው? አታካብዱ…¡ » ለምትሉ ፤ ሳትቸገሩ ከብዳችሁ እንድትኖሩ ሳታፍሩ የከበረ ስሙን ጥሩ!

"ስምህ ይቀደስ" 【ማቴ. ፮፥ ፲】የምንለው! የአምላካችን እናቱ ለትውልደ ትውልድ የሆነ ምሕረቱን ስትመሰክር "ስሙም ቅዱስ ነው! " 【ሉቃ. ፩፥፵፱】ያለችው … የወል ስም ሳይሆን "ወላዲ ተወላዲ ሠራፂ" በሚባልበት ግብር የሚታወቅ አባት (አብ) ልጅ (ወልድ) እና መንፈስ ቅዱስ የሚባል የተለየ ስም አምላካችን ስላለው ነው።

☞አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፣ እግዚአብሔር ፣ ሥሉስ ቅዱስ!

“ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።” 【መዝ. ፳፪፥፳፪】

በጉባኤ መኃል ያልጠራነውን ስም ቢያንስ በተናጥል ስንገናኝ ፣ በግል የስልክ ጥሪዎችቻችንና በውሥጥ የጽሑፍ መልእክት እስክንሸማቀቅበት አልያም በቸልታና በልምድ ስንተወው መታየታችን ያሳዝናል።

የሚያሳፍረው ስሙን አለመጥራት እንጂ ለመክበር የከበረ ስሙን መጥራትስ አልነበረም!

"ስሙን አግኑት በምግባር በሃይማኖት ጸንታችሁ ለጌትነቱም ተገዙ … አሁንም በፍጹም ልቡናችሁ በፍጹም አንደበታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት ስሙንም ሁልጊዜ አመስግኑት"【ሲራ። ፴፱፥፲፭/፴፭】

ስለዚህ የተዋህዶ ልጆች ሁል ጊዜ ስሙን እንዲህ እያልን ማመስገን ይገባናል ፦

"ይክበር ይመስገን ሥሉስ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ይመስገን ፣ ክብር ምስጋና ለቅድስት ሥላሴ ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን! "

እናስተውል የጣኦታትና የአጋንንትን ስም መጥራት እንደሚያረክሰው ሁሉ የአምላክን ስም መጥራትም ይቀድሳል።

"ዳግመኛም የአማልክትን የጣዖታትን ስም በአፋቸው አይጥሩ ፣ ፡ሰይጣንንና መላእክቱንም አይጥሯቸው ፣ ስሙንም በጠሩ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ይለያልና ፣ በእርሱ ፈንታም መንፈስ ርኩስ በላያቸው ያድራል ።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፳፯፥፬】

መንፈስ ቅዱስ የሚያቀርበውን ፣ ረድኤተ እግዚአብሔር የሚያሳድረውን ፣ ርኩሳት መናፍስት እኩያት አጋንንትን የሚያርቀውን ስም በክብር ጠርተን በስማችን በክብር እንድንጠራ እርሱ ይፍቀድልን ይርዳንም።

አንብባችሁ ስታበቁ እግረ መንገድ ይኽን መልሱልኝ "ባላችሁበት ሀገር የሠዓት አቆጣጠር እንደምን አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? እንደምን ዋላችሁ? እንደምን አመሻችሁ? "

አንድነቱን ሦስትነቱን ካለማወቅ ወደማወቅ የከበረ ስሙን ካለመስማት ወደመስማት ያደረሰን አምላካችን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይክበር ይመስገን። በቅዱስ ስሙ ለመቀደስ ያብቃን 🙏 በቸር ያሰንብተን !

[ከቴዎድሮስ በለጠ ✍️... ጥቅምት በዓታ ፳፻፲፭ ዓ·ም·]
👍158
የድንግል ማርያም ልጆች (ሐራዊ) ORTHODOX TEWAHIDO:
የጠፋው ልጅ

    ስለ ጠፋው ልጅ ታሪክ ስንነጋገር በዚህ ታዳጊ ወጣት የእያንዳንዳችን ምስል በጥቂት እንመለከታለን።

ምንም እንኳን ታሪክ ቢሆንም እኛ ማን እንደሆንን ምን እንደምናስብ አመልካች ነው።መልካችንን ያሳየናል፣እኛ ራሳችንን ከምናውቀው በላይ እግዚአብሔር እያንዳችንን የበለጠ ያውቀናል።

ይኽንን ታሪክ ስናዳምጥ ስቶቻችን ሕይወታችንን ቆም ብለን መርምረናል።መልካም ይህ ታሪክ የእኔ ሕይወት ይመለከታል ብለን ያሰብንን ስንቶቻችን ነን?

   አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት ወጣቱ ልጅ አባቱን እንዲሁ አለው"አባቴ ሆይ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠ   ኝ አለው።

"(ሉቃ 15፥11-15)።ገንዘቡን ከፍሎ ድርሻውንም ሰጠው።ስቶቻችን እግዚአብሔርን "የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ ብለን ጠይቀነዋል?እንደአባትነቱ ከእግዚአብሔር ጋር ልንነጋገር ይገባል።ተገቢም ነው።

አንዳንድም ጊዜም እንደ ጠፋው ልጅ ምሳሌ ስ ሜታዊያን ሆነን ስሜትን ተላብሰን እግዚአብሔርን የማይገባ ነገር ልንጠይቀው እንችላለን።እርሱ ለእኛ ባለው ፍቅር ምክንያት ልመናችንን ይሰማል።

ፈቃዳችንንም ይፈጽማል።ታማኝነቱም፣ርኀራኄው ለእኛም ያለው ምህረት ይፈቀድነውን ይፈጽምልን ዘንድ ይደርገዋል።አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን ድርሻችንን አድርገን ልንመለከት እንችላለን።

ነገር ግን ሁልጊዜ እግዚአብሔር ስንጠይቀው ስጦታችን ልናስታውሰው የሚገባ ታላቅ ነገር አለ።እርሱም በመስቀሉ ላይ በደላችንን በእንጨት ላይ ባይሸከምልን ኑሮ ከገንዘብህ የሚደርሰንን ክፍል ስጠ ኝ ብለን ለመጠየቅ ባልተቻለን ነበር የሚል ነው።እኔ ምንም ድርሻ አልነበረኝም።

የወደቀው አዳም ነ ኝ።የኔ ድርሻ ይህ ዓለም ነበር።

እርሱ ግን በመስቀል ላይ በተደረገ ሕይወትን በሚሰጥ መስዋትነቱ በእግዚአብሔርም ጸጋ እኔ እኔን መሆን ተችሎኛል።

እርሱም የእግዚአብሔር ልጅነት ነው።አሁን የልጅነት ሳልጣን አለኝ።ስለዚህ "የሚደርሰኝን ክፍለህ ስጠኝ"እንደሚል እንደጠፋው ልጅ አልሆንም።

ጌታ እንዲህ በማለት ይመልስልሀል"ድርሻህን የሚገባህ በመስቀል ላይ ሰጥቼሀለው።

ድርሻህን ስለሰጠሁህ ከእኔ ጋር ልትቆም ይገባሃል።ይኸንን ድርሻ በዚህ ልታጠፋው አይገባህም ወደ ሌላ ሥፍራም መሄድ አይቻልህም።

በውጭ ያለው ዓለም ምን ዓይነት ዓለም እንደሆነ አውቀዋለሁ።

ለዚህ ነው ሰላምና ደኃንነት ያሉትን ሰማይ የሰጠሁህ።ሊዚህ ዓለምና ከሚመጣው ዓለም ደስታህ ፍጹም ይሆንልህ ዘንድ።"

     ምድራዊው አባት ገንዘቡን አካፈለው።የእግዚአብሔር ሩኀሩኅነት እንመለከታለን።በአባት የተመለሰውን የቱንም ይህል ከእርሱ ጋር ብንነጋገር እርሱ ሰውን ስለሚወድ፣ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ፣ቸር ራሱን እስከመስቀል ድረስ አሳልፎ የሰጠ ታማኝ ሆኖ እንመለከታለን።እንዲህ አለ ድርሻህን ትፈልጋለህ?ያንተ ድርሻ ይኸው።በአንድ መልኩ ድርሻችንን ይሠጠን ዘንድ በሌላ መልኩ ወደ እርሱ እንመለስ ዘንድ በመሥኮትል ላይ ተቀምጦ ይመለከተናል።የእግዚአብሔር ድምፅ እንዲህ ይላል"እውድሃለው ለአንተ የማስበው ነገር መልካም የሆነውን ነገር ነው።እኔ የማልወስድብህ ነጻ ፈቃድን በአንተ ውስጥ አስቀምጫሁ።"

    ነገር ግን በዚህ ተቀምጬ እስክትመለስ ድረስ ፈቃድህንም አሳልፈህ እስክትሰጥኝ ደረስ እጠብቅሃለሁ።

ይቀጥላል

# ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

የጠፋው ልጅ  ክፍል 2

ጠፍተህ ልትሄድ እንደምትችል አውቃለሁ።ለጥፋትና በኃጢአት ሕይወት እንደምትኖርም አውቃለሁ።ነገረ ግን ጥ በበኛ ሆነህ ወደ እኔ ወደ አባትህ ቤት ትመለስ ዘንድ እጠብቅሃለሁ።የጠፋው ልጅ ብዙ ስለቸገረ ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ አሰበ።(ሉቃ11፥13)ረጅም ጊዜ አልፈጀበትም።እኛ ወደ ኃጢአት ለመሮጥ ምን ያህል እንፈጥናለን?ከእግዚአብሔር  ለመራቅ ሕይወታችንን በችግር መካከል እንዲሁም በፈተና ውስጥ የምናልፍበት ጊዜ ምም ያህል ነው?

     ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም ማድረግ የሚገባውን ነገር ምን እንደሆነ አላሰበም።አንዳንድ ጊዜ በኃጢአት ጊዜያዊ ደስታ እንታውራለን።ውጤቱን አናስታውሰውም።ከመሄዱ በፊት ጥቂት ቀናት  ስለነበሩት በነዚያ ጊዜያት ማድረግ የሚገባውን ነገር ማሰብ ነበረበት።በአባቱ ቤት የምኖረው በምጽዋት ነበርን?ብሎ ማሰብ ሁሉ ይጠበቅበት ነበር።በዚህ መኖር እወዳለሁ።ደኃንነት ይሰማኛል፣ይወደኛል እኔም እወደዋለሁ አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ ይህ ታላቅ ጥፋት ነው በማለት ነበረበት።ከአንተ የወሰድሁት ይኸው።በዚህ ሥፍራ በመልካም ድኅንነት እኖራለሁ ማለት ነበረበት።ይሆነው ግን ይህ አልነበረም።አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት ላለመስራት እንቃወማለን።ውሳኔ ከወሰንን በኋላ  በውሳኒያችን የተወሰነ ጊዜ እንጸናለን።ከጥቂት ቀንም በኋላ ትንሹ ልጅ ገንዘቡን ሰንስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።የደረሰበትን ነገር እናውቃለን።እንደምታውቁት ብዙዎቻችን ኃጢአትን የምንሠራ ብቻ አይደለንም።ኃጢአትን ጽድቅ ለማድረግ የምሰራም ነን እንጂ።በነበረበት በሩቅ አገር ሀብትና ንብረቱን በተነ።አሁን ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ለመገመት አዳጋች አይሆንም፤

አስቀድሞ በአባቱ ቤት ነበረ።የአባቱን ቤት በፈቃዱ ተወ።ወደ ሩቅ አገር ሄደ።ሁሉንም  ነገር አጣ።ገና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ኃብቱን አጣ  በጥፋት ሕይወት ውስጥ የያዙት ሁሉ ማጣት የተለመደ ነው።

     በእግዚአብሔር ቤት በምንመላለስበት ወራት ክርስትና የሚሰጠን የጸጋ ሀብት አለ።ይህ የተትረፈረፈ ሀብት ነው።ነገር ግን የሚያጠፉት አይደለም።ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ በመካፈላችን ልክ የራሳችንን ገንዘብ እንደሚጨምር የመንፈስ ቅዱስና ሀብትን እንቀበላለን።ከንሥሐ ብዙ እናተርፋለን።ኪሳችንንም በተትረፈረፈ ጸጋ እንሞላለን፣ከዚያ ወደ ጎዳና እንወጣለን።አንድ  ነገር እንደነበረ እናውቃለን።የሚጠቅመኝን ነገር አጥብቄ ይዤ ቢሆን ኑሮ ወደ  ፈተና ባልገባሁ ነበር።ይህ ማለት ከተሰጠኝ ጸጋ የተወሰነውን እከፍላለሁ ማለት ነው።ያንን አልፌ ሌላ የምትፈተንበት ሁኔታ ያጋጥመኛል።አልዋሽም መዋሸት ኃጢአት ነውና እላለሁ።

    መዋሸት የተወሰነ ዋጋ እንድከፍል ያደርገኛል እንዲህ እያለ ይቀጥላል።ስለዚህ በማንኛውም ጊዜ በፈተና መካከል ቁሜ አልበድልም እላለሁ ያም ዋጋን ያስከፍለኛል።በኪሴ ውስጥ ያጠራቀምኩትን ጸጋ ጨርሼ የቆምሁ ሁኛለሁ።ለምን?ምክኒያቱም ጤናማ በሆነ ጊዜ እከፍላለሁ በተመሳሳይ ሁኔታ እቀበላለሁም።ስለዚህ በኪሴ ውስት የሚፈጠሩ ገንዘብ ይኖረኛል።ነገር ግን ይለኝን ሁሉ በምከፍልበትና ወደ ኪሴ የሚገባ አንዳች ነገረ  በማይኖርበት ሁኔታ የጠፋው ልጅ እንዳደረግው ሁሉንም ነገር ይጣሁ እሆናለሁ።

ከአባቱ ቤት የወሰደው ማንኛውም ነገር፣ከርሱ ጋር የነበረው የገንዘብ ከረጢት አሁም ባዶ ሆኗል።የጠፋው ልጅ ያለውን ነገር ከጨረሰ በኋላ በዚያች አገር ረኻብ ተነሣ።(ሉቃ11፥14)ሰይጣን ሐሰተኛና የሐሰት አባት ነው።እድንኮበልል ያደርገናል፤የውሸት ሰላምን ይሰጠናል፤ይፈትነናል፤ባዶ ተስፋን ያሣየናል በመጨረሻ የምትሰጡት አንዳች ነገር ሲጎድላችሁ ይጥላችኋል።በድንገት ረኻብ ሆነ።ለምን አሁን ሰይጣን የማይፈልገን የማንጠቅመው ሆነናል።ወደሩቅ አገር ወስዶናላ፤የውሸት ሰላምና ጸጥታ የሚመስል ነገርን ሰጥቶናል።ሰይጣን ወደ ሩቅ አገር ሂድ እውነተኛ የሆነ የመረጋጋት ጊዜን በዚያ ታሳልፋለህ ይልኻል።ምንም አይነት ዕንቅፋት አይገጥምህም።ከአንተ ጋር እንሁን አብረን ወደ ሩቅ አገር እንሂድ ያላል።ተመልከት ልዩ የሆነ ምቾት አለ ይላል።ገንዘብ ከራቀ በኋላ ግን እንዲሁ ይላል።
👍8
ከዚህ በኋላ ብዙ የምትጠቅመ ኝ አይደለህም በሩቅ አገር አድርሶ ተስፋችን ጨርሶ እንዲሟጥት ያደርገናል።የምንመልሰው እንዳች አይኖረንም አስቀድሞ የፈተነን እንጠመድበት የነበረው ነገር ተመልሶ የምንጠመድበት ኃጢአት ሆኖ ይቀርባል።በርቀት ነኝ የሚለውን አሳብ ስንመለከተው መልካም አሳብ መስሎ ይታየናል።ምክንያቱም ከአባቴ ቤት ርቄ በራሴ ለመቆም እንደሚቻለኝ አስመስሌኛልና።እውነታው ግን ከአባቴ ቤይ ርቄ የሄድኩበት ቀን ለእኔ የውድቀት መጀመሪያ መሆኑ ነው።ማንም አያውቀኝም ማንም ሳያውቀኝ የወደድሁትን እየሠራሁ እኖራለሁ ብሎ ማሰብ ታላቅ ውስንነት ነው።የሚያውቀኝ የለም ማለት የሚረዳኝ የሚያግዘኝ የሚደግፈኝ የለም ማለት ነው።

ይህ ደግሞ አስጨናቂ ነገር ነው።ከአባቴ ቤት ጋር ያለኝ ግንኙነት ተቋርጦ እውነተኛ የሆነ ኪሣራ ላይ ነኝ።

    የጠፋው ልጅ አሁን ይጨነቅ ጀመረ(ሉቃ 15፥14)።

ነጻ የምንሆንበትን ጊዜ ብዙ ነገሮችን ማውጣትና ማውረድ ቀላል በሆነ መንገድ እንደምናገኛቸውም ማሰብ የተለመደ ነው።

በአባቱ ቤት ረሐብ፣ጥም ቅዝቃዜ ተሰምቶት አያውቅም።ምክንያቱም ሁሉም ነገር የተትረፈረፈ ነውና።

ፍልስፍና ሁልጊዜ በሞላ ነገር ውስጥ ሆነው የሚያሰላስሉት ነው።ይህ ማለት ምንም የጎደለህ ነገር እስከሌለ ድረስ ስለብዙ ነገሮች ለማሰላሰል ጊዜ ይኖርሀል።

ነገር ግን ስትራብ፣ስትጠማ፣ልጆችህን መመገብ ሳይቻልህ ሲቀር ሌላ ነገር ውስጥ ካለህ ለፍልስፍና ጊዜ የለም።

ያለህበት ሁኔታ እውነታ የሚያሳየው ይህንን ነው።

    ከአባትህ ቤት ሳለሁ የሞላልህ፣ደኅነትህ የተጠበቀ ነህ።

እንዲህ ብለህ ታስባለህ።ይህ ለምኔ?በውጭ የተሻለ ነገር አለ ትላለህ።የጠፋው ልጅ ከአባቱ ቤት ከወጣ በኋላ በድንገት የነበረውን ያጣ ጎዶሎ፣ያጣውን ነገር የሚናፍቅ ሆነ።

ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች  ከአንዱ ጋር ተዳበለ።እርሱም እሪያ ሊያሠማራው ወደ ሜዳ ሰደደው(ሉቃ15፥15)ከነዚያ አገር ዜጒች ጋር ተቀላቀለ።

በብቸኝነት ጊዜ ብዙ ነገሮችን እናደርጋለን።አደገ ኛ የሆኑ ሁኔታዎችን እንለምዳለን፤አደገኛ ከሆኑ ሰዎች ጋርም እንውላለን።

የምናገርገው ይኼንን ነው፣በችግርና ባለመረጋጋት ጊዜ የሚከሰተው ይህ ሁኔታ ነው፣ከብዙ ሁኔታዎችና ሰዎች ጋር መጋፈጥ ዕጣ ፈንታችን ይሆናል።

እነዚያ ዜጒች ምን አደረጉለት ?ወደ ዓሣማ ሜዳ ሰደዱት።

ሰውዬው ይህ አባቱ ከመሞቱ በፊት የሚደርሰውን ድርሻ የሚጠብቅ የጠፋ ልጅ ታሪክ ነው።

የሚደርሰው ድርሻ ከወሰድ በኋላ ወደ ሩቅ አገር ሂዶ የነበረውን ነገር ሁሉ በተነ።

    "እሪያዎች ከሚበሉት አሠር ሊጠግብ ይመኝ ነበር።

የሚሰጠውም አልነበረም።(ሉቃ 15፥16)ይህ ልጅ ሀብታም አባት የነበረው፣በታላቅ ክብር ይኖር የነበረ ብዙ እርሻና አገልጋዮችም የነበሩት ነበር።

አሁን እንዳች ነገር የሚሰጠው ያጣ ሁኗል።ይህ ሁሉ ነገር ለእርሱ ምን ይጠቅመዋል?የሴይጣን ሰሯ እንደዚ ነው።

ሁሉን ነገር ካሳጣን በኋላ በቁጥጥሩ ሥር ያደርገናል ፈቃዱን የምንፈጽም ባሪያዎቹ እንሆናለን።በመከራ የምንኖር በኃጢአት ላይ ኃጢአትን የምንፈጽም በኃጢአትም እግረ ብረትም የታሠርን እንሆናለን።

እናገርበት የነበረው አንደበት ተሰጥቶንም የነበረ ተጋድሎ ከእ ኛ ይወስድብናል።በፈቃዳችን ምርኮኞች እንሆናለን።ራሳችንን አሳልፈም እንሰጣለን፣ነገር ግን ተስፋ አለን።

...አስታውሱ የግምኙነት መረቡ ተቋርጧል።ወደ አባቱ ቤት ሊመልሱት የሚችሉ ድልድዮችን ሰብሯል (አቃጥሏል)።አባቱ ግን ከልጅ ጋር የነበረው ግንኙነት የተቆረጠ አልነበረም።

ተስፋ አለ።የመመለስ መንገድ አለ።እንዲህ ብሎ አሰበ።እንጀራ  የሚትርፋቸው የአባቴ ቤት ሙያተኞች ብዙ ናቸው።(ሉቃ15፥17)ወደራሱ ተመለሰ እኔ ግን በዚህ በራብ እጠፋለሁ አለ።

ከኃጢአት ለመመለስ የመጀመሪያው ደረጃ አባት አለኝ ይቀበለኛል፣ለመመለስ መንገድ አለ ብሎ ማሰብ ነው።ይህንን ከጠፋው ልጅ ጋር ሆነን ልናሰላስል ይገባል።

ተነስቼ ወደ አባቴ ቤት እሄዳለሁ።አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ   በደልሁ ወደ ፊት ልጅህ ልባል አይገባኝም።(ሉቃ15፥18)በዚህ ምንባብ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቃላት አሉ።እነርሱም ተነሥቼ እሄዳለሁ የሚሉት ናቸው፣

ጠፍተህ ልትሄድ እንደምትችል አውቃለሁ።

ለጥፋትና በኃጢአት ሕይወት እንደምትኖርም አውቃለሁ።ነገረ ግን ጥ በበኛ ሆነህ ወደ እኔ ወደ አባትህ ቤት ትመለስ ዘንድ እጠብቅሃለሁ።

የጠፋው ልጅ ብዙ ስለቸገረ ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ አሰበ።(ሉቃ11፥13)ረጅም ጊዜ አልፈጀበትም።

እኛ ወደ ኃጢአት ለመሮጥ ምን ያህል እንፈጥናለን?ከእግዚአብሔር  ለመራቅ ሕይወታችንን በችግር መካከል እንዲሁም በፈተና ውስጥ የምናልፍበት ጊዜ ምም ያህል ነው?

     ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም ማድረግ የሚገባውን ነገር ምን እንደሆነ አላሰበም።አንዳንድ ጊዜ በኃጢአት ጊዜያዊ ደስታ እንታውራለን።

ውጤቱን አናስታውሰውም።ከመሄዱ በፊት ጥቂት ቀናት  ስለነበሩት በነዚያ ጊዜያት ማድረግ የሚገባውን ነገር ማሰብ ነበረበት።በአባቱ ቤት የምኖረው በምጽዋት ነበርን?ብሎ ማሰብ ሁሉ ይጠበቅበት ነበር።በዚህ መኖር እወዳለሁ።

ደኃንነት ይሰማኛል፣ይወደኛል እኔም እወደዋለሁ አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ ይህ ታላቅ ጥፋት ነው በማለት ነበረበት።ከአንተ የወሰድሁት ይኸው።

በዚህ ሥፍራ በመልካም ድኅንነት እኖራለሁ ማለት ነበረበት።ይሆነው ግን ይህ አልነበረም።

አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት ላለመስራት እንቃወማለን።ውሳኔ ከወሰንን በኋላ  በውሳኒያችን የተወሰነ ጊዜ እንጸናለን።

ከጥቂት ቀንም በኋላ ትንሹ ልጅ ገንዘቡን ሰንስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።የደረሰበትን ነገር እናውቃለን።

እንደምታውቁት ብዙዎቻችን ኃጢአትን የምንሠራ ብቻ አይደለንም።ኃጢአትን ጽድቅ ለማድረግ የምሰራም ነን እንጂ።

በነበረበት በሩቅ አገር ሀብትና ንብረቱን በተነ።አሁን ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ለመገመት አዳጋች አይሆንም፤

አስቀድሞ በአባቱ ቤት ነበረ።የአባቱን ቤት በፈቃዱ ተወ።ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

ሁሉንም  ነገር አጣ።ገና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ኃብቱን አጣ  በጥፋት ሕይወት ውስጥ የያዙት ሁሉ ማጣት የተለመደ ነው።

     በእግዚአብሔር ቤት በምንመላለስበት ወራት ክርስትና የሚሰጠን የጸጋ ሀብት አለ።ይህ የተትረፈረፈ ሀብት ነው።

ነገር ግን የሚያጠፉት አይደለም።ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ በመካፈላችን ልክ የራሳችንን ገንዘብ እንደሚጨምር የመንፈስ ቅዱስና ሀብትን እንቀበላለን።

ከንሥሐ ብዙ እናተርፋለን።ኪሳችንንም በተትረፈረፈ ጸጋ እንሞላለን፣ከዚያ ወደ ጎዳና እንወጣለን።

አንድ  ነገር እንደነበረ እናውቃለን።የሚጠቅመኝን ነገር አጥብቄ ይዤ ቢሆን ኑሮ ወደ  ፈተና ባልገባሁ ነበር።

ይህ ማለት ከተሰጠኝ ጸጋ የተወሰነውን እከፍላለሁ ማለት ነው።ያንን አልፌ ሌላ የምትፈተንበት ሁኔታ ያጋጥመኛል።አልዋሽም መዋሸት ኃጢአት ነውና እላለሁ።

    መዋሸት የተወሰነ ዋጋ እንድከፍል ያደርገኛል እንዲህ እያለ ይቀጥላል።

ስለዚህ በማንኛውም ጊዜ በፈተና መካከል ቁሜ አልበድልም እላለሁ ያም ዋጋን ያስከፍለኛል።በኪሴ ውስጥ ያጠራቀምኩትን ጸጋ ጨርሼ የቆምሁ ሁኛለሁ።

ለምን?ምክኒያቱም ጤናማ በሆነ ጊዜ እከፍላለሁ በተመሳሳይ ሁኔታ እቀበላለሁም።ስለዚህ በኪሴ ውስት የሚፈጠሩ ገንዘብ ይኖረኛል።

ነገር ግን ይለኝን ሁሉ በምከፍልበትና ወደ ኪሴ የሚገባ አንዳች ነገረ  በማይኖርበት ሁኔታ የጠፋው ልጅ እንዳደረግው ሁሉንም ነገር ይጣሁ እሆናለሁ።
👍91
ከአባቱ ቤት የወሰደው ማንኛውም ነገር፣ከርሱ ጋር የነበረው የገንዘብ ከረጢት አሁም ባዶ ሆኗል።የጠፋው ልጅ ያለውን ነገር ከጨረሰ በኋላ በዚያች አገር ረኻብ ተነሣ።

(ሉቃ11፥14)ሰይጣን ሐሰተኛና የሐሰት አባት ነው።እድንኮበልል ያደርገናል፤የውሸት ሰላምን ይሰጠናል፤ይፈትነናል፤ባዶ ተስፋን ያሣየናል በመጨረሻ የምትሰጡት አንዳች ነገር ሲጎድላችሁ ይጥላችኋል።

በድንገት ረኻብ ሆነ።ለምን አሁን ሰይጣን የማይፈልገን የማንጠቅመው ሆነናል።ወደሩቅ አገር ወስዶናላ፤የውሸት ሰላምና ጸጥታ የሚመስል ነገርን ሰጥቶናል።

ሰይጣን ወደ ሩቅ አገር ሂድ እውነተኛ የሆነ የመረጋጋት ጊዜን በዚያ ታሳልፋለህ ይልኻል።ምንም አይነት ዕንቅፋት አይገጥምህም።ከአንተ ጋር እንሁን አብረን ወደ ሩቅ አገር እንሂድ ያላል።

ተመልከት ልዩ የሆነ ምቾት አለ ይላል።ገንዘብ ከራቀ በኋላ ግን እንዲሁ ይላል።

    ከዚህ በኋላ ብዙ የምትጠቅመ ኝ አይደለህም በሩቅ አገር አድርሶ ተስፋችን ጨርሶ እንዲሟጥት ያደርገናል።

የምንመልሰው እንዳች አይኖረንም አስቀድሞ የፈተነን እንጠመድበት የነበረው ነገር ተመልሶ የምንጠመድበት ኃጢአት ሆኖ ይቀርባል።

በርቀት ነኝ የሚለውን አሳብ ስንመለከተው መልካም አሳብ መስሎ ይታየናል።ምክንያቱም ከአባቴ ቤት ርቄ በራሴ ለመቆም እንደሚቻለኝ አስመስሌኛልና።

እውነታው ግን ከአባቴ ቤይ ርቄ የሄድኩበት ቀን ለእኔ የውድቀት መጀመሪያ መሆኑ ነው።ማንም አያውቀኝም ማንም ሳያውቀኝ የወደድሁትን እየሠራሁ እኖራለሁ ብሎ ማሰብ ታላቅ ውስንነት ነው።

የሚያውቀኝ የለም ማለት የሚረዳኝ የሚያግዘኝ የሚደግፈኝ የለም ማለት ነው።

ራሳችን መመልከታችን ብቻውን በቂ አይደለም።ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ነው።ሁለተኛው እርምጃ መሄድ ነው።ምን ይህል ጊዜ ተቀምጠን አሰብን?ይህንን ነገር እጀምራለሁ ለማለት ምን ያህል ጊዜ ቀጠሮ ያዝን።አዲስ የአመጋገብ ዕቅድ፣የገንዘብ ዕቅድ፣አዲስ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ዕቅድ ሁልጊዜም የምለው ነገ እጀመራለሁ ነው።ነገ የሚመቸን ቀን ነው ምክንያቱም ፈጥኖ እንደሚመጣ አናስበውምና።ነገን ነገ ይወልደዋል።ቀጠሮአችን በዚህ መልኩ ማረፊያ ማብቂያ የሌለው ቀጠሮ ይሆናል።ዛሬ ተስሥቼ ወደ አባቴ ቤት እሄዳሁ ልንል ይገባናል።

    የጠፋው  ልጅ የተማረው ይሄንን ነው።ሁላችንም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ መማር አይጠበቅብንም።ከዚህም በበለጠ ፈጥነን ወደ አባታችን ቤት የምንመለስበት መንገድ መማር ይጠበቅብናል።እሣት እንደሚያቃጥል ለማወቅ የግድ እጃችንን ከእሳት ላይ ማስቀመጥ አይጠበቅብንም።የጠፋው ልጅ ትህትናን ከመከራው ተመሯል።መመለስ እንዳለበት አውቋል።ንስሐ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።ወደ አባታችን የምንመለሰው እንዴት ነው?እነዚህ አለሁ በሉት አባታችሁን፣አባታ ሆይ ይቅር በለኝ ስሜትህን ጒድቻለው የሰጠኸኝን ነፃ ፈቃድ እንደማይገባኝ ተጠቅሜበታለሁ።ቃልህን አልሰማሁምና ስለዚህ ነገር ይቅርታ አድርግልኝ።ለአንተ ስሜትና አባታዊ ፍቅር አልተጠነከኩም።ስስታም በመሆኔ ይህንን ይህል ዘመን ወደ አንተ ሳልመለከት ቀርቻለሁ።አዝናለሁ የአባታችንን ስሜት እንደጎዳን መገንዘብ ይኖርብናል።ከጠፋው ልጅ ጋር ሆነን እንዲህ ማለት ይኖርብናል።

     አባቴ ሆይ በሰማይ በፊትህም በደልሁ ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገ ባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።

(ሉቃ 15፥21)ተነሣና ወደ አባቱ ዘንድ መጣ።ሊመለስ መልካም እንደሆነ ተገነዘበ።ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ ገና በሩቅ እንዳለ አባቱ በርኅራኄ ይሄን ወደ እርሱ ተመለከተ።"ሮጦም አንገቱን አቀፈው ሳመውም።እግዚአብሔርም የወደደውን ሁሉ ስንሰራ  ከእርሱ የራቅንበትን ጊዜ ይመለከታል፣ ይህንን ትዕግስቱን አድንቁ እንጂ ቸልተኛ አትሁኑ።ልጁ ገና በሩቅ ሳለ አባት ወደ ልጁ  ሮጠ።ልጁ የበር ደውል ደውሎ እዚህ ነኝ የሚል አቀባበል አይደለም።አባት ለካ እዚህ ነህ አላለም አባት ልጁ በናፍቆት እየተጠባበቀ ነበር። እግዚአብሔር ያደረገው ያንን ነበር።እግዚአብሔር ወደ እርሱ ለመመለስ ልባችንን ዘንበል ስናድርግ ፈጥኖ ወደ እኛ ይመጣል።አይዘገይም።ይገባዋል ስህተቱን እንዲያውቅ አደርገዋለሁ አይልም።ይህ አሳብ ሰውኛ አሳብ ነው።ይመገብ የነበረው ከእሪያዎች አሸር ነበርና ልብሱ ሲቆሽሽ እርሱም አድፎ ሊታይ ይችላል።ምናልባትም እንደ እሪያዎች ሊሸት ይችላል።እግዚአብሔር የሚቀበለን እስከ ኃጢአታችን ነው።ራሳችንን ልንሰጥ በፈቃዳችን ወደ እግዚአብሔር መመለስ እስከተቻለን ድረስ።

   የጠፋው ልጅ እንዲህ አለ።"አባቴ ሆይ በሰምይና በፊትህ በደልሁ ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም።"እርሱን እርሳው አሁን ተመልሰሀል፣አዲስ ሰውም ሆነኻል፣ወደ እኔ መጥተኻል፣እርሱም ንስሐ ነው።ይቅርታ መጠየቅህን ተመልክቻለሁ።ከዚህ በላይ የሚጥብቅህ ነገር የለም ።እግዚአብሔት ሊረዳን ይፈልጋል፣ሊይድነን ይወዳል፣ሊወደን ይፈልጋል።

     አባት ለባሪይዎቹ እንዲህ አላቸው።ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት ለእጁም ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ።

(ሉቃ 15፥21)ተነሣና ወደ አባቱ ዘንድ መጣ።ሊመለስ መልካም እንደሆነ ተገነዘበ።ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ ገና በሩቅ እንዳለ አባቱ በርኅራኄ ይሄን ወደ እርሱ ተመለከተ።"ሮጦም አንገቱን አቀፈው ሳመውም።እግዚአብሔርም የወደደውን ሁሉ ስንሰራ  ከእርሱ የራቅንበትን ጊዜ ይመለከታል፣ ይህንን ትዕግስቱን አድንቁ እንጂ ቸልተኛ አትሁኑ።ልጁ ገና በሩቅ ሳለ አባት ወደ ልጁ  ሮጠ።ልጁ የበር ደውል ደውሎ እዚህ ነኝ የሚል አቀባበል አይደለም።አባት ለካ እዚህ ነህ አላለም አባት ልጁ በናፍቆት እየተጠባበቀ ነበር። እግዚአብሔር ያደረገው ያንን ነበር።እግዚአብሔር ወደ እርሱ ለመመለስ ልባችንን ዘንበል ስናድርግ ፈጥኖ ወደ እኛ ይመጣል።አይዘገይም።ይገባዋል ስህተቱን እንዲያውቅ አደርገዋለሁ አይልም።ይህ አሳብ ሰውኛ አሳብ ነው።ይመገብ የነበረው ከእሪያዎች አሸር ነበርና ልብሱ ሲቆሽሽ እርሱም አድፎ ሊታይ ይችላል።ምናልባትም እንደ እሪያዎች ሊሸት ይችላል።እግዚአብሔር የሚቀበለን እስከ ኃጢአታችን ነው።ራሳችንን ልንሰጥ በፈቃዳችን ወደ እግዚአብሔር መመለስ እስከተቻለን ድረስ።

   የጠፋው ልጅ እንዲህ አለ።"አባቴ ሆይ በሰምይና በፊትህ በደልሁ ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም።"እርሱን እርሳው አሁን ተመልሰሀል፣አዲስ ሰውም ሆነኻል፣ወደ እኔ መጥተኻል፣እርሱም ንስሐ ነው።ይቅርታ መጠየቅህን ተመልክቻለሁ።ከዚህ በላይ የሚጥብቅህ ነገር የለም ።እግዚአብሔት ሊረዳን ይፈልጋል፣ሊይድነን ይወዳል፣ሊወደን ይፈልጋል።

     አባት ለባሪይዎቹ እንዲህ አላቸው።ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት ለእጁም ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ።

አንድም ቀን የምንሄድበት የዘላለም መኖሪያችን ነውና።መንግስቱን የምወርስና በጥበቃውም ሥር የምንኖር እንሆናለን።መንግሥቱን ይምንወርሰው እግዚአብሔር ካልተውን እና ከተውንም ፈጥነን በንስሐ ወደ እርሱ መመለስ ሲቻለን ነው።ወደራሳችን እንመልከት እሄዳለሁ እመለሳለሁ እንበል ፣ተነስተን እንሄዳለን፣በፍቅር ምክንያት እግሩ ላይ እንወድቃለን በንስሐና በኑዛዜ ስሕተታችንን እናምናለን።አሁን የሚቀጥለው የእግዚአብሔር ድርሻ ነው።አንገታችንን ያቅፋል ይስመናል፣ራቁትነታችንን ይሸፍናል ለእጃችን ቀለበት ለእግራችን ጫማ እንዲኖረን ያደርጋል።የሰባውን ጥጃ ያመጣል።እግዚአብሔርና የሰማይ ሠራዊት በመመለሳችን ሐሤት ያደርጋሉ።ምሥጋና ይሁን አንድ አምላክ በሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን

ቴሌግራም
👍62👏1
ብዙዎች ብቁ እንዳልሆኑ አንዳች ነገር እንደሚጎድላቸው በማመን ፣ የችግሮቻቸው ሁሉ ምንጭ ስለ ራሳቸው የያዙት መጥፎ አመለካከት መሆኑን ለማስተዋል ይቸገራሉ።

ለራሳቸው እየደጋገሙ ፣

፨ ብቁ አይደለሁም ፤ ለመውደቅ የተፈጠርኩ ነኝ

፨ በፍፁም ድባቴ ውስጥ እንድኖር የተበየነብኝ ፣ ደስታ ጨርሶ የማይገባኝ ነኝ

፨ እናቴ በምንም ነገር ተስፋ የለህም/ሽም ትለኝ የነበረው ሁሉ እውነት ነው

፨ ምናልባትም ባልወለድ ይሻል ነበር ፤ አሁንም ብሞት ለሁሉም ግልግል ነበር

፨ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ ፤ እኔ ግን አልችልም

፨ ከሰዎች ዘንድ ዋጋ የማይገባኝ አስቀያሚ ነኝ

፨ ደደብ ስለሆንኩ በትምህርት ተስፋ የለኝም

፨ ሁሌም በሌሎች የተገፋሁና ተቀባይነት የሌለኝ ነኝ ... ..

እና ሌላም ሌላም ክፉ ነገርን ይነግሩታል።
እነኚህ አባባሎች በሙሉ ለራሳችን የምንሰጠውን ዝቅተኛ ግምት ማሳያ ምልክቶች ናቸው። ከመሀላቸው አንዱን እንኳን ለራሳችሁ የመናገር ልማድ እንዳላችሁ ከታዘባችሁ ፤ ይህ

የቴሌግራም ቻናል ይጠቅማቸዋል

ለእናንተ ነው።


#ቴሌግራም

https://www.tg-me.com/+2gD-YRvEKZo1MmZk
https://www.tg-me.com/+2gD-YRvEKZo1MmZk
https://www.tg-me.com/+2gD-YRvEKZo1MmZk

🔴SUPPORT ON YOUTUBE🔴

https://youtu.be/cCQcrthTTmE
https://youtu.be/cCQcrthTTmE
https://youtu.be/cCQcrthTTmE

      
👍51👏1
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ!

ለህዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቡፁዕ አባታችን አቡነ አብርሐም መሪነት የተዘጋጀ። ከህዳር 2 እስከ 4 በባሕርዳር መስቀል አደባባይ ደ/ም/ቅ ፊልጶስ ገዳም።

በእለቱ ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሐም፣ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ኤርሚያስ፣ ሊ/ሊቃውንት ስማዕ ኮነ መልአክ፣ መምህር አባ ገ/ኪዳን፣ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ፣ ዘማሪ ቴውድሮስ እና ሌሎች በከተማችን የሚገኙ ዘማሪያን ዘማሪ አብርሐም፣ ዘማሪ አባይነህ፣ ዘማሪት መሰረት እና ዘማሪ ሐ/ልዑል ይገኛሉ።
ከጌትሽ ባህርዳር ገጽ የተገኘ
11👍7
ክቡራን ወዳጆቼ! መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ ለልጆቻችን ሁሉ የጀመርነው አገልግሎታችን ይዳረሰ ዘንድ ይህንን የዩቱብ ገፃችንን SUBSCRIBE በማድረግና ቪድዮዎቹን SHARE በማድረግ አብራችሁን ዝለቁ!
* ልጆቻችንን አብረን እናሳድጋቸው!
እግዚአብሔር ያክብርልኝ!
👍94
" ገብርኤል ላእክ ወዜናዌ ዳኅን ወሰላም
ገብርኤል መልእክተኛ የደኅንነትና የሠላምን ብሥራት ተናጋሪ" 【ቀሌ ፮፥፵】

🍀 "ያገለግሉት ዘንድ የከበረ ስሙን ያመሰግኑ ዘንድ የሰማይ መላእክትን እርሱ አዘዘ፤
#መላእክትም_ሕይወትን_ወደሚወርሱ_ሰዎች_ሁሉ_ይላካሉ።"
☞ [፩ኛ መቃቢያን ፭፥፲፰]

https://youtu.be/EA2T156Hddc
👍51
👍9
"አ…ት…ማ…ረ…ኝ"

#ጸሎትሰ ይእቲ ተናግሮተ ሰብእ ኀበ እግዚአብሔር ልዑል። (ጸሎትማ ይኽች ናት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርባት)

‘ሚጸልይ ሰው ጸሎቱ ወደ እግዚአብሔር የሚሳብበት ይሁን አፍ ንባብ ይነዳ ልብ ጓዝ ያሰናዳ እንደሚለው ዓይነት እንዳይሆን! (ወአንብቦቱኒ ትኩን ዘባቲ ይከውን መንፈስ ዘያንሠሐሰሐ መንገለ ፈጣሪ)

በሕሊናችን የምንጸልይ ብንሆን በጎ! በአንደበታችን የምናነበንበው ቢሆን ደግሞ ለልቡናችን እንንገረው በአንደበታችን የምንናገረውን ሕሊናችን ይተርጉመው! [እመኒ በሕሊና ባሕቲቱ፤ ወእመኒ በልሳን፤ ከመ ይተርጕም ለሕሊና]

......ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ - አትማረኝ- አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል......(የአፍ ቃሉ አትማረኝ በሕሊና መሻት የልብ ትርጉሙ ግን ማረኝ)

አቡነ ያሳይ ከሰባቱ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ጠፍጣፋ ድንጋይ /ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡/ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ - አትማረኝ- አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡

አቡነ ያሳይ በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው “አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?” አሏቸው፡፡

“አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው “አትማረኝ” እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው በማለት መለሱላቸው፡፡

“እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው “ማረኝ” እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡

አትማረኝ እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም “ማረኝ” እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አባት አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸውም በውኃ ላይ እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡

“አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፡፡ እባክዎ ያስተምሩኝ” ይሏቸዋል፡፡

አቡነ ያሳይ የእኚህ አባት መብቃት ተመልከተው “አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል” ብለዋቸው ይሔዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ተጠርቷል፡፡

ዛሬስ የበዛው #በአፉ_ማር #በልቡ_አትማር ባይ ነውና ኃጢኣት በአፋችን እየረገምን በልባችን ግን አጥብቀን የምንመኛት ድኩማን ነንና የልቡናችንን እግሮች ወደሰላም መንገድ ያቅናልን! ያኔ የልቡናን መሻት ዐይቶ እንደቸርነቱ ሁሉን ይማር !
👍213
👍11
2025/07/14 22:08:00
Back to Top
HTML Embed Code: