#ይዘዙን!
በፈለጉት ዲዛይን በጥራት እንሰራለን !
#ከአልባሳት
➛ #ጋቢ እና #ፎጣ
➛ #ነጠላ እና #አልጋ ልብስ እና ለሴቶች የእጅ ቦርሳ በፈለጉት ዲዛይን እና ጥለት እንሰራለን
➻ #ቲሸርት እና #ሱሪ ባማረ ዲዛይን እንሰራለን
(#ለበዓላት፣ #ለፅዋ ማህበር፣#ለሰርግ፣ #ለልደት)በብዛት ካዘዙን በሚፈልጉት ቀን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እንሰጥዎታለን !
መጪው #ጥምቀትም አይደል ? ቲሸርት ለማሰራት ወደ አዲስ አበባ መሄድ አይጠበቅብዎትም ! ከወዲሁ ወደኛ ጎራ ብለው የፈለጉትን ዲዛይን መርጠው ይዘዙን! በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራልዎታለን!
➤ለመምህራን እና ለህክምና ባለሙያዎች #ጋዎን እናዘጋጃለን !!
የንፅህና መጠበቂያ
ቆሻሻን ድራሹን የሚያጠፉ
➛ #የልብስ ሳሙናዎች
➛እና ወደር የሌለው #ፈሳሽ ሳሙና እና #ላርጎ እኛጋ አለ።
➛አልኮል እና ሳኒታይዘር አለን!
#ጧፍ እና #ሻማ ከፈለጉ በብዛት እና በጥራት አምርተን እናቀርብልዎታለን !
ዋጋቸው እጅግ ተመጣጣኝ ! በጥራት ደግሞ አንደራደርም !
ኑ ! የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸመት ገዳሙን ይደግፉ!
የጂንካ አንቀፀ ብፁኣን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም !!
የገዳሙ አስተዳደር የአባ ኤፍሬም
+251989810622

👍17
«ካቶሊካዊው» ቅዱስ ደቅስዮስ ‘Catholicos’ Saint Dexius
⚜🍁⚜🍁⚜🍁⚜🍁⚜🍁⚜🍁⚜🍁⚜
በዘር ከመወለድ የራቀ በሰው ህሊና ከመታሰብና በመላእክት አእምሮ ከመመርመር በላይ የሆነ አንዱ ወልድ ሰውን ለማዳን ያለመለወጥ ከሰማይ ወርዶ ጉድለትና መወሰን ሳይኖርበት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሕፀን አደረ።
በእርሷ ማሕፀን እርሱ ስለእኛ ሰው የሆነባት ያቺ ዕለት ፦
#ለእርሱ ፦ ዕለተ ትስብእት (የተፀነሰባት ቀን)
#ለእርሷ ፦ ዕለተ ብሥራት (የምሥራች የሰማችበት ቀን)
#ለእኛ ፦ ዕለተ ትፍሥሕት (ደስታን ገንዘብ ያደረግንበት ቀን) ናት።
አንዱ ወልድ በግብረ መንፈስ ቅዱስ በማሕፀነ ድንግል የማደሩና በተዋህዶ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የሚነገርበትን ቀን ቤተክርስቲያን የምታስበው መጋቢት ፳፱ እና ታኅሣሥ ፳፪ ነው። የታኅሳሱን በዓል አባቶች ተውላጥ ይሉታል።
ቤተክርስቲያናችን ከምትዘክራቸው ፴፫ቱ የእመቤታችን በዓላት ውስጥ አምስቱ በወርኃ ታኅሳስ ታስበው ይውላሉ
(በ፫ በዓታ ፣ በ፳፩ ወርኃዊ ተዝካረ ዕረፍታ ፣ በ፳፪ ተውላጥ ለበዓለ ብሥራታ፣ በ፳፰ በዓለ ጌና ፣ በ፳፱ ልደተ ፍቁር ወልዳ ናቸው)
የታኅሳስ ፳፪ቱን በዓል በታላቅ ደስታ በለውጥ እንድናከብረው ያደረገ እርሱን ግን በማንም የማንለውጠው ታላቁ አባታችን ቅዱስ ደቅስዮስ ነው።
"ለዐርክ ምእመን አልቦቱ ተውላጥ ⇨ ለታመነ ወዳጅ ለውጥ የለውም" (ሢራ. ፮ ፥ ፲፭)
ለደግነቱ ሚዛን የማይገኝለት በፍቅረ ድንግል ማርያም የተነደፈ ክብሯን አብዝቶ ለመመስከር የጸጋዋን ታላቅነት ካደረገችው ተአምራት ጋር አንድነት የጻፈልን ቅዱስ ደቅስዮስ የጥልጥልያ (የጥልጥያ) ኤጲስ ቆጶስ ነው!
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ «አንዳንዶች» በደረሱበት ልክና በገባቸው መጠን (ምንም እንኳ በቅንነት የተደረገ መሆኑን ባልክድም) ያለደረጃና ያለበቂ ማስረጃ፣ ያም ባይሆን ያለ ሥፍራው በወተት ቦታ አጥንት ለአንባቢ እያሰናዱ ከቅድስናው ውፁኣን የሆኑትን በመጻሕፍተ ቅዱሳን አበው ሳይቀር የተወገዙትን አቅርበው «አባቶቻችን» አልፎ አልፎም «ቅዱስ» ሲሉ መመልከትን ለመድን ተለማመድንም ፤ በአንጻሩ ደግሞ በጽድቅ በቅድስና የደመቁትን አባቶቻችንን በእምነት ጸንተው በምግባር ቀንተው ማለፋቸውን ከሚመሰክሩ «እሙራን ወክሱታን» የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት ውጪ በማጣቀስ ወደ ተዋህዶ በረት ጉቡኣን ሆነው ሳለ ለማራቅና ለመንቀፍ የውጭ አስረጂ ሲመዘዝባቸው ማየቱንም ልንለምደው ነው።
በሃይማኖተ አበው አባ ብንያሚን ከሚያውቀው ሐሳብ ባይስማማለትና ከቀደሙት መጻሕፍት መልእክቱ ሲርቅበት የተላከለትን ጦማር ዐይቶ መልእክቱንና ላኪውን ብቻ ሳይሆን ተላላኪዎቹን ጭምር እንዲህ ብሎ መውቀስ ጀመረ ፦ አንሰ ረከብኩ ነገረ እንዘ አነብብ መጻሕፍቲከ ዘፈኖከ ሊተ ምስለ ሰብእ መትሕላን እለ ኢኮኑ ፍጹማነ ወልቦ አእምሮ ጥዩቀ…
የዛሬው መልእክቴ በቀደሙት ክርክሮች ላይ ነገር ለማክረር አልያም የተሻለ ሐሳብ ኖሮኝ ነገሩን በማስረጃ ለማዳበር ሳይሆን ይህ የማህበራዊ አውታር ክርክር መንድ የከፈተለት «ደቅስዮስምኮ ካቶሊካዊ ነው» ብሎ መሞገቱ ቢገርመኝ ድንግል እናቴ "አሁንስ በዓይኔ በብሌኑ መጣህ" ስትል የሰማኋት መሰለኝና እኔም እንዲህ አልኩ
ቅዱስ ደቅስዮስስ የብሥራቷን ቀን በታላቅ ደስታ በለውጥ እንድናከብረው ያደረገ እርሱን ግን በማንም የማንለውጠው ታላቁ አባታችን ነው።
"ለዐርክ ምእመን አልቦቱ ተውላጥ ወለሥኑ አልቦ መድሎተ ⇨ ለታመነ ወዳጅ ለውጥ የለውም ለደግነቱም ሚዛን አይገኝለትም " (ሢራ. ፮ ፥ ፲፭)
የቀደሙንስ በመንገዳቸው እንግዳ ነገር ሲያገኛቸውና ከሚያውቁት ሳይስማማላቸው ቢቀር ያሰነብቱታል ፣ ይጸልዩበታል ፣ ከመምህራን ይመክሩበታል «የለም እንዲህ ሊል ሽቶ ነው» ብለው እንግዳውን ሐሳብ አቅንተው ከቀድሞ እምነታቸው ያስማሙታል "ዘይዌልጥ ቃለ እኩየ ኀበ ሠናይ ወይዘርዕ ሰላመ ማእከለ አኀው ይሣየጥ ሕይወተ ለርእሱ= ክፋውን ወደ በጎ ለውጦ በወንድሞች መካከል ፍቅርን የሚዘራ ሰው ሕይወትን ገንዘብ ያደርጋል" ይላልና።
ወደ ቅዱስ ደቅስዮስ እንመለስ
ደቅስዮስ (ቅዱስ ዘጥልጥልያ ) ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡናው የሚወድዳትና በተቻለው ሁሉ የሚያገለግላት የተባረከ ሰው መሆኑን ተአምረ ማርያም፣ ነገረ ማርያም፣ መጽሐፈ ስንክሳር፣ መጽሐፈ ሜላድ (ድርሳነ ልደት) ፣ ድርሳነ ገብርኤል፣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ድርሳናት … ይነግሩናል።
[ወሀሎ ፩ ኤጲስ ቆጶስ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ዘጥልጥልያ ዘስሙ ደቅስዮስ ጻድቅ ብእሲ ወፈራሄ እግዚአብሔር ወያፈቅራ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል በ፪ኤ ማርያም ወላዲተ አምላክ ፈድፋደ ወውዳሴሃ አፉሁ ይነብብ ወልቡ ይጐሥዕ ወይትቀነይ በዐቢይ ጻሕቅ] ተአምረ ማርያም
ቅዱስ ደቅስዮስ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ የእመቤታችንን ተአምራት ሰብስቦ በመጽሐፍ ያኖረ ፍቅሯ እንደ እሳት እያቃጠለው የሚኖር የተወደደ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ያደረገላትንና በእርሷ ለእኛ የተደረገልንን ገቢረ መንክራት አሰባስቦ ተአምረ ማርያምን የጻፈልን እርሱ ነው!
⇨ ዳዊት በትንቢት ሲናገር “የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው።” መዝ፹፮፥፫
⇨ እርሷም ደርሶላት ስትመሰክር “ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።” ሉቃ ፩፥፵፱ ብላለች። ተአምር ማለት ይህ ነውና ፦ ለእነርሱ የተደረገውና በእነርሱ የተደረገው መንክር ወመድምም የሚዘገብበት!
በወርኃ ታኅሳስ በሚነበበው መጽሐፈ ሜላድ ላይ በስመ መንግሥቱ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ደቅስዮስ በጻፈው ተአምረ ማርያም ላይ የተአምሯን መቅድም አጽፎ ወደ ኢትዮጵያ ኹሉም አብያተ ክርስቲያናት እንደላከ ተጽፏል።
በዚያውም ላይ የእመቤታችንን የመጽነሷን ቀን ከወርኃ ጾም ብሎም ከጌታችን ተዝካረ ሕማም አንስቶ ከልጇ ልደት ስምንት ቀን ቀድሞ እንዲከበር አብሣሪና ተበሣሪን ከመበሥር ጋር በምስጢር እንዲተባበር ታኅሳስ በባተ በሃያ ሁለተኛው ቀን በዓለ ብሥራት ብሎ በደስታ እንዲከበር ያደረገ ነው።
እርሱ (ቅዱስ ደቅስዮስ) ይሄን ሲያደርግ እርሷ (ቅድስት ድንግል ማርያም) በእጇ ንጹሕና የከበረ ልብስ ከተቀደሰና ማንም የማይቀመጥበት መልካም ዙፋን ይዛለት በፊቱ ተገለጠች።
[አስተርአየቶ ለኤጲስ ቆጶስ እግዝእትነ ቅድስት ድንግል በ፪ኤ ማርያም ገባሪተ ሠናያት ወወሃቢተ ጸጋ ወሀሎ ውስተ እዴሃ ልብስ ክቡር ወንጹሕ ወመንበር ቅዱስ ወሠናይ]
ልብሱ በሰው እጅ ያልተሰፋ ነው! ዙፋኑም ሌላ ሰው የማይቀመጥበት ነው! በዓሏን በደስታ ቢያከብር የሚደሰትበት ክብሩን ለመግለጥ የተሸለመው ነው "ወሶበ አብዓለ ላቲ በዛቲ ዕለት ወሀበቶ ልብሰ ዘኢተገብረ በእደ ሰብእ" እንዲል።
በማሕሌተ ጽጌውም
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”
(ደቅስዮስ ቅዱሱን ተአምርሽን ሲጽፍ ለድካሙ ዋጋ እንዲሆን ልብስና ዙፋን አገኘ፤ ችጋርኛውን ባለጠጋ የምታደርጊ ድንግል ማርያም ሆይ ለማሕሌቴ ዋጋ እንዲሆን አትሮንስና ያማረ ልብስ ሥጪኝ)
ቅዱሱ በክብር ያረፈበትም ቀን ብሥራትን በተውላጥ በታላቅ ክብር ባከበረበት በዚህ ቀን [ታኅሳስ ፳፪ ] ሆነ በረከቱ ይደርብን 🙏
ዕለቱ ከሊቁ ቅዱስ ካወዳጀን አይቀር ጥቂት ማለፊያ ነጥብ እግረ መንገድ ላንሳ!

👍6❤1
በመጻሕፍቶቻችን ደቅስዮስ ዘጥልጥልያን ተብሎ የተነገረው በሌሎቹ Ildephonsus (Hildefuns) Archbishop of Toledo የሚለውን እንደሚወክል ተነግሯል።
እንደ ምዕራብያኑ ሐተታ ስፔን በታላቁ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ትምህርት ክርስትናውን ከተቀበለች በኋላ መንጋውን ለመምራት በተነሱ እረኞች ዝርዝር ውስጥ 32ኛው የቶሌዶ ሊቀ ጳጳሳት እንደሆነ የሚነገርለት «Archbishop of Toledo» (657–667) ‘ቅዱስ’ ኢልድፎንሱስ (Ildephonsus) አንዱ ነው።
ኢልድፎንሱስ በትላልቆቹ የታሪክ መዛግብት ሳይቀር በኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ደቅስዮስ እየተባለ የሚነገርለት ቅዱስ አባት መሆኑ ተመልክቷል። (የካቶሊክና የኢትዮፒካ ኢንሳይክሎፒዲያ ከዋሊስ ባጅ የተአምረ ማርያም ትርጉምና ከሌሎች መዛግብ ጋር ተባብረው በመረጃ ይህን ጠቅሰዋል)
ቶሌዶን በቄልቄዶናውያኑ መንበር ሥር ካቶሊኮች እንደጠቀለሏት ይታወቃል፤ ይሁን እንጂ የእነርሱም ደቅስዮስ ቢሆን «በንጹሕ የቅድስና ሕይወት ያሸበረቀና የእምነቱ ኦርቶዶክሳዊነት ጎልቶ የሚታይ» ተብሎ የተመሰከረለትን አውጋንዮስ ካልዕ (ዘይንእስ) መንበር ተክቶ የተሾመ በመሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ላለመሆኑ ማስረጃ ለማቅረብ ይቸገራሉ። (አውጋንዮስ የደቅስዮስ አጎትም ጭምር መሆኑን ልብ ይሏል)
Eugenius II (the Younger) Archbishop of Toledo (647 – 657) ⇨ Piety breathes throughout, and the orthodoxy of his faith is notable.
በግል ምልከታዬ ግን ከላይ አጥኚዎቹ በመረጃ ካተቱት የማቀራረብ ታሪክ ውስጥ ኢልድፎንሱስ ከቅዱስ ደቅስዮስ ጋር በሰው እጅ ያልተሠራ ልብስ ከእመቤታችን ከመቀበሉ፣ ጥልጥልያ የሚለው ለቶሌዶ ትርጉም ከመቅረቡ ውጪ የተአምሯን መጽሐፍ ስለመጻፉ፣ የብሥራቷን በዓል ስለማክበሩ፣ ማንም የማይቀመጥበት ዙፋን ስለመቀበሉና ከእርሱ በኋላ የተነሳው ሊቀጳጳሳት 33ኛው የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ (እንደእነርሱ ገለጻ Quiricus 667–680] በድፍረት ‹‹እርሱም (ደቅስዮስም) ሰው እኔም ሰው፣ እርሱም ኤጲስቆጶስ እኔም ኤጲስቆጶስ›› ብሎ በትዕቢት ተናግሮ በዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ ወድቆ እንደሞተ የሚነገር ሀተታ የለም፡፡
የተለየ ልብስ ከእመቤታችን በመቀበል የምናውቃቸው ሌሎች አባቶችም ታሪካቸው በሰፊው ተዘግቦ እናገኛለን።
ለምሳሌ
🍁 ቅዱስ ኒቆላዎስ ( St. Nicholas, Santa Claus Or Father Christmas)
መጽሐፈ ስንክሳር በዚህ ጉዳይ የሚከተለውን ይመሰክራል፤
" ወእምቅድመ ይሠየም ኤጲስቆጶሰ ርእየ ራእየ ዘከመ መንበር ዐቢይ ንቡር ወልብሰ ክህነት ክቡር በኀቤሁ ወዘከመ ይቤሎ ብእሲ ብርሃናዊ ልበስ ዘንተ ልብሰ ክህነት ወንበር ዲበ ዝንቱ መንበር። ወካዕበ ርእየ በካልዕ ዕለት ዘከመ እግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማር ያም እሙ ለንጉሠ ስብሐት ወሀበቶ ልብሰ ክህነት ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት ወሀቦ ወንጌለ።"
【 ኤጲስቆጶስነትንም ከመሾሙ ፊት ታላቅ ዙፋንና የከበረ የክህነት ልብስ በእርሱ ዘንድ ተቀምጦ ብርሃንን የለበሰ ሰውም ይህን የክህነት ልብስ ልበስ በዙፋኑም ላይ ተቀመጥ የሚለውን ራእይ አየ። ሁለተኛም በሌላ ቀን ለክብር ባለቤት እናቱ የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክህነት ልብስን ስትሰጠው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወንጌልን ሲሰጠው አየ። 】
የጋሥጫው ሊቅ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታ ውስጥ ከቅዱስ ደቅስዮስ ጋር ቅዱስ ኒቆላ(ዎስ)ን አያይዞ እንዲህ ብሏል፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ
ሰላም ለኪ
【ሰላም ላንቺ ይሁን! ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድሞ ለኒቆላዎስና ለደቅስዮስ (የከበረ ልብስ) እንደሰጠሻቸው ማርያም ሆይ ለእኔም የደስታና የተድላ ልብስን ስጪኝ】
🍁 አባ ዳንኤል ዳግማዊ ደቅስዮስ
የሥዩመ ሳባ እና አመተ ሥላሴ ልጅ የሆነ በ9ኛው መክዘ ከመጡት ካልዕ ሰላማ (ሰላማ ዘአዜብ ቀዳማዊው ሰላማ በመጡ ከ618 ዓመት በኋላ የመጡ መተርጉም) አስኬማን የተቀበለ ከእመቤታችን እጅ ነሐሴ ፮ ቀን የክብር ልብስን ያለበሰችውና ኤጲስ ቊጵስናን ያስሾመችው ታላቁ መስተጋድል አባ ዳንኤል ዳግማዊ ደቅስዮስ እየተባለ ተጠርቷል።
የዳግማዊ ደቅስዮስ አባ ዳንኤል ገድል ዘወርኃ ነሐሴ እንዲህ ይላል ፦
«ወሀበቶ ልብሰ ሰማያዌ ከመ ልብሰ ዓፅፈ ደቅስዮስ ኤጲስ
ቆጶስ። ወበውእቱ ጊዜ ሤመቶ ሢመተ ኤጲስ ቍጵስና ከመ ደቅስዮስ ኤጲስ ቆጶስ ፍቁረ ዚአሃ ለአቡነ ዳንኤል ዘደብረ ማርያም ቆርቆር በዛቲ ዕለት አመ ፮ ለነሐሴ። ወአልበሰቶ ካዕበ በይእቲ ዕለት በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት በጊዜ ነግህ ልብሰ ክብር ከመ ደቅስዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዓፅፈ ሃይማኖት
ጽጉየ። ወበጊዜሃ ለብሰ ልብሰ ክብር ሠናየ። ወትቤሎ ዳግማዊ ኤጲስ ቆጶስ ድንግል ደቅስዮስ አንተ አባ ዳንኤል ርቱዓ ሃይማኖት። ሤምኩከ ወንዕድኩከ በእንተ ሠናይ ግብርከ። ባሕቱ ዮም ይትፌጸም በላዕሌከ ሥርዓተ ዓርዑተ ምንኵስና በእደ ዝንቱ ብፁዕ ወኅሩይ ሱታፌሁ ለዓቢይ ወክቡር ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ዘኢትዮጵያ። ውእቱኒ ጳጳስ ዳግማዊ ሰላማ መተርጕም ዘአዜብ ብሂል ውእቱ ይሁበከ ወያለብሰከ አስኬማ መላእክት ዲበ ሐቌከ ወአክሊለ ቆብዕ ዲበ ርእስከ »
የእኛ ቅዱስ ደቅስዮስ ኬልቄዶናዊ (ኬልቄዶናዊነት የሀገር ዜግነትን ሳይሆን የጉባኤ ከለባት አባልነትን ለማመልከት የገባ ነው) ያልነበረ ያልሆነና የማይሆን እንደሆነ እሙን ነው!
ካቶሊካዊ ማለት በጭራሽ ኬልቄዶናዊ ማለት አይደለም። ካቶሊካዊት የሚለው ስያሜ የሚገባት የእኛዋን ኦርቶዶክሳዊት ርትዕት ፍኖት ነው።
ታዲያ ካቶሊካዊ የሚለውን ዘርፍ ከኬልቄዶናውያኑም መግፈፍ ከእኛ ውጪ የማን ሥራ ሊሆን ነው?
በመሠረተ እምነታችን የጉባኤያት ድንጋጌ [statement of faith ☞ THE CREED] ላይ የቤተክርስቲያንን ባህርያት ሊቃውንቱ ሲገልጡ በአሐቲ(In one) ቅድስት (holy) እንተ ላዕለ ኵሉ (catholic), ጉባኤ ዘሐዋርያት (apostolic Church) ቤተክርስቲያን እናምናለን ይላል። በዚህ መነሻ ካቶሊክ የሚለው የቤተ ክርስቲያናችን ስም ነው ትርጉሙ ኵላዊ ዘኵሉ እንተ ላዕለ ኵሉ (ኹላዊት የኹሉ በኹሉ) ማለት ነው። "concerning the whole, universal & general"
ቤተክርስቲያንን ካቶሊክ ኤጲስ ቆጶሳቱን ካቶሊኮስ ማለት በእኛ ዘንድ እንግዳ ሆኖ እንጂ በጽባሓውያኑ በአርመንና በሶርያ ያሉትን አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት Catholicos-Patriarchs ብሎ መጥራት የተለመደ ነው!
ሐሳቡ እንጂ ቃሉ አያጣላንም! አልፎ አልፎ የማንግባባው «ምን ልንል እንደፈለግን እና ምን እንድንል እንደሚፈለግ» መካከል ባለው ልዩነት ነው። [Most of us get disappointed when our expectations are not met.]
ቅዱስ ደቅስዮስን ሲገልጡት ካቶሊካዊ የሚለው ቃል አያጣላንም። ካቶሊካዊ ሲሉ ምንን ለማለት እንደፈለጉ ይታወቅ እንጂ!
“ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና። ” ☞ 2ኛ ጢሞ 2፥14
አጥር ቅጥሯ በማይፈርስ መሠረቷ በማይናወጽ ለዘለዓለም ጸንታ በምትኖረው አዳራሽ በተዋህዶ ሃይማኖታችን ያጽናን!

👍6👏1
የቅዱስ ደቅስዮስ በረከቱ ፣ እርሱ አብዞት የወደዳት የድንግል እናታችን ፍቅሯ ፣ ሰማያዊ በረከትን ለቅዱሳኑ የሚያድል የመድኃኔዓለም እረኝነቱ በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር።
☞ በቴዎድሮስ በለጠ ለታኅሣሥ ብሥራት ፳፻፲፫ ዓም ተፅፎ የነበረ ✍ አዲስ አበባ

👍2❤1
የጥምቀት በዓል የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት (Emergency Medical Service at Epiphany)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የድንገተኛ ሕክምና ክፍል በአደባባይ በዓላት ላይ የምናደርገውን የሕክምና አገልግሎት በመቀጠል ዘንድሮም የጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጀት ላይ ይገኛል። ይህ አገልግሎት የሚሰጠው ከከተራ እለት ጀምሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱት 3 ቦታዎች እና ሰዓታት ሲሆን የሚመቻችሁን ቦታ እና ሰዓት ቅጹን በመሙላት እስከ ጥር 3 (January 11) ድረስ ባለው ጊዜ እንድታሳውቁን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
1. ጃን ሜዳ፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00
2. አበበ ቢቂላ ስታዲየም፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00
3. ጎንደር ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 - 6:00
ለዚህ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
Specialties needed for our Emergency Medical service at Celebration of Epiphany:-
Emergency Physician
General Practitioners
Internal Medicine
Pediatrics
Nursing
Pharmacists
Orthopedics
Health Officers
Public Health professionals
ጤና ባለሙያዎች ቅጹን ለመሙላት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfXvAjlOO0thRvvX33vt5TO1EVYWUwjT0pMcSRkIKkltJETZA/viewform?usp=pp_url
አገልግሎታችንን ለመደገፍ የምትሹ በሚከተሉት አማራጮች መለገስ ትችላላችሁ፦
አሐዱ ባንክ፡ 0004857810101
ንግድ ባንክ፡ 1000355318021
ዳሽን ባንክ፡ 0472399237011
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ: 3359501002471
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 7000036276989
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 013081005174100
በግብዐት ማገዝ የምትሹ በስልክ ቁጥር 0913726877 ይደውሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!
EOTMA for all by all!

👍5
ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት።
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥
ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአንስት ። አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ትሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን ወውስቴታ ጽላተ ኪዳን ። ፲ቱ ቃላት እለ ተጽሕፋ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር ። ቀዲሙ ዜነወነ በየውጣ እንተ ይእቲ ቀዳሜ ስሙ ለመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ ወኮነ ዓራቄ ለሐዲስ ኪዳን ። በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመኃይምናን ወለሕዝብ ንጹሐን
☞ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
በሰንበተ ክርስቲያን እሑድ የሚጸለይ
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴ

ከሴቶሽ ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ። ከተለዩ የተለየች በውስጧም የኪዳን የሕግ ጽላት ያለባት የምትባይ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ። ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ዓሥሩ ቃላት ናቸው። ያለመለወጥ ካንቺ ሰው የሆነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን መጀመሪያ ስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሓን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው።
☞ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ብዕለት ቅድስቲ ሰንበት ክርስቲያን ዝንበብ ዝጽለ ናይ ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲት ኣምላኽ ምስጋና።

ኦ ካብ ኵለን ኣንስቲ ብርኽቲ ዝኾንኪ ማርያም ፍቅርቲ ተሰመኺ፡ ንስኺ እታ ቅድስተ ቅዱሳን እትበሃል
ካልኣይቲ ቀመር (ክፍሊ) ኢኺ፡ ኣብ ውሽጣ ኸኣ ብኢድ እግዚኣብሔር ዝተጻሕፋ ዓሠርተ ቃላት (ትእዛዛት) ናይ ኪዳን ጽላት ዘለዋ፡ ኣቐዲሙ ብየውጣ ዓሠርተ ትእዛዛት ነገረና፡ ንሳ ኸኣ ንመድሓኒና ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳመይቲ ስሙ ኢያ፡ ብዘይ ምልዋጥ ካባኺ ሰብ ዝኾነ ኢየሱስ ክርስቶስ ንሓድሽ ኪዳን መተዓረቒ ኮነ፡ ንሱ ብምፍሳስ ቅዱስ ደሙ ንምእመናን ኣንጺሕዎም፡ ንኣሕዛብ'ውን ቀዲስዎም ኢዩ፡
☞ ቅድስት ድንግል ለምንልና።
GUYYAA SANBATA KIRISTAANAATTI KAN KADHATAMU GOOFTAA KEENYA KAN DEESSE GALATA GIIFTII KEENYA DURBOO MAARIYAAM.

Yaa Maariyaam, dubartoota hundumaa keessaa kan eebbifamte, jaalatamtuus jedhamte. Adda kan ta'an irraa adda kan taate, Tsillaatiin seera waadaa (kakuu) ishee keessa jira kan jedhamtu kutaan lammaffaa siidha. Seerri sunis abboommii kurnan quba Waaqayyoon kan barreeffamaniidha. Otoo hin jijjiiramiin sirraa nama kan ta'e Fayyisaan keenya Iyyasuus Kiristoos maqaasaa isa tolaa ta'e dursee yawixaatti (jechoota kurnan) quba Waaqayyoon barreeffaman nutti hime. Kakuu haaraafis araarsituu ta'e. Dhangala'uu ulfaataa dhiigasaatiin gartuusaa amantoota qulqulleesse.
☞ Yaa Qulqulleettii nuuf kadhadhu.
A HYMN OF PRAISE FOR THE SUNDAY

THOU Wast named “Beloved Woman”, O blessed among women Thou art the second chamber, in that thou “Holiest of Holies” and in it was the table of the Covenant and on it were the Ten Words which were written by the fingers of God. He (i.e the Father) made known this to us first of all by “Yawta” (i.e Iota), which is the first [letter] of the Name of our Redeemer JESUS CHRIST, who become Incarnate of thee without Change, and become the Mediator of the New Covenant, and by the Shedding of His Holy Blood He purified the Believers and the people Who were pure. And Because of this were all Magnify thee, O our Lady, thou ever pure God - bearer. We beseech Thee and lift our eyes to Thee, so that we may find Mercy and Compassion With the Lover of Men.
ከፈለገ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤት ፍሬዎች https://youtu.be/VAnYDVurvmU

YouTube
44ተኛው የፈለገ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤት ዓመታዊ የምስረታ በዓል 22/04/2015ዓ/ም
#ፈለገ_ቅዱሳን_ቲዮብ #felege_kidusan
👍10❤3
በአንድ ወቅት ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ በደል ፈጸመ። የሕዝቡን ቁጥር ብዛትና የሠራዊቱንም ኃይል ብቃት ያውቅ ዘንድ ይቆጠሩልኝ በሚል የእግዚአብሔርን ሕዝብ (እስራኤልን) ሕዝቤ ለማለት ቃጣው! ታዲያ ድምራቸውን ለማወቅ ከዳን እስከቤርሳቤህ ያለውን ሕዝብ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብንና ሌሎች የሠራዊቱን አለቆች አስጨንቆ እንዲቆጠሩ ትዕዛዝ ሠጠ።
"አስተፋቅዶሙ ለሕዝብ ወኈልቆሙ" ይላል በሕዝብ መካከል እየተመላለሱ ዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በፈጀ ቆጠራ ለንጉሡ ስምንት መቶ ሺህ ጦረኞችና (ዕደወ ኃይል) እና አምስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሕዝብ ቆጠርን አሉት።
ያን ጊዜ ያደረገው ነገር ተገቢ እንዳልነበር የተረዳው ቅዱስ ዳዊት በልቡ አዘነ።
“ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን፥ አቤቱ፥ ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።” [ 2ኛ ሳሙ 24፥10]
የማይገባ በማድረጉ ከአምላኩ ተለይቷልና ያን ታላቅ ነቢይና ንጉሥ እግዚአብሔረወ ማነጋገር ትቶ ባለ ራእይ ጋድን ላከበትና “ኅረይ ለከ ዘይከውነከ” አለው (የሚሻልህን ምረጥ ሲለው) ከሚታዘዝበ ሦስት ቅጣት መካከል አንዱን አስቦና መርምሮ የሚበጀውን ለራሱ እንዲመርጥ ተጠየቀ!
① የሦስት ዓመት ረኀብ
② የሦስት ወር ስደት
③ የሦስት ቀን ቸነፈር [ቁ 13]
በእርሱ መበደል ምክንያት በሕዝቡ ላይ ስለሚመጣው ቁጣ የዳዊት ምርጫው እንዲህ በሚል ነበር በባለራእዩ ጋድ በኩል ቸነፈሩን የመረጠው «ተመንደብኩ እደቅ ውስተ እደ እግዚአብሔር … "
“ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ አለው።” ይላል [ቁ 14]
“ ውጣ፥ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ አለው።” [ቁ 18]

👍9❤1
#ዳዊት_ከተቃጣ_መቅሰፍት_የዳነባት_የኦርና_አውድማ
━━━━━━━✦༒🛐 ༒✦━━━━━━━
ክርስቶስን ልናውቀው በሚገባ ልክ እንደመጠናችን የሚሰብክልን የሐዲስ ኪዳን ቅዱስ መጽሐፍ መነሻውም መድረሻውም ዳዊት ነው፤ ነቢየ እግዚአብሔር ልበ አምላክ።
የሐዋርያቱ የምሥራች በወንጌለ ማቴዎስ የሚጀምረውና በራእየ ዮሐንስ የሚጨርሰው ክርስቶስን በዳዊት እየገለጠው ነው!
☞ “የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።” ማቴ. 1፥1
☞ “እኔ ኢየሱስ… የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።” ራእይ 22፥16
የዳዊት ልጅ የተባለው ክርስቶስ ለዳዊት ፈጣሪው ነው! ለፈጣሪው አባት የተሰኘና አምላክ ፦ ወልደ ዳዊት ፣ እማ’ምላክም ፦ ወለተ ዳዊት ተብለው የተጠሩበት ደገኛው ገር (የዋህ) ሰው ቅዱስ ዳዊት ዛሬ ታኅሳስ 23 የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው! በረከቱ ይደርብን።
እንዲህ ያለ ጭንቅ ሲደርስ በሽታና ፍቅር መጣቱ ሲያይል አምላከ ዳዊትን እንዲህ እያልን ደጅ እንጥና «ተዘከረነ እግዚኦ አምላከ ምሕረት በእንተ ዳዊት ገብርከ»
እርሱ ዳዊት ከታዘዘ ደዌ ከተቃጣ መቅሰፍት እንዴት ማምለጥ እንደሚቻል ያውቃልና!

መልሶም ስለ እርሱ በደል ሌሎች እንዳይቀጡበት በሕዝቡ ሳይሆን እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን እነዚህ በጎች ምን አደረጉ? እያለ ለመነ፤ እግዚአብሔርም አዘነና ጋድን ልኮ እንዲህ አለው
“ ውጣ፥ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ አለው።” [ቁ 18]
ዳዊትም ወደ ኦርና ሔደና መቅሠፍቱ ከሕዝቡ ላይ ይከለከል ዘንድ አውድማውን ከአንተ ገዝቼ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ልሠራ ነው አለው።
ኦርና ግን እንኳን ቦታውን በገንዘብ ሊሸጥለት ጭራሽ የአውድማውን እቃ ከነበሬው ቀንበር መስዋዕቱን ለማቅረቢያ እንደ እንጨት ያገለግል ዘንድ በነፃ ልሥጥህ አለው፤ የገዛ በሬዎቹንም ጭምር እንደሚቀርብ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ እንዲሰዋ አሳልፎ ሊሰጠው ወደደ እንጂ ልሽጥልህ አላለውም!
ዳዊት ግን ለበደሌ "በዋጋ ከአንተ ገዝቼ ያለዋጋ ለአምላኬ ላቅርብ" አለውና አውድማውን ከነበሬው በሃምሳ ሰቅል ብር ገዛው።
“በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠልና የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርም ስለ አገሪቱ የተለመነውን ሰማ፥ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።” [2ኛ ሳሙ 24፥25]
ዋጋ አውጥተን ያለ ዋጋ ለአምላክ ሰጥተን ሥርየትን ገንዘብ እንድናደርግ በቸርነቱ ይርዳን!
በቅዳሴያችን መግቢያ ካህኑ ከቤተልሔም የመጣውን መስዋዕት ተቀብሎ መሰዊያውን (ታቦቱን) እየዞረ እንዲህ የሚል ጸሎት ያደርሳል …
« አምላካችን እግዚአብሔር በምድረ በዳ የአቤልን ቊርባን የተቀበልህ ፣ የኖኅን በመርከብ ውስጥ ፣ የአብርሃምንም በተራራ ላይ ፣ የኤልያስንም በቀርሜሎስ ተራራ #የዳዊትንም_የኤያቡስ_ወገን_በምትሆን_በኦርና_ዐደባባይ ፣ የድሃዪቱንም መሐለቅ በቤተ መቅደስ የተቀበልህ ለቅዱስ ስምህ ያቀረብነውን የኃጥዓን ባርያዎችህን መባና ቊርባን እንደነርሱ ተቀበል፡፡ የኀጢኣታችንም ቤዛ ይሁን በዚህ ዓለም በጎ ዋጋን ስጠን በሚመጣውም ዓለም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡»
ለእኛምኮ ከታዘዘ ደዌ ከተቃጣ መቅሰፍት ዋጋ ከፍሎ ዳዊት የገዛት አማናዊቷ የኦርና ዐደባባይ (ዐውደ ኦርና) ፣ የኦርና እርሻ (ገራህተ ኦርና) ፣ የኦርና አውድማ (ምክያደ ኦርና) ወለተ ዳዊት ድንግል ማርያም ናት።
እኛም ከአባቶቻችን ጋር ልጇን እንዲህ እያልን እንለምነው "ዘተወከፍከ ቊርባነ ለዳዊት በዐውደ ኦርና ከማሁ ተወከፍ መባነ ወቊርባንነ ለኃጥኣን ሕዝብከ" 🙏
በኋላ ዘመንም አምላካችንም የኦርናን ምሥጢር ከድኅነት ጉዳያችን አገናኝቶ ከዚህ በላይ ከፍ ሲያደርገው የእግዚአብሔርን ቤት ልጁ ሰሎሞን እንዲያንጽበት በሞርያ ተራራ የሚገኘውን የኦርና አውድማ መረጠለት!
“ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።” [2 ዜና 3፥1]
ለእኛ ለወንጌል ልጆች የሞርያ ተራራ የኦርናም እርሻው ሥፍራ ከነፍሳችን የድኅነት ምሥጢር የማንነጥላት መስተምሕርት ለአበ ምሕረት ወላዲቱ እናታችን ድንግል ማርያም ናት! የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት የቀረበባት ወለተ ዳዊት እህተ ሰሎሞን እርሷው ናትና።
እርሷ፦
የሊቀ ካህናቱ መቅደስ
የአማናዊው ብርሃን መቅረዝ!
እርሷ ፦
የከበረ እንቍ የተገኘባት መዝገብ
ለቀዛፊው ሊቀ ሐመር መርከብ!
እርሷ ፦
አዲሲቷ እምቦሳ ነጩን በግ የምታሳድር
የሰማያዊው ሕብስት መከማቻ የመና ጎሞር!
እርሷ ፦
መሰዊያ የምትባል የሰማያዊው ቁርባን እናት
የፍጥረቱ መታረቂያ የሐዲስ ኪዳን የሕግ ታቦት!
እርሷ ፦
የፀሐየ ጽድቅ ወላዲቱ ሰማይ
ደብረ ሞሪያ ዐውደ ኦርና እመ አዶናይ! ናት።
ለዚህ ነው የሁላችን አባት አባ ጊዮርጊስ
🍁 ደብረ ሞሪያ ናትና "አንቲ ውእቱ ደብረ መድኃኒት ዘብኪ ድኅነ ይስሐቅ እመጥባህት" የሚላት።
ዐውደ ኦርና፣ ምክያደ ኦርና፣ ገራህተ ኦርና ናትና እንዲህ እያለ ይጠራታል ከነምክንያቱም ይገልጣታል።
አንቲ ውእቱ ገራህተ ኦርና !
ዘብኪ ሦዓ ዳዊት መሥዋእተ መድኃኒት ለፈጣሪሁ
መቅሰፍተ ብድብድ ፅኑዕ አመ ኮነ ለሕዘቢሁ
አንቺ የኦርና እርሻ
ዳዊት የሠዋብሽ ከፈጣሪው ፈውስን ሲሻ
የታዘዘ ደዌ ማራቂያ የተቃጣ መቅሰፍት ማሸሻ
☞ ♰✙✚ ✛✠✞†✜✟♱☜

👍10
ዛሬም
✧ ፍጥረቱ በሥጋ ጉልበት ከመመካት በሠራዊት ብዛት ከመታበይ የሚመለስባት ፣
✧ ሰዎች ሁሉ ከመጣው ዐዳዊ ሕመም (ተላላፊ በሽታ) የሚድንባት፣
✧ ሕዝቡ ከዘረኝነት ቁስሉ የሚሽርባት፣
✧ ወገኖቻችን እርስ በእርስ ከመበላላት ቁርባን ሠርተው ልጇን ሰውተው ከታዘዘ ደዌ ከተቃጣ መቅሰፍት የሚፈወሱባት ዐውደ ዖርና ወለተ ዳዊት ድንግል ማርያም ናት!
ትሁት የዋህና ኅሩይ በሆነ በባርያው በቅዱስ ዳዊት ጸሎት፣ ደብረ ሞርያ ዐውደ ኦርና በምትባል በእናቱ በድንግል ማርያም ቃልኪዳን በአበ ኵልነ ብርሃነ ዓለም አባ ተክለሐይማኖት ምልጃ አምላካችን ሁላችንን ይማረን 🙏
🌴 በቴዎድሮስ በለጠ ታኅሳስ ፳፫ (ዕረፍቱ ለዳዊት) ፳፻፲፫ ዓም ተፃፈ ✍ ከወደ ደብረ ሊባኖስ
https://youtu.be/ZymQCgTnuUY

ዲ /ን ዶ /ር ቴዎድሮስ በለጠ የኦርና አውድማ 2 ሳሙ 24 ፥ 16
✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን::ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙhttps://www.youtube.com/channel/UCol_...እግዚአብሔር ያክብርልን
👍8