Telegram Web Link
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
Photo
ሌላ ሰበር ዜና

የግብፅ እህት ቤተክርስቲያን ሲኖዶስም የህገ ወጥ ሹመት በተመለከተ በይፋዊ መግለጫ አሁን ውጉዙ ከመአርዮስ ብላ ውድቅ አደረገች

𝗢𝗳𝗳𝗶𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗦𝘁𝗮𝘁𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁 𝗯𝘆 𝘁𝗵𝗲 𝗘𝗰𝘂𝗺𝗲𝗻𝗶𝗰𝗮𝗹 𝗥𝗲𝗹𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻𝘀 𝗖𝗼𝗺𝗺𝗶𝘁𝘁𝗲𝗲 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗛𝗼𝗹𝘆 𝗦𝘆𝗻𝗼𝗱 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗖𝗼𝗽𝘁𝗶𝗰 𝗢𝗿𝘁𝗵𝗼𝗱𝗼𝘅 𝗖𝗵𝘂𝗿𝗰𝗵

Cairo-Egypt: The Ecumenical Relations Committee of the Holy Synod of the Coptic Orthodox Church rejected the new schism which arose in the 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮𝗻 𝗢𝗿𝘁𝗵𝗼𝗱𝗼𝘅 𝗖𝗵𝘂𝗿𝗰𝗵 under the leadership of Abuna Sawiros by consecrating around 26 Bishops uncanonically at Woliso Bealewold (The Nativity of Christ) church, Oromo and installation of himself as the patriarch of Oromo. The Ecumenical Relations Committee published a statement regarding the same on 24th January 2023.

H.G. Anba Thomas, Metropolitan of Qusia & Mir the rapporteur of the Ecumenical Relations Committee in the statement said that the Coptic Orthodox Church does not recognize any ordination outside the scope of the legal patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, only Abouna Matthias 1 is recognized as the Patriarch of the Ethiopian Tewahedo Church and declared solidarity with the Ethiopian Church
👍2
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
Photo
+ ዶግማና ቀኖና
በ ቀሲስ ዶ/ር
መብራቱ ኪሮስ የቀድሞ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ዲን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ሰሞኑን “ዶግማ እንጂ የማይለወጠው፣ ቀኖና ሊሻሻልና ሊቀየር ይችላል” የሚል ነገር በተደጋጋሚ ሲነገር ሰምተናል፡፡ አባባሉ ከፊል እውነታ አለው፡፡ የተነገረው ግን፣ ለሕገ ወጡና ለተወገዘው ሢመት ሽፋን ለመስጠት ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ ከላይ ባለው ርእስ ትንሽ ነገር ለማለት እሞክራለሁ፡፡

ዶግማ ምንድን ነው? ቀኖናስ?

ዶግማ በዓለም አቀፍ ጉባኤያት (ecumenical councils) የጸደቀ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያን ከአበው የተቀበለችውን እምነት የምትገልጥባቸው አስተምህሮዎች ደግሞ doctrines ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- “ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነው” ይህ ዶግማ ነው፤ “ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት” ይህም እንደዚሁ፡፡ የክርስቶስን አምላክነት ለማይቀበሉ አርዮሳውያን፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያን አስተምህሮ (doctrine) ተከትላ መልስ ሰጥታለች፤ ስትሰጥም ትኖራለች፡፡ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ (Theotokos) ብለው ለመቀበል ለሚቸገሩ ንስጥሮሳውያን ደግሞ፣ እንዴት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም “ወላዲተ አምላክ” እንደምትባል የምንገልጥበት ወይም የምናስተምርበት ዶክትሪን፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ያስተማረው ትምህርት ነው፡፡

እነዚህ አስተምህሮዎች በዓለም አቀፍ ጉባኤያት የተወሰኑ ሲሆን፣ ውሳኔያቱን ከተጨማሪ ጉዳዮች ጋር የቤተ ክርስቲያን አበው በቀኖናት (canons) አጽድቀዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ325 ዓመተ እግዚእ (AD) የተጠራው ጉባኤ ኒቅያ 20 ቀኖናት አሉት፡፡ እነዚህንና ሌሎቹን ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ ውሳኔያት፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ከርስቲያን Holy Canons (ቅዱሳት ቀኖናት) በማለት ትጠራቸዋለች፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳት ቀኖናት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በዓለም አቀፍ ጉባኤያተ አበው የጸደቁና የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ የሚያንጸባርቁ (ከዶግማዋ ጋር የሚስማሙ እንጂ፣ የማይጋጩ) ናቸው፡፡

“ቀኖናት ይሻሻላሉ/ ይለወጣሉ?” የሚል ጥያቄ ቢነሣ፣ መልሱ “እንደ ቀኖናው አይነት ይወሰናል፤ የሚለወጥና የማይለወጥ አለ” ነው፡፡ ለምሳሌ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት ወይም የመለኮትና ትስብእትን ተዋሕዶ አስመልክቶ ቅዱሳን አባቶቻችን የወሰኗቸው ቀኖናት Dogmatic Canons ስለሆኑ ማንም ተነሥቶ ሊለውጣቸው አይችልም፡፡ Practical የሆኑ ጉዳዮችን በሚመለከቱ ቀኖናት ላይ ግን፣ በሐዋርያት መናብርት የተሾሙ አበው ወይም የእነርሱ ተከታዮች (ተላውያነ አበው) የሆኑ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጉባዔ (ቅዱስ ሲኖዶስ) ማሻሻያ ማድረግ ይችላል፡፡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው practical canons መካከል አንዱን ልጥቀስ፡፡ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን፡- ቅስና መሾም የሚገባው ሰው 30 ዓመት የሞላው እነደሆነና ኤጲስቆጶስ ደግሞ በ50 ዓመቱ መሾም እንዳለበት የሚደነግግ ቀኖና ነበር፡፡ በሂደት ግን ቤተ ክርስቲያን ተምረውና በቅተው ለተገኙ ልጆቿ 30 ወይም 50 ዓመት ባይሞላቸውም የቅስና እና ጵጵስና መዓርግ ሰጥታለች፡፡

ወገኖች! Apostolic Succession (ሐዋርያዊ ሰንሰለትን) በመጠበቅ ተወዳዳሪ የሌላት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 2000 ዓመታት በተቀደሰው ትውፊት (Holy Tradition) አማካኝነት ቅዱሳት መጻሕፍትንና ከእነርሱ የሚመነጨውን ርቱዕ (የቀና) አስተምህሮ ያስረከበችን፣ ማንም የመሰለውን መላምት እያመጣ ከቀጥተኛው (ኦርቶዶክሳዊ) መንገድ እንዳይወጣ አጥር ሆነው የሚጠብቁ Holy Canons (ቅዱሳት ቀኖናት) ስላሏት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የአምልኮ ውበት እና ሥርዓት፣ Protestantism ውስጥ ካለው ቀውስ (chaos/anarchy) ጋር
በማነጻጸር መረዳት ይቻላል፡፡ “ቀኖና የሚሻሻል ነገር ነው” በሚል ጥራዝ ነጠቅ አነጋገር፣ በዘመናት ተፈትኖ ያለፈውንና በምድር ላይ ሆነን ሰማያዊ ሐሴትን እንድንለማመድ የሚያደርገንን ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ ሸርሽረን እንደ አንዳንድ ሥርዓት እንደሌላቸው ቤተእምነቶች ወደ ሥርዓት አልበኝነት እንዳንገባ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
👍23
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
Photo
#ውግዘትን #በተመለከተ #ፍትሐ #ነገሥት #ምን #ይላል?
ፍት. ነገ. ፬፣፷፩ "ሊቀ ጳጳሳት ያወገዘውን ጳጳስ መፍታት አይችልም"። ስለዚህ እነ አቶ አካለ ወልድ ብፁዓን አባቶችን አውግዘናል ያሉት ከቤተክርስቲያን ትምህርት ያልተስማማ ከእግዚአብሔር ሕግ ያፈነገጠ መሆኑን ሁሉም ሊያውቀው ይገባል። ከእግዚአብሔር ጋር እልህ መግጠም ለማንም አያዋጣም። ቅዱሳን አባቶቻችንና መንፈስቅዱስ በሠሩልን ሥርዐት የምንመራ ከሆነ እነ አቶ አካለ ወልድ ጳጳሳትን ማውገዝ አይችሉም። ምክንያት:-

፩) ሊቀ ጳጳሳት ያወገዘውን ጳጳስ አይፈታውምና። ሊቀ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከሲኖዶስ ጋር ሆነው ከሥርዐት ውጪ የሆኑ ሦስት ጳጳሳትንና በማናለብኝነት የተሾሙ 25 መነኮሳትን አውግዘው አቶ ተብለው እንዲጠሩ ተወስኗል። ስለዚህ አቶ ተብለው ከቤተክርስቲያን ተወግዘው ከተለዩ በኋላ ማንኛውንም ሰው የማውገዝ ሥልጣን የላቸውም። በሊቀ ጳጳሳቱና በሲኖዶሱ አስቀድመው ተወግዘዋልና።

፪) ከቤተክርስቲያን ተለይቶ የወጣ ሰው ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አካል ማውገዝ አይችልም። ምክንያቱም ምንም ሥልጣን የለውም። ሥልጣኑ በቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ተነስቷል። በሌለ ሥልጣን አውግዣለሁ ማለት አስቂኝ ነገር ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም አኃት አብያተ ክርስቲያናት የሲኖዶስን ውሳኔ አክብረው ተቀብለዋል። እነርሱም በነ አቶ አካለወልድ መወገዝ ተስማምተዋል። ስለዚህ ምንም ዓይነት ፍትሕ መንፈሳዊ በሌለበት በጉልበትና በመሰለኝ የሚለወጥ የቤተክርስቲያን ሕግ የለም።

ስለዚህ የተከበራችሁ ምእመናን ሁልጊዜም ውግንናችሁ ለክርስቶስ አካል ለሆነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን እና ለአስተምህሮዋ ይሁን። አስተምህሮዋ ደግሞ በፍትሐ ነገሥት እንደተቀመጠው ነው። አለበለዚያ ከአመፀኞች ጋር ብታምፁ ግን ሰይፍን ብትመረኮዙ ራሳችሁ ትጠፋላችሁ እንጂ ቤተክርስቲያን እንደማትጎዳ ስነግራችሁ በታላቅ ደስታ ሆኜ ነው። ምክንያቱም መሠረቷ ክርስቶስ ነውና።

© መ/ር በትረማርያም አበባው
(የፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ መምህር)
👍114👏1
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ቀን፡ - 18/05/2015
“በዓለም ሳለችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” 【ዮሐ 6፥33】

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የአንድነት ገዳማት ኅብረት መልእክት
ከቅዱስ ፓትርያርካችን ጀምሮ በየደረጃው ያላችሁ የመንጋው እረኞቻችንና ሕዝበ ክርስቲያን፣ ለአኀት አብያተ ክርስቲያናት፣ እውነተን ለምትፈልጉ እና ለምትከተሉ የሰው ልጆች በሙሉ ሰላምታችን ከያለንበት ቅዱሳን መካናት ይድረሳችሁ።
የምናስተላልፈውን መልዕክትም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጊዜያችሁን በመስጠት እንድትመለከቱት እኛ ታናሽ እና ደካማ የሆን ገዳማውያንና ገዳማውያት በአምላከ ቅዱሳን ስም
እንማጸናችኋለን፡፡

መልዕክታችንም ለሚከተሉት አካላት ይሆናል፡ -

፩. ለቅዱስ ፓትርያርካችን፡ - እስካሁን በአደረጉት በዕንባ የታገዘ የእረኝነት ተግባርዎት የረዳዎትን አምላክ እናመሰግናለን ወደፊትም እንለምናለን፡፡ ነገር ግን ይህ የተቀደሰ የመንጋው ጥበቃ ተግባርዎት በዚህ ከባድ የፈተና ጊዜ ይበልጡኑ ከዕንባዎት ጋር ለእርስዎ እና ለእኛ ይሆን ዘንድ እስከ አሁን ድረስ ከባዱን ፈተና ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደተወጡት አሁንም እግዚአብሔር በሚወደው እውነት ብቻ ጸንተው እንዲቆሙ እና በዚህም የሚቀበሉት መከራ ካለ የእውነተኛ እረኛነት ምድራዊ ደሞዙ ይኸው ነው እና ከእረኝነትና አባትነት ተግባርዎ አንዲትም እርምጃ ወደ ኋላ እንዳያፈገፍጉ እኛ ደካማ ልጆችዎት በቅዱሳኑ ስም እንማጸንዎታለን፡፡

፪. ለብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፡ - እስካሁን በዘመነ ሲመተ ክህነታችሁ ክፉውንም በጎውንም አሳልፋችኋል። የአሁነ ግን ከሁሉ የከፋ ይመስላል፤ የሚከፋው ግን በእውነት በመኖር እና ለእውነትም የሚከፈለውን መከራ የምትሸሹ የምታፈገፍጉ ከሆነ እንጂ በእውነት ላይ ለእውነት ከቆማችሁ እናንተም ከብራችሁ ቤተ ክርስቲያንንም የምታስከብሩበት ጊዜ አሁን ስለሆነ ደስ ሊላችሁ ይገባል። ይህ ግን ፍርሐትን፣ምቾትን፣ማስመሰልን ይጠላል በምትኩም

ጥብአት፣መከራ እና እውነት ይስማማዋል። ስለዚህም የእስካሁኑን ሁሉ ድክመታችሁን አስወግዳችሁ ማስፈራሪያቸውን ሳትፈሩ እውነትን እንድትገዟት እንጂ እንዳትሸጧት ደካሞች ልጆቻችሁ አደራ እያልናችሁ ምናልባትም አንድ አንድ ደካማ ጎኖችንና ማስመስያን እየፈለጉ የሚጠቃቅሱ ቢኖሩም በምትባሉት ነገር ሁሉ ግድ ሳይሰጣችሁ ለመንጋው እረኝነት ያበቃቻችሁን ቤተ ክርስቲያን ከማስከበር የበለጠ ምንም ተልዕኮ እንደማይኖራችሁ ታውቃላችሁና እውነትን በመኖር ለእኛ ለበጎቹ ምሳሌ ሁኑን፡፡
በቅድሚያ ስለልጅነት ድፍረታችን ይቅርታ አድርጉልንና ይህ ሁሉ የሆነው በእናንተ በእረኞቹ እና በእኛ በበጎቹ የክርስትናውን ዓላማ እና ተግባር እንደሚገባ ያለመኖር ነው፡፡ ስለሆነም ወደፊት እንዴት መኖር እንደሚገባን ከራሳችሁ ጋር እና በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ምከሩ። እኛንም መንገዱን በማሳየት ምሳሌ ትሆነን ዘንድ ደካሞች ልጆቻችሁ በቅዱሳን ስም እንማጸናችኋለን፡፡

፫. ሲመተ ኤጲስ ቆጶስ ሰጥተናል ላላችሁ ሊቃነ ጳጳሳት እና “ኤጲስ ቆጶስነት ተሹመናል" ላላችሁ መነኮሳት፡ - በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የፈጸማችሁት ተግባር ስህተት መሆኑን እኛ ደካሞች ገዳማውያን በትህትና ድፍረት ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም ያለው አማራጭ ሁለት ነው - አንደኛው በፍጹም ንስሐ ያሳዘናችኋትን ቤተክርስቲያን ደስ ማሰኘት እና እናንተም ምድራዊ እና ሰማያዊ ሰላም ማግኘት፤ ሁለተኛው ደግሞ ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን አንድነት መለየት ነው᎓᎓ ነገር ግን ሁለተኛው አማራጭ ለእናንተም ለእኛም ሀዘን ነውና የመጀመሪያውን አማራጭ ትተገብሩት ዘንድ እኛ ደካሞቹ በፍፁም ፍቅርና ትህትና በአምላከ ቅዱሳን እንማጸናችኋለን፡፡ በዚህም ቤተክርስቲያን /የሰማይ መላእክትና ምድራውያን ክርስቲያኖች/ ደስ ይስኙ፤ጠላት ዲያብሎስም ይፈር በቤተክርስቲያን ውስጥ ችግር እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፤ስለምን ችግር ኖረ ብንል ግን ምክንያቱ ሁለት ነው፡ -
• እኛ /እረኞቹና በጎቹ ክርስትናውን እንደሚገባ ስለ አልኖርነው᎓᎓
• በምድር ያለችው ቤተክርስቲያን ተጋድሎዋን ያልጨረሰች በፈተና ውስጥ ያለች
ስለሆነች::
ታድያ ይህን ችግር ለመፍታት የሄዳችሁበት መንገድ በእኛ በደካማ አእምሮአችን ኢኦርቶዶክሳዊ፣ኢሃይማኖታዊ መንገድ መሆኑ ነው እና ትልቁ ስህተት እባካችሁን ወደ

ኦርቶዶክሳዊ መንገድ ወደ ሃይማኖታዊ መንገድ ተመለሱ ብለን በአምላከ ቅዱሳን ስም እንለምናችኋለን፡ መመለሳችሁም ከልብ እንዲሆን ስለፍቅር አምላክ እንማጸናችኋለን።

፬. ለአበው ካህናት፣መምህራን፣ሰባክያነ ወንጌል እና ዲያቆናት፡ - እናንተም የሰሞኑን እና የእስካሁን /የቆየውን የቤተክርስቲያን ችግር ለመፍታት መጀመሪያ ከራሳችሁ ጀምሩ፣ ሰውነታችሁን ለመንፈሳዊ ነገር አሰልጥኑት፡፡ ከዚያም ለምትመሩት፣ ለምታስተምሩት ሁሉ በእውነት እና በፍቅር ምሳሌ ሁኑ፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም ከእውነት ጋር እንዲቆምና ለእውነት ዋጋ እንዲከፍል /ከመከራው እንዲሳተፍ እና ከመከራዉም እንዳይሸሽ/ እናንተ ቀዳምያን በመሆን አትጉት፡፡ አለበለዚያ ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ክህነት እና ኃላፊነት ባትይዙትና ባትቅበሉት የተሻለ ነበር። ከፊታችሁ እግዚአብሔር መልካም ዕድል አመቻችቶላችኋል እና ይህን በመከራ ውስጥ ያለን በረከት ትሳተፉ ዘንድ እኛ ደካሞች ገዳማውያን ለተልዕኮ በምትፋጠኑላት ቤተ ክርስቲያን ስም አደራ እንላችኋለን፡፡

፭. ለአብነት ተማሪዎች እና ለመንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት፡ - የወደፊት የቤተክርስቲያን ተረካቢዎች ስለሆናችሁ ሙሉ ሕይወታችሁን ለቅድስና፣ ለንጽህና የተዘጋጀ አድርጉ። ምክንያቱም ክህነታዊ አገልግሎት ዋናው መሰረቱ የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ በጸሎት እየተጋችሁ የእውነተኛ ደቀ መዝሙር ተግባር በመፈጸም፣በማስተዋል የድርሻችሁን ትወጡ
ዘንድ አደራ እንላለን፡፡

፮. ለቤተክርስቲያን ማኅበራት፣ሰ/ት/ቤት እና ወጣቶች፡ - ዘመኑን ዋጅቶ በመስራት እስካሁን ባደረጋችሁት ሱታፌ ቤተክርስቲያን ታመሰግናችኋለች᎓᎓ ነገር ግን ዛሬ እና ነገ /አሁንና ወደፊት/ ከዚህ በላይ መሥራት እንዳለባችሁ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡ ደግሞም የተከሰተውን ችግር ለመፍታት፡-
• ከማንኛውም የቤተክርስቲያን አካል ጋር ተግባብቶ በመስራት • ሕዝበ ክርስቲያኑን ግንዛቤ በማስጨበጥ • በጾምና በጸሎት ተግቶ በማትጋት
• ጎሰኝነትን በመጸየፍና በማስወገድ
• እርስ በእርሳችሁ ተቀናጅቶ፣ተግባብቶ እና ተናቦ በመስራት
• ይህን በመሳሰለው በጎ ሥራ ሁሉ የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ በቤተክርስቲያናችን
ስም አደራችን የጠበቀ ነው፡፡

፯. ለምዕመናን እና ምዕመናት /ሕዝበ ክርስቲያን/ ፡- እስካሁን ቤተክርስቲያን በምትፈልጋችሁ ሁሉ የልጅነት አስተዋጽኦዋችሁን አበርክታችኋል፡ ነገር ግን ካለፈው ይልቅ የወደፊቱ ተግባራችሁ ለእናንተ እና ለቤተክርስቲያን ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ትህትናን ገንዘብ በማድረግ ሃይማኖትን ከምግባር በማስተባበር ቤትክርስቲያን ከእናንተ የምትጠብቀውን ሁሉ በማድረግ እራሳችሁ በምትከብሩበት እና ሰማያዊ ዋጋ በመታገኙበት መከራ ውስጥ ለማለፍ አታመንቱ ከምድራዊ ይልቅ ሰማያዊውን አስቡ በዚህም ሐሰትን፣ፍርሐትን ግብታዊ ስሜትን እና ማመንታትን ከእናንተ አርቃችሁ በእውነትና በእምነት ከእረኞቹ ጋር በመተባበር ለእናታችን ቤተክርስቲያን የሚጠበቅባችሁን ተግባራት ሁሉ እንድትወጡ ደካሞች ገዳማውያን በአምላከ ቅዱሳን ስም አደራ እንላችኋለን፡፡
👍81
፰. ለሕጻናት: - በእናንተ በረከት እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን እና ሀገራችንን ከገጠማት ፈተና እንደሚታደጋት እምነት አለን፡፡ ስለሆነም እናንተም በሕጻን ማንነታችሁ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምኑ ቤተሰቦቻችሁንም እንድታተጉ በዚሁም ቂርቆሳውያን መሆናችሁን እንድታስመሰክሩ እኛ ገዳማውያን አባቶቻችሁና ገዳማውያት እናቶቻችሁ እናንተ ሕጻናት ወደ እርሱ ትመጡ ዘንድ በወደዳችሁ አምላክ ስም አደራ እንላችኋለን፡፡ የነገይቱ ቤተ ክርስትያን የእናንተ ነችና ከዚህ ዘመን የተሻለች ቤተ ክርስቲያን ትኖራችሁ ዘንድ በጸሎታችንም እንለምናለን፡- / ማሳሰቢያ መልእክቱን ማንበብ የሚችሉ ህጻናት እራሳቸው እንዲያነቡ ማንበብ ለማይችሉ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው እንድታነቡላቸው አደራ
እንላለን፡፡/

፱. ለአኀት አብያተ ክርስቲያናት፡ - ሃይማኖት ዘር፣ሀገር እና ባንዲራ/አርማ/ የለውም፡፡ ዘሩ ክርስትና፣ ሀገሩ ሰማያዊ ባንዲራው /አራማው መስቀል ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የገጠማት ፈተና የእናንተም ነው እና በጸሎታችሁ፣በሀሳባችሁ በምክራችሁ፣በመልዕክታችሁ፣ በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከእውነተኛዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን መከራ ተካፋይ እንድትሆነ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ስም እኛ ደካሞቹ ገዳማውያን አደራ እንላችኋለን፡፡

፲. ለመንግስት፡ - ምድራውያን መንግስታት በምድር የሚያስተዳድሩትንና የሚመሩትን ሁሉ በእውነትና በፍትሕ እንዲመሩ የተቀበሉተ ኃላፊነት ግድ ይላቸዋል፡፡ ስለሆነም እስካሁን የሰራችሁትን ክፉም ሆነ በጎ እንተወውና ሰሞኑን ለተፈጠረው ችግር የመንግስት አስተዋጽኦ እንዳለው ይሰማናል። ምክንያቱም በችግሩ ውስጥ ተዋናይ መሆን ወይም ችግሩን አይቶ እንዳላየ ማለፍ አንዲት ሀገርን ከሚያስተዳድር አካል አይጠበቅም። ይልቁንም የቤተክርስቲያኗን ዶግማና ቀኖና በጠበቀ መልኩ ቤተክርስቲያኒቱ ችግሩን ለመፍታት በምትሄድበት መንገድ ሁሉ ተባባሪ መሆን ይጠበቅበታል። ያለበለዚያ የችግሩ ፈጣሪ እና ለችግሩ ዱላ አቀባይ ከመሆን ተለይቶ አይታይም᎓᎓ ሕዝበ ክርስቲያኑ መንግስት በምድራዊ ነገር በእኩልነት እና በፍትሕ እንዲመራው ይፈልጋል እንጂ ሃይማኖቱን ለማዳከም የሚሰራ ሆኖ ሲያገኘው የመንግስትና የሕዝበ ክርስቲያን ግንኙነት እግዚአብሔር እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ከሚያደርጉት ግንኙነት አይበልጥምና መከራን በመቀበል ሰማያዊን ዋጋ ለማግኘት ምዕመናንና ምዕመናት የሚጠበቅባቸውን ሃይማኖታዊ ግዴታ ለማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ሊታወቅ ይገባል። መንግስት ምድራዊውን ዓለም ሲመራልን ሃይማኖት ደግሞ ሰማያዊውን ሀገር ያወርሰናልና፡፡ ቤተክርስቲያን ሰማያዊት ብትሆንም ተጋዳይቱ ቤተክርስቲያን በሀገር እና በምድር ላይ ነው ያለችው᎓᎓ ስለሆነም ምድራውያን መንግስታት ህልውናዋንና መብትዋን አክብረው ሊያስከብሩላት የተገባ ነው᎓᎓የመንግስት ትንሹ ግዴታ ህግን ማስከበር ነው ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጠረውን ህገ ወጥ ድርጊት ማስቆምና ህገወጥ ድርጊት ፈጻሚዎችንና ተባባሪዎችን ሥርአት ማስያዝ ከመንግስት የሚጠበቅ መንግስታዊ ግዴታ ነው፡፡

፲፩.ለፓለቲከኞች፡ - ፖለቲከኞች ከቤተክርስቲያን መንፈሳዊ መአድ እንካፈል ሲሉ ቅድስት ቤትክርስቲያን የፖለቲካ እሳቢያቸውን ሳትመለከት ከመሶቧ ትመግባቸዋለች ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ፖለቲካቸው ከረጢት ሊያስገቧት ሲሉ ችግሮች
ይፈጠራሉ፡፡ስለሆነም የፖለቲካ ፓርቲ እና ፖለቲከኞች የቆማችሁለትን ርዕዮተ ዓለም በእውነት መሥረትነት ላይ እንድትተገብሩና ሰው የምድርና የሰማይ ፍጥረት መሆኑን አውቃችሁ በምድር በሚኖርበት ጊዜ ሁሉ ሃይማኖቱን በነጻነትና በሥርዓት እንዲያከናውን በችግሩም ጊዜ መፍትሔ ለማምጣት የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡

፲፪.ለኢትዮጵያውያን በሙሉ፡ - ኢትዮጵያውያን ታሪካችን እንደሚነግረን ሃይማኖተኛነት ፍትሕ፣መከባበር፣ መረዳዳት እና የመሳሰሉት የበጎ ሰው ተግባራትን ገንዘብ ያደረግን ነን:: ዛሬ ግን የኛ መገለጫ ያልሆኑ እኩይ ተግባራት ተዋናይ ከሆን ሰነበትን፡፡ ስለሆነም በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላውን ተግባራት ሁሉ ከእኛ በማራቅ የቀድሞ በጎ ተግባራችንን አጽንተን በመያዝ ምድራዊ የጋራ ቤታችንን በፍቅር እንኑርባት ያለበለዚያ

ሰው የሚያምንበትን ሰማያዊ ቤት አፈርስብሃለሁ ሲሉት ወይም ለማፍረስ ተባባሪ ሲሆኑ ዘላለማዊ ሕይወቱን ለማግኘት በሚያደርገው ተጋድሎ ሀገራችን ለምድራዊ ኑሮአችን እሾክ እንዳትሆን ያሰጋል። ኢትዮጵያውያን ሆይ ምድራዊ ቤታችንን በአንድነት እና በፍቅር እንኖርባት ዘንድ አንዱ በአንዱ ላይ ከመነሳሳት ተቆጥበን የኅብረት ቤታችንን የጋራ ሰላማችንን ለመጠበቅ የሰውነት ግዴታችንን እንወጣ፡፡

ማጠቃለያ
የችግራችን መፍቻ ቁልፍ ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብሮ መገኘት ነው፡፡ ስለሆነም የገጠመንን ችግር ለመፍታት ሁለት አበይት ተግባራትን እነርሱም ፡-
1. ጾምና ጸሎት
2. ሰማዕትነትን (መከራ መቀበልን) ለመፈፀም ወደ ኋላ ማፈግፈግ የለብንም፡፡ ጾምና ጸሎት እንኳን በቤተክርስቲያንና በሀገር ላይ ፈተና ተጋርጦ ይቅርና በየእለቱ የምንተገብረው ክርስቲየናዊ ተግባራችን ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ችግሩን እንዲፈታልን በግል፣በቤተሰብ፣በኅብረት በመሆን በጾም በጸሎት መበርታት ይጠበቅብናል፡፡ ይኸውም
. ሳናቋርጥ በመጸለይ ፤ 1ኛ ተሰ 5፡17-18
. ከጥሉላት ምግብ በመራቅና መናኛውን በመመገብ ፤ መዝ 108፡24 ፤ዳን 10፡2-3 . ከአልጋችን ወርደን መሬት ላይ በመተኛት ዳን 9፥3 ፤ አስቴር 4፡3
በተሰበረ ልብ ከልቅሶ ጋር ሆኖ ፤ ኢዮኤል 2፡12 ። እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎበኘን ዘንድ ተግተን እንለምን፡፡
ሰማእትነት (መከራ መቀበል) የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ ዘር ነውና ከቅዱስ ፓትርያርካችን ጀምሮ ሁላችንም ሰውነታችንን ለሰማእትነት እናዘጋጅ ዘንድ እኛ ደካሞች ገዳማውያን በአምላከ ቅዱሳን ስም አደራ እንላለን ፡፡ ይኸውም፡-
የጊዜ
የገንዘብ
የእውቀት
የአካል
የጉልበት
- የሕይወት ሰማእትነት ለሚጠይቀው ሁሉ ምንም ሳናመነታ በእውነት ፣ በጥብአት (ክርስቲያናዊ ድፍረት)፣ በፍቅር (ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ ) የሚጠበቅብንን ማድረግ ነው :: ሮሜ 8 ፥ 35
ምንአልባት አንዳንዶች ሰማእትነት ለመቀበል ንሰሐ ስለአልገባሁ እፈራለሁ ልትሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን የቤተክርስቲያናችን የሰማእትነት አስተምህሮ እንደሚነግረን አንድ ሰው ንሰሐ ሳይገባ በመጣው መከራ ውስጥ እራሱን በሰማእትነት በማሰለፉ _ ሰማእትነቱ ኀጢአትን ማስተሰርይ ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳን ሰማዕታት እንደ አንዱ ያስቆጥረዋል፡፡ ስለሆነም መከራን ፣ ሰማዕትነትን ለመቀበል ሰውነታችንን ጨክነን ማዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ የቤተክርስቲያን ትንሳኤ ይሆናል፡፡
ወደፊት ምን ይደረግ ?
አሁን የገጠመን ሰሞነኛ ችግር እኛ የሚጠበቅብንን ካደረግን ይፈታል ብለን እናምናለን፡፡
ነገር ግን ችግሮቻችን ስር የሰደዱና ለችግሮቹም ሁላችን ተጠያቂዎች ነን፡፡ ስለሆነም የነገይቱን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ወደ ቀድሞ ማንነቷ ትመለስ ብሎ ለመፍትሔው ያለምንም ማመንታት፡-
👍62
የምንኩስና እና የክህነታዊ ሕይወቱን አነዋወር የክርስትናውን አነዋወር አስተዳደሩን
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን እና እንደሚገባ መተግበር አለብን፡፡ ይኸንንም በማድረግ እንደ ፈቃዱ ለመኖር :-
ከዘረኝነት ጎጠኝነት
ከራስ ወዳድነት
ከጥቅም ፈላጊነት
በአጠቃላይ ከስነ ምግባር ብልሹነት / ከሥጋ ሥራዎች ራሳችንን መለየት ያስፈልጋል። ገላ 5፥19-21
ለዚህም ከቅዱስ ፓትርያርካችን ጀምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ሁላችን የቤተክርስቲያን አካላት በእውነት መንገድ ላይ ቆመን ተጋድሏችንን ልንፈጽም ግድ ይለናል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ እኛም አብረን ቤተክርስቲያንንም ወደ ቀድሞ ማንነቷ ስትመለስ እናያለን፡፡
አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ᎓᎓ ኤር 5፥21
ስለድፍረታችን ሁላችሁንም በክርስቶስ ስም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ነገር ግን “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፡፡" 1ኛ ዮሐ 4፡18 የሚለውን አምላካዊ ቃል አብነት አድርገን ነው፡፡
ችግሮቻችን ሁሉ ተፈትተው በምድር የእግዚአብሔር ልጆች በሰማይም የመንግስቱ
ወራሾች እንሆን ዘንድ
የእግዚአብሔር ቸርነት
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የቅዱሳን መላእክት ጠባቂነት
የቅዱሳን ሁሉ ተራዳኢነት
በዚህም ዘመን ያሉ የእውነተኞቹ አበው እና እማት ጸሎት የህጻናቱ በረከት ከእኛ ጋር ይሁን፡፡
አምላከ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንና ሀገራችንን ህዝቡን ሁሉ ይጠብቅ :: አሜን፡፡

【ማሳሰቢያ- መልእክቱን ያስተላለፉላችሁ ገዳማት በርካታ ሲሆኑ ከቦታ መራራቅ አንጻር እነዚህን ማህተሞች ብቻ አድርገናል፡፡】
👍3
👍3
መልፅክተ ገዳማት pdf.pdf
12.6 MB
3👍1
2025/07/13 18:51:14
Back to Top
HTML Embed Code: