Telegram Web Link
የቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ በቤተ ክርስቲያናችን ኦፊሻል የዩቱብ ቻናል ተከታተሉ ። በዚያውም ሰብስክራይብ አድርጉ ። በጣም አሳዛኙ ነገር አሁን ሰሞኑን ነው 373k የገባው እንጂ 260k ነው የነበረው ። ይኸ ምን ማለት መሰላችሁ የራሳችንን ትተን የሌላውን ያውም የማይጠቅመንን ነው የምናሞቀው ። ስለሆነም ሚዲያችንን እናበረታታ ።



https://www.youtube.com/live/5m0qgfjKolU?feature=share
👍7
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
Photo
እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶአል

#Ethiopia | "ሕዝባችን በሕገ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ከአቅዋማችን እንደጸናን እንድታውቁ እንፈልጋለን:: እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶአል:: እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው::

በጸሎት ትጉ:: ነገ ጠዋት ዝርዝር ሁኔታውን እንገልጻለን"

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

"በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው

* ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤
* በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤
* የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤

እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡

በዚህም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡

እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

"አባቶቻችን አንተን ተማመኑ:: ተማመኑ አንተም አዳንኻቸው"
መዝ. 21:4
👍5012
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
Photo
ሰበር ዜና
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

EOTC TV
👍75👏91
#ሰበር_ዜና
በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግበዋል።
👍20
2025/07/08 15:26:20
Back to Top
HTML Embed Code: