Telegram Web Link
. መፃጉዕ እና ኒቆዲሞስ
【 ዮሐ ፫ / ዮሐ ፭ 】
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥
የዐቢይ ጾም ሳምንታት ከ፶ ሚሊየን ሕዝብ በላይ ባላቸው ተዋህዶን በሚያምኑ በጽባሓውያኑ ኦርቶዶክሳውያት አብያተ ክርስቲያን ዘንድ [ Eastern Christian churches adhering to Miaphysite Christology; Oriental Orthodox Churches】እኛ ከዘወረደ እስከ ሆሳዕና እንደምንዘክረው ከሆሳዕና በቀር በስያሜ የተለያየት መታሰቢያ ተሠጥቶት ይዘከራል
በብዙዎቹ ① ከብካበ ቃና ☞ ② ለምጻሙን ማዳኑ ☞ ③ ሽባውን ማዳኑ ☞ ④የከነናዊቷ ሴት እምነት ልጇን ማዳኑ ☞ ⑤ እኩለ ጾም/ በዓለ መስቀል ☞ ⑥ ደጉ ሳምራዊና ጀርባዋ የጎበጠች ሴት ☞ ⑦ ዘእውሩ ተወልደ ☞ ⑧ ሆሳእና ይታሰቡበታል።

በዚህ ውሥጥ በየሳምንታቱ የእነዚህ ታሪኮች መጻፍና መዘከር ምክንያቱ ታሪክ ‘አዋቆች’ ብቻ እንድንሆን አይደለም። ለምሳሌ በቅዱስ መጽሐፍ የቅዱሳን እና የርኩሳን፣ የቡሩካንና የርጉማን ፣ የጻድቃንና የኃጥዓን ታሪክ ሁሉ ተዘግቧል ምክንያቱ ደግሞ በሁለት መንገድ መረዳት ይቻላል። እንድንታነጽና እንድንገሠጽ

፩) የመልካም ሰዎች ታሪክ ⇨ ለጽናት በተስፋ ለመጽናናት
“በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።” 【ሮሜ ፲፭፥፬】

፪) የአመጸኞች ታሪክ ⇨ ለተግሳጽ
“ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።” 【፩ኛ ቆሮ ፲፥፲፩】

በዚሁ መንገድ ሊቃውንትና መና**ፍቃን ፣ የካዱና የጸኑ ፣ በጎ ሠሪዎችና ክፉ አድራጊዎች … ግለሰቦችም ታሪካቸው ተዘግቦ ተነግሯል። ዐላማው እንደቀድሞው ለሁለት ጥቅም ነው ፤

፩) መልካም አድራጊዎች እንድናውቃቸው ምሳሌና አብነት እንድናደርጋቸው
☞ "ወአእምርዎሙ ለእለ ከመዝ ⇨ እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን እወቁአቸው”
【፩ኛ ቆሮ ፲፮፥፲፰】

፪) ክፉ አድራጊዎችን ግን እንድናውቅባቸው ለመጠንቀቅ
☞ "ተዓቀቡ አንትሙሂ ወዑቅዎሙ ለከለባት ወዑቁዎሙ ለገበርተ እኪት ⇨ ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ።” 【ፊል 3፥2】

መፃጉዕና ኒቆዲሞስም በ፫ ክፍል ታሪክ የዚህ መንገድ አስተማሪዎች እንዲሆኑ በዐቢይ ጾም ሰንበታት የሚታሰቡ ግለሰቦች ናቸው

✧ ክፍል 【፩】 በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ እና ምዕራፍ ፭

ኒቆዲሞስ ☞ ወሐሎ አሐዱ ብእሲ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወመልአኮሙ ለአይሁድ
ወውእቱ መጽአ ኀበ እግዚእ ኢየሱስ ቀዲሞ ሌሊቱ

መፃጉዕ ☞ ወሐሎ አሐዱ ብእሲ ዘሠላሳ ወሰመንቱ ክረምቱ እምዘደወየ ወኪያሁ ርእዮ እግዚእ እግዚእ ኢየሱስ ይሰክብ ውስተ ዐራቱ

ልዩነት
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታው የመጣ
መፃጉዕ ጌታው ወደ እርሱ የመጣ
ኒቆዲሞስ ቀድሞ በሌሊት የሚገሰግሰው ከጌታው እግር ስር ሊማር (ለትምህርት)
መፃጉዕ ቀድሞ ወደ መጠመቀቂያው ውኃ ለመውረድ ደጅ የሚጠና ምኞቱ ሊማር (ለምሕረት)
ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ፣ ባለ ሥልጣንና ባለሀብት
መፃጉዕ ምሁረ ደዌ ፣ ሰው የሌለው ፣ ድኃ (ንብረቱ አልጋው ብቻ)
ኒቆዲሞስ ስሙ የተጠቀሰ መፃጉዕ ግን በህመሙ ደረጃ መገለጫው እንጂ በስም ያልተጠቀሰ 【የመፃጉን ስም አልተጠቀሰም መፃጉዕነት የደዌ መጽናት እንጂ ስም አለመሆኑን ልብ ይሏል ፤ ልክ እንደ አልአዛርና ነዌ (ባለጠጋው) 】

ስሙ አለመጠቀሱ ባለመታመኑ ነው፤ የጻድቃን መንገድና የታመኑ ሰዎች ስም መታወቁ በመንግሥቱ እውቅና እንዳላቸው ያስገነዝባልና
“ኄር እግዚአብሔር ለእለ ይትኤገስዎ በዕለተ ምንዳቤሆሙ ወያአምሮሙ ለእለ ይፈርህዎ ⇨ እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።”።【 ናሆም 1፥7】
“እስመ እግዚአብሔር የአምር ፍኖቶሙ ለጻድቃን ወፍኖቶሙሰ ለኃጥኣን ትጠፍእ ⇨ እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።”
【 መዝሙር 1፥6】

✧ ክፍል ፪
በአይሁድ ክስና ውንጀላ ውስጥ
☞ መፃጉዕ ወደ አይሁድ ሔዶ ክርስቶስን ከሰሰ ☞ ለክርስቶስ መገደል ምክንያትም ሆነ
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፻፫ ጀምሮ እንደተነገው
«ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው። ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።

☞ ኒቆዲሞስ ግን አይሁድ ወደእርሱ በመጡ ጊዜ ጥብቅና የቆመና እንዳይያዝ የሞገተ ሆኑ ተገኝቷል
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፯ ከቁጥር ፶ ጀምሮ
« ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ፦
⁵¹ ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው።»

✧ ክፍል ፫

መጻጉዕ ፦ ጌታውን በዕለተ ዓርብ በጥፊ መትቶ የመታበት እጁ ሰሎ ቀርቶ ከደዌው የታረቀ
ቀድሞ እንዲህ ሲል አስጠንቅቆት ነበር "ናሁኬ ሐየውከ ዑቅ ኢትአብስ ዳግመ እንከ ከመ ዘየአኪ ኢይርከብከ ⇨ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።” 【ዮሐ ፭፥፲፬ 】
እርሱ ግን "በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን? ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።” 【ዮሐ ፲፰፥፳፪】

ኒቆዲሞስ ፦ በከበረና ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ገዝቶ ለአምላኩ የመግነዝ ሥርዓት ፈጸመ፤ ከስውሩ ደቀመዝሙር ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ሆኖ አምላኩን ሥጋ ከመቃብር አውርዶ አካሉን በአዲስ በፍታ ሸፍኖ ወደ አዲስ መቃብር ያኖረ
【 ዮሐ ፲፱፥፴፰ እስከ ፵】
«ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።
የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።»

ኒቆዲሞስ በልሳነ ጽርእ ኒኮዴይሞስ "Νικόδημος" ይባላል በትርጉሙ ኒኮስ (νῖκος) እና ዴይሞስ (δῆμος) አገናኝቶ መዋዔ እም ሕዝቡ ይለዋል ከሕዝቡ ድል ያደረገ "victorious among his people" ይለዋል

ቤተክርስቲያናችን ሦስት ጊዜ ትዘክረዋለች
፩) የዕረፍቱን መታሰቢያ ነሐሴ ፩ ቀን ሠይማ
፪) በዐቢይ ጾም ደግሞ የ፯ኛ ሳምንት መጠሪያን ሠጥታ
፫) ለሁልጊዜው ደግሞ የቤተመቅደሱን አጥር ቅጥር እንደመግነዙ በመቁጠር የመግቢያ በሩን አዕማድ ለዮሴፍና ኒቆዲሞስ መታሰቢያ እንዲሆናቸው በማውሳት

የቅዱሱን የማታ ሰው የኒቆዲሞስን በረከት በሁላችን ላይ ያሳድርብን!

መልእክቱን በድምጽና በምስል ለመከታተልና ለመስማት በተከታዩን ሊንክ ታግዘው ማግኘት ይችላሉ
https://youtu.be/jkIgQ87W4Zw?si=LRACYvXhUAYJDQkp
╔​✞═•┉✽✥✥✽┉•═✞╗
❀………#ነገረ_ናርዶስ ………❀
╚✞═•┉✽✥✥✽┉•═✞╝

“ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።” 【 ዮሐ ፲፪፥፫】

ሊቃውንት በትርጓሜ “ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሐተ ☞ የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ይመስገን” ይላሉ!
ለዚህ መነሻውቸው አፈወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ዐለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰውን ሰው ያዳነበት ጥበቡ የረቀቀ መሆኑን በተናገረበት ክፍል የገለጠው ነው። እንኳን መክበሪያችን ለሆነው ሰሙነ ሕማማት አደረሳችሁ! ?

በመልካም መዐዛው ምሽት እስኪ ጥቂት ስለነገረ ናርዶስ እያነሳን ከመጽሐፍ እና ከመምህራን አፍ የተገኘውን እንማማር

#ናርዶስ / #ልጥረ_ናርዱ
°°°°°°°°•••°°°°°°°°°°°°°
የዕብራይስጡን ( נֵרְדְּ ) ኔርድ መነሻ ያደርጋል በግሪኩ ደግሞ (πιστικός) ፒስቲኮስ ይለዋል። አንዳንዶች ግን ከግሪኩ ናርዶስ (νάρδος ☞ nardos) ጋር ያምታቱታል ያ ማለት ግን በሳይንሳዊ ስሙ ናርዶስ ስትሪካ [Nardus stricta] የሚባለውን የሳር ዐይነት የሚወክል ሲሆን እንደስንደዶ ያለ የምንጣፍ ሳር (matgrass) የምንለው ነው

ይህኛው ናርዶስ ግን ከላይ እንደተመለከተው በእብራይስጡ ኔርድ የሚለውን መነሻ ይዞ ናርዲኖን ይላል በትርጉም ልጥረ ዘናርዱ ☞ የናርድ ንጥር (spikenard) ማለት ነው። 【የጠራ የነጠረ የበራ የተጠበቀ ንጥር / ልጥር ይባላል!】ባለመልካም ሽታ ስለሆነ መዓዛው የተወደደ ቅባት ወይም በከፍተኛ ገንዘብ የሚገዛ ስለሆነ ዋጋውም የተወደደ ሽቱ ነው ናርዶስ !

የእኛውም ግዕዛችን ለወንድ ናርዳዊ ለሴት ናርዳዊት ብሎታል ይህም ከናርድ የተገኘ/ች እንደማለት ነው። በእርግጥ ናርድ የሚባለው የሽቱ / የቅባት መገኛ ተክል ነው፤ ታዲያ ያንኑ መነሻ በማድረግ ናርዶስ ሲል ከቅጠሉ ከቡቃያው ከአበባው የተገኘ የነጠረው ወይም የጣፈጠው መረቅ ሽቱ ማለት ነው የናርድ ናርዳዊ/ት እንደማለት።

ናርዶስ የሚለውን ለሰዎች በስመ ተጸውኦና በማዕረግ ዘርፍ የመጠቀም ልማድ አለ፤ በቤተክርስቲያናችን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳን መኻል ጥር ፬ ቀን የሚከበሩ አባ ናርዶስ የሚባሉትን የደብረ ቢዘን ገዳም መስተጋድል ቅዱስ አባት እናገኛቸዋለን። እሊኽም ያለበትር በጥላቸው እባብ የሚገድሉ በጽናት የሚጋደሉ ቅዱስ አባት እንደ ነበሩ መጽሐፈ ስንክሳር ይነግረናል።

ከቅዱሳኑም መካከል በሚስበው መልካም የምግባር መዓዛቸው እና በጸና የተጋድሎ ሕይወታቸው አርአያ የሆኑ ምሳሌነታቸውም የተመሰከረላቸው ናርዶስ እየተባሉ በሊቃውንት የተወደሱ አሉ። ለአብነት ያኽል ቅዱስ ኡራኤል ፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም ፣ ንጉሡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስን… ከብዙ በጥቂቱ ማንሳት ይቻላል።

【መልክአ ዑራኤል ቁ ፳፮】
ናሁ ጸገየ ጽጌ ማኅሌት
ወናሁ ፈረየ ፍሬ ስብሐት
ዘእምጒንደ መስቀል ተረክበ በቀራንዮ ገነት
ዑራኤል ናርዶስ ዘመዓዛሁ ሕይወት
ስብሐቲነ ያምዕዝ መዓዛሁ ከመ ዘሱራፊ ማዕጠንት።
ቅድመ ገጸ ሕያው ክርስቶስ ወእሙ ቅድስት
【እነሆ በቀራንዮ የተክል ቦታ ከጉንደ መስቀል የተገኘ ጽጌ የምስጋና አበባ አበበ። የምስጋና ፍሬ አፈራ። ዑራኤል ሆይ፤ ሕይወትን የሚያድስ መዓዛው የጣፈጠ ተክለ ናርዶስ ነውና ጼና መዓዛው በሕያወ ባሕርይ በክርስቶስና በክብርት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ፊት እንደ ሱራፊ ማዕጠንት ባለ መዓዛ መዓዛው የምስጋናችንን መዓዛ ያጣፍጥልን አሜን።】

【መልክአ ሀብተ ማርያም ቁ ፳】
ሰላም ለመዛርዒከ ለድኩማነ ልብ ብላዝ
እለ ስፉሐት እማንቱ ለገቢረ ሠናይ ትእዛዝ
ሀብተ ማርያም ናርዶስ ዘደብረ ሊባኖስ አርዝ
እምንዕስከ ዘተሠቀይኮ እም ተክለ ሃይማኖት ውኂዝ
ይኩነኒ ተስፋ ለወልድከ ትኩዝ

【መልክአ ኢየሱስ ሞዐ ቁ ፳፯】
ሰላም ለእራኅከ አርአያ ክርስቶስ አቡሁ
ዘኢአፀወ ምሕረተ በላዕለ ነዳያን አኃዊሁ
ኢየሱስ ሞዐ ናርዶስ ለጽጌ ጽድቅከ በመዓዛሁ
ምስካብ ሥጋከ ለእስጢፋኖስ ጽርሑ
አናስረ ዓለም ታስግድ ወታገኒ ናሁ

【መልክአ ይምርሃነ ክርስቶስ ቁ ፲፩】
ሰላም ለእራኅከ ጒንደ አጻብዕ ወአጽፋር
ካዕበተ ዐሥር
ይምርሃነ ክርስቶስ ናርዶስ ዕፀ ጽጌ ገነት ሥሙር
ሠውረኒ በጽላሎትከ ኢይልክፈኒ ሐሩር
ወኢያጽልሙኒ ነፋሳት ወቁር

ዛሬ የሕማማት ረቡዕ የመልካም መዓዛ ቀን ነው፤ በዚህ የከበረ ሽቱ ባለሽቱዋ ማርያም (ማርያም እንተዕፍረት ) ጠረንዋን የሚቀይረውንና መልካም መዓዛ የሚያጎናጽፋትን ጌታችንን በእንባዋ አጥባ በጸጉሯ አብሳ የቀባችው ይህን ሽቱ ነበር ።

“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።” 【ማር ፲፬፥፫】

አልባስጥሮስ የሚለው【ἀλάβαστρον ☞ alabaster】 በልማድ ራሱ ሽቱ እየተባለ ቢገለጽም የናርዶሱ ማስቀመጫ ሙዳየ ዕፍረት ወይም የሽቱ መያዣ ቢልቃጥ/ብልቃጥ (perfume vase) መሆኑን መረዳት ይገባል።

«ወመልአ ቤተ መዐዛሁ ለውእቱ ዕፍረት» የዚህ የናርዶስ ሽቱ መዓዛ ቤቱን ሲያውደው የማርያም ታሪኳ ተለውጦ የይሁዳ ሌብነቱ ተገልጦ ታየ፤ የትዕቢተኞችን በደል የሚገልጥ የትሁታንን ኃጢዓት የሚውጥ ሆነ ናርዶስ!

የናርዶሱ ከየት መጣ ታሪክ ዳዊት ሰሎሞን ከተቀቡት የተረፈ ከልጅነት ወዙ ጋር ተደባልቆ የተቀመመ መሆኑን መተርጉማን እንደሚከተለው ያትቱልናል

ይህች ሴት ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጽፍሯ ይህ ቀራት የማትባል መልከ መልካም ናት። መላ አካሏን የሚያሳይ መስታወት አላት ልብሷን አኑራ መልኳን አይታ
«መፍረስ መበስበስ ላይቀር እንዲህ ማማር ምን ይረባል የዚያስ የዚያስ ኃጢአት የሚያስተሠርይ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል አሉ ለሱ የምቀባው ሽቱ ገዝቼ እሄዳለሁ»
ብላ በዝሙት የሰበሰበችው ሦስት መቶ ወቄት ወርቅ አላት ይዛ ሄደች። ዲያብሎስ ታመልጠኛለች ይህን ጊዜ ላስታት ብሎ ቀድሞ ከምታውቀው አንዱን መስሎ በአምሳለ ወሬዛ ሠናየ ላህይ ከመንገድ ቆያት። «ወዴት ትሄጃለሽ ?» አላት፤ ዝም አለችው «አንች ባትነግሪኝ እኔ እነግርሽ የለም " እንግዳ ወንድ መጥቶብሽ ለእሱ ልትቀቢው ሽቱ ልትገዥ ትሄሻለሽ» አላት «አዎን» አለችው።
«ይህም አይደለም ፍቅሩ ያላለቀለት ወንድ መጥቶብሽ ለዚያ የምትቀቢው ሽቱ ልትገዥ ትሄጃለሽ» አላት ፤ ደግማ «አዎን» አለችው
«ይህም አይደለም በጥቂት ገንዘብ ብዙ ገንዘብ የሚሸጥ ነጋዴ መጥቶብሽ ለእሱ የምትቀቢው ሽቱ ልትገዥ ትሄጃለሽ» አላት፤ ለሦስተኛ ጊዜ መልሳ «አዎን» አለችው !
«ሁሉንም አዎን አዎን ትያለሽ ማናቸው ነው ?»አላት።
       «እንግዳ ወንድ መጥቶብሽ አልክኝ ከዚህ ዓለም ልዩ የሚሆን ጌታ መጥቷል። ፍቅር ያላለቀለት ወንድ መጥቶብሻል ላልክኝ ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት እንዲል። የሰው ፍቅር አገብሮት ሊሞት መጥቷል። በጥቂት ገንዘብ ብዙ ገንዘብ የሚሸጥ ባለጸጋ ነጋዴ መጥቶብሻል ላልከኝ አዎን በጥቂት ትሩፋት ብዙ ክብር የሚሰጥ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥተልና ለእሱ የምቀባው ሽቱ ልገዛ እሄዳለሁ» ብላ ስሙን ብትጠራበት እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ ጠፍቶላታል።
       ከዚህ በኋላ ሃድኖክ የሚባል ባለ ጸጋ ነጋዴ አለ ሄዳ
«ለነገሥታት የሚገባ ሽቱ አምጣ» ብላ ሦስት መቶ ወርቅ ሰጠችው በሀገራቸው ሐሰት የለምና «ይህን ያህልስ የሚያወጣ የለኝም» አላት እሱ የማያውቀው እናቱ የምታውቀው ዳዊት ሰሎሞን ተቀብተውለት የተረፈ «ዕፍረተ ናርዱ» ነበር ከእንዲህ ያለ ቦታ አለ ሽጥላት ብላው ሽጦላት አምጥታ ቀብታዋለች። ይህ ብቻም አይደል ጌታ ግብፅ ሲወርድ ሰሎሜም ፈያታይ ዘየማን ይዘውት ሳለ ከልብሱ ላይ ወዛ ቢያጽቡት ሰፈፈ ይህን በዕቃ አኑረውታል ይህም ተጨምሮበታል።

ናርዶስ ባለመልካም መዐዛ ቅባት ብቻ ሳይሆን በብዙ መንገድ ፍቱን መድኃኒት ጭምር ነው። መድኃኒትነቱንም  ከልማዳዊ የባህል ሕክሞና ዘርፍ አንስቶ  በአያሌ ጥናት በተደገፉ የዘመናችን ሳይንሳዊ የሕክምና ምርምር ጭምር  የተመሰከረለት ነው።

በእርግጥ የዓለም የጤና ድርጅት እንዳረጋገጠው 80እጅ የሚሆነው የምድራችን ነዋሪ ባህላዊ ህክምናን ለጤናው መጠበቅ ምርጫው ያደርጋል [About 80% of the world population totally depends on traditional medicine systems for their primary health care needs]

በቀደመው ልማዳዊ / ባህላዊ ህክምና ጥናት (Ethnomedical research) ሚናው ላቅ ያለው የናርድ ተክል በዘርፈ ብዙ ጥቅሙ  ለረቀቀው የሳይንስ ጥናት (Scientific ethnomedical studies)  እንደመነሻ ሆኖ በብዙ ጥናት የተደገፈ የጤና ችግሮች  ማቅለያ በመሆን ለነገረ ሰብእና   ለመድኃኒቶች ግኝት ጥናት እገዛው ከፍ ያለ ነው።

በሳይንሳዊ ስሙ Nardostachys jatamansi [ዕፀ ናርድ ☞ የናርዶስ ተክል] ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት አጥኚዎች ይመሰክራሉ በተለይ በህክምናው ረገድ  ✧ሥሩ (Root) ✧የሥሩ ግንድ (Rhizome) ✧ግንዱ (Stem) ✧ቅጠሉ (Leaves) ✧አበባው (Flower) እና ✧መላ ተክሉ (Whole plant) እየተቀመመ ከጭንቀት የአእምሮ ሕመም እስከ ነቀርሳ (ካንሰር) ድረስ በመድኃኒትነት በብዙ ዘርፍ ያገለግላል።

በክኒን (Tablet) በሽሮፕ (Syrup) በሚዋጥ ባለሽፋን እንክብል (Capsule ) በቅባት (Oil ) በዱቄት (Powder ) እንዲሁም በሌሎች መንገዶች (Granules & Paste) እየተዘጋጀ በዘመናዊ ሕክምናውም ረገድ ለዘርፈ ብዙ ጤና መታወክ መፍትሄ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

አፈወርቅ በድርሳኑ ፬ኛ ክፍል የጠቀሰውን መነሻ ያደረግነውን መድረሻ አድርገን እናብቃ

       «እስመ እግዚኣብሔር ይትባረክ ስሙ ሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሓተ እስመ ተሠግዎቱ ለወልድ ወሕማማቲሁ በእንተ ፍቅረ ሰብእ የዓቢ ወይፈደፍድ እምተፈጥሮተ ዓለም ወአምጽኦቱ እምኀበ ኢሀልዎ ውስተ ሀልዎ»

☞ ስሙ ይክበር ይመስገንና እግዚአብሔር የልጁን ሕማምና ሞት ክብር ምስጋና ብሎ ጠራው ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ብሎ  ሰው መሆኑና መከራ መቀበሉ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ከመፍጠሩ በእጅጉ  ይበልጣል! 
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በምክንያት ሲያስረዳ
   «ፍጥረተ ዓለም ይኤምር ኀበ  አፍቅሮቱ ሰብአ አላ ሕማማቲሁ ባሕቱ ይከብር ፈድፋደ። ☞ ዓለሙን መፍጠሩ ሰውን መውደዱን ያስረዳል። የሕማሙ ነገር ግን እጅጉን ልቆ የከበረ ነው»

በምን አበላልጦት እንዲህ ይላል ቢሉ
☞ ዓለሙን በመፍጠሩ አልደከመበትም፤ በማዳኑ ደክሞበታልና። ☞ ዓለሙን በመፍጠሩ አላዳነበትም መከራ በመቀበሉ  አድኖበታልና።
☞ ሲፈጥር ያየው የለም፤ መከራ ሲቀበል ሁሉ እያየው ነው፤

ማኅየዊትና መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ጠረናችንን በመልካም መዓዛው ለውጦ ለቁስላችን መድኃኒት ለሞታችን ሕይወት የሆነን ክርስቶስ ከበረከተ ሕማማቱ አያጉድለን! 

🌴 በቴዎድሮስ በለጠ ሕማማት ረቡዕ ምሽት ሚያዝያ  ፳፫ ቀን  ፳፻፲፮ ዓ.ም.  
📍 የምድር ጌጥ ደብረ ሊባኖስ
#ቆዳ_ለሐመረ_ብርሃን

በአዲስ አበባና አካባቢው የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በረከት አያምልጣችሁ። እንደዋዛ የምትጥሉትን የፍየሎችና የበጎች ቆዳ ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የታሪክ ባለቤት መሆን የምትችሉበት መንገድ ተመቻችቶላችኋል ስለዚህ በየሚቀርባችሁ ቦታ ወስዳችሁ በመስጠት ጥሩ ምንጭ ኢትዮጵያን በጥራት አስቀጥሉ።
የእንስሳቱ ቆዳ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ብራና ሁነው ይጠብቋችኋል።

የፍየል እና የበግ ቆዳ ለሐመረ ብርሃን
የትንሣኤ ዕለት ሚያዝያ 27

📍 ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት
📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል
📍 አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት
📍 ሰአሊተ ምሕረት
📍 ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል

ለበለጠ መረጃ፦ 0966767676 | 0944240000 | 0909444400 ይደውሉ።
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ [Paschal troparion & Greeting] #የፋሲካ_አመላለስና_ሠላምታ
᳀͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͞ ͟͞ ̸ ͟͞ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ✙ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᳀

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን👋 ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! 🙏 በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።

🤝
መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦  በመጨባበጥ [handshake] በመተቃቀፍ [hugging] አልያም በጉንጭ በመሳሳም [cheek kissing] ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” [holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης ] እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን #አካላዊ_ፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!

🙇 
"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው።

🙋
የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ።

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው [Paschal troparion] እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው [Paschal Greeting] ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽር (ግሪክ)   #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል።

#ምሕዛል_ዘትንሣኤ [Paschal troparion] የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም [χριστος ανεστη] የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው።

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

#ቃለ_ባሕ_ዘትንሣኤ [Paschal Greeting] «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ።  በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ይኩን ሰላም!

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ!

በውጪው ግን ሰጥቶ መቀበል እንጂ አመላለስ የሌለው ባለ አጭር ይዘት ሆኖ በተለያየ ስያሜ የሚጠራ ነው The Paschal Greeting / the Easter Acclamation / The Paschal troparion / Christos anesti…
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 (ተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος))
የበዙቱ የቀደመ መነሻውን ከግሪኩ ተውሰው ሰላምታውንም በሰጣዊ ተሰጣዊ (ሰጪና ተቀባይ) ቃል ልውውጥ ይከውኑታል እንዲህ ሲሉ

#ሰጣዊ ☞ ክሪስቶስ አኔስቲ Χριστός ἀνέστη! Christ is Risen! ✧ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

#ተሰጣዊ ☜ አሊቶስ አኔስቲ "Ἀληθῶς ἀνέστη! " - "Truly He is Risen!" or "He Has Risen Indeed!" ✧ (አሜን) በአማን ተንሥአ

በአረማይኩ ግን ጥቂት የተሰጣዊ ምላሽ ልዩነት ያለው ሆኖ ይነገራል

☞ ክሪስቶስ ሃሪያቭ ኢ ሜሬሎዝ Քրիստոս հարյա՜վ ի մեռելոց: Christ is risen! ክርስቶስ ተንስሥኣ እሙታን

☜  ኦርኺያል ኤ ኻሮውቲዮን ክሪስቶስ Օրհնյա՜լ է Հարությունը Քրիստոսի: Blessed is the resurrection of Christ!" ቡሩክ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ

በሀገርኛ ልሣናት አገባቡ እንዲህ ሊገለጥ ይችላል

⇝ በአማርኛ (☞ ክርስቶስ ተነስቷል ፣ ☜ በእርግጥ ተነስቷል!)

⇝ ኦሮሚፋ /Oromiffa (☞ Kiristoos du'aa ka'eera ፣ ☜ Dhugumaan ka'eera)

⇝ በትግሪኛ (☞ ክርስቶስ ተንሢኡ፣ ☜ በኻቂ ተንሲኡ)

⇝ በጉራጊኛ (☞ ክርስቶስ ተረሳም ፣ ☜ በውረም ተረሳም)
.
.
.
⇨ (በሌሎችም ሀገርኛ ልሳናት የቻላችሁትን ጨምሩበት)



(ከቴዎድሮስ በለጠ ☞ በማዕዶት ፳፻፲፪ ዓ.ም. ተጽፎ በማሻሻያ ለዛሬ በድጋሚ የተለጠፈ )
. #የአዳም_ሐሙሱ
▭▭◎⃝◎⃝◎⃝ ◎⃝◎⃝◎⃝◎▭▭

ባምስት ቀን ተኩል ፡ በተስፋ ለመዳን
በቃል የተሠጠች ፡ የቃል እናት ኪዳን
«ከልጅ ልጅህ» ተብላ ፡ ወርዶ ሊያቆም ርደት
የአዳም ሐሙሱ ፡ ማርያም የኛ ልደት!

✧ እምድኅረ ሐሙስ መዋዕል ወመንፈቀ መዓልት እምሕረከ ወእሰሃለከ በብዝሐ ሳህልየ ወምሕረትየ ወእወርድ ውስተ ቤትከ ወአሐድር ውስተ ከርስከ በእንቲአየ ☞ ከአምስት ቀን እና ከግማሽ ቀን በኋላ እምርሐለሁ ይቅርታም አደርግልሃለሁ በይቅርታዬ ብዛትና በምሕረቴ ብዛት ወደአንተ ቤት እወርዳለሁ ስለአንተም ድኅነት በወገንህ ማሕጸን አድራለሁ
[መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ፫፥፲፱]
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
2024/05/19 00:52:24
Back to Top
HTML Embed Code: