Telegram Web Link
፮) መለካውያን ኦርቶዶክስ:- መለካውያን ኦርቶዶክሶች (የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬን እና ሌሎችም ካሉ) እንደ እኛ እንደ አኃት አብያተ ክርስቲያናት (ኢትዮጵያ፣ አርማንያ፣ ሶርያ፣ ግብፅ፣ ሕንድ፣ ኤርትራ) መንፈስ ቅዱስን ዘሠረፀ እምአብ በማለት አንድ ናቸው። በዚህ አንድ ብንሆንም ክርስቶስን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለታቸው ግን እንለያያለን። መለካውያን ኦርቶዶክሶች ከካቶሊክ የተለዩት በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ከካቶሊክ ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ይህ ደግሞ ስሕተት እንደሆነ ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፫ በሚለው ትምህርታችን ተማምረናል። ካቶሊኮች ግን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በሚለው ክሕደት ላይ መንፈስ ቅዱስን ዘሠረፀ እምአብ ወእምወልድ በማለት ይክዳሉ። አብ ወልድን የወለደው፣ መንፈስ ቅዱስን ያሠረጸው ቅድመ ዓለም ነው። ቅድመ ዓለም ነው ስንል መነሻ አለው ማለታችን አይደለም። ከሰው መታሰብ በላይ ነው ያሰኘው ይህ ነው። ሊቁ በሃይማኖተ አበው "ዘኢየኀልቅ ልደቱ" ያለውም ሁልጊዜም ወልድ ሲባል ይኖራል ለማለት ነው እንጂ ሁልጊዜ ይወለዳል ማለት አይደለም። ዘኢየኀልቅ ልደቱ ሲል ልደት ወልድና ከሚለው ጋር በምሥጢር ይገጥማል።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ቀጣይ በክፍል ፭ ቀሪዎቹን እንመለከታለን ይቆየን።
ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል

"ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)።
አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።
#ግንቦት_11

#ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ

ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።

ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።

ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።

ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።

በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።

ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።

ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።

ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።

የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።

ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።

ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
አንዳንድ ክርስቲያኖች ላይ የማየው ድክመት..

በጭፍን እንዲሁ መምህር የተባለውን ሁሉ መከተል ስህተት ውስጥ እንድንወድቅ ያደርጋል.. የሆነ ርእስ ላይ ጥያቄ ከፈጠረባችሁና መላሹ ሲመልስ “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” ብሎ የሚመልስ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከአባቶች ሰፋ ያለ ማስረጃ እንዲያቀርብ 👉ጠይቁት..

ሰፋ ያለ ማስረጃ ከሁለቱ ማቅረብ ካልቻለ ቢያንስ ለጊዜው የራሱ የሰውዬው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ብላችሁ አትያዙ.. ቅዱስ ትውፊት የሁሉም መመዘኛ ነው..

@Apostolic_Answers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አጭር ግን ቶሎ እጅ የሚያሰበስብ ቃል ነው። ቅዳሴ ላይ በሰማሁት ቁጥር ሁሌ “እንዴት ሆኜ አይቶኝ ይሆን?” እንድል የሚያደርገኝ ጉልበታም ንግግር ነው።

“እግዚአብሔር ያያል!”
🌷 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †🌷

🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷

=>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::

+ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::

+በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:-
እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::

+እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::

+የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::

+እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::

††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷†††

=>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር::

+አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው::

††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: †††

=>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)
2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)
3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ

=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
“እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ዮሐ. 6፥63)
***
የክርስትና አስተምህሮ አመክንዮአዊ ቀመር እና የቃላት ብያኔ ብቻ አይደለም። ጌታችን እንደነገረን ከዚያ የሚያልፍ መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። በመሆኑም አንድ ንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት ቢገኝም 'መንፈሱን' ካልተረዳን እንስታለን። ያ አገላለጽ የተነገረው ምንን ለማጠየቅ ነው? ምን ብለን ብንረዳው ደግሞ ስህተት ይሆናል? ብሎ ትውፊታዊ መረዳትን ይጠይቃል። አንዳንዶቹ አገላለጾች ደግሞ እጅግ ትልቅ ቅጥነተ ህሊና ይጠይቃሉ። ከእነዚህ አንዱ 'ፈጣሪ ወፍጡር' የሚለው ትምህርት ነው።
ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮች እንኳ ክርስቶስን 'በሥጋው ፍጡር' ማለት በትክክለኛ ዓውዱ ከተነገረ ስህተት ባይሆንም ምእመናን እንዳይደናገሩ በነገረ ሃይማኖት ሐተታዎች ውስጥ በብዛት አንጠቀመውም ይላሉ። (Catholic Encyclopedia)
ይህ ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ውስጥም ያለ ነው። እኔ እስከማውቀው በአምልኮ መጽሐፎቻችን ውስጥ አይነገርም። እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኘው በአንዳንድ ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ነው። ይህ የሚያመለክተው አገላለጹ በቅጥነተ ህሊና ከነሙሉ ዓውዱ ካልተረዱት ምእመናን 'በሥጋው ፍጡር ስለሆነ በሥጋው አናመልከውም' ብለው እንዳይሰናከሉ ነው።
'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ሲባል፦
1. የለበሰው ሥጋ ዘላለማዊ ህልውና ያልነበረው የእኛ የተፈጠረ እውነተኛ ሥጋ ነው ለማለት ነው።
2. የሰው ልጆች ሐዲስ ተፈጥሮ (መታደስ) ከእርሱ የተጀመረበት ዳግማይ አዳም፣ በኲረ ፍጥረታት መሆኑን ለመናገር ነው። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ያልነሳውን አላዳነምና።
3. ሌሎችም።
***
ነገር ግን ከነዚህ እሳቤዎች መጠንቀቅ ደግሞ ይገባል፦
1. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው አምልኮ አይገባውም ማለት አይደለም። የክርስቶስን ሥጋ ከመለኮቱ ለይተን በመለኮቱ ብቻ እናምልክ ካልን የማይከፈለውን አንዱን ክርስቶስን እየከፈልነው ነው፤ ስለ መዳናችን ሰው የሆነውን ክርስቶስን ስለእኛ ሰው በመሆኑ ዝቅ እያደረግነው ነው። ስለ ሕዝቡ ሲል ከአባቱ ዙፋን ወርዶ ሕዝቡ የሚለብሱትን መናኛ ልብስ ለብሶ የሚታደገውን የንጉሥ ልጅ ውለታ ባለመረዳት 'በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሥ አናይህም' ብሎ እንደመሳለቅ ነው።
2. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ማኅየዊ (ሕይወትን የሚሰጥ) አይደለም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ እንዳለው ሥጋውን እና ደሙን መቀበል ከንቱ በሆነ!
3. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ለአብ ይገዛል ማለት አይደለም። አብ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስምን ሰጠው የተባለ በሥጋው ነው። ታዲያ ይህ ከፍታ ከመገዛት የማያወጣ ከሆነ ከቅዱሳን የጸጋ ክብር በምን በለጠ? ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለው ከፍጡራን ግብርናት እስካልወጣ ድረስ ምን ቢከብር ለእርሱ የሚገባ ክብር አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተነገሩ የትሕትና ንግግሮች ከማዳን ግብሩ እና አርአያነቱ (economy of salvation) አንጻር የምንረዳቸው ናቸው። ካልሆነ ግን በክርስቶስ ዘንድ ሰው ከመሆኑ የተነሣ ዘላለማዊ ተዋርዶ ገብቷል ያስብላል።
በሥላሴ አካላት ዘንድ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈስ ዘላለማዊ ክብርና ምሥጋና አለ። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ የተነሣ በወልድ ዘንድ የፍጡር አምልኮ ግዴታ አልወደቀበትም። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ይህን አብም አይፈልግም፤ ወልድም አይሰጥም።

Bereket Azmeraw
ስብከታችን እኛን ራሳችንን መለወጥ ሳይችል ሌሎችን እንዲለውጥ መመኘት ሞኝነት ነው። መጽሐፋችን በእኛ ላይ መልካም ለውጥን ካላመጣ ሌላው ገዝቶ እንዲያነበው ማስተዋወቅ ከንቱ ድካም ነው። ስብከታችን፣ መጽሐፋችን መጀመሪያ መለወጥ ያለበት እኛን ራሳችንን ነው።

አንድ መጽሐፍ ወይም ስብከት ከሚከተሉት ነገሮች ቢያንስ በአንዱ ሊጠቅመኝ ይገባል።

ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖረኝ ማድረግ
የክህሎት እድገት እንዲኖረኝ ማድረግ
ሃይማኖታዊ ዕውቀት እንዲኖረኝ ማድረግ
ከክፉ ሥራዎች ማራቅ
የሕይወትን መንገድ ማሳየት
መልካምን እንዳስብ ማድረግ

አለበት። እኛ ስድብን ሳንተው ሌላው ሰድብን እንዲተው መስበክ አስቂኝ ነው። እኛ መኖር ያቃተንን ሕይወት ሌሎች እንዲኖሩት አብዝቶ መናገር ከንቱነት ነው። ሌሎች የእኛን ቃል ሰምተው ሊለወጡበት ይችላሉ። እኛ ግን እንደ ገንዳ ሆነን እንቀራለን። የክርስትና ሕይወት በልብ የሚያስቡት፥ በቃል የሚናገሩት፣ በተግባር የሚያሳዩት ሕይወት ነው።

በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማደግ እናንብብ፣ እንማር፣ እንጠይቅ።

© በትረ ማርያም አበባው
ይህ ሰው ድሀ፣ ለማኝ ወይም ቤት አልባ አይደለም ይልቅስ በአለም ስነ-ጽሁፍ ገዝፎ የሚታየው ሊዮ ቶልስቶይ ነው። ቶልስቶይ በሩሲያ ውስጥ ሰፊ መሬት እና ትልቅ ሀብት የነበረው ቢሆንም፤ ሀብቱን ሁሉ ለድሆች፣ ለምስኪኖች፣ ለችግረኞች እና ለቤት ፈላጊዎች በመስጠት የራሱን ህይወት ባልተጋነነ መለኩ የኖረ ሰው ነው።

ታዋቂ ከምንላቸው አባባሎችሁ መኃል፦

"ስለ ሀይማኖት ብዙ አትንገረኝ፣ ነገር ግን በድርጊትህ ውስጥ ሃይማኖትህን እንዳይህ ፍቀድልኝ።"

“ህመም ከተሰማህ በህይወት አለህ፤ የሌሎችን ህመም ከተሰማህ ግን በውኑ አንተ ሰው ነህ”
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"

"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"

"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"

ዲ/ን ያረጋል
በምሥጋና ዐረገ፤ ቤተ ክርስቲያኑንም ከፍ ከፍ አደረጋት።
***
እየታያቸው ከፍ ከፍ አለ፤ የባሕርይ ክብሩን የምታመለክት ደመና ተቀበለችው። በእርሱ ዕርገትም አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ሆና ከፍ ያለች እና በሰማያዊ ሥፍራ የተቀመጠች ሆነች።
የዚህ ዓለም ኃያላን የሚያናንቋት ሐረገ ወይን የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯ በምድር ቢሆን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ናቸው። ይህ ምን ይደንቅ!
አንዳንድ አገልጋዮቿ በሥርዓተ አምልኮዋ በዘፈቀደ እና በቸልተኝነት የምንመላለስባት ቤተ ክርስቲያን በመንቀጥቀጥ የሚያገለግሉ ሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት ያላት ናት። በላይ በበጉ ዙፋን የምትቀድስ ናት! ለዚህ ጸጋዋ አንክሮ ይገባል!
ይህ ሁሉ የሆነው ግን ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባቱ ያቀርበን ዘንድ በእኛ ሥጋ ከፍ ከፍ ብሎ በአብ ቀኝ በመቀመጡ የተሰጠን ጸጋ ነው።
***
"እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።"
***
(ሉቃ. 24፥50-53)
ከንቱ ውዳሴን አልወድም ያለ ሰው ሲሰድቡት ከተከፋ በከንቱ ውዳሴ ላይ ውሸታምነትን ደርቦ የያዘ መሆኑን እንረዳለን። ሲሰድቡት ለምን ተሰደብኩ ብሎ ለክብሩ የሚጨነቅ፣ አንድ ሰው ክፉ ቃል ተናገረኝ ብሎ የሚቦልክ ወይም ከጓደኝነት የሚያወጣ ሰው ሐዋርያዊ አይደለም። ሐዋርያት ጌታን ሲከተሉ መጀመሪያ እከብር ባይ ልቡናን ትተው ነው። እውነትን በመናገራቸው የደረሰባቸውን ነቀፋ፣ ስድብ፣ መደብደብ፣ በሰይፍ መቀላት በደስታ ተቀብለውታል እንጂ አላጉረመረሙም። ሐዋርያዊ የሆነ ሰው መሪው ክርስቲያናዊ ዓላማው ነው እንጂ የሰዎች ሙገሳና ጩኸት አይደለም። ከንቱ ውዳሴን አምርረን መጥላት አለብን። መመስገን ያለበት በሁሉ ፍጹም የሆነ እግዚአብሔር ነው። አንድም ተጋድሏቸውን ጨርሰው በአፀደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ናቸው። ክርስቲያን እንደ ጌታው ከምድር ከፍ ብሎ መውጣት (ማረግ) ይገባዋል። ሐዋርያት የሰውን ሙገሳ ንቀው የኖሩት ከሰው ተለይተው እንደ ጌታቸው ከፍ ከፍ ብለው በመውጣታቸው ነው።

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ
በሰማይ የሀሉ ልብነ

© በትረማርያም አበባው
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ ሕይወት ነኝ" ብሏል

ክርስቶስ 'እኔ ሕይወት ነኝ' ሲል እውነተኛ ሕይወት በእርሱ ተጀምሯል፣ በእርሱም ትቀጥላለች፣ እናም በእርሱ ያበቃል ማለት ነው። በክርስቶስ አምኖ በእርሱ የሚኖር ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ያገኛል፣ እርሱ የማይጠፋ የሕይወት ምንጭ ነውና…

ክርስቶስ ሕይወት ነው ምክንያቱም በኃይሉ ከሞት በመነሣቱ እና በትንሣኤው የዘላለም ሕይወትን መንገድ ስለጠራልን። ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነት ከሕይወት ጋር ያለን አንድነት ነው፣ ዐዲስ እና ክቡር ሕይወት እንድንኖር ብርታት ይሰጠናልና…

በክርስቶስ ያለው ሕይወት እውነተኛ ሰላምና ደስታ የተሞላ ሕይወት ነው። በክርስቶስ ስንሆን፣ ሕይወትን በፍፁም ትርጉሙ፣ ከሞት በላይ የሆነና ጊዜን የሚጋፋ ሕይወት እናገኛለን።

አቡነ ሺኖዳ
🌹🌸💐 🇳 🇮 🇾 🇦  𝗗𝗲𝗰𝗼𝗿 💐🌸🌹



የ 𝗗𝗲𝗰𝗼𝗿 ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋሉ


🎈 ለ ሰርግ                           🎈 ለ ልደት
🎈 ለ ቤት ምርቃት                 🎈 ለ ልጆች ልደት
🎈 ለ ተማሪዎች ምረቃት         🎈 ለ ሆቴል ምረቃ
🎈 ለ 𝗙𝗮𝘀𝗵𝗶𝗼𝗻 𝗦𝗵𝗼𝘄        🎈 ለ 𝗛𝗼𝗻𝗲𝘆𝗺𝗼𝗼𝗻
🎈 ለ ስብሰባ አዳራሾች          🎈 ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች

🎈 በቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች | ኘሮግራሞች|

🎯  ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !


📞 Phone Number . 

+251961064953.  +251703504953

🙍‍♀ Contact .  @Niyafkr 


        
👇 ይህን ተጭነው የ Telegram ቻናሎን  ማግኘት ይችላሉ !👇


█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸



Niya Decor , Niya Decor , Niya Decor , Niya Decor 


🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹

👇 ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከፈረጉ ከስር ያለውን ይጫኑ 👇
2024/06/16 01:05:43
Back to Top
HTML Embed Code: