Telegram Web Link
የዐቢይ ጾም (ስድስተኛ ሰንበት ገብርሔር)

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፡፡  ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡

ምስባክ     መዝ. 39÷8 

"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ 

ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡

 ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"


ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥

 ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።

 በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።


ወንጌል

ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤ ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና፡- አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ አሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡

 ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
10👍7👏2🕊2🔥1
🔴 ዳግመኛ በሥጋው ይመጣል || የዐቢይ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ዳግመኛ በሥጋው ይመጣል
       የዐቢይ ጾም ጉዞ
           ክፍል 4
Size:-124.5MB
Length:-2:14:27

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
5👍1
#ገብር_ኄር
የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24 እና 25 የምጽአት ምንባባት ናቸው
ሁለቱም ምእራፎች በደብረ ዘይት የተሰጡ የጌታ ትምህርቶች ናቸው
የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 25
• ስለ ዐሥሩ ደናግል(አምስቱ ልባሞችና አምስቱ ሰነፎች)
• ስለ ገብር ኄር(ቸር አገልጋይ) ፣ ገብር ምእመን(ታማኝ አገልጋይ) እና ገብር ሐካይ (ሰነፍ አገልጋይ)
• ስለ መጨረሻው የሚናገር ምእራፍ ነው

ገብር ኄር መጠሪያ ስም (ስመ ተጸውዖ ) አይደለም
የብዙ አግብርት ኄራን መገለጫ ቅጽል ነው
ገብር ኄር የሚለው አገላለጽ
• ቸር አገልጋይ
• ታማኝ አሽከር
• ጥበበኛ/ብልህ አገልጋይ የሚለውን ሁሉ የሚወክል ነው
መነሻ ምሳሌው አንድ ንጉሥ አገልጋዮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለአንዱ አንድ መክሊት ሰጥቶ ነግዱና አትርፎ ብሎ ወደ ሩቅ ሀገር ሄዶ ሲመለስ እንደተቆጣጠራቸው የሚናገር ነው ማቴ 25፥14
• ባለ አምስቱ አምስት አትርፎ አሥር አድርጎ
• ባለ ሁለቱ ሁለት አትርፎ አራት አድርጎ ሰጥተዋል
• ባለ አንድ መክሊት ግን ቀብሮ አቆይቶ ያንኑ አምጥቶ ከሃሜትና ከማንጎራጎር ጋር አስረክቧል
ሁለቱ ወደ ጌታ ደስታ ግቡ ተብለው ገብተዋል ባለ አንዱ ግን ወደ ጨለማና ስቃይ ስፍራ ተልኳል
ምሥጢር 👇
ገብር ኄር ክርስቶስ ነው
1. ቸር ነውና ቸርነቱንም በባሪያ መልክ ተገልጦ ተገርፎ ተገፎ አሳይቶናል
2. አምስቱን ግብራት በአምስቱ መክሊት አንጻር አርብቶ አሳይቶናልና
አምስቱ ግብራት👇
• ተአምኖ ኀጣውእ
• ጥምቀት
• ተባህትዎ
• ምንኵስና
• ሰማዕትነት ናቸው

ክርስቲያናዊ ገራኅተ መስቀል (የመስቀል እርሻ=መሰማሪያ) ከነዚህ የወጣ አይደለም
ጌታ ያላደረገው እኛ የምናደርገው አዲስ በጎ ነገር የለም
..ሁሉም እርሱ አብነት የሆነበት ነው!!!

መክሊት ጸጋ ወይም ስጦታ በሚለው የሚተካ ምሥጢራዊ ቃል ነው
መክሊት👇
• ሃይማኖት ፣ ፍሥሓ፣ትዕግሥት፣ ምሕረት፣ተስፋ
• ሙሉ አካል
• አምስቱ ሕዋሳት
• አእምሮ ጠባይዕ
• አእምሮ መንፈሳዊ
• ክርስቲያናዊ ምግባር
• ሥልጣነ ክህነት
• መንፈሳዊ ዕውቀት /ትምህርት ተብሎ ይተረጎማል
ሁሉንም ለምድራችን ለሃይማኖታችን ለበጎ ነገር መጠቀም ገብር ኄር አሰኝቶ ወደ ዘለዓለማዊ ደስታ ያስገባል!
እነዚህን አካላት በክፋትና በተንኮል መቅበር ደግሞ "ገብር ሐካይ" ክፉ ባሪያ፤ ሰነፍ አገልጋይ፣ ጨካኝ ሰው አሰኝቶ ያስፈርዳል ወደ ሲኦል ወደ ገሃነመ እሳት ወደ እንጦርጦስ ያስወርዳል።

በጎውን እንድናስብ ከአግብርት ኄራን እንድንቆጠር እግዚአብሔር ይርዳን !!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል

👉 @ortodoxtewahedo
👍24👏4🙏3🥰2
“ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።” — ማቴዎስ 25፥29


እንዲሁ ... ባለችው ጥቂት ነገር ይህ አነሰኝ ሳይል ለሚያመሰግን ይበልጡኑ የሚሻው ነገር ይበዛለታል፤ ሁሌ ለሚያማርርና ለእርሱ የማይሆንን ነገር እግዚአብሔር ለምን አልሰጠኝም ብሎ ሁሌ ለሚናገር ሰው ግን ያለችውም ጥቂት ነገር ትወሰድበታለች፤

በመክሊታችን እንድናተርፍ ይርዳን፤
መልካም ሰንበት😊

@ortodoxtewahedo
👏209👍7
250 ሺህ አዳዲስ አማንያንን በማስተማር ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጨመር ሥራ መሰራት መቻሉ ተገለጸ።

መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

የማኅበረ ቅዱሳን የ6 ወር ሥራ አመራር ጉባኤ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱም ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ማኅበሩ በርካታ ሥራዎችን መስራቱ ተገልጿል።

መምህር ዋሲሁን በላይ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን
በሪፖርታቸውም በ10 ቋንቋዎች ስብከተ ወንጌል ተደራሽ የማድረግ፣በደረጃ አንድ 7500 መምህራን እና በደረጃ ሁለት 600 መምህራንን አሠልጥኖ የማሰማራት፣250ሺህ አዳዲስ አማንያንን በማስተማር ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጨመር፣ሙያዊና ማኅበራዊ ፕሮጀክቶችን የመተግበርና ሌሎች ተግባራት መከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በቀጣይም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ወይይት የሚካሄድ ይሆናል።

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

@ortodoxtewahedo
👍275👏4
“ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ፤” — ሚክያስ 7፥8

....

የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ዙሪያችንን ከቦ መጥፎ ሀሳብን መሸነፍን በመንፈስ መዛልን ለአዕምሯችን የሚያሳስበንን እና መውደቅን ብቻ እንድናስብ የሚያደርገን ጠላታችንን ዲያቢሎስን "ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁ" በሉት መውደቅን ብቻ አታስቡ ... ቅዱስ ጊዮርጊስን በ፯ ዓመታት መከራ ያጸናውና ወደርሱ ራሱን ያቀረበን የማይጥል ቸር አምላክ ነው ያለን፤

ብሩኅ ማክሰኞ ለሁላችን😊

@ortodoxtewahedo
🙏319👍8🔥1
🔴ሂዶ አተረፈበት|| የማትረፍ ጉዞ ||...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ሄዶ አተረፈበት /የማትረፍ ጉዞ
       የዐቢይ ጾም ጉዞ
           ክፍል 5
Size:-113.8MB
Length:-2:02:54

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
👍12
በጌታችን የዕለተ አርብ የመከራ ጊዜ ላይ የነበሩ በወንጌል በልዩነት የተጠቀሱ ሰዎችን ማንነት ለዩ...

@ortodoxtewahedo
👍1
ማርቆስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵¹ ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፥ ⁵² ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ። ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ይህ በነጠላ የተሸፈነ ጎበዝ ማን ነው?
Anonymous Quiz
36%
ስምዖን ቀሬናዊ
21%
ቅ/ ማርቆስ ወንጌላዊ
12%
መጻጉዕ
14%
የአስቆሮቱ ይሁዳ
16%
ቅዱስ ጴጥሮስ
👍181
“ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ ቆሞ ነበር። እንግዲህ በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀው ሌላው ደቀ መዝሙር ወጣ ለበረኛይቱም ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው።”
— ዮሐንስ 18፥16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ይህ በሊቀ ካህናቱ ግቢ በረኛ (ጥበቃ) የታወቀው የተባለው ማን ነው?
Anonymous Quiz
21%
ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
23%
ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
39%
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ
17%
ቅዱስ ሉቃስ
🙏7👍2
ዮሐንስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ስለምን ትጠይቀኛለህ? ለእነርሱ የተናገርሁትን የሰሙትን ጠይቅ፤ እነሆ፥ እነዚህ እኔ የነገርሁትን ያውቃሉ አለው። ²² ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን? ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው። ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ይህ ጌታን በጥፊ የመታው ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
48%
መጻጉዕ
19%
ይሁዳ
10%
ስምዖን
23%
ሳውል
👍2
††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መድኃኔ ዓለም †††

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

*ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

*በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

*ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

*ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

*በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)

††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን::

††† ከቅዱሳኑ በዚሕች ዕለት:-

††† ከ80 ዓመታት በላይ በገዳም የኖረ: የገዳማውያን ሞገሳቸው: የመነኮሳትም ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ አርፏል::

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ንግሥናን ከሊቅነት: ጽድቅን ከሰማዕትነት ጋር የደረበው ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውዴዎስ አንገቱን ተከልሏል:: ቅዱስ ገላውዴዎስ የጻድቁ ዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ ነው::

††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

††† መጋቢት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ (ፍቁረ እግዚእ)
2.ቅዱሳት አንስት (ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ)
3.ቅዱሳን ባልንጀሮች (በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ)
4.ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
5.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት አለቃ)
6.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (የኢትዮዽያ ንጉሥ)
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
3.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
👍15🥰4
ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
10👍2
" ትጉሃን በሰማያት የሚያመሰግኑት እርሱ የእሾህ ዘውድ ደፋ ከወንበዴዎች ጋር በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቀለ ልዑላኑ እየፈሩ በፊታቸው እራሳቸውን የሚያዋርዱለት እርሱ አሚሰቅሉት ፊት ለህማም ራሱን አዋረደ፡፡ ሰማይና ምድር የተሸከመውን በዕፀ መስቀል ላይ ደካማ እንጨት ተሸከመው ሰማይ እና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ጠባብ መቃብር ወሰነው፡፡ "

#አኮቴተ ቁርባን ዘቅዱስ ቄርሎስ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
20👍2🙏1
ኦ አርምሞ ዘመጠነ ዝ አርምሞ ?
ኦ ትዕግስት ዘመጠነ ዝ ትዕግስት?
ኦ ሂሩት ዘመጠነ ዝ ሂሩት ?
ኦ ፍቅር ዘመጠነ ፍቅረ ሠብ ?
( ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው ? ይህን ያህል ዝመታ እንደምን ያለ ዝመታ ነው ? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው ?

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
14👍2🥰2👏1
2025/07/12 16:00:38
Back to Top
HTML Embed Code: