Telegram Web Link
🛑 NEW || ልደታ ለማርያም || እግ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ወደ መቅደሱ ይመጣል
             
Size:-35.7MB
Length:-38:32

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍9
#ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

“ናሁ ውስተ አድባር እገሪሆሙ ለሰብአ ዜና ወይዜንዉ ሰላመ እነሆ የምሥራችን የሚሰብክ ሰላምን የሚያወራ (ሚጠትን የሚናገር) ሰው እግሮች በተራሮች ላይ ናቸው"
(ትን.ናሆም 1፣15 ትርጓሜ ቅዱስ ዮሐንስ አወፈርቅ)
በውጭ አህጉረ ስብከት ተመድበው ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በመፈጸም ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ 1 ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ወደ ሀገር ቤት በመግባት ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን እንዲሳተፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ጥያቄ ማቅረቧ ይታወቃል፡፡

መንግሥትም ሀገራዊ ተቋማትን ለማጠናከር ያለው ቁርጠኝነት የጸና መሆኑን በገለጸበት መግለጫ እንደተመለከትነው የሀገራችንን ሰላም ለማጽናት፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን የታሪክ ገጽታ ለመጠበቅ ተቀራርቦ መነጋገር የተሻለ መፍትሔ መሆኑን ተረድቶ ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር ገብተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን እንዲሳተፉ መፍቀዱን ተረድተናል፡፡

በመሆኑም መንግሥት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀብሎ ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር እንዲገቡ በመፍቀዱና ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ወደፊትም እግዚአብሔር በሰጠን ምድር፣ አባቶቻችን ባቆዩልን ሀገር አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ለሀገራችንና ለሕዝባችን በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታችንን በማጠናከር በጋራ : ለመሥራት ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo
👍10
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፻፴፪ ኛው መደበኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”

#ሐዋርያት ፳፥፳፰

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
🥰14👍61
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📚👉መናፍቃን ከሚያነሷቸው 3 ጥያቄዎች መካከል⁉️
1)የጌታችን እኔ የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለበት።
2)የጌታችን እናት አልተነሳችም
3)ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው።
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት መልስ የሚያገኙበት ቻናል ነው። አሁኑኑ ይቀላቀሉ በማርያም ❗️
        👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █          
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


         👇👇👇
             🔔
     🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

⛪️ኦርቶዶክሳዊ ስብከት⛪️
🤗ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🤗
❤️ትምህርቱን በይቱብ❤️
ከታች ባለው ሊንክ ሰብስክራቭ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
👍32🙏1
ሥራ አስኪያጅ? ግን ወዴት ሊያስሔዱት ነው?
👍2
እኒህ ሦስቱ:-

፩. የተሸከሙት ሸክም ያላጎበጣቸው

፪. የመከራ ቀን ጥብዐታቸው

፫. መከራውን ያለፉበት ጥበባቸው

፬. ለሲኖዶሳዊ ልዕልና ተጋድሏቸው

እናት ቤተ ክርስቲያንን በጃት!

"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
 
#ሐዋርያት ፳፥፳፰

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍128🙏5
አባ ሳዊሮስን በአጭሩ - ግቡና መርምሩ

+ + + + +

ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ቤተክርስቲያን መከራ በምትቀበልባቸው ወቅቶች፣ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ስታልፍ... አንድ አይነት አሻራ ወይም አንድ አካል ከሁነቶቹ ጋር ተያይዞ ሲነሳ መስማት የተለመደ ሆኗል። ከሚነድ እሳት ጀርባ ከሚጨስ ጭስ ጀርባ ክብሪት እጃቸው ላይ የሚገኝ ሰው። ይህ አጋጣሚ ብቻ ለመሆኑ ግራ ያጋባኛል። እስኪ ጥቂት አጋጣሚዎችን እናንሳ፦

👉 ዘጠናዎቹ መጨረሻ የሚሊንየሙ መጀመሪያ ቤተክርስቲያንን ሊውጥ የመጣው ተሐድሶ ልባችንን በእሳት ሲለበልበው በነበረበት ወሳኝ ወቅት... እሳቸው ከሌሎቹ አባቶች በልዩነት የተሐድሶዎችን የቴሌቪዥን ፕሮግራም (የታኦሎጎስ)፣ የአደራሽ (የቦሌ ፋና ፓርክ) ገባኤያቸውን ሲባርኩ ነበር!

👉 በየ ሀገረ ስብከቱ የቤተክርስቲያንን ቀኖና የጣሱ የተሐድሶ አራማጆች ሲታገዱና ሲወገዱ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ግን እነዚሁ አራማጆች ያለ ማንም ከልካይ በአውደ ምህረት ላይ ሲፈነጩ... እሳቸው በግልጽ ማንም እንዳይነካቸው ከለላ ይሰጡ ነበር!

👉 ቤተክርስቲያን አንድነቷን ተነጥቃ በሕገወጥ መንገድ "የኦሮሚያ ቤተክህነት" የሚባል አካል ሲመሰረት... ከነ ቀሲስ በላይ ጀርባ እርሳቸው ነበሩ!

👉 የቤተክርስቲያንን መሠረት ያናጋው፣ ልብንም ያቆሰለው መፈንቅለ ሲኖዶስና መፈንቅለ ፓትርያሪክ ሙከራ ሲደረግ፣ ያ የጫካ ውስጥ የሕገወጥ ሹመት ሲካሄድ... አቡነ ሳዊሮስ ከዋነኛ ተዋናዮቹ መካከል ዋነኛው ሰው ነበሩ!

👉 አንዳንድ አባቶች መንበረ ሰላማ በሚል ሽፋን ከእናት ቤተክርስቲያን ህጋዊ ሲኖዶስ ሲለዩና ሲገነጠሉ... እሳቸው መቀሌ ተጉዘው "በርቱ!" የሚል የማበረታቻ መልእክት ያስተላለፉ ሰው ነበሩ!

👉 በተደጋጋሚ በገንዘብ የኑፋቄ እንቅስቃሴዎችን በቤተክርስቲያን ላይ ከሚያደርገው ጸጋዬ ሮቶ (ፍኖተ ጽድቅ) ጀርባ... አለምገና ሰበታ ላይ ባለው ኢንቨስትመንት ተጠቅሞ ቤተክርስቲያንን ሲያደማ ከለላው እሳቸው ነበሩ!

👉 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቤተክርስቲያንን ህልውና ለመጋፋት በሚመስል መልኩ በክልል ደረጃ ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጪ የሐይማኖት ጉባኤ አደረጃጀት ሲፈጥር... እሳቸው ከጀርባ ነበሩ! ከፍ ብሎም የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖቶ ሰብሳቢ ሆነዋል!

👉 እነሆ ብልጽግና ጥቅሙን የሚያስከብርለት የቤተክህነት ተሿሚ ሲሻ እሳቸው እጩ ስርአስኪያጅ ሆነው ብቅ ብለዋል።

ምንግዜም ቤተክርስቲያን ላይ ፈተና ሲመጣ እሳቸው ከጀርባ አሉ።
....

በብጹእ አባታችን በጎ በረከቶት ይደርብን አባታችን ይሄ ሁሉ አጋጣሚ ይሆን? እላለሁ፤
እርሶ ከወ/ር እጅጋየሁ ጀርባ ነበሩ፣ የበጋሻውም ከለላ ነበሩ፣ ቤተክርስቲያን ከሚፈትኑ ንኡስ ብሔርተኞችም አጋር ነበሩ፣ ከቀሲስ በላይና ከኃይለ ሚካኤል ጀርባ ሆነው የኦሮሚያ ቤ/ክህነት ምስረታ ላይ ቡራኬ ሰጪ ነበሩ፣ ቀጥሎም የቤተክርስቲያንን ህልውና ተጋፍተው በወሊሶ ጫካ መነኮሳትን ሊያጰጵሱ ሲሞክሩ ነበር፣ ቀጥሎም የፕትርክና ልብስ አሰፍተው መፈንቅለ ፓትርያርክ ሲያደርጉ ነበረ፣ ቀጥሎም የመንበረ ሰላማ ተገንጣዮቹን አይዟቹህ ሊሉ በአካል ሄደው ነበረ፣ ብልጽግና ቤተክርስቲያን ባሳነሰበት መድረክ ሁሉ እርሶ አሉ፣ አሁን ከስርአተ ቤተክርስቲያን ባፈነገጠ ሁኔታ በ5ኪሎ የ4ኪሎ ፖሊት ቢሮ ለመሆን የስርአስኪያጅነት ቅስቀሳ እያስደረጉ ነው.... አባታችን ለቤተክርስቲያን እየጠቀምኳት ነው ብለው ያምናሉ?
...
Maryamawit Henok Lemessa

+ + + + +
ይኽም ኾኖ ሲኖዶስ የጸሐፊነት ዕድል ሰጥቷቸው ነበረ። ያኔ ያጠፉት ብዛት ቀላል አልነበረም። ከሲኖዶሱ አባላት አንድም ጊዜ ወይ በጸሐፊነት ወይ በሥራ አስኪያጅነት ያላገለገሉ ሞልተዋል። ወደዚያ ማማተሩ ይሻላል።
👍133🔥1
አይደረግም ‼️

የቤተ ክርስቲያን የሴራ ፖለቲካ አስፈፃሚ እንድትሆን መከራዋ እንዲበዛ ካልተፈለገ በስተቀር አባ ሳዊሮስን በየትኛው መልካም ስራው ይመረጣል ኸረ እረፉ ነገ የምትቆጩበትን ስራ ዛሬ አትስሩ እባካችሁ አባቶች የምእመናን እንባ አይገዳችሁም ወይ ?

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👏12👍4💯21
🙏ከሹመቱ ምርጫ በፊት የህንፃው ምረቃ ጥድፊያ

👉በቀድሞው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ በአሁኑ በሸገር ሀገረስብከት ስር የሚገኘው የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ የነበረ ህንፃ ግንቦት 10 , 2017 ዓ.ም እንደሚመረቅ የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል ፦

👉በዚህ ምርቃት ላይ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ለጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሹመት ድጋፍ ለማግኘት ሆን ብለው ይህንን ቀን የመረጡ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን በመረጃውን በማድረስ ፣

👉በዚህ ምርቃት ላይ በርካታ ጳጳሳት እንደተጠሩ ፣ብሎም በዚህ ምርቃት ላይ ለሚገኙ አባቶች ስጦታ የብር መስቀል እጅ መነሻ እና በቂ መስተንግዶም እንደተዘጋጀ እንዲሁም የዚህ ዝግጅት ዋና እስፖንሰር ፣ የፍኖተ ጽድቅ ባለቤት አቶ ጸጋዬ መሆናቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ለኢትዮ ቤተሰብ አድርሰውናል ፣

👉እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ከዚህ ቀደምም በአባ ሳዊሮስ ጋባዥነት የተከናወነ ሲሆን ፣ ይህ መርሀግብር ጳጳሱ እና ግብራበሮቻቸው ላሰቡት የቡድን የምርጫ ቅስቀሳ ይረዳቸው ይሆን? ዝርዝሩን በመደበኛ መርሀግብራችን ይጠብቁን ፦

ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም ድምፅ

ምንጭ 👉 ኢትዮ ቤተሰብ

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍5
ተመሰጌን
የበፊቱ ፓስተር የአሁኑ ባለማዕተብ ተሙ!
ለ34 ዓመት በፕሮቴስታንት ውስጥ ቆይቷል

ለአንድ አመት በጥሞና ቆይቷል። ለ interview ሲጠየቅ እራሱ መጀመሪያ ክርስትናን ልኑረው ነው መልሱ።

ተሙ ሁለት ቸርች ከነምዕመኑ ያስጠመቀ ጀግና ነው።
ክርስቶስ ስለበራልኝ ነው ወደ ኦርቶዶክስ የመጣሁት በማለት መስክሯል። እንዲህ በማለት.......

"ፕሮቴስታንት ጋር አብዛኛው ጊዜ ቸርች የግለሰብ ነው ነገር ግን እውነተኛ ቸርች የግለሰብ ሳይሆን የክርስቶስ ነው ።
እሮብ እኮ ፓስተር እከሌ ይመጣል ተብሎ ይኬዳል ስለዚህ ህዝቡ የሚሄደው ነቢይ ደመቀን ወይም ኢዩ ጩፋን ለመቀበል እንጂ ኢየሱስን ለመቀበል አይደለም።

አሁንም መምጣት የሚፈልጉ አሉ ነገር ግን እንደሚታወቁ ደሞዝ ይከፈላቸዋልና ስንወጣ ምን እንሆናለን ነው የሚይአሳስባቸው።

በዚህ አጋጣሚ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጀት መድባ ትልቅ ሥራ ብትሰራ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም ከመጡ ቸርቻቸውን ዘግተው ነው የሚመጡት ሌላ ስራ የላቸውም።
የፕሮቴስታንት ቸርች ጭስ አልባ ኢንዱስትሪ ነው።

ብዙኦች ገና ይመጣሉ ትዝታው እራሱ ይመጣል አይታችሁት እንደሆነ የእሱ ትችት የክርስቶስ ትምህረት ላይ ሳይሆን በግለሰብ ነው። ኦርቶዶክስ ደግሞ በግለሰብ አትለካም እኛ ሰዎች ደካማ ነን አንድ ጳጳስ ፣ አንድ ቄስ ሳተ አንድ ዲያቆን ተሳሳተ ማለት ኦርቶዶክስ ተሳሳተች ማለት አይደለም።

በዚህ አጋጣሚ የኦርቶዶክስ ወጣቶች ጀግና ናቸው፣ ዘመዴ፣ ወገኔ የምላቸው የበፊት ጓደኞቼ ሁሉ የእግዚአብሔር ሰላምታ እራሱ ሲነፍጉኝ ኦርቶዶክሳዊያን ግን በፍቅር ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ህብረት እንድጨመር ምክንያት ሆኖዉኛል"

በማለት ገልጿል። በርታ! 💪

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍82
ዜኖኩ ጽድቀከ
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ
ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ(፪)
በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ
አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)

ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ(፪)
ቃላትህን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጥኩ
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስተማርኩአቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
👍1
መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡

ቤተክርስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚአብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡

ሕያው እግዚአብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና
እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር
ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡

ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የመላእክት የምስጋናውን እንጀራ
ያበላን የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ እንቁ ነው።

በረከቱ ይደርብን!

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
👍2
2025/07/13 20:25:34
Back to Top
HTML Embed Code: