Telegram Web Link
ሃቢብ ጊዮርጊስ ግን ቤተ ክርስቲያንን አልከሰሰም፤ ሸክሟን ተሸከመ እንጂ።

፩. የዘመኑ ታሪካዊ ቀውስና የቤተ ክርስቲያን ፈተና

በዐሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃና በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ፣ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ እጅግ ውስብስብ ከሆኑት ፈተናዎች እያስተናገደች ነበር። ቀውሱ የውጭ ጫና ብቻ ሳይሆን፣ ከውስጥ የመነጨና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና የሚፈታተን ነበር። ይህ ድክመት በአስተዳደር መላሸቅ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በሙስናና በአንዳንድ አገልጋዮች የሥነ ምግባር ውድቀት ተገልጧል። ከዚህም በላይ፣ የትምህርተ ሃይማኖት ዕውቀት በእጅጉ ተዳክሞ፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት ጥራትና ስፋት በእጅጉ ቀንሶ ነበር።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የዚያን ዘመን አሳሳቢ ገጽታ ሲመሰክሩ እንዲህ በማለት ሁኔታውን ያጠቃልሉታል፡-

“በሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ፣ ስብከቶች ደረቅና ሕይወት አልባ ነበሩ፤ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ከሞላ ጎደል አልነበሩም፤ ድንቁርና በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ፣ እንዲያውም በቀሳውስቱ መካከል እንኳ ሰፍኖ ነበር።”

ይህ ምስክርነት እንደሚያሳየው፣ ችግሩ የገጸ-ድካም ጉዳይ አልነበረም። ይልቁንም፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልዕኮና የአደረጃጀት መሠረት ያናጋ፣ ብዙዎችን ተስፋ ሊያስቆርጥና ለዓመፅ ወይም ለመለያየት ሊዳርግ የሚችል ጥልቅ መንፈሳዊና መዋቅራዊ ቀውስ ነበር። እንዲህ ባለ ከባድ ወቅት፣ የአንድ አማኝ ቤተ ክርስቲያናዊ ንቃተ ህሊና (ecclesiological consciousness) እና ታማኝነት በእጅጉ ይፈተናል።

፪. የዲያቆን ሃቢብ ጊዮርጊስ መነሣትና የመስዋዕትነት መንገድ
በዚህ መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ነበር ሃቢብ ጊዮርጊስ የተባለው የብርሃን ሰው የተነሳው። እርሱ በቤተ ክርስቲያን ያደገና ዲያቆን እንደመሆኑ፣ የችግሮቹን ስፋትና ጥልቀት ከውስጥ ሆኖ ተመልክቷል። የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ድክመት፣ የአገልጋዮቿን የዕውቀት ማነስና የሕዝቡን መንፈሳዊ ጥማት ተገንዝቧል። ነገር ግን፣ እንደ ብዙዎቹ፣ ጣቱን ለመቀሰር፣ ለማሳጣትና ለማጣጣል፣ የውግዘት ድምፅን ለማሰማት ወይንም በራሱ አካሄድ የቤተክርስቲያኒቷን አካሄድ ልከልስ ማለትን አልመረጠም። ይልቁንም፣ በታማኝ አገልግሎትና ሸክምን በመሸከም ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ሰጠ። መንገዱ የክስ ሳይሆን የመስዋዕትነት ነበር፤ ይህም በገላትያ 6፡2 ላይ ያለውን “የአንዱን ሸክም አንዱ ይሸከም፣ እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” የሚለውን ሐዋርያዊ ትዕዛዝ ሕያው ምስክርነት ነው።

ገና ከወጣትነቱ ጀምሮ ለትምህርት በነበረው ጥልቅ ፍቅር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀጣይ ትውልድ የማነጽ ኃላፊነት በራሱ ላይ ጫነ። የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ንቅናቄ በመላ ሀገሪቱ በማደራጀት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትና ወጣቶች የኦርቶዶክሳዊት እምነታቸውን እንዲያውቁና እንዲኖሩባት መሠረት ጣለ። በካይሮ ሥነ-መለኮታዊ ኮሌጅ ውስጥ በአካዳሚክ ዲንነትና በመምህርነት ሲያገለግል፣ ዕውቀትና መንፈሳዊነት የተዋሐደላቸውን አገልጋዮች አፈራ። ድርጊቱ ሁሉ ይመነጭ የነበረው፣ ቤተ ክርስቲያንን በአስተዳደራዊ ድክመቶቿ ውስጥ እያየ እንኳ፣ የማይነቀንቅ የክርስቶስ አካልና የድኅነት ታቦት መሆኗን ካመነበት ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ እምነት ነበር።

ለዚህም ነው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የአንድን ሰው ታማኝ አገልግሎት ፍሬያማነት ሲመሰክሩ፣ እንዲህ ያሉት፡-

“የሰንበት ትምህርት ቤት ንቅናቄ ከሃቢብ ጊዮርጊስ በቀር ሌላ ፍሬ ባያፈራ ኖሮ እንኳ፣ እርሱ ብቻ በቂ ነበር።”

፫. የመዋቅር ድክመትን ከሃይማኖት ስህተት መለየት
የሃቢብ ጊዮርጊስ ጥበብና ሥነ-መለኮታዊ ልሕቀት ከሁሉ በላይ የሚገለጠው፣ በዘመኑ የነበረውን የመዋቅር ድክመት ከቤተ ክርስቲያን ንጽሕተ ሃይማኖት ጋር ባለማደባለቁ ነው። ቤተ ክርስቲያን በትምህርተ መለኮቷ ኑፋቄን ታስተምራለች ብሎ አንድም ቀን አልከሰሰም። ሥርዓቷን አላጣጣለም፤ ቀኖናዎቿንና ይትባሕሎቿን "ካልከለስኩ" አላለም። ችግሩ ያለው በሐዋርያት በኩል በተሰጠችው የቀናች እምነት ላይ ሳይሆን፣ ያችን እምነት በሚያገለግሉና በሚያስተዳድሩ ሰዎች ላይ በሚታየው ድካም እንደሆነ በሚገባ ተረድቶ ነበር።
ይህ መረዳት፣ ቤተ ክርስቲያን መለኮታዊ-ሰብዓዊ (Theanthropic) ተቋም መሆኗን ከመቀበል ይመነጫል።

እርሷ፣ እንደ ክርስቶስ አካል፣ በመለኮታዊ ተፈጥሮዋ ቅድስት፣ ፍጽምትና ከስህተት የጸዳች ናት፤ ነገር ግን በውስጧ የሚያገለግሉት ሰዎች የሰብዓዊ ድካም ተገዢዎች ናቸው። ቅዱሳን አባቶች ይህንን ልዩነት በሚገባ አስተምረዋል። ለምሳሌ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የክህነትን ቅድስናና የአገልጋዩን ግላዊ ድካም ሲለይ፣ የክህነቱ ኃይል የሚመነጨው ከሰውየው ማንነት ሳይሆን ከክርስቶስ ሹመት መሆኑን ያስረዳል። ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያም ንስጥሮስን የታገለው፣ የአንጾኪያን ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ለመናድ ሳይሆን የተሳሳተውን የሃይማኖት ትምህርት ለማረም ነበር።

ስለሆነም፣ የሃቢብ ጊዮርጊስ መፍትሔ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ አዲስ ሥርዓት መመሥረት ሳይሆን፣ በውስጧ በመሆን፣ በትሕትናና በመታዘዝ፣ ያንን ሰብዓዊ ድካም መፈወስና ማነጽ ነበር። ሥራው ሁሉ የሚያሳየው ይህንን ነው፡- በገዛ አረዳዱ "የተበላሸውን" ብሎ የገመተውን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማረም አልሞከረም፤ ይልቁንም ያንን ያልተበረዘ ትምህርት ለተራበው ሕዝብ ለማድረስ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

፬. ትምህርቱ ለዛሬው ትውልድ፡- የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ተዛምዶ

ይህ የታሪክ ትምህርት በዘመናችን ላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅና አስቸኳይ መልእክት አለው። ዛሬ በርካታ ምእመናን በአስተዳደራዊ ብልሽቶች፣ በመንፈሳዊ አመራር ድክመትና በአንዳንድ አገልጋዮች ሥነ ምግባር ጉድለት የተነሣ በብስጭትና በቅሬታ ተሞልተዋል። ይህ ስሜት መነሻው ቅን ሊሆን ይችላል።

ችግሩ ያለው ለዚህ ስሜት በሚሰጠው ምላሽ ላይ ነው። ብዙዎች፣ ልክ በሃቢብ ጊዮርጊስ ዘመን እንደነበሩት ተቺዎች፣ መላዋን ቤተ ክርስቲያንን ይወቅሳሉ፤ ሐዋርያዊ ትውፊቷን ይጠራጠራሉ፤ አልፎ ተርፎም በግል አስተያየታቸውና ፍልስፍናቸው ያንን ትውፊት ለመተካት ይዳዳሉ። ከዚህም የከፋው፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትይዩ መዋቅሮችንና ርዕዮተ ዓለሞችን ለመገንባት መሞከር ነው፤ ይህም አንድነቷንና ሐዋርያዊ ሥርዓቷን በእጅጉ ይጎዳል። ይህ አካሄድ፣ የቅዱስ ኢግናጥዮስ ዘአንጾኪያ "ከኤጲስ ቆጶሱ ውጭ ምንም ነገር አታድርጉ" የሚለውን ሐዋርያዊ መመሪያ የሚጻረር ነው።

፭. ኦርቶዶክሳዊው የማነጽ መንገድ፡-
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያንን የምትረዳበትና የማነጽ አካሄዷ ግልጽ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 4፡11–13 ላይ፣ ክርስቶስ ራሱ ለቤተ ክርስቲያኑ "ሐዋርያትንና ነቢያትን፣ ወንጌላውያንንም፣ እረኞችንና አስተማሪዎችንም" የሰጠው፣ "ቅዱሳን … ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፣ ለክርስቶስም አካል ሕንጻ" እንደሆነ ያስረዳል። መዋቅርና ሥርዓት የተሰጠው ለማነጽ እንጂ ለመበታተን አይደለም።

የማረምና የማነጽ ሥራ እንዴት መከናወን እንዳለበትም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስቀምጣል። በይሁዳ መልእክት 1፡22 ላይ "አንዳንዶችንም በምትለዩበት ጊዜ፣ ምሕረት አድርጉላቸው፤ ሌሎችን ግን ከእሳት እየነጠቃችሁ በፍርሃት አድኗቸው" ይላል። ይህ ቃል፣ ችግሮችን የምንቀርብበት መንገድ በጥበብና በልዩነት መሆን እንዳለበት ያስተምራል እንጂ ሁሉን በአንድ ላይ የመውቀስ አካሄድን አይደግፍም።
ዋናው መሠረታዊ እውነት ይህ ነው፡- እውነተኛ ለውጥና ትንሳኤ የሚመጣው ቤተክርስቲያንን በመክስና በግላዊ የክለሳ አካሄድ ሳይሆን፣ በታማኝ አገልግሎትና የጋራ ሸክምን በመሸከም ነው።

፮. ሸክሙን መሸከም ወይስ ጣትን መቀሰር?
ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የምትፈልገው ተጨማሪ ከሳሾችንና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚተቹትን አይደለም፤ የምትፈልገው የሃቢብ ጊዮርጊስን ዓይነት መንፈስ የተላበሱ ልጆችን ነው። ችግሩን ከማራገብ ይልቅ የመፍትሔው አካል የሚሆኑትን፤ የቤተ ክርስቲያንን ሸክም በትከሻቸው ተሸክመው የክርስቶስን ሕግ የሚፈጽሙትን።

ስለዚህ፣ እያንዳንዱ የበሰለ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ራሱን ሊጠይቅ ይገባል፡- እኔ የቤተ ክርስቲያንን ሸክም አግዤ እየተሸከምኩ ነው? ወይስ በቁስሏ ላይ ጣቴን እየቀሰርኩ፣ የውግዘት ድንጋይ እየወረወርኩ ነው?

የዛሬው ጥሪ፣ ልክ እንደ ሃቢብ ጊዮርጊስ፣ ኃላፊነትን መውሰድ ነው። ይህ ደግሞ በፍቅር፣ በዲሲፕሊን፣ በትሕትናና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱ አካሉ በሆነችው ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ባለ ጽኑ እምነት የሚከናወን የተቀደሰ ተግባር ነው።

©አቦርሃም ሲሳይ
        
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
🔴ድንቅ ወቅታዊ መልእክት‼️የዘመኑ የም...
መንክር ሚዲያ-Menker Media
የዘመኑ ምንኩስና ሕይወት ከቀደሙት ጋር ሲነጻጸር
  
           
Size:-76.8MB
Length:-1:22:58

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#ወንድማችንን ፍቱት

ሊቀ ትጉኅን ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ዛሬ ከግል ቢሮአቸዉ ወጥተዉ ወደ ተሽከርካሪያቸዉ ሲያመሩ ለጥያቄ እንፈልግዎታለን ተብለዉ ደህንነት ነን ባሉ አካላት መወሰዳቸዉን ከቤተሰቦቻቸዉና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ከሰማን ቀናት አለፊ ።

ይሁን እንጂ መምህር ደረጀ ነጋሽ እስከ አሁን ያሉበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ አልታቻለም።
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
2025/07/03 22:56:28
Back to Top
HTML Embed Code: