Telegram Web Link
#በከንቱ_አምተናታል

ዮሴፍ በጽኑ መረበሽ የተያዘበት ወቅት ነበር። የእመቤታችን መፀነስ ከሚያወቀው ተፈጥሯዊ አካሔድ ውጪ ስለሆነበት ልቡ ክፉኛ ተሸብሮ ነበር። በእርግጥ ዮሴፍ በእመቤታችን መፀነስ መደናገጡ ብዙም ላያስደንቅ ይችላል። መካን ሆነው ሳለ በልመናቸው ብርታት የወለዱ አሉ÷ እንደነ ሣራ በስተርጅናቸው የፀነሱም አሉ። የእርሷ ግን የተለየ ነው በድንግልና የወለደ ከእርሷ በፊትም ይሁን ከእርሷም በኋላ አልተገኘም።

መጻሕፍት እንደሚነግሩን ዮሴፍ ግን ከመደነቅ ይልቅ ከንግድ ሲመለስ ያገኘው ፈላስፋው ዮሐንስ "ይህቺ ሴት ካንተ ነው የፀነሰችው" ብሎ የተናገረው ቃል ከድንጋጤ አድርሶታል። በዚህም ምክንያት ነበር "መኑ ቀረጸ አክናፈ ድንግልናኪ" ብሎ የመፀነሷን ነገር የጠየቃት። ንጽሕት የሆነች እርሷ ግን "መልአኩ አክብሮ ከነገረኝ ውጪ ሌላ ምንም የማውቀው የለም አለችው" የእመቤታችን ትሕትና መግለጽ የሚቻለው አንደበት የለም ቃሏና ምላሿ ሁሉ በትሕትና የታሹ ናቸው።

ዮሴፍ አሁንም ቢሆን ከጥርጣሬው መዳን አልቻልም አንድ አንድ ጊዜ ፍርሐት እና የሰዎችን ወቀሳ ማስታወስ ወደ ጥርጣሬ አሮንቃ ውስጥ ይከተናል አረጋዊው ዮሴፍም የሆነው እንዲሁ ነው። ይህንን ጥርጣሬውን ልታስወግድለት የወደደች እመቤታችን ግን አአዕዋፍ እንዲራቡ የሚያደርግ አአዕዋም እንዲያፈሩ የሚያደርግ ማን ምስሎሃል? ብላ ከግሰጸችው በኋላ ከደጃቸው የቆመ ደረቅ ግንድ ነበር እርሱን አለምልማ አሳየችው። መልአኩ ትፀንሺያለሽ ብሎ ባበሠራት ወቅት ይህ እንዴት ይሆንልኛል ብትለው "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" ብሎ የመለሰላትና እርሷ በተግባር አሳየችው። በተረቱበት መርታት ልማድ ነው።

እመቤታን ያለውንድ ዘር በድንግልና የመጸነሷ ነገር ምትሐት ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን ብትገልጥለትም። ለቆጠራ ወቅት ግን ይዟት ይወጣ ዘንድ ፈራ። ከእግዚአብሔር ሥራ ይልቅ ፍርሐታችንን እናምነዋለን በዚህም በተሳሳተ እምነታችን የእግዚአብሔር ዓላማ አደናቃፊዎች ሆነን እንገኛለን። ዮሴፍም ያለ ወንድ ዘር እንድትጸንስ ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሐይል ሳያስተውል ይዟት ሲወጣ ግን አይሁዶች ሊፈጥሩት የሚችሉት ትንኮሳ አስፈራው።

ይዟት ቢወጣ ሕጋቸውን ቢያስቀራት ደግሞ ያደረገውን ዓውቆ ጥሏት ወጣ እንዳይሉ ወሪያቸውን ፈርቶ ሳለ መልአኩ ከያዘው ፍርሐት አርቆ ይዟት ይወጣ ዘንድ አዘዘው። ዮሴፍ በመልአኩ ትዕዛዝ ይዟት ቢወጣም የዲያቢሎስ የግብር ልጆች የሚሆኑ በትጠጣው ለሞት የሚያደርሳትን ማየ ዘለፋን ትጠጣልን አሉ። የአምላክ እናት እርሷ ግን ማየ ዘለፋን ከጠጣችው በኋላ እነርሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ከወትሮው አበራች ጽድልት ሆና ታየች ከፀሐይ ይልቅ አብርታ ተገኘች በጊዜ የተቀሩት አይሁድም ይህን ቢመለከቱ "ይህችን ብላቴና በከንቱ አምተናታል" አሉ።

የእመቤታችንን ክብር ከመናገር እርቀው በከንቱ የሚያሙ ሰዎች የበቀሉት ገና በማኅጸን ሳለች ነው። መወለዷን የጠሉ ዳግመኛ የመውለዷን ነገር አለወደድዱምና በጊዜው ነውር እንደተገኘባቸው ሴቶች እርሷን በከንቱ አሟት። እውነት ደቆ ሐስት ረቆ ባየለበት በእኛ ዘመንም ዓይነ ልቦናቸው የታወረባቸው በከንቱ ያማሉ። የእግዚአብሔርን ሳይሆን የግብር አባታቸውን የዲያቢሎስን ድምፅ እየሰሙ በቅዱሳኑ ላይ በከንቱ ይናገራሉ። ከሁሉ ልቆ የታየው ግን የአይሁድ ከንቱ የሆነው ሐሜታቸው ሳይሆን ስለ ክፉ ፈንታ ክፉ ያለመለሰች የእመቤታችን ትሕትና ነበር።

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
          
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ
ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወሥነ
ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ
ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ
ፈጠርከ፤ ፀሐየ ወወርኀ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ ወአልዓላ
እምኵሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ፤

#ትርጉም
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የገባህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድክ፤ ምድርን በአበቦች
ያስጌጥክ፤ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው ? የምድረ በዳውን
አራዊት ከወዳጆችህ ጋር ያስማማህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ
ማነው፤ ጉንጮቹ እንደ ዋልያ እንቦሳ ፈጣኖች ናቸው፤
አንደበቱ ጣፋጭ ነው፤ ተወዳጅነቱ እንደ ፌቆ ግልገል ነው፤
ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፤ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፤
ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ፤ ምድርን በአበቦች ያሸበረቅህ፤
ሰንበትን ያከበርካት ከዕለታትም ለይተህ ከፍከፍያደረግኻት፤
አቤት!! እንዳንተ ይቅር ባይ ማንም የለምና ኹሉም አንተን
ተስፋ ያደርጋሉ።
#እንኳን_ለዓለም_ጌታ_ለፍጥረታት_አምላክ_ለነገስታት_ንጉስ_ልዑለ_ባህሪ_ለሆነው_ለአምላካችን_ለመድሐኒታችን_መድኃኒዓለም_ወርሀዊ_በዓል_አደረሰን !

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
2025/07/05 15:35:29
Back to Top
HTML Embed Code: