Telegram Web Link
" #ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ..."

#መዝ 8፣2
_

" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"

#ማቴ 21፣9

#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም

#ሆሳህና በአርያም ለወልደ ዳዊት

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ሰላምሽ_ዛሬ_ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 


ለመቀላቀል👉
@ortodoxtewahedo
🌿 🌴 ሥርዓተ ዋዜማ ወማኅሌት ዘሆሣዕና 🌿 🌴

ሥርዓተ ዋዜማ

በእምርት ዕለት በዓልነ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤
ወስብኩ በደብረ መቅደስየ፤
እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር፤
ሆሣዕና በአርያም፤
ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል።

አመላለስ፦

ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል፤/2/
ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል/4/

ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ (መዝ: ፳፫)

ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።

እግዚአብሔር ነግሠ (መዝ: ፺፪)

ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘርድአነ፤
ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
ንፍሑ ቀርነ በጽዮን በዕለተ ሠርቅ፤
በዕምርት ዕለት በዓልነ።

በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኃቤከ (መዝ: ፻፵)

ደቂቅኒ እንዘ ይጸርሑ፤
ወሕዝብኒ ኪያሁ ይሴብሑ፤
ደቂቅኒ እንዘ ይጽርሑ።

ይትባረክ (ጸሎተ ፫ቱ ደቂቅ: ፱)

ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ እሥራኤል፤
ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልአ ዓውደ እክል፤
በረከተ ምክያዳተ ወይን።

ሰላም

ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ዓርገ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም፤
ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን፤
ወበልዋ ለወለተ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ ጻድቅ ወየዋህ ዘእሤቱ ምስሌሁ፤ ወምግባሩ ቅድመ ገጹ፤
ወይከውን ሰላም በመዋዕሊሁ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሥርዓተ ማኅሌት

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤
ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤
ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ

ሰላም ዕብል ለዘዚአክሙ ቆም፤
ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ዘአልብክሙ ዓለም፤
እምኔክሙ ፩ በእንተ ፩ አዳም፤
እመኒ በምድር ተወክፎ ለነግደ ጲላጦስ ሕማም፤
ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም።

ዚቅ፦

እምሆሣዕናሁ አርአየ ተአምረ ወመንክረ፤
ዘኢተገብረ እምቅድመዝ፤
ወኢይከውን እምድኅረዝ።

በዐቢየ እግዚዕ ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ምስለ አቡሁ አሐደ ፈቃድ፤
ቅድመ ገፀ ጸላዒ ጽኑዕ ማህፈድ፤
ተፅዕነ ዲበ ዕዋል ዘእሳት ነድ፤
ያጹ ሆሳዕና ዘአብ ወልድ

በዐቢየ እግዚዕ ፦

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ፦

ዘበእንቲአሃ ኢሳይያስ ጸርሐ፤
እንዘ ይብል አብርሂ አብርሂ ተፈስሒ በንጉሥኪ በጽሐ፤
ኢየሩሳሌም ዜነዋ ፍስሐ

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ፤
ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤
አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ፤
አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።

ዚቅ፦

ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ ፳ኤል፤
ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልአ ዓውደ እክል፤
በረከተ ምክያዳተ ወይን።

በዐቢየ እግዚዕ ዚቅ ፦

ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለመትከፍትከ ከመ ልብሰ ክህነት ሎግዮ፤
ጊዜ ጸዓተ ፍትሕ ዘፆረ አርዑተ መስቀል በቀራንዮ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ በግዓ መድኃኒት ወአስተሥርዮ፤
አስተዳሎከ ለርእስከ ውስተ ዓፀደ ግፍዕ ተርእዮ፤
ወኲሎ በዘይደሉ አቅደምከ ሀልዮ።

ዚቅ፦

ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ፤
አርዑተ መስቀል ፆረ፤
እስከ ቀራንዮሰ ሖረ፤
ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ።

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላምን ለአእጋሪከ እለ ጠብዐ ለቀዊም፤
ቅድመ ጲላጦስ ፈታሒ መስፍነ ይሁዳ ወሮም ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘትማልም ወዮም፤
ኀበ ወረደ ወነጠበ ዝናመ አእጋሪከ ደም፤
ለመስቀልከ በሰጊድ ሰላም።

ዚቅ፦

ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት፤
ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል።

በዐቢየ እግዚዕ፦ መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለአፅፋረ እግርከ በደመ ቅንዋት እለ ተጠምዐ፤
እስከ ጽዕዳዌዎን ለብሰ ልብሰተ ጠባይዕ ካልዐ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰቅልከ በአፍዐ፤
ከመ ይዜኑ ሂሩትከ ወእከውዕን ስምዐ፤
መምህረ ረሰይኩከ ረስየኒ ረድዐ ።

ዚቅ፦

አስተይዎ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት ለዘያዳ ሆሳዕና በክብር ሰቀልዎ ዲበ ዕፀ መስቀል፤ አይሁድ ዐማፅያን

መዝሙር፦

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ፤
ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ፤
ሀገረ እግዚአብሔር፤
ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን፤
አዕሩግ ወሕፃናት፤
ነሢኦሙ አዕጹቀ በቀልት፤ እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ተጽኢኖ ዲበ ዕዋል፤
ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም፤
በትፍሥሕት ወበኃሤት ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ።

አመላለስ፦

በትፍሥሕት ወበኃሤት/፪/
ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ/፬/

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
Audio
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል
                      
Size 23.MB
Length 1:08:39

  በርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
Audio
ሆሳዕና

Size:- 19.6MB
Length:-1:25:37

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል
                      
Size 23.MB
Length 1:08:39

  በርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
#ሰሞነ ህማማት

#ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት
ሰኞ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ
” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። ይህ ቀን አንጽሖተ ቤተመቅደስ የፈጸመበት ሰኞም ይባላል ።

ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ሰሙነ_ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

#የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

(ስምዐ ጽድቅ መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

  ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ሥርዓተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ  ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ
    ┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈

❖ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡

❖ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን  እስከ ይዌድስዋ  ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡

❖ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና  በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና  ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ  ይመራሉ፡፡

❖ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፤ በመቀጠል

#ትእዛዝ

❖ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ)

❖ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም "

❖ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም"

❖ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም "

❖ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት"

#ትእዛዝ

❖ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ።

❖ ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለሕማሙ  ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"

#ትእዛዝ

❖ ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡

❖ በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

❖ ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

#ትእዛዝ

❖ ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤

"ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤  ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

#ትእዛዝ

❖ ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡

ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

አብኖዲ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን ፤

ታዖስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ማስያስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ኢየሱስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ክርስቶስ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

አማኑኤል ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

ትስቡጣ ናይን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

#ትእዛዝ

❖ ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡

❖ ይኸውም በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል፡፡

#በመጨረሻ ጊዜ

❖ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)

❖ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)

❖ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ  እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡ /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
             ይቆየን

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 5ቱ ሀዘናት

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ፣ በወወልድ፣ በወመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፭ቱ ታላላቅ ኀዘናት ማን ማን ናቸው ቢሉ?

ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኅዘናት የትኛው ይበልጣል ብሎ በጠየቃት ጊዜእመቤታችንም ልጄ ወዳጄ ሆይ ባንተ ምክንያት ካገኙኝ ኅዘናት እነዚህን አምስቱ ይበልጣሉ ብላ እመቤታችን የጠቀሰቻቸው ታላላቅ ኅዘናት የሚከተሉት ሲሆኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እነዚህን ያንችን ኅዘናት እያሰበ የጸለየ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል።

#፩ኛ - ስምዖን በቤተ መቅደስ ትንቢት በተናገረ ጊዜ።

===>ስምዖን የተባለው፦ አረጋዊው ስምኦን ነው የእመቤታችን ሐዘን የሚጀምረው ገና አንድዬ ልጇን ከመውለዷ በስምተኛው ቀን ነው ቤተመቅደስ ይዛው በሄደች ጊዜ አረጋዊው ስምዖን “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል (ልጅሽ በቀራንዮ ይሞታል)” ሉቃስ 2፥34-35 ብሎ በነገራት ጊዜ ድንግል ማርያም አምርራ አዘነች አለቀሰች።

እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት። ሉቃ (2፡34-35)

#፪ኛ - ከቤተ መቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ።

ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።

ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን
መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። ሉቃ (2፡41-48)

#፫ኛ - በጲላጦስ አደባባይ በገረፉህ ጊዜ::

በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም።

የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ አላቸው። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ዮሐ (19፡1-5)

#፬ኛ - በዕለተ ዓርብ በሰቀሉህ ጊዜ።

ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።

ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ።ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን። እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። ዮሐ. (19፡17-2

#፭ኛ- ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደ አዲስ መቃብር ባወረዱህ ጊዜ።

ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።

በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። ዮሐ (19፡38-42) እንዚህን አምስቱን የእመቤታችን ሐዘናት እያሰበ ያዘነ ዝክሯን የዘከረ በአማላጅነቷ የታመነ ዋጋው ከቶ አይጠፋበትም፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን

።።።አሜን አሜን።።።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

#እንኳን ለሰሙነ ሕማማት በሰላም አደረሰን/ አደረሳችሁ

እነዚህን የሰሙነ ሕማማት ቀናት ከሁሉ አሰቀድመን በፍርሃት ና በርአድ በመንቀጥቀጥ የክርስቶሰን ሕማሙን ፣ ግርፋቱን ፣ ስቃዩን ፣ በመስቀል ተቸንክሮ ራሱን ስለ ሁሉ ቤዛ አድርጎ የደረሰበትን መከራ ስቃይ እያሰብን የምናሳልፈው ሳምንት ነው፡፡

በተጨማሪ በሕማማት ሰሞን ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ ፦

➊የዕብራይስጥ(hebrew)
➋የቅብጥ (ግብጽ) (coptic)
➌የግሪክ (ጽርዕ) (greek) ቃላት ይገኛሉ፡፡
የእነዚህ ቃላት ትርጉም በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

♦️ኪርያላይሶን ፦
ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነዉ፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

♦️ናይናን ፦
የቅብጥ(ግብጽ) ቃል ሲሆን "መሐረነ / ማረን" ማለት ነዉ፡፡

♦️አብኖዲ ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "አብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ ፡፡

♦️ታኦስ ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን "ጌታ / አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "ታኦስ ናይናን" ሲልም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

♦️ማስያስ ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "መሲሕ" ማለት ነዉ፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

♦️ትስቡጣ ፦
"ዴስፓታ" ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ደግ ገዢ" ማለት ነዉ፡፡

♦️ሙዳሱጣ ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን "ነበልባላዊ" ማለት ነዉ፡፡

♦️ መዓግያ ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን "እሳታዊ" ማለት ነዉ፡፡

♦️አንቲፋሲልያሱ ፦
ቃሉ "በመንግስትከ / በመንግስትህ" ማለት ነዉ፡፡

♦️አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲፋሲልያሱ ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚኦ በዉስጠ መንግስትከ / አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነዉ፡፡

♦️አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በዉስጠ መንግስትከ / ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

♦️አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ መንግስትከ / የሁሉ የላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

♦️ኤልማስ ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን "አምላኪየ / አምላኬ" ማለት ነዉ፡፡

♦️አህያ ሸራህያ ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "ያለና የሚኖር" ማለት ነዉ፡፡

እነዚህ ከላይ ያሉና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች በቀጥታ የተወሰዱ ናቸዉ፡፡

✿✿✿መልካም የሰሙነ ሕማማት ወቅት ይሁንልን ✿✿✿

ስብሐት ለከ፤
ሰጊድ ለአቡከ፤
ዕበይ ለመንፈስከ፤
ወምህረተ ፈኑ ለሕዝብከ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡

ሙሉዉን ያነበበ ብቻ አሜን ይበል፡፡

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽዐነ በፍሥሐ ወበሰላም


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ
#JOIN #OUR #CHANNE

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ይህ ሳምንት ከሰርከ ሆሳዕና እስከ ትንሣኤ ያሉትን ቀናት
ያካትታል::

#የጌታን መከራ እንግልት መሰቀል መሞት መቀበር የምናስብበት ነው:: ለእኛ ሲል የተቀበላቸውን 13ቱ ሕማማተ መስቀል በማሰብ በልቅሶ በስግደት በጸሎት ልናሳልፈው
ይገባል:: በዚህ ሳምንት ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው::
በመስቀል መባረክ ማማተብ መሳቅ መሳሳም ከሴት ጋር
መገናኘት ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው
የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ
ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ
ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም::
እግዚአብሔር ይፍታህ አይባልም ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን
ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት እንኳ
ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን
ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ
የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው መጠጡም ንጹህ
ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ
ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው:: ጸሎቱ
ውዳሴማ ርያም አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሕማማት መዝሙረ
ዳዊት ነው:: የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም:: የጾሙ
ሥርዓት ምን ይመስላል ካሉ፡
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15

ቁጥር 578፡ በሊህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ
ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን
ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡
ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል
እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው
ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን
የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡

ቁጥር 590፡ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል
አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ
ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡

ቁጥር፡ 593፡ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም
በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ
መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ
ጋር አይተኛ፡፡

ቁጥር 597፡ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ
በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና
የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ
እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ
ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን
ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ
ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን
ወዴት አለ?

ቁጥር 599፡ በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፡፡
ከጥሉላት መከልከል ይገባል፡፡ አያግቡም፡፡

ቁጥር 600፡ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት
መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡
በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና
የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን
ይነበብ እንጅ፡፡

ቁጥር 601፡ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን
የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ
ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ
ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ
ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም
ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት
ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን
ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡
ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና
ይደረግለታል፡፡
የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡
1. እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል መሳሳም
2. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ
3. መስቀል ማሳለም እና መሳለም
4. ክርስትና ማስነሣት
5. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ
6. ክህነት መስጠት
7. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ
8. መሳቅ መጫዎት መጨፈር
9. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ
10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡


https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
2024/06/17 15:52:17
Back to Top
HTML Embed Code: