Telegram Web Link
🔴 ይሰቀል እያሉ ይጮሁ ነበር || እጅ...
Enqo silassie
ይሰቀል እያሉ ይጮሁ ነበር
              መድኃኔዓለም
Size:-134MB
Length:-2:25:02

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ኦ አርምሞ ዘመጠነ ዝ አርምሞ ?
ኦ ትዕግስት ዘመጠነ ዝ ትዕግስት?
ኦ ሂሩት ዘመጠነ ዝ ሂሩት ?
ኦ ፍቅር ዘመጠነ ፍቅረ ሠብ ?
( ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት  ነው ? ይህን ያህል ዝመታ እንደምን ያለ ዝመታ ነው ? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው ?

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
👍10🥰3🔥2🙏2👏1
ኒቆዲሞስ ፯ ሣምንት ዐብይ ጾም

ኒቆዲሞስ የትህትና፣ የትጋትና የጽናት አብነት ነው።

ኒቆዲሞስ ማለት:- በግሪክ ቋንቋ “አሸናፊ/ነት” ማለት ነው፡፡

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡

በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ስልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በህዝቡ ላይ የሚመፃደቁ ነበሩ፡፡

በዘመናቸው እውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ለመሆን ወደዚህ ዓለም ሲመጣ አልወደዱም ነበር። እርሱ ግን የትህትና ባለቤት በመሆኑ ሁሉን ችሎ ያስተምር ነበር።

ዮሐ ፫÷፩-፲፪ ፣ ማቴ ፭÷፳
ማቴ ፲፮÷ ፮ ኢየሱስም፦ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።

እግዚአብሔር አምላክ ትዕግስቱን ሰጥቶ ክፉውን በመጠየፍ ደግ ደጉን ብቻ በመስራት የመንግሥቱ ወራሾች፣ የስሙ ቀዳሾች ያድርገን፣ ወዶና ፈቅዶ ለዚህ ዕለት እንደ አደረሰን ሁሉ እንድ በደላችን ሳይመለከት ቀሪውን ጊዜ ያስፈጽመን አሜን!

" ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ"

@ortodoxtewahedo
👍2011👏1
#አብርሀምን ላምላክ ወገን ያደረግው

#በሀዋርያት ላይ መንፋሱን የላከው

#ሰለስቱ ደቂቅን ከሳት ያወጣቸው

#ከተራቡ እናብስት ድንኤልን ያዳነው

#ከእደ ረበናት ሶስናን የረዳት

#እንድ እምነት እሱም ተዋህዶ ነው

#ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና ዓለምን የሚያሸንፋው እምነታቹ ነው

1ኛ ዩሐ 5፥4

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍318🙏5👏2🔥1
እግዚአብሔር የአምር ፤ እግዚአብሔር ያውቃል

...

ማርያም ድንግል ትጸርሕ በቤተ መቅደስ።

ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ጸርሐት ሲል ነው ተናገረች አለ።አመ ይወጽኡ እስራኤል እምግብፅ አመ ይትነሥኡ ላዕሌሁ ዕልዋን እንዲል ። ጸርሃት አለ ጮሆ የተናገሩት ሩቅ እንዲሰማ ነገሩ ፅንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳልና ጸርሐት አለ እንጂ ተናገረች ሲል ነው ።

ወትብል የአምር እግዚአብሔር ከመ አልብየ ዘየአምርባዕደ: ወኢምንትኒ ዘእንበለ ድምፀ ቃሉ ለመልአክ ዘአብሰረኒ በክብር ወይቤለኒ ሰላም ለኪ ኦቅድስት ድንግል።

ምልዕተ ክብር እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ አንድ አካል ይሆናል ብሎ መልአኩ አክብሮ ከነገረኝ ነገር በቀር ምን ምን የማውቀው እንደ ሌለኝ እግዚአብሔር ያውቃል ብላ ጸርሐት፤ ተናገረች አለ።

እመቤታችን የብፅዓት ልጅ ናት ሶስት ዓመት ሲሆናት እናት አባቷ ወስደው ለካህናት ሰጥተዋታል። ካህናትም ከቤተ መቅደስ አገቧት። ከቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት ትኖራለች ይህ አሥራ ሁለት ካባት ከናቷ ቤት ሶስት። አሥራ አምስት ዓመት ሲሆናት አይሁድ ናሁ ወርዘወት ወለተ እስራኤል መጠነ አንስት አደረሰች ቤተ መቅደስ ታሳድፍብናለች ትውጣልን አሉ። ዘካርያስ ገብቶ እንደ ምን ትሆኝ ብሎ ቢጠይቃት ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ እንጂ እኔ ምን አውቃለሁ አለቺው ። ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን አስቈጥረህ ብትራቸውን ከቤተ መቅደስ አግብተህ አውጣ አለው ።

ብትራቸውን ሰብስቦ ከቤተ መቅደስ አግብቶ ቢያወጣው። ከበትረ ዮሴፍ "ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ኢትፍራህ ነሢኦታ ለማርያም ፍሕርትከ" የሚል ተቀርፆ ተገኝቷል ርግብም ወርዳ ከራሱ ላይ አርፋበታለች ዕፃም ቢጣጣሉ ለሱ ደርሳዋለች። በዚያም በዚያም ሆነ እንካ ካላሰናበትንህ አትንካ ብለው ሰጡት ከዚህ በኋላ ከቤቱ ወስዶ አኖራት ጊዜው ዓፀባ ነበርና ንግድ ሂዶ ሶስት ወር ኑሮ ቢመለስ ዮሐንስ የሚባል ፈላስፋ ወዳጅ ነበረው ሊጠይቀው መጣ ተጫውተው ሲሸኘው ፈላስፋ ነውና በመልኳ ዓውቆ ይህች ብላቴና ፀንሳለች ካንተ ነዉ ከሌላ አለው። እኔስ እንኳን የገቢር የሐልዮ አላውቅባትም አለው እንግዲያውስ ገብተህ ጠይቃት አለው ገብቶ ኦ ወለተ እስራኤል መኑ ቀረፀ አክናፈ ድንግልናኪ ቢላት እኔስ መልአኩ አክብሮ ከነገረኝ በቀር ሌላ አላውቅም ብላ ተናግራ ነበርና ጸርሐት አለ

በዚያውስ ላይ አዕዋፍ እንዲራቡ አዕዋም እንዲያፈሩ የሚያደርግ ማን መስሎሃል አለችው ከደጁም የቆመ ደረቅ ግንድ ነበረ አለምልማ አሳይታዋለች ከዚህ በኋላ ለበዓል የሚወጡበት ጊዜ ቢደርስ ይዣትም ብወጣ ሴሰንሽ ብለው በደንጊያ ወግረው ይገድሉብኛል፤ ትቻትም ብሄድ ያረገዘች ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ እንዲሉ ያደረገውን ዓውቆ ትቷት መጣ ይሉኛል ብሎ። ወወድቀ ዮሴፍ ውስተ ጽኑዕ መዋግደ ሕሊና እንዲል ይኸነን ሲያወጣ ሲያወርድ መልአኩ ይዘህ ውጣ አለው ይዟት ወጣ፤ ከዚህ በኋላ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና፤ ማየ ዘለፋ ትጠጣልን አሉ ማየ ዘለፋ ቢያጠጧት ብርህት ጽፏልት ሁና ተገኝታለች ወአጽደለ ገጻ እምብርሃነ ፀሐይ ዘወርኃ ኔሳን እንዲል በዚህ ጊዜ አይሁድ ይችን ብላቴና በከንቱ አምተናታል ብለው ስለ ጮሁ ጸርሐት አለ

አንድም ካህናት ዕለት ዕለት ኦ ድንግል አኮ ለዮሴፍ ዘተፍሕርኪ ለተቃርቦ አላ ከመ ይዕቀብኪ ንጹሐ እስመ ከማሁ ኮነ እያሉ የሚያመሰግኑ ስለሆነ እንዲህ አለ፤


.... ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍1311👏2
ምንም ቢያሳስባችሁ ቢያስጨንቃችሁ እንዲህ በሉ፤

... እግዚአብሔር ያውቃል ...

በማኅጸኗ መወሰን የሌለበት መለኮት ውሱን ከሆነ ስጋ ጋር አንድ አካል ሆነው የተዋሐዱባት ፤ የተሞሸሩባት ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም ያለችውም ይህን ነው፤

በምድር ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ የማይመረመር የምስጢራት ምስጢር በማኅጸኗ የተፈጸመ እናት "እግዚአብሔር ያውቃል" ካለች እኛማ ለሚያስጨንቁን ምድራዊ ለሆኑ ነገሮች ምንኛ "እግዚአብሔር ሆይ አንተ ታውቃለህ" ልንል ይገባናል...

@ortodoxtewahedo
18👍4👏2
“ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።”
— 1ኛ ሳሙኤል 15፥22

.............................................

ደስታችሁን ነገ በሚጠፉ ከናንተ ጋር በማይቆዩ ነገሮች ላይ መስርታቹህት ከሆነ እመኑኝ አንድ ቀን ይመጣል፤ "ለምን ይህን ነገር አጣሁት ብላችሁ ስታዝኑና ስትጨነቁ ራሳችሁን እንደምታገኙት" ፤ ይልቁንስ እግዚአብሔር ሆይ ስለሰጠኸኝ ነገር ሁሉ ምስጋና ይገባሀል እያላችሁ ዘወትር ሕያው የሆነ ቃሉን አድምጡ አንብቡ በልባችሁም አሳድሩት፤ "ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም" ብሏልና ከማያልፍ ከእርሱ ጋር አብረን እንሁን፤
ያኔ ዛሬ አገኘሁ ዛሬ አጣሁ
ያኔ ዛሬ ደስ አለኝ ዛሬ ግን ደበረኝ
ከሚሉት ከፍ ዝቅ የሚሉ ስሜቶች ወጥተን
"እግዚአብሔር ወሀበ ፤ እግዚአብሔር ነስአ"
"እግዚአብሔር ሰጠ ፤ እግዚአብሔር ነሳ"
ብለን እውነተኛ ደስተኞች እንሆናለን፤

@ortodoxtewahedo
👍284🙏1
Audio
"ቃል ሥጋ ሆነ"
ዮሐ1÷14
ክፍል 1

Size:-51:42
Length:-18MB
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
4👍2
Audio
"ቃል ሥጋ ሆነ"
ዮሐ1÷14
ክፍል 2

Size:-58:16
Length:-20.3MB
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
12👍2🙏1
የሚያዚያ ወር የፀሐይ ጸዳልን ብሩኅነት በድርሰታቸው ከጠቀሱት አባቶቻችን አንዱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው፤

እመቤታችንን ከሚመስሉባቸው እልፍ ምሳሌዎች አንዱ በዚህ ወር ፀሐይ ነው፤

በሃይማኖት የሚጋደሉት ጋሻ ጦር የሚዘፍኑት መሰንቆ የዘፈን ዕቃ የልዑል እግዚአብሔር የምስጋና ኃይል የአየራት ምጥቀታቸው የሰማያት ልዕልናቸው፡፡ የምድር መሠረት የቀለያት ጥልቀት #የሚያዝያ_ፀሐይ_ብርሃን፡፡ የጨረቃና የከዋክብት የነ አርዮብ ብርሃን ፀዳላቸው መልካቸው የምድረ በዳም አበቦች ፀዳል የገነት አበባ መልክ በውስጣቸውም የተዋሀድሽ መዓዛ ድንግል ሆይ ላፍንጫ የሚከረፋው የኃጢአት ክፉ ሽታ ወደ ሰማይ እነዳይወጣ በሃይማኖት ሽቱ አጣፍጭኝ፡፡


ሐሳባቸውንም በዚህ ኃያል በሆነ ብርሃን እየመሰሉም እንዲህ ሲሉ ይለምኗታል ...

በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ ልቡናዬን በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት የተቃጠለ የተሟሟቀ አድርጊው፡፡ ከሰይጣን ወገን የሚገኘውን የልቡናዬን መቀዝቀዝ ስንፍናዬንም አርቂው፡፡ ሐሳቤም በመንፈስ ቅዱስ ሙቀት የተሟሟቀ ይሁን ጽጋግና ጨለማም ከኔ ይራቅ ልቤም እንደመብረቅ ብርሃን ይብራ፡፡ #እንደሚያዝያም_ፀሐይ _በኃይል_እንደሚታይ_ይሁን፡፡ በማናቸውም ነገር ሁሉ ችግረኛ አታድርጊኝ፡፡ እናትም ለልጆቿ እንድትተጋ ለገዳጄ ሁሉ ትጊ፤


በእውነት ይህች ብርህት ንጽሕት እናታችን ፤ "እውነተኛው የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ" ያለ የእውነተኛው ብርሃናችን የመድኃኒታችን እናት ሕይወታችንን ብሩኅ ታድርግልን፤

ይህን ወርኅም የበረከት የረድኤት ያድርግልን🙏🏻

@ortodoxtewahedo
👍194🙏2
(፩)ልደታ ለማርያም እናቴ

#ድንግል ሆይ
የነብያት-ትንቢታቸው
የሐዋርያት-ሞገሳቸው
የሰማዕታት-አክሊላቸው
የመላእክት-እህታቸው
የምንዱባን-እናታቸው
የነዳያን - ምግባቸው
የደካሞች-ምርኩዛቸው
የደናግል-መመኪያቸው
አንቺ ነሽ🌹
እመቤቴ ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው እንኳን አደረሳችሁ🌹🌹

👉 ልደታ ለማርያም

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡

💠መልክአ ኤዶም

የቃል ኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን ።

@ortodoxtewahedo
20👍8👏1
."ሆዳችሁ ጠግቦ ከምታቀርቡት አንድ መቶ ጸሎትና ተራራ ከሚያርድ ድምጻችሁ ይልቅ በጾም ውስጥ ሆናችሁ የምታቀርቡት አንድ ጸሎት ተሰሚነት አለው።"

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

@ortodoxtewahedo
18👍4👏2
#መዝሙር_ዘሆሳዕና
"ወእንዘ ሰሙን"

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ መልዕክታት
ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን ዕብ 9÷11- ፍ ም
ን/ዲ 1ጴጥ 4÷1-12
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 8÷2
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

#ትርጒም
ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ::

#የዕለቱ_ወንጌል
ዮሐ 5÷11-31

ቅዳሴ: ዘጎርጎርዮስ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍71
" #ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ..."

#መዝ 8፣2
_

" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"

#ማቴ 21፣9

#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም

#ሆሳህና በአርያም ለወልደ ዳዊት

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ሰላምሽ_ዛሬ_ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 


ለመቀላቀል👉
@ortodoxtewahedo
👍158👏4🥰2🙏2
🔴 ቀድሞ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሄድ ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ቀድሞ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሄድ
       የዐቢይ ጾም ጉዞ
           ክፍል 6
Size:-52.16MB
Length:-56:1

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
🙏11👍4👏1
2025/07/10 08:27:42
Back to Top
HTML Embed Code: