Telegram Web Link
🔴 ሆሳዕና || ጌታቸው ይፈልጋቸዋል ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ጌታቸው ይፈልጋቸዋል
              ሆሳዕና
Size:-111.4MB
Length:-2:00:19

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።

ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።

ምንጭ ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@ortodoxtewahedo
ሰሙነ ሕማማት
👉 ረቡዕ

ምክረ አይሁድ ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው /ሉቃ ፳፪፥፩-፮/ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።


እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

👉 @ortodoxtewahedo
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ

#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡

#የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሰላም።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Audio
ሕማማት

 "በሕማማት የሚደረጉና የማይደረጉ ነገሮች"          
                          
Size:- 26MB
Length:-1:14:43
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
   "ጌታዬ እጠበኝ"
እግሮቼ የዛሉ ብዙ የተጓዝኩኝ
በቀኝ በግራ ስል መድረሻ ያጣሁኝ
ከጠባቧ መንገድ መርጬ ሰፊውን
በሰፊው ጎዳና ላይ እታች ስኳትን
ንጽሐ ሰውነቴን በበደል ያቆሸኩ
ንጽሐ ልቦናዬን በክፋት ያሳደፍኩ
በኃጥያት ቀንበር ሸክሜ ያጎበጠኝ
ውስጤ ክፋት ሞልቶት ጉልበቴ የከዳኝ
በነፍስ በስጋዬም እጅግ ደካማ ነኝ
ምህረትን የምሻ ተግባር የጎደለኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ልክ እንደ መጻጉ እንደ ምስኪኑ ሰው
ባህር ውስጥ ሚከተው ዘመድ እንደሌለው
መዳንን ትሻለክ ብለክ የጠየከው
በባህር ውስጥ ሚከት የለኝም መልካም ሰው
ብሎ እንደመለሰው
አይደለሁም እኔ አልጋ ላይ የቀረው
አካሌ የከዳኝ የቆምኩ የመሰለኝ
አልጋህን ተሸክመህ ሂድም እንዳትለኝ
በኃጢያት በሽታ መታመሜን ማላምን
መድኅኒት እንዳላገኝ ህመሜን ምሸሽግ በሽተኛ ሰው ነኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንደ ባለሽቶዋ መግደላዊት ማርያም
አንተ ባረፍክበት ማንም ባይጠራትም
ከእግሮችህ ስር ወድቃ ሽቶዋን አፍስሳ
በእንባዋ አጥባ በፀጉራ አብሳ
ከኃጢያት እስራት ስትፈልግ መላቀቅ
በንሰሃ ልንቦናዋ ምህረትን ስጠይቅ
እንደ ሰዎች ሳይሆን ልቧን ተመልክተክ
ዳግም እንዳበድዪ ብለህ እንደማርካትክ
አይደለሁም እኔ ከእግር ስር የምወድቅ
ሽቶን የማላፈስ እንባዬም ነው ደረቅ
ለታይታ የምኖር ሰዎች ምን ይሉኛል ምል
በኃጥያት ቆሽሼ ንጹህ ሰው ስመስል
የምህረት ቀኔን በከንቱ ማሳልፍ
ልበ ደንዳና ነኝ ምግባሬም የሰንፍ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀድመህ እንደነገርከው ለሐዋርያው ጴጥሮስ
ሥስቴ እንደሚክድህ ፍርሃት በልቡ ሲነግስ
አላቀውም ብሎ ዶሮ እስኪጮህ ድረስ
የንሰሃው ዶሮ ለጸጸት ሲያነቃው
ፊትህን አዙረህ በትዝብት ስታየው
መበደሉን ገብቶት ህሊናውን ሊወቅስ
የንሰሀን እንባ ከአይኖቹ ቢያፈስ
ምህረትን ሲሻ መጸጸቱን አይተክ
በደሉን እረስተክ ንስሀውን ተቀበልክ
እኔ ግን ደካማው በጊዜዬ ያልነቃው
ኃጥያቴን እያወኩ ንስሃ ያልገባው
የንሰሃው ዶሮ ሰልሶ ቢጮህም
ፊትህም ወደኔ በምህረት ቢዞርም
ኅሊናዬ ገብቶት ልቤ አልደነገጠም
የንስሃም እንባም ከዐይኖቼ አሎጣም
።።።።።።።።።።።።።።።፡።፡።።።።።።።።
እናም ጌታዬ ሆይ እኔ ምለምንክ
በኃጥያት ላደፍኩኝ እንዲሆነኝ ምህረትክ
በበደል ዳክሬ ቆሽሻለውና
ሆሳዕና ጌታ ፈጥነህ ወደኔና
ደንዳናውን ልቤን እንድታለሰልሰው
የልቤን መዝጊያ በር በፍቅርህ ስበረው
በኃጥያት ሸክም የዛለ አካሌን
ጉልበቴ ሆነከኝ ልስበረው ቀንበሬን
እንደ መጻጉ አልጋን ባልሸከም
የኃጥያት እግሬ ነጽቶ በንጽሐ እድቆም
ከኃጥያት ልንፃ በፍቅርህ እጠበኝ
ከበረዶም ይልቅ በምህረትህ አንፃኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
                ገጣሚ፦ በላይ ኃ/ሚካኤል

@ortodoxtewahedo
#ፀሎተ ሀሙስ

#ሀሙስ ምሽት ጌታችን ያደረገልን ትህትና ዮሐንስ 13

እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ
እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም
ትላላችሁ።

እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ
እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ
ይገባችኋል።

እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ
ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።

እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም።
መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። 17 ይህን ብታውቁ
ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
ስለ ሁላችሁ አልናገርም እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ
ነገር ግን መጽሐፍ፦ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን
አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።

በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከአሁን ጀምሬ
አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር በመጀመሪያነት ያጋሩት፦
በሰሞነ ህማማት የሚገኙ እለታትና ስያሚያቸው ........እለተ ሀሙስ -በዚህ እለት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ለመግለፅና ለአርያነት ፀሀፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲፀልይ በማደሩ ምክንያት ፀሎተ ሀሙስ በመባል ይታወቃል ፡፡

ትህትና ፍቅር መታዘዝ እንድሁም የአገልግሎትም ትርጉም
ለማስረዳትና ለማስገንዘብ እርሱ ጌታ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ህፅበተ እግር በመባልም እንደሚጠራም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ ፡፡

ሀዋርያው ቅዱስ ዮሀንስም እግራቸውን አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንድህም አላቸው ያደረኩላችሁን
ታስተውላላችሁን እንግድህ ጌታ መምህር ስሆን እግራችሁን
ካጠብሁ እናንተ ደግሞ ለታናናሾቻችሁ እንድሁ ታደርጉ ዘንድ ይገባችኀል ሲል ተናግራል፡፡ ይኸውም ዮሀንስ ወንጌል 13 ፣12
- 20 በዝርዝር ይገኛል ፡፡

ይህ ለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋየ ነው እንካችሁ
ብሉ ይህ ፅዋ ለእናንተ የሚፈሰው የሀዲስ ኪዳን ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ሚስጥረ ቁርባንን የመሰረተበት ወይንም
እራሱ ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሚስጥረ ቁርባንን የጀመረበት እለት በመሆኑ የሚስጥር ቀን በመባል ይጠራል ፡፡

ይኸውም የሰው ልጆች ስጋውንና ደሙን ተቀብለው ከእርሱ ጋራ
አንድነትንና ህብረትን እንድኖረን ጥንተ ጠላት ዳቢሎስን ድል
ነስተን ሰማያዊዩን እርስት እንድንወርስ ሊያደርግ ነው፡፡ ይህም በማቴወስ 26 ፣ 26 - 29 በዝርዝር ይገኛል ፡፡

አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጎት ቀስ ብለው
መጥተው የያዙበት ስለሆነ በዚህ እለት በለ ሆሳስ ወይም ብዙ
የጩኸት ድምፅ ሳይሰማ የቅዳሴ ስርአት ይፈፀማል ፡፡

ስለሆነም መላው ህዝበ ክርስቲያን በዚህ የህፅበተ ሚስጥር የፀሎት እለት በሆነው በዚህ እለት በንስሀ ታጥበው የጌታን ስጋና ደሙን እንድቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅኖት ታስተምራለች ፡፡

እኛም በንስሀ ታጥበን ወደ አምላካችን ቀርበን ስጋወ ደሙን
ልንቀበል ይገባናል የጌታችን ቸርነት ፍቅሩ የእመ አምላክ
የንፅሒተ ንፁሀን የድንግል ማርያም ምልጃ የመላክት ጥበቃ
የሠማአታት ፀጋ በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን
አሜን አሜን !!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
.#የሕማማት_ጥያቄዎችና_መልሶቻቸው

1. በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም?
👉🏾የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ በኋላ ነው
በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው።
በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት
በሰሞነ
ሕማማት በቤተክርስተያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ የማማተብ ስርዓት የለም።

2. በሰሞነ ሕማማት ለምን አንሳሳምም?
👉🏾ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማሰረዳት።
ከዚሀ በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት
በሰሞነ ሕማማት እሰከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም።
3. በሰሞነ ሕማማት የማይፈቀዱ ሌሎቸ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
👉🏾ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮችን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን መከራ ሕማም በማሰብ በፆም በስግደት
በጸሎት ማሳለፍ
በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ።
4. ስለ ሰሞነ ሕማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?
👉🏾ነብዩ ኢሳይያስ "በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል "
ኢሳ.53፤4 ይላል።
ሕማማት የሚለው ቃለ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወሰደ ሲሆን የጌታን
መከራ የምናስብበት ሳምንት ነው።
የጌታችንን ሞቱን ሕማሙን ማሰብ መዘከር እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እነዲህ ይላል፦
" ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ.11፤26።
ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት ቢሆንም
ለክረስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው
እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ''እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ
ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ
ይለወጣል'' ዮሐ16፤20
በእርግጥ ኃዘናችን ትንሳኤውን እሰክናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን እናዝናለን
በትነሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን።
👉🏾ሰኞ አይሁድ እንዴት እንደሚይዙት ለመማከር ክፉ ጉባኤያቸውን ጀመሩ።
''በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው
በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ ጌታ ኢየሱስንም በተንኮል ሊያስይዙት ሊገሉትም ተማከሩ" ማቴ26፡3_4።
ይህንን ጉባዔ ቅዱሰ ዳዊት የከፉዎቸ ጉባዔ እያለ ይጠራዋል።
"ብዙ ውሾች ከበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ" መዝ21፤16 አይሁድ ሰኞ የጀመሩትን ዕረቡ ውሳኔአቸውን አጠናቀው በምሴተ ሐሙስ ከዕራትና ከቁርባን በኋላ ሰይፍ ጎመድ ይዘው መጡ።

በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው ያዙትም እስከ አርብ ስድስት ሰአት
ሲያንገላቱት ቆይተው ከብዙ መከራ በኋላ ሰቀሉት ዘጠኝ ሰአት ላይ ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ከቅዱስ ስጋው ለየ። ከአሰራ አንድ ሰአት በፊት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በምስጋና ገንዘው ቀበሩት።

ከሕማሙ ከመከራው በረከት ያሳትፈን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።

👉🏽ትምህርቱ ለሌሎችም ይጠቅማልና ሼር ያድርጉ!
#ዕለተ_ዓርብ#ዕለተ_መድኃኒ

#በዲ/ን_በረከት_አዝመራ

"#ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤ ጌታችን (መምህራችን) ሆይ! ለመስቀልህ እንሰግዳለን፡፡"
***
"ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤ ኃይል ክብር ምስጋና እና ብርታት ለአንተ ይገባል"
በሰሙነ ሕማማት #በስግደት ወቅት ደጋግመን የምንለው #ምስጋና ነው:: ጌታችን ለሰው ልጆች #ድኅነት መከራ ተቀብላሏል: በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ስለእኛ ሞትን በፈቃዱ ቀምሷል:: ይህ ድካም የመሳላቸው ብዙዎች ናቸው:: (አጋንንት፣ ብዙኃኑ አይሁድ፣ መናፍቃን)
ቤተ ክርስቲያን መከራውና ሞቱ የድካም ሳይሆን የካሳ መሆኑን እና ብርቱ የሰው ልጆች ጠላቶች (ኃጢአት፣ ሞት፣ ዲያብሎስ) የተሸነፉበት መሆኑን በማወቅ 'ኃይል ክብር ምስጋና እና ብርታት የአንተ ነው' በማለት ታመሠግነዋለች:: ይህን ምሥጋና ቀድሞ መላእክት #በመስቀሉ ሥር #እየሠገዱ ተናግረውታል::ኪርያላይሶን (ጌታ ሆይ ማረን)
ክርስቶስን ለመከራ ያደረሰው የሰው ኃጢአት ነው:: መከራና ሞቱም #የምሕረት ምንጭ ነው:: በዚህም ምክንያት ኃጢአታችንን እያሰብን እና በመስቀል የተገለጠውን #ምሕረት እና #ፍቅር እያመንን 'ኪርያላይሶን ጌታ ሆይ ማረን' እያልን እንሰግዳለን:: 'እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ' በማለትም ደጋግመን

#እንማጸናለን::
ምስባካት እና ምንባባት
ዲያቆናት ከዳዊት መዝሙር ስለ መከራው እና ሞቱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሚያሳዝን ዜማ ይሰብካሉ፤ ሕዝቡም በስግደት ይቀበላል:: ካህናትም በየሰዓታቱ የተደረጉ ድርጊቶችን የሚገልጹ #የወንጌል ምንባባትን ያነባሉ:: ሁሉም በስግደት ይታጀባሉ፤ በየመካከሉ ካህናት የእጣን ማእጠንት እየወዘወዙ ያጥናሉ:: ይህም #ክርስቶስ መልካም መዓዛ ያለው ንጹሕ #መሥዋዕት ሆኖ መቅረቡን ያዘክራል:: የሕዝበ ክርስቲያኑ #ጸሎትና ተዘክሮም ከዕጣኑ ጋር አብሮ ያርጋል::

"አምነስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ..."

ካህናቱ እየመሩ ሕዝቡ እየተከተሉ 'አምንስቲቲ ' እያሉ በሚያሳዝን ዜማ ይጸልያሉ:: 'አቤቱ በመንግስትህ አስበን' ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቁጭ ተብሎ ራስ በነጠላ ውስጥ ይሸፈናል:: ጸሐይ ስትጨልም እና የክርስቶስ #ዘላለማዊ ንጉሥነት ሲገለጥ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ (ፈያታዊ ዘየማን) #የጸለየው ጸሎት ነው:: ከሁሉ ቀድሞ #ገነት ያስገባውን ጸሎቱን ጸሎታችን አድርገን እንጸልያለን::
የድል ቀን
ቤተ ክርስቲያን ሕማሙን ትካፈላለች እንጂ ጌታ በግድ የተሰቀለ ይመስል የሽንፈት #ኃዘን አታዝንም:: ይልቁንም በድካም: በሞት የተገለጠ ፍቅሩን እያሰብን ትእዛዙን እየጠበቅን ከእርሱ ጋር ለመኖር ቃል ኪዳናችን እናድሳለን:: የሚታዘነው ፍቅሩ ሊታየው ላልቻለ እና አሁንም ወደ #መድኃኒት ክርስቶስ መቅረብ ላልቻለ ነው::

በዕለቱ የሚነበቡ የነቢያት መጻሕፍት የድል ቀን መሆኑን ነው የሚነግሩን:: ዓርብ በስድስት ሰዓት የሚነበበው የኢሳይያስ ትንቢት "በዚያም ቀን፡— አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ። እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኗልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ። ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፡— እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ። ታላቅ ሥራ ሠርቷልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ። አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሏልና ደስ ይበልሽ ፤እልልም በዪ" ይላል:: (ኢሳ. 12:1-6)

በዐሥራ አንድ ሰዓትም "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ: የተመሰገነ እግዚአብሔርን እናመስግነው" የሚለው የእሥራኤላውያንን መዝሙር እንዘምራለን:: እሥራኤል ይህን #ምሥጋና ያመሰገኑት ባህር ከፍሎ እና ፈርኦንን አስጥሞ ወደ #ተስፋዋ ምድር ስላሻገራቸው ነው:: ቤተ ክርስቲያን የምትዘምረው ሞትን አጥፍቶ፣ ዲያብሎስን አሸንፎ፣ ሲኦልን በርብሮ ወደ #ገነት መንግሥተ ሰማያት ስላሻገረን ነው::

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
✞ ተፈጸመ✞

"ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)

ተፈፀመ የሚለው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነፍሱን ለወዳጆቹ ሲሰጥ ከመሞቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻ ቃል ነው። " ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)። ተፈፀመ በግሪክ "ቴትለስታ'ይ" (τελείωσε /Tetelestai) ማለት ሲሆን ትርጉሙም ወደ ፍፃሜ ማምጣት፣ መጨረሻ መድረሱን፣ ማከናወንን ፣ ማለቅን የሚያሳይ ነው። በእርግጥ አማኑኤል TETELESTAI/ ተፈፀመ ሲል ምኑ ይሆን የተፈፀመው? ብሎ የሚጠይቅ ህሊና ያስፈልገናል።

አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ አባቱ የሰጠውን ስራ ለመስራትና ለመፈፀም አምላክነቱን እንደመቀማት ሳይቆጥር በአባቱ በራሱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደ ዓለም እንደመጣ አስታውቆናል። ከመጣም በሇላ አባቱን የሚያከብር ስራን ሰርቷል "እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ" (ዮሐ 17: 4) እንዲል። ሊሰራ የመጣው የጠፋነውን የሰው ልጆች ሊፈልግና ሊያድን ዘንድ ነው ። በምድር ሲመላለስ የስራው ፍፃሜ የነበረውንም ነፍሱን ስለወዳጆቹ በመስጠት ፈፀመው ። ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል የሽንፈት ቃል አይደለም የድልና የአሸናፊነት እንጂ ወደ ዓለም የመጣሁበትን ስራ በሞት ጨረስኩ፣ ህዝቦቼን በሞት አዳንኩ ፣ የኃጢአትን ኃይል ድል ነሳሁ ፣ በሞቴ ሞትን ገደልኩ ፣ በመከራዬ ለመንግስቴ ህዝብን ማረኩኝ ሲል ተፈፀመ አለ እንጂ!

የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ተፈፀመ ብሎ ስለሞቱ ሲናገር "በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው" አለ።

የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስና ሐዋርያው የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ ስለዚህ ድንቅ ነገር በድርሳኑ ‹‹ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፡፡ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ፡፡ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፡፡ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፡፡ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፡፡ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፤›› እያለ ያወሳል።

በአማን ኢየሱስ ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል አስቀድሞ የገባው የአድናችኋለሁ ተስፋ አርብ ተፈጸመ ፣ የሴቲቱ ዘር የእባቡን ራስ እንደሚቀጠቅጥ የተነገረው ተስፋ ተፈጸመ ፣ የኩነኔና የእርግማን ዘመን በሞቱ ተፈጸመ (ገላ 4፥4) ፣ የእግዚአብሔፍ ፍቅር በመስቀል ሞት ፍጹም ሆኖ በመገለጥ ተፈጸመ/ ተከናወነ/ ፣ እኛ እንጸድቅ ዘንድ የኃጢአት ቅጣት በመስቀል ላይ ተፈጸመ ፣ ወደ ሰማይ እየወጣ በአምላካችን ፊት ይከሰን የነበረው የዲያቢሎስ የክስ መብት በክርስቶስ ሞት ተፈጸመ። ዛሬ ይከሰን ዘንድ ወደ ሰማይ ቢወጣ በጌታ በኢየሱስ እጆች ላይ የሚታዩ ችንካሮችና በልብሱ ላይ የሚታየው የደም ነጠብጣብ አፉን ይዘጋዋል። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ የነበረው ጥል በራሱ በጌታችን አስታራቂነት ለአንዴ ተፈጸመ። የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ማለቱ ለእንዴና ለዘላለም የእግዚአብሔርን ምህረት የምናስታውስበት ድምጽ ሆነ ። የበረታ ጌታ ሁላችንንም በቸርነቱ አዳነን እርሱ ተፈፀመ ሲል የኛ ደስታ ፣ የኛ መዳን ፣ የኛ ተስፋ ፣ የኛ መቤዠት በእግዚአብሔር ወልድ በተፈፀመልን የዘላለም ኪዳን ደም መፍሰስ በእውነት ተፈጸመ!!!

ለታረደው በግ ለእርሱ መጀመሪያ ከሌለው አባቱ ጋርና ቅዱስ፣ መልካምና ህይወት ሰጪ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ሁሉ ይገባዋል። አሁንና ለዘላለም ለትውልደ ትውልድ አሜን!

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ጌታችን በመስቀሉ ከ6-10 ሰዓት በመስቀልላይ ሳለ የተፈጸሙ 7ቱ
ተአምራቶች፤

1ኛ. ፀሐይ ጨለመች
2ኛ. ጨረቃ ደም ሆነች
3ኛ. ከዋክብት ብርሃናቸውን ነሱ
4ኛ. የቤተመቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ
5ኛ. ዐለቶች ተሰነጣጠቁ
6ኛ. መቃብራት ተከፈቱ
7ኛ. የሞቱት ተነሡ፤ ማቴ.27፤45-46

ጌታችን ከ6-9 ሰዓት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር
ቃላት

1ኛ.ኤሎሄኤሎሄ ኤልማስላማሰበቅታኒ ማቴ.27፤46
2ኛ. እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡
ሉቃ.23፤43
3ኛ.አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራእሰጣለሁ፡፡ ሉቃ.23፤46
4ኛ.አባት ሆይየሚያደርጉትን አየውቁምናይቅር በላቸው፤ሉቃ.2334
5ኛ. እናትህ እነኋት፤ እነሆ ልጅሽ፤ዮሐ.19፤26-27
6ኛ. ተጠማሁ፤ ዮሐ.19፤30
7ኛ. ተፈጸመ፤ ዮሐ.19፤30

13ቱ ሕማማተ መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)
ስብሐትለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱድንግል
ወለመስቀሉክቡር


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👆👆👆👆👆👆👆👇👇👇
2025/07/06 13:08:56
Back to Top
HTML Embed Code: