Telegram Web Link
"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"

2ኛ ቆሮ 5 : 4

@ortodoxtewahedo
35😢10👍7🕊4
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

#በሀገርም ውስጥ ሆነ ከሀገርም ውጭ ለምትኖሩ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ *እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና፤ በህይወትና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን አሜን።


*በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ በሰማያትም ላሉት እርቅን ሰላምን አደረገላቸው*
*( ቆላ፡ 1 ÷ 19 )*

*ለኃጢአት ሞትን ለፅድቅ እንድንኖር፡ እርሱ ራሱ በሥጋዉ ኃጢያታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፣ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ፣ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበረና፣ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችሃል*
(2ኛ ጴጥ 2÷24)

🌹 *እ* 🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ኳ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ለ*🌹
🌹 *ብ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሃ*🌹
🌹 *ት*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ሣ*🌹
🌹 *ኤ*🌹
🌹 *ዉ*🌹
🌹 *ዋዘማ*🌹
🌹 *በ*🌹
*ሠ*
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ም*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ደ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሳ*🌹
🌹 *ች*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ደ* 🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሰ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *በ*🌹
*ዓ*
🌹 *ሉ*🌹
🌹 *የ*🌹
🌹 *ሠ*🌹
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ም*🌹
*የ*
🌹 *ደ*🌹
🌹 *ስ*🌹
🌹 *ታ*🌹
🌹 *የ*🌹
🌹 *መ*🌹
🌹 *ተ*🌹
🌹 *ሳ*🌹
*ሰ*
🌹 *ብ*🌹
🌹 *ና*🌹
🌹 *የ* 🌹
🌹 *በ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ከ*🌹
🌹 *ት*🌹
🌹 *በ*🌹
*ዓ*
🌹 *ል*🌹
🌹 *ይ*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ች*🌹
*ሁ*
🌹 *ይ*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ል*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ሜ*🌹
🌹 *ን* 🌹
🌹፡፡🌹

*የመሰቀሉ ቃልለምጠፉት ሞኝነት ፣ ለእኛ ለምድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው ።
(1ኛ ቆሮ 1÷18)_*

*ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ፡ ( ገላ ፮ ÷14 )*

❤️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❤️
❤️ወለወላዲቱ ድንግል❤️
❤️ወለመስቀሉ ክቡር🕊

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍164🙏2👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል "

1ቆሮ 15÷20

#እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሠላምና ጤና አደረሳችሁ አደረሰን!

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
"እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ"

መዝ 77÷65

#መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ ።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍4
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ /OrtdooxTewahido/ አባላት በሙሉ::

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ አደረሰን አደረሳችሁ!!!



💐💐💐👉
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
ዓግአዞ ለአዳም
ሰላም እም
ይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም!!!!!💐💐💐

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
🙏4👍1👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#እዩና እመኑ ሰዎች

እዩና እመኑ ሰዎች
ድንጋዮ ተፈቃቀወላል
ኢየሱስ በእኩለ ሌሊት
በኃይሉ ሞትን ድል ነስቷል(2)

እልልታ ለዚህ ይገባል
ግርግርታ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ
ሲኦልም ተመሰቃቅሏል(2)

መላእክቱ ነጭ ለብሰው
ምስራቹን አበሰሩ
ተነስቷል ኢየሱስ ብለው
ለዓለም እንዲናገሩ(2)

እዩና እመኑ ሰዎች
ድንጋዮ ተፈነቃቅሏል
እየሱስ በእኩለለሊት
በሃይሉ ሞትን ድል ነስቷል(2)

እልልታ ለዚህ ይገባል
ግርግርታ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ
ሲኦልም ተመሰነቃቅሏል(2)

#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ
👇👇 👇👇
http://t.meortodoxtewahedo
👍81👏1
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤

በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጥተናል÷ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል ። ሙታን የነበርን ሕያዋን÷ ምድራውያን የነበርን ሰማያውያን÷ ሥጋውያን የነበርን መንፈሳውያን ሆነናል።


"ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፡ ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ? ፤ የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤" 1ኛ ቆሮ 15÷55



«እኛ አገራችን በሰማይ ነውና÷ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠ ባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋች ንን ይለውጣል። » ፊል ፫፥ ፳-፳፩።


ናፍቆታችን ሁሉ በትንሣኤ ያገኘነውን ጸጋ እውን ማድረግ ነው።
«ድንኳን የሚሆነው ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና። በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና÷ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድን ለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።» ይላል። ፪ኛቆሮ ፭፥፩-፪።



ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡-
«ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ÷ እድፈትም ለሌለበት÷ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ» ብሏል። ፩ኛጴጥ ፩÷፫።


ቅዱስ ጳውሎስም፡-
«በሚመጡ ዘመ ናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳ የን ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነ ሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊው ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።» ብሏል። ኤፌ፪÷፮-፯።



መልካም የትንሣኤ በዓል 😊

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
7👍4👏1🙏1
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
📍 ሕማማት 📍

📍በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ተጽፎ በ ቢኒያም ብርሃኑ የተተረከውን ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ለማግኘት
👇👇👇
1👍1
ወንድሜ ጓደኛህ ማነው?
እህቴ ጓደኛሽ ማናት?

እንደ አርማትያሱ ዮሴፍ ያለ ጓደኛ ካለህ/ሽ እንዳንተ/እንዳንቺ ያለ እድለኛ ሰው በዚህ ምድር የለም፤ ዮሴፍ ከሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ ጋር ለኔ ላንተም ለዓለምም ሁሉ የተቆረሰውን ስጋ የፈሰሰውንም ደም የክርስቶስን አካል ከመስቀል ላይ እንወስድ ዘንድ ንጉሥ ጲላጦስን እንለምነው ብሎ እንደሄደ እናስብ እስኪ፤
እንዲወስዱ ከተፈቀደላቸውም በኋላ ገንዘው ዮሴፍ ለራሱ ባዘጋጀው አዲስ መቃብር እንደቀበሩት ወንጌል ይነግረናል፤

እንደ ዮሴፍ እንደ ኒቆዲሞስ ያለ ጓደኛ ያለህ እንደሆነ ዘወትር የሚያወራህ ነገር ይህን ነው...

ና እንሂድ ፤ ስለኛ ሲል የተቆረሰውን ስጋ እንውሰድ ፡ ስለኛ ሲል የፈሰሰውን ደም እንውሰድ ፤ ለእርሱ በሚሆን በአዲስ ልቦና በንስሐ ባነጻነው አካላችን ሰውነታችንም በልተነው ጠጥተነው የእኛ አካል እናድርገው፤....

በሦስተኛው ዕለት የመቃብሩ ስፍራ በብርሃን እንደተመላ ና እኛም መጠን ምሳሌና ልክ በሌላው በዚህ መለኮታዊ ብርሃን እንሞላ...

ጓደኛ ካሉ እንዲህ የሚል ነው...
ጓደኝነታችንን ለድኅነት ያድርግልን🙏

እንዲህ ያሉትን በእውነት ያብዛልን😊


በብርሃኑ እንድንመላለስ ለዚህች ዕለት ያደረሰን አምላካችን ይክበር ይመስገን🙏

መልካም የትንሣኤ በዓል፤

በዐለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን
ሚያዚያ ፲፪ ፳፻፲፯ ዓ.ም
በዓለ ትንሣኤ ሌሊት ፮ ሰዓት

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
8👍3👏1
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
የ100 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️
የጥበብ አገርዋ ወዴት ነው? ማደረያዋስ ወዴት ነው? ቦታዋ ወዴት ነው? የጐዳናዋስ ፍለጋ በወዴት ተገኘ?

ባሕሩን ተሻግሮ በቀይ ወርቅ የገዛት ማነው? ከደመናትስ በላይወጥቶ ያወረዳት ማነው? መዋቲ ጐዳናዋን አያውቃትም፣ በሰውም ዘንድ የለችም።

ከሰው ሁሉ ተዘነጋች ከሰማይ አዕዋፍም ሁሉ ተሠወረች እርስዋን የገዙ አብ ከእግዚአብሔር ጋራ ተወዳጁ እርስዋን የሚጠሏት ሞትን ይወዳሉ፣ ከፀሐይ ይልቅ ታምራለች ከከዋክብትም አኗኗር እርስዋ ቀዳማዊት እንደ መሆንዋ ከብርሃን ጋራ ስትነጻጸርትገኛለች፣

በእርጅና ሳለች ሁሉን ታድሳለች በየትውልዱም በጻድቃን ሰውነት ትፋለሳለች።

ከከበረ ዕንቍ እርሷ ትበልጣለች ፣ ክብርም ሁሉ መጠንዋ አይደለም፣ ምክር ዕውቀት አላት፣ ጽንዕ አእምሮም አላት፣ ነገሥታቱም በእርስዋ ይነግሣሉ፣ ኃያላንም በእርስዋ እውነትን ይጽፋሉ፣

ደጋጎቹ በእርስዋ ይከብራሉ፣ መኳንንትም በእርስዋ ምድርን ይይዛሉ፣ የሚወዷትን ትወዳለች፣ ሕጓን የሚጠብቁትንም ትጠብቃለች፣ እርስዋንም የሚሹ ባለሟልነትን ያገኛሉ፣

በእውነት መንገዶች ትመላለሳለች ፣ በእውነት ፍለጋም ትመላለሳለች፣ ለሚያውቋት ሰዎች ብዕልን ትሰጣቸው ዘንድ መዝገባቸውንም ተድላን ትመላ ዘንድ፣

ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ያውቃታል ሁሉን የሚረዳ እርሱ ጐዳናዋን አሳመረ፣ እርሱ ለባለሟሉ ለያዕቆብ ለቅዱሱም ለእስራኤል ሰጠው፣ ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ታየች እንደ ሰውም ተመላለሰች ፣

እነሆ ቤትን ሠራች ሰባት አዕማድንም አቆመች የእርሷን እርድ አረደች፣ በማድጋዋም የእርሷን ወይን ጨመረች፣ የእርሷንም ማዕድ አዘጋጀች

አገልጋዮቿን ላከች፣ በረጅም ስብከት ሰነፍ የሆነ ሰው ወደ እኔ ይምጣ እያለች ፣ እውቀት ያነሳቸውንም ትጠራለች፣ የኔን ኅብስት ብሉ ፣ የእኔን ወይንም ጠጡ፣ ስንፍናንም ትታችሁ ኑሩ እያለች።

ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው፣ በሥጋው መሥዋዕትነት ያዳነን፣ በደሙም ፈሳሽነት የተወዳጀን ለመንግሥቱም የመረጠን ለዘለዓለሙ።

ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

እንኳን አደረሳችሁ 🙏


https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
11👍9🕊2🥰1👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ-
ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ-
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ-
አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ-
አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ-
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ-
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ-
ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👍11👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"አንድ ሰዉ በእግዚአብሔር ዕቅፍ ውስጥ እንዳለ ካወቀና እግዚአብሔር ሁሉን ያከናዉንልኛል ካለ ልቡ ፍጹም ይሆናል።"

+ማር ይስሐቅ+

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
👍17💯1
ብፁዕ አባታችን። ድንግል ማርያም ቤዛዊት አትባልም ብለው ድምዳሜ ሰጥተው ሲያስተምሩ ሰማሁ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይባልም ብለን ከምንደመድም እንዲህ ብንል አይሻልምን?

🥀እናታችን ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም እንላታለን። ክርስቶስን ቤዛችን ስንለው በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ስላዳነን ነው። ድንግል ማርያምን ቤዛዊት ስንላት ግን ቤዛኩሉ ክርስቶስን ስለወለደችልን ነው። ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን አድኗልና ነው። ምክንያተ ድኂን ስለሆነች ነው። ልጇ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ብሎ እንዳስተማረን እሱን ብርሃን እርሷን ደግሞ የብርሃን እናት እንላታለን። ልጇ አምላክ ስለሆነ እርሷ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። አምላክን የወለደች የአምላክ እናት ማለት ነው። ቤዛዊት ናት ስንል በጸጋ እንደሆነ ልብ እናድርግ። ምናልባት በባሕርይው ቤዛ ሆኖ ያዳነን ክርስቶስ ብቻ ነው ለማለት ፈልገው ከሆነ መልካም ነው።

🥀ንስጥሮስን ክርስቶስ ላይ ያለው የምንታዌ (Dualism) እይታ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ ከማለት አደረሰው። ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው የሆነ አምላክን አምላክ የሆነ ሰውን ነው እንጂ ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻን) አልወለደችም። ነገረ ክርስቶስን ከድንግል ማርያም በበለጠ የሚያውቀው ፍጡር የለም ። እርሷ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር ተንከራታለች። በመስቀልም ጊዜ ከጽንዐ ፍቅሯ የተነሳ ከመስቀሉ ሥር አልቅሳለች። ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ እንሰግድላታለን። ነገር ግን ለእርሷ የምናቀርበው ስግደት እና ምስጋና የአክብሮት ስግደትና ምስጋና ነው እንጂ እንደ አምላክ የአምልኮ ስግደት አይደለም።

🥀ድንግል ማርያም ዓለም ጣዖትን በማምለክ ጨለማ ውስጥ ሳለ ብርሃንን የወለደችልን እናታችን ናት። ድንግል ማርያም ዓለም ለሰይጣን በመገዛት ባርነት ውስጥ ሳለ በመስቀል ተሰቅሎ የእኛን ሞት ሞቶ ነጻነት የሚያጎናጽፍ ጌታን ወለደችልን። ዓለም ተርቦ ነበር። እሷ ግን የሕይወት እንጀራን ወለደችልን። ድንግል ማርያም የትሕትና እናት ናት። ምሥጢራዊም ናት።ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ተብሏል። እውነትን ይዛ ሳለ በሐሰተኞች ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሆነች።

የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ

ቤዛነት ምንድን ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን፣ መቤዠትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።

ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።

©በትረ ማርያም አበባው


ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍191
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍8
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
.#የእለቱ_መልእክት ⬇️


በአንድ ህንፃ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።ሚስትየው አዘውትራ በመስኮት መስታወት ውስጥ ወደ ጎረቤቶቿ ጊቢ የማየት ልምድ ነበራት።እናም አንድ ቀን አሻግራ ጎረቤቶቿ አጥበው ያሰጡትን ልብስ ስታይ ቆይታባሏን ጠራችውና "ውዴ ልብሶቹን አየሀቸው በደንብ አልነፁም ምናልባት ማጠብ አይችሉም ይሆናል" አለችው።በሌላ ቀንም እንዲሁ የጎረቤቶቿን ልብሶች ካየች በሗላ ባሏን ጠርታ"ዛሬም ሳያፀዱ ነው ያጠቡት ምናልባት ሳሙና የላቸውም ይሆናል አልያም ውሀ የላቸውም" አለችው።
በሌላ ቀንም እንዲሁ በመስታወት ውስጥ አሻግራ ስታይ አሁንም ልብሶቹ አልነፁም። አሁንም ባሏን ጠርታ "ዛሬም ልብሶቹ አልነፁም በእርግጠኛነት ሰዎቹ ሰነፎች ናቸው"አለችው።
አንድ ቀን
ማለዳ እንደ ለመደችው አሻግራ ስታይ ያየችውን ማመን አቃታት።ልብሶቹ ያለወትሯቸው በጣም ነፅተዋል ባሏን ጠራችውና
"ተመልከት ልብሶቹ ነፅተው!!!!!" አለችው።
ባሏም
"ውዴ.....በጠዋት ተነስቼ መስታወቱን ስላፀዳሁት እኮ ነው።እስካሁን የቆሸሸ የመሰለሽ ልብሶቹ ቆሽሸው ሳይሆን መስታወቱ ቆሽሾ ስለ ነበር ነው። አሁን በንፁህ መስታወት እውነታውን ተመልከቺ "አላት።
ምን ለማለት ፈልጌ ነው::ጥቃቅን ነገሮች እውነታን እንዳናይ ይጋርዱናል። የምናይበትን መነፅር ስናስተካክል ሁኔታዎችም አብረው ይስተካከላሉ።
እስቲ የሰውን ጉድፍ ከመጠቆማችን በፊት ጉድፉ አይናችን ላይ አለመኖሩን እርግጠኛ እንሁን!!

መልካም ቀን 💚💛❤️
35👍17🙏5
🔴 እንደተናገረ ተነሥቷል || መልካም ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እንደተናገረ ተነስቷል
             
Size:-35.5MB
Length:-38:20

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍62🙏2
"ሰዎች ማን እንደሆኑ ሲያሳዩህ በመጀመሪያው ቀን እመናቸው" ትላለች ማያ አንጀሎ

ይህንን ጽሑፍ ከትናንት በስቲያ ጽፌው ስሜታዊ ሆኜ እንዳይሆን በሚል ትንሽ ቆይቼ ልመልከተው ብዬ አሳደርኩት:: በቆይታ ሃሳቤ ሊቀየር ስላልቻለ እንደወረደ ለጥፌዋለሁ:: የምናገረው ነገርም እሳቸው ስለ ድንግል ማርያም ከተናገሩት አይከፋም:: ነገረ ሃይማኖታዊ መልስ ከበቂ በአደባባይ ተሰጥቶበታል:: ጉዳዩ ላይ ግን የምለውን ልበል::

ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር:: ጌታ በወንጌል "ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል:: በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደኃ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል:: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ማኅበር ለማጥራት ጊዜው አሁን ነው::
"ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን?" የሚል ኢያሱያዊ ጥያቄ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው::

ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን:: ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር::

ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን:: አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ ፣ በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ ፣ ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ::

ያሁኑ ጳጳስ ትንሽ የሚለዩት ምንም ፈሊጥ የሌለው ያልተለሳለሰ ምንፍቅና ስለሚናገሩ ብቻ ነው:: የሆነ ቪድዮ ላይ Faith Alone የሚለውን የሉተር ትምህርት የኦርቶዶክስ ቆብ ደፍተው ሲሰብኩ ትንሽ እንኩዋን አላፈሩም:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል:: በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው:: ቤተ ክርስቲያን መናፍቃንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም::

በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም:: ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም:: የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም:: እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም:: ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን:: "የበራላቸው" ለመባል የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም::

ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም:: ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን::

ርጉመ ይኩን ዘይረግመኪ
ወቡሩከ ይኩን ዘይባርከኪ
ነገራተ ክልዔ ኢይርሳዕ ልብኪ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ገሊላ ፳ኤል

ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም.

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
18👍14
ሰበር ሰበር ዜና
የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
*****
ሚያዚያ ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
*****
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
++++++++++++
መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን እመቤታችን
ቤዛ አይደለችም የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን እንደተመለከተ ገልጾ የማኀበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጸድቆ በተሰጠው ደንብ መሠረት በማኅበራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ተገቢውን ክትትልና አስፈላጊውን እርምት የመስጠት ሓላፊነት ያለበት በመሆኑ በደብዳቤው ለተጠቀሱ አምስት ነጥቦችን በማኅበሩ በኩል አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው በጥብቅ አሳስቧል።

መምሪያው በጻፈው ደብዳቤ ላይም በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍92
2025/07/13 17:09:27
Back to Top
HTML Embed Code: