Telegram Web Link
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ °+

=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ
እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ
ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ
አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን
እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::

<< ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >>

+ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ
ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ::
እነርሱ
ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው::
ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ
አደገ:: ገና
በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና)
ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም
አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ
ትምሕርት ይህ
ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2
ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ
ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና
እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ
መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ
ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ
ሲኖር
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ
ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ::
ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን
ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

+ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ
ራዕየ
ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ
ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው
ሳይታክት:
ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና
ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ
አንክሮ
ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና
ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

+ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና
የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ
ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል
የለም::
ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::

+ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት
ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ
መካከል "
አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ
የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ
10 ዓመት
አቁሞታል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው
ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት
ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ
አወገዛት::
እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ
አጋዘችው::

+በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/
ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::

+አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ
(ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ
ታጥቆ ሲጸልይ
ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ
ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ
ተመለከተ::

+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው::
ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ
ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም::
ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ"
ብሎ በጉባኤ
መካከል ጠየቀው::

+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ
ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ
አላወቃትም'
ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ
ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል::
እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ
መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ
መልክ
ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

+አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ
ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም
ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ
ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ
ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም
የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን
ምስጋናም
ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ
ወጥተዋል::

+ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን:
ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት
የተነሳ ታላቅ
ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::

ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኳር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -

+እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ
ይክፈለን::

+ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56
ዓመታት
በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት
ተፈጽመዋል::

+እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ
በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት
ቃል ኪዳን
ተቀብላለች::

❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር
ያድለን::

❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር)
2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው)
3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን
የተቀበለችበት)
4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ
5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ
7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ)
8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት)
9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ
3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6፡ ቅዱስ ላሊበላ
7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ

++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር
አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች
አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት
ሁሉም ያበራል::
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን
አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት
ይብራ:: +"+ (ማቴ.
5:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት
ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት
ይብራ::

+ (ማቴ.5:13-16)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >


#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
#ያንተን ስራ ያንተን ክብር ፣
ማን ይመራመር ።
እግዚአብሔር ምን ይበል እኛ ቅጥ ብናጣ ፣
በስምንተ ሺ በቀጠሮ መጣ።

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇
@Ortodoxtewahedo
የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።

ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።

"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር ! እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘ ነው።


@Ortodoxtewahedo
ሻሸመኔ እና መሃል አዲስ አበባ ላይ እርሳቸው በለኮሱት እሳት ምክንያት በጥይት ለተቆሉ ምዕመናንን ጸጸት ወይም ሀዘኔታ አላሳዩም።

ላፈረሱት ቅኖና ፣ ለተዳፈሩት ክብር ፣ለፈጸሙት የስርዓት ህጸጽ ይቅርታ አልጠየቁም። ይልቁንስ ዛሬም ድረስ ትክክል እንደሆኑ ይሰማችዋል።

ከክርስቶስ ይልቅ ዘር እና ቋንቋቸውን አሳይተው በሥጋ ዋሻ የተጠለሉት የሌላ ቤተ እምነት ተከታይ የሆኑ ጭምር እንዲከተሏቸው ፊት ለፊት ቆመዋል።

ወጥቼበታለው ካሉት ዘር በእምነታቸው ብቻ ካህናት አባቶች እና ምዕመናንን እየተለቀሙ ሲገደሉ አንድ ቀንም -ስለልጆቼ- ብለው ቃል አላወጡም።

እርሳቸው ስርዓት ማፍረስ ትክክል እንደሆነ ፣ አመጸነት አዋጭ እንደሆነ በገለጡት ቤተክርስቲያን ውስጥ ቀጣይ 3 ዓመት ምን እንደሚከሰት እንግዲህ እናያለን።

እንግዲህ ምን እንላለን ? መንፈስቅዱስ የዘገዬ ቢመስልም በእውነት ይፈርዳል!!!

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
አልተገለገላችሁም አገለገላችሁን እንጂ !

ብጹአን አባቶች ብጹዕ አቡነ አብርሃም እና ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ
በረከታችሁ ይደርብኝ ። ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለከፈላችሁት ተጋድሎ ውለታን የማርሳ የታመናችሁለት ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም ባላችሁ ኃላፊነት ብርታቱን ይስጣችሁ ።

በተለይ ብጹዕ አቡነ አብርሃም ለአስራ አንድ ዓመታት ደብራችንን በአስተዳዳሪነት ባገለገሉበት ወቅት የነበርዎትን መንፈሳዊነት እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት ያሳዩትን ትጋት እንኳን እኛ ምዕመናን ማንም የሚመሰክረው ሃቅ ነው ።

አንዳንድ ያልታደሉ ሰዎች ሹመትን ይገለገሉበታል የታደሉት ደግሞ በዓላማ እና በጽናት በቆራጥ መንፈሳዊነት ጭምር መንጋውን ያገለግሉበታል ። ለዚህ ምሳሌ ስለሆናችሁን እንደ ልጅነቴ ዝቅ ብዬ ባላመሰግናችሁ ያጸናችሁ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይቅር አይለኝም ።

በምትካችሁ ለተሾማችሁት ት ብጹዐን አባቶች መልካም የኃላፊነት ጊዜ ይሆንላችሁ ዘንድ ምኞታችንም ጸሎታችንም ነው ።

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
ለቅድስት ቤተክርስቲያን ላደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ ለከፈሉት መስዋዕት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁሌም ስትዘክረው ትኖራለች

አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ክብር ይገባቸዋል 🙏


#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
የቆያችኋባቸው መናብርት ከእናንተ በፊት በተራ የሚዳረሱና ማንም ጉዳይ የማይላቸው "የዙር ወንበሮች" ነበሩ። ከእናንተ በኋላ ያ ተቀይሯል። በገሐድም፣ በኅቡዕም፣ በመልከ ብዙ ግንባር (alliance) ከያዛችሁት ርቱዕ መንገድ እንድትናጠቡ የሚደረገውን ያልታዘብን አይደለንም። ያልተደረብንላችሁ እውነት ተደራቢ ስለማትሻ ነው። ባሰባችሁበትና ባሰብነው ልክ ተቋሙን ለመለወጥ እንዳልቻላችሁ እናውቃለን። ያንን የኃላፊነት ቀንበር ግን ብቻችሁን አትሸከሙትም። እንጋራችኋለን። በሦስት ዓመት የሠላሳ ዓመት ሰቆቃ የሚመዝን ድካም ውስጥ እንደ ነበራችሁ እንረዳለን። በዚህም "አባቶቻችን" ስንል አናፍርባችሁም። እናመሰግናለን። ቤተ ክርስቲያን ታመሰግናችኋለች።

ለቅድስት ቤተክርስቲያን ላደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ ለከፈሉት መስዋዕት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁሌም ስትዘክረው ትኖራለች


#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
የብልጽግናው ዋና ሴራ አስኪያጅ ባለሙሉ ሥልጣን ሆኖ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተቀምጧል፡፡ በመጨረሻም ሰዎቹ እንደፎከሩት፣ እንደቀሰቀሱት ቤተ ክርስቲያንን ከነሁለንተናዋ ተረክበዋል፡፡ ያ ሁሉ ግርግር፣ ያሁሉ እስር፣ ያ ሁሉ ቅስቀሳ ለዚህ ነበር፡፡

የኢትዮ ፎረሙ ዘገባ ወገባቸውን የመታው፣ ሴራቸውን ቀድሞ ያጋለጠባቸው ለዚህ ነበር፡፡ ያንን ሲያጣጥሉ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች አሁን እርማቸውን ያውጡ፡፡ ሁኔታዎችን ባለመረዳት ጭምር ቤተ ክርስቲያናቸውን አዘናግተዋታልና፡፡ አሳዛኞች፡፡

ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል ቀንደኛ የነበረውን ሰው፣ 'መክፈል ምን ይሠራልሃል፣ ገብተህ ሙሉውን ተረከብ እንጂ' በሚለው የብልጽግና ፈሊጥ ምክንያት ይኸው በቦታው ላይ አስቀምጠውታል፡፡ አሁን ከልካይም፣ ተቆጭም ገልማጭም፣ አምቢ ባይም የላቸውም፡፡ የፈለጉትን የሚሹትን የሚያደርጉበትን ሥልጣን ይዘዋል፡፡ ምክትላቸው ቄስ በላይ ገንዘብ ሠርቆ ታሠረባቸው እንጂ ያኔ ጀምረው ያቀዱት ይኸንን ሙሉ ወረራ ነበር፡፡

ቦታውን የፈለጉት ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ሊሠሩላት ሳይሆን ሊሠሩባት፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊያዋርዷት፣ ሊዘርፏት፣ ሊቀሟት ነው፡፡ ለብልጽግናም ሰጥ ለጥ ብላ እንድትገዛ ለማድረገ ነበር፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያ በገጣባ አህያ ተወራለች፡፡ ጫካ ሄዶ ሲኖዶስን ከከፈለ ሰው በላይ በክርስትናው ገጣባ አህያ ከየትም አይገኝም፡፡ ገጣ አህያ ደግሞ ጠባዩን ባለፈው አስረድቻለሁ፡፡ ክህደቱ፣ ሸፍጡ፣ ዘረኝነቱ ያመረቅዝበታል እንጂ የሚድንበት አንዳች እድል የለውም፡፡ በድለዳል፣ በጨርቅ ወዘተ ብታለባብሰው የሚሆን አይደለም፡፡

አሁን ያ ጸጉሩ መሸበቱን ለማየት ቆራጩን ሲያጣድፈው ለነበረው ሰው 'ሲወድቅ ልታየው ምን ያስቸኩልሃል እንዳለው' ቤተ ክርስቲያንም ጸጉሯን ተላጭታ፣ ሸበቶውን በግላጭ ፊታችን ወድቆ አየነው፡፡ መልኳ ተቀየረ፣ ያለ ተቆርቋሪ ቀረች፣ አሳልፋ ተሰጠች፣ ሲሞናዊነት ዐይኑን ጨፍኖ መላዋን ወረራት ማለት ነው፡፡

አሁን ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቃትን የተጠናከረ ስደት፣ ሊሆንባት የታቀደውን፣ ማንንም መጠየቅ አያስፈልገንም፣ ራሳችን ፊት ለፊታችን መከራዋን ሲገለጥ አየነው፡፡ ሳዊሮስ መከራ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሳዊሮስ አሳልፎ ሻጭ ነው፡፡ የምናውቅለት ታሪኩ ይኸ ነው፡፡

አሁን ያኔ 'ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር እርስዎ እኮ ቤቱን ትተውታል፣ እስከዛሬ እኮ እንዲህ አልነበረም' ያለውን ቃል ለመፈጸም፣ ቤተ ክርስቲያንን ለብልጽግና አሳልፎ የሚሰጥበትን ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡

በኦሮሚያ የሚደረግ የቤተ ክርስቲያን ስደት፣ በዐዲስ አበባ የሚደረግ የቤተ ክርስቲያን ወረራ ያለማንም ተቆጭና ገልማጭ ያስፈጽሙታል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ከላይ እስከ ታች፣ ከታጠቀ ኃይል እስከ ስለላ መረብ ተብትበው ተቆጣጥረውታል፡፡ 'ምንም አታመጡም እንዳሉት' አድርገውታል፡፡

አሁን ሁሉም በእጃቸው ነው፣ ዛሬ ደግሞ በጻዕር ላይ የነበረውን ጠቅላይ ቤተ ክህነትንም ፈጽመው ገድለውታል፡፡ ያንን ያደረጉት ደግሞ 'በመንፈስ ቅዱስ ይመራሉ' የተባሉት አባቶች ሲሆኑ በመንፈስ ቅዱስ መመራታቸውን ትተው እነ ከድር በጠቆሟቸው መሠረት የእነ ከድርን አባት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ (ሴራ) አስኪያጅ አድርገው መርጠዋል፡፡

በእኔ በኩል ቤተ ክርስቲያኔን የተቀማሁት ዛሬ ነው፣ ዛሬ የግመሉን ወገብ የሰበረው የመጨረሻው በትር ቤተ ክርስቲያን ላይ አርፎል አይቸዋለሁ፡፡ ምእመናን ሰሚ እንደሌላቸው፣ ጠላት ደግሞ የፈለገውን ነገር የማድረግ አቅሙን ያሳዩበት ነው፡፡ ሰማያዊቷን ቤተ ክርስቲያን ሊቀሙን ባይችሉም፣ የሰማያዊቷን ቤተ ክርስቲያን ማሳለጫ የሆነችውን የምድራዊቷን ቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ያላቸውን ኃይል ተጠቅመው ከምእመናን መቀማት የቻሉበት ቀን ተደረጎ ይወሰዳል፡፡

አሁን ውሉ ወደማይታወቅ፣ እጅግ በሚያሳስብ ጨለማ ተወርውረናል፣ መዋቅሩም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወድቋል፡፡

ዳሩ ግን ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ ይኖራት ይሆን? ለዚህስ የሚረባረቡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይኖሩ ይሆን? ምእመናን ሰፊ ትግል ይጠይቀናል፡፡ ይኸንን ችላ ብለን የተውን እንደሆነ፣ በመዋቅሯ ሽባነት ስደት፣ ፈተና፣ የመንጋ ነጠቃ መከራ ስትቀበል የቆየችው የነበረችው ቤተ ክርስቲያን፣ አሁን ደግሞ በቅሰጣ ባልሆነ ነገር ግን በሁለንተናዊ ነጠቃ ሙሉ በሙሉ ልናጣት የምንችልበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡

አሁን ድርሻው የምእመናን ነው፡፡ እለ ከድር በመረጡላቸው፣ ፖለቲከኞች እንደፎከሩት ባስቀመጡላቸው ሰው ሴራ አስኪያጅነት እየተመሩ ቀጣዩን ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያናቸውን በማፍረስ ይተባበራሉ? ሰውየውም ቃል እንደገቡት ቤተ ክርስቲያኗን ከነሁለንተናዋ ለብልጽግና ሲያስረክብ ዝም ብለው ያዩ ይሆን? የሚሉት ጥያቄዎች በቀጣይ የሚታዩ ይሆናሉ፡፡

ሰፊ ትግል፣ ሰፊ ርብርብ የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ወድቀናል፡፡ አሁን መተኛት እንኳን የሚቻለው በአንድ ዐይን ብቻ ይሆናል፡፡ አሁ ይሉኝታ ሊኖር አይገባም፣ አሁን የውጭና የውስጥ የሚባል ጠላት ቀርቷል፣ አሁን ያለው የውስጥ ጠላት ሆኗል፡፡ የውጩም ከነመሣሪያው ውስጥ ገብቶ ተጠቃሏል፡፡

ትግሉም ዋጋ የሚያስከፍል ዋጋም የሚያሰጥ ነው የሚሆነው፡፡

አንቺ ቤተ ክርስቲያን መጽናኛ ይስጥሽ!
2025/07/06 02:25:17
Back to Top
HTML Embed Code: