Telegram Web Link
#ፍትህ ለሊቁ

ይህ ዘመን የቤተ ክርስትያን የስደት ዘመን ነው ።
ያለ ጥፋት ያሰሩሀል የፈለጉትን የሚደረግበት ሊቁ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከታሰረ 13 ቀን ሆነው ።
ኦርቶዶክስ መሆን ወንጀል ነው ?????

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡

ቤተክርስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚአብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡

ሕያው እግዚአብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና
እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር
ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡

ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የመላእክት የምስጋናውን እንጀራ
ያበላን የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ እንቁ ነው።

በረከቱ ይደርብን!

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐፅማቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

@ortodoxtewahedo
#ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ መታመሙን ሰማን ለህክምና የሚሆነው ብር ያስፈልገዋል እና የተቻለንን እናድርግ በዝማሬው ብዙ አትርፈናል ፣ተጠቅመናል ጤናው ተመልሶ እንድናየው አባታችንን እንርዳው።
#እግዚአብሔር ይማርህ አባታችን!!!🙏❤️🙏
#አካውንቱን 1000481007287
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ/ወልደመስቀል
አባካችሁ ሼር አድርጉ ለሌሎችም ይድረስ

@ortodoxtewahedo
ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።
**

ብፁ
ዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣የደቡብ ኦሞና
አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ ሲያካሒዱት የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸውና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት የልዑካን ቡድን አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብሮሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገው
ላቸዋል።

በመቀጠልም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል መርሐ ግብር የሚካሔድ ሲሆን በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርተ ወንጌል፣ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተው የአቀባበል መርሐ ግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@ortodoxtewahedo
"አትጨነቁ ያሳያችሁኝ ፍቅር ጥንካሬ ሰጥቶኛል ብለዋል።" በኩረ መዘምራን ኪነጥበብ

ቤተክርስቲያን ያሳደገቻቸው በአለም ዘሪያ ያሉ ያልደወሉለት ፕሮፌሰሮች እና ዶክተሮች የሉም...የሆነው ሆኖ መቅረዝ ሆስፒታል በVIP አቀባበል ተቀብሎ በኩረ መዘምራን ሕክምናውን ጀምረዋል። ቤተክርስትያን ያፈራቻቸው ዶክተሮች እና ነርሶች ተረባርበው... "የሚቻል ቢሆን ከእድሜአችንም እየቀነስን በጨመርንልህ" ብለው እንደ ህመምተኛ ሳይሆን እንደ ንጉስ ተቀብለው አስተናግደውታል። አሉ የተባሉ ስፔሻሊስቶች አይተውታል ክትትል እያደረጉለት ነው።

ሁላችሁም መቅረዝ ሆስፒታል እንድትጎበኙት ተጋብዛችሁዋል። በዛውም ህሙማንን የመጎብኘት ልማድን እናካብት።

አብርሀም ሀይሉ

@ortodoxtewahedo
ሩስያ ሐገረ እግዚአብሔር
"በሩስያ ዮሽካር ግዛት የሚገኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም
በረከቱ ይደርብን ::

@ortodoxtewahedo
2024/05/22 00:04:22
Back to Top
HTML Embed Code: