Telegram Web Link
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ

ከ40 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን አሰርተው ሀገረ ስብከታቸው በዘንድሮ ቀይረዋል በረከትዎ ትድረሰን ተጉህ እረኛ ብፁዕ አባታችን።

@ortodoxtewahedo
† ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል †

የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል የተተከለው በ1905 ዓ.ም በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ነው። የመጀመሪያውን መቃኞ ያሰሩት ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ጽላቱም በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረና ከዚያ መጥቶም በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተቀመጠ ነበር።

ታድያ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ያሰሩት የመጀመርያው መቃኞ ለአገልግሎት ምቹ ስላልነበር ሁለተኛ መቃኞ ድጋሚ ተሰርቶ ታቦቱ እንዲገባ ተደርጓል።

ንግሥት ዘውዲቱ በግንቦት 28 በ 1914 ዓ.ም የአማኑኤል በዓል ተገኝተው ሲያስቀድሱ ምርጊቱ ተደርምሶ ሲወድቅ በማየታቸው ሦስተኛ መቃኞ እንዲሰራ አዘዙ። የደብሩ አስተዳዳሪ በጊዜው የተክለ ሃይማኖትን ቤተ ክርስትያንም አንድ ላይ ያስተዳድሩ የነበረ በመሆኑ ንግሥቲቷ የቤተ መንግስታቸውን አጣኝ የመጀመርያው አስተዳዳሪ ሆነው ደብሩን እንዲጠብቁ አደረጉ። አለቃው ሦስተኛውን መቃኞ አሰርተው ታቦቱ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ገባ።

በ1920 ህዝቡ እየበዛ በመምጣቱ አገልግሎቱ እንዲሰፋ ስላስፈለገ በንግሥት ዘውዲቱ አማካኝነት አዲስ ሕንጻ ቤተ መቅደስ ግንባታ ተጀመረ። በ1931 ታህሳስ 28 ቀን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ታቦቱ ወደ መንበሩ ገብቷል። ንግሥት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ ያረፉ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ደግሞ ክብ ቅርጽ ነበረው።

አሁን ያለው ቤተ ክርስቲያን በጥር 28 ቀን 1969 ዓ.ም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን የወቅቱ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩት በሊቀ ሊቃውንት ንቡረ ዕድ አባ ተፈራ መልሴ አስተባባሪነት በምእመናን ርብርብና በቅዱስ አማኑኤል አከናዋኝነት ግንቦት 28 ቀን 1978 ዓ.ም ተጠናቆ ታቦተ ህጉ ወደ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል።

@ortodoxtewahedo
"የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን" የተባለው ስብሰባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማግለሉ ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ አስታውቋል!

@ortodoxtewahedo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስሙት ብዙ ታተርፉበታላቹ እጮኝነት ላይ ላላቹ እና ገና
ለምትይዙ በእውነት ቃለህይወት ያሰማልን አባታችን ።

@ortodoxtewahedo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ሰማይና ምድር የረጋበት ቀን

#እርገት

እርገት፦ በአካል፣በመንፈስ እና በነፍስ ወደላይ መውጣት ነው
እርገት፦የነፃነት እና የድል ምልክት ነው
እርገት፦ዘለዓለማዊነት ነው
እርገት፦ናፍቆት ነው
እርገት፦ ተስፋ ነው
እርገት፦ መለኮታዊ ተአምር ነው
እርገት፦ ምስጢር ነው
እርገት፦ ክብር ነው
እርገት፦ የኛ ማረግ ማረጋገጫ ነው
እርገት፦የመንፈሳዊነት እጣነ ሞገር ነው

ሰውየው "ዛሬ የሚከበረው በዓል ትርጓሜው ምንድን ነው" ይለዋል ሰውየው መልሶ ይህንን አታውቅም? ዛሬማ "ሰማይና ምድር የተረጋጋበት ቀን" ነዋ አለው ይባላል ብዙ ጊዜ የኛን ያለማወቅ ወደሌሎቹ ጭምር የምናስተላልፈው በልበ ሙሉነት እና በድፍረት ጭምር ነው"ይህንን አታውቅም?" ማለቱ ሲገርም ያስተላለፈው የተሳሳተ መልእክት ደግሞ ሌላ ትግርምት ይፈጥራል።

በሆነ አጋጣሚ ዐውደ ምሕረቱ ተሰጥቶን ማይክ ከጨበጥን በኋላ ከዐውደ ምሕረቱ ሥር የተቀመጡት ሁሉ ምንም የማያውቁ እየመሰለን የእግዚአብሔር ሳይሆን የግል ስሜታችንን የምንገልጽባቸው አጋጣሚዎች እጅግ ብዙ ናቸው ይህ አጋጣሚ ታላላቅ ስህተቶች የሚፈጽሙበት አጋጣሚ ነውና ለሰሚ ጆሮዎች መጠንቀቅ ይገባል ይኸው ዛሬ ድረስ የእርገት በዓል ሲከበር "ሰማይና ምድር የረጋበት" የሚለው የነ......ትምህርት በልበ ቀሊላን ፀርፆ ግራ እያጋባን ይገኛል።


ሉቃስ 24፦
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁰ እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
⁵¹ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
⁵² እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
⁵³ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።

@ortodoxtewahedo
Audio
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ

Size:-38.8MB
Length:-1:51:17

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
የዕርገት መንገድ
        
Size:-54MB
Length:-2:34:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
.
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
========================

ሰኔ 7/2016 ዓ.ም (የጋ/አ/ዞ/ሀ/ስ አርባምንጭ )

በጋሞ እና አካባቢው ዞኖች አህጉረ ስብከት በአርባ ምንጭ ከተማ በደብረ መ/መድኃኔዓለም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ 7-9/2016 ዓ.ም የሚካሄደውን ታላቅ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ተጋባዥ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ዘማሪያን በዛሬው እለት ወደ አርባ ምንጭ ሲገቡ በጋሞ አባቶች እና በርካታ ቁጥር ባላቸው ማህበረ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

@ortodoxtewahedo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመምህር ተስፈየ አበራ ትምህርቶች የምትቀበሉ እና ትክክል አይደለም የምትሉ በኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትና በመረጃ ሀሳብ ስጡ ????

@ortodoxtewahedo
2024/06/16 16:08:21
Back to Top
HTML Embed Code: