Telegram Web Link
Audio
የዕርገት መንገድ
        
Size:-54MB
Length:-2:34:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
.
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
========================

ሰኔ 7/2016 ዓ.ም (የጋ/አ/ዞ/ሀ/ስ አርባምንጭ )

በጋሞ እና አካባቢው ዞኖች አህጉረ ስብከት በአርባ ምንጭ ከተማ በደብረ መ/መድኃኔዓለም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ 7-9/2016 ዓ.ም የሚካሄደውን ታላቅ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ተጋባዥ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ዘማሪያን በዛሬው እለት ወደ አርባ ምንጭ ሲገቡ በጋሞ አባቶች እና በርካታ ቁጥር ባላቸው ማህበረ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

@ortodoxtewahedo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመምህር ተስፈየ አበራ ትምህርቶች የምትቀበሉ እና ትክክል አይደለም የምትሉ በኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትና በመረጃ ሀሳብ ስጡ ????

@ortodoxtewahedo
“በጋሞ የሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለመርዳት፣ ባህሉን ለማጠናከር የምታደገርጉት ሥራ ሁሉ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ለሰው በሚገባው በራሱ ቋንቋ ማስተማር የሚያስደስት ነው፡፡”
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማትና የስብከተ ወንጌል አስተባባሪ የተመሠረተበትን 24ኛ ዓመት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ አከበረ፡፡
ዘጋቢ መ/ር ጌታቸው በቀለ
(#EOTCTV ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም )
+++++++++++++++++++++++++++++++++++ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር አገልግሎቱን እያካሄደ የሚገኘው የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማትና የስብከተ ወንጌል ማስተበባበሪያ የተመሠረበት ዋና ዓላማ በጋሞ የሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመርዳት፣ ስብከተ ወንጌል በጋሞኛ ቋንቋ ለማስፋፋት በመሆኑ፤ የተመሠረተበትን ፳፬ ኛ ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ አክብሯል፡፡
በዕለቱም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባስተላለፉት መልእክት “የ፳፬ኛ ዓመት በዓላችሁን ለማክበር በመብቃታችሁ እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡ ቅዱስነታቸው አያይዘውም “በጋሞ የሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለመርዳት፣ ባህሉን ለማጠናከር የምታደገርጉት ሥራ ሁሉ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ለሰው በሚገባው በራሱ ቋንቋ ማስተማር የሚያስደስት ነው፡፡ የጀመራችሁትን የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን መርዳት፣ በጋሞኛ ቋንቋ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት የምታደርጉትን በጎ ሥራችሁን ቀጥሉበት፤ እግዚአብሔር የሚወደው ይህን ሥራ ነው፡፡ እናንተ አሁን የምትሠሩትን ሥራ ልጆቻችሁም የእናንተን ፈለግ ተከትለው በበጎ ነገር እንዲሠማሩ አስተምሯቸው፡፡” በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላለውፈዋል፡፡
የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማትና የስብከተ ወንጌል አስተባባሪ ኮሚቴ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሟላ፣ የአገልጋዮች ደመወዝ በወቅቱ እንዲከፈል፣ ፈዋሽ የጠበል ቦታዎች ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ፣ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃቸውን በጠበቀ በዘመናዊ ሕንጻ እንዲገነቡ እያደረገ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማትና የስብከተ ወንጌል አስተባባሪ ኮሚቴ በስብከተ ወንጌልም ምእመናን በሚገባቸው በጋሞኛ ቋንቋ ወንጌል በማስተማር፣ መዝሙር በማስጠናት ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በቋንቋው የሚያስተምሩ መምህራን ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲሁም በየሰንበት ትምህርት ቤቶች የተማሩ ደቀመዛሙርት በየጉባኤያቱ እና ማኅበራት ጋር እየተገኙ እንዲያስተምሩ እየተደረገ መሆኑን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
በገዳማትና አድባራት በሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች ጋሞኛ ክፍል በአዲሱ የቤተክርስቲያን ሥርዐተ ትምህርት መሠረት ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ከአንድ ሺህ አንድ መቶ በላይ በተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ቤታቸው የፈረሰባቸውን ጉባኤያትና አባላት መልሶ ከማቋቋም አንጻር በዚህ ዓመት እንጦጦ እና አካባቢው አንድ፣ አየር ጤና እና ጀሞ ሦስት፣ ሸገር ከተሞች ሁለት ጉባኤያት መልሰው እንዲቋቋሙ ማድረጋቸውን የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል፡፡

@ortodoxtewahedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🔹 ✥● ከሚከተሉት ውስጥ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ በየትኛው ትጠራ ነበር?? ✥●
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
2024/06/17 03:10:02
Back to Top
HTML Embed Code: