Telegram Web Link
​​​​ 🍁የባል አይነቶች🍁
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉



3⃣💐 ባሪያ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉

መኖር የሚሻው ራሱን እንደ ንጉስ፣ ሚስቱን እንደ ባሪያ እየቆጠረ ነው። ሚስቱ እንደ ጥንት
ባህል ድንበር ያለፈ አክብሮት እንድትሰጠው ይፈልጋል። በመጀመሪያ ስሙ መጠራት
አጥብቆ ይጠላል።


4⃣💐የጋራ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉

ለሁሉም ሴቶች ባል ነው😁። ከህጋዊ ሚስቱ ይበልጥ ለቅምጦቹ ፍቅር እና እንክብካቤ ይቸራል። ለሌሎች ሴቶች ገንዘብ መበተን ያረካዋል። ብዙ የሴት ጓደኞችን ያፈራል።
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
ይቀጥላል 🥀VOTE🥀 አድርጉ
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
@pclovee

@jaden_36 በሚለው Username ብቻ ነው የሚያገኙት ሌሎች በእኛ ስም የተከፈቱ ቻናሎች የእኛ ስላልሆኑ እኛን አይወክሉም‼️‼️‼️‼️‼️‼️
.........?
ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች ጥሩ ጓደኝነትም ይሁን ትዳር፤ የስራ ግንኙነትም ይሁን የፍቅር፤ ከሰዎች ጋር የምንመሰርታቸው ግንኙነቶች በህይወታችን በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። ነገር ግን ብዙ ፈተናዎችንም ይዘው ይመጣሉ።

በእነዚህ ግንኙነቶች ውስጥ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ ጥቂት ነጥቦችን ይዘን ቀርበናል።

1. ግጭት ሲፈጠር አይደናገጡ
ሁሌም ቢሆን ግጭትን የምናስተናግድበት መንገድ ወሳኝነት አለው። የተለያዩ ሃሳቦች እና ፍላጎቶች ሁሌም ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ።

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት የሚፈጠር ግጭት ግን ሁሌም ቢሆን መጥፎ አይደለም። ጓደኝነት የሚጠነክረውና የሚያድገው በልዩነታችን ስለሆነ፤ ግጭት እንደውም ለግንኙነት መሰረት ሊሆን ይችላል።

ግጭትን በቀላሉ ለመፍታት በመጀመሪያ ሌላኛው ሰው እየተሰማው ያለውን ነገር ለመረዳት መሞከርና ሃዘኔታ ማሳየት፤ እንዲሁም እኛ ጥፋተኛ ከሆንን ሃላፊነት ለመውሰድ መዘጋጀት የመጀመሪያው ነገር መሆን አለበት ይላሉ ታዋቂዋ የጥንዶች ህክምና ባለሙያ ኢስተር ፔረል።

''ሁሌም ቢሆን ሌላኛው ሰው ምን አጠፋ ሳይሆን እኔ ምን አጠፋው ብለን መጠየቅ አለብን። ምን ላስተካክል ብለን ማሰብ አለብን''። 2. ራስን መሆን
ብዙ ጊዜ ቸኩለን ወደ አንድ ግንኙነት ውስጥ እንገባና በግንኙነቱ ሂደት ውስጥ ራሳችንን ያጣን ሊመስለን ይችላል። ሁሌም ቢሆን ለራሳችን ጊዜ መስጠትና ለሌላኛውም ሰው ቢሆን የብቸኝነት ጊዜ መስጠት ጠቃሚ ነው።

የሚወዱትንና የሚያዝናናዎትን ነገር በተቻለ መጠን ላለመተው ይሞክሩ።

3. አብሮ መዝናናት
በማንኛውም አጋጣሚ አብረው የሚያሳልፉትን ጊዜ የማይረሳ ለማድረግ ይሞክሩ።

አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛትና የተለያዩ ዝግጅቶችን ለመታደም ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ግንኙነቱን ወደ ተሻለ ቦታ ይወስደዋል።

ቢቻል የሚገናኙበትን ጊዜ ቀደም ብሎ መወሰንና ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ምናልባት አብረውት ጊዜ ማሳለፍ የሚፈልጉት ሰው በስራም ይሁን በሌላ ነገር የሚጠመዱ ከሆነ፤ በሳምንት ወይንም በወር አንድ ጊዜ እራት መብላት ወይም ከከተማ ወጣ ብሎ መዝናናት ጠቃሚ ነው።

4. በግልጽ መነጋገር
እስቲ ለማስታወስ ይሞክሩ፤ በጣም ትንሽ በሚባል አለመግባባት ከፍተኛ ጥል አጋጥሞዎት ያውቃል?

ሃሳብን ግልጽ እና ቀላል በሆነ መልኩ መግለጽ አለመግባባትንና አላስፈላጊ ግጭቶችን ይቀንሳል። ሁሌም ቢሆን መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ለሌኛው ሰው የተለየ መልእክት የሚሰጥ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።


5. ሁሉንም ነገር ከአንድ ሰው አለመጠበቅ
ይሄ ነጥብ በተለይ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ላሉ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ ነው። የፍቅር ጓደናችን ወይም የትዳር አጋራችን ላይ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ከፍተኛ ጫና ልናሳድር እንችላለን። ሁሌም ቢሆን አጋራችን አፍቃሪ፤ ስሜታችንን የሚረዱ፤ በራሳቸው ሚተማመኑ፤ የገንዘብ ችግር የሌለባቸው፤ ተጫዋች ወ.ዘ.ተ እንዲሆኑ እንጠብቃለን።

ከእነዚህ መካከል በአንዱ ሲሳሳቱ ግን፤ በሙሉ ግንኙነቱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ይህ ተገቢ አይደለም፤ ምከንያቱም አንድ ሰው ሁሉንም ነገር በትክክል ሊሰራ አይችልም። ለአንዳንድ ፍላጎቶቻችን ሌሎች ሰዎችንም ማካተት ይጠቅማል።

6. ጥሩ ጊዜያትን መለስ እያሉ ማስታወስ
ህይወት ሁሌም ቀላል አይደለም። ስለዚህ በየትኛውም ጊዜ ያሳለፉትን ጥሩ ትዝታ መለስ እያሉ ማስታወስና መነጋገር ከባዱን ጊዜ ለመርሳት ይጠቅማል።

አንድ ሰው ትዳር ሲመሰርት ወይም ልጅ ሲወልድ በተቻለ መጠን ከጓደኛና ቤተሰብ ጋር ሰብሰብ ብሎ ደስታን መግለጽ የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ።

7. እርዳታ ለመጠየቅ አለመፍራት
ከአንድ ሰው ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን፤ የሚሰማንን ነገር ለመናገርና እርዳታቸውን ለመጠየቅ መፍራት የለብንም።

የሚያስፈራንን ነገር ለመናገር ድፍረት ሊኖረን ይገባል። 8. ደግነትና አድናቆትን ለሌሎች ማሳየት

ስለ አንድ ሰው እያሰቡ ከሆነ፤ በስልክም ይሁን በአጭር የጽሁፍ መልእክት ስሜትዎን ይግለጹ። ባልደረባዎ ወይም ጓደኛዎ ከባድ ቀጠሮ ካለባቸው ለማስታወስ ይሞክሩ። እንዴት እንዳለፈም መጠየቅ የመተሳሰብና የእምነት ስሜትን ይፈጥራል።

በሰሩት ስራ ውጤታማ ሲሆኑም መደሰታችንን መግለጽና አድናቆትን መቸር ያስፈልጋል።

9. ትክክለኛውን ሰው ብቻ ለማግኘት አይሞክሩ
አንድ ሰው ከትክክለኛው ሰው ጋር ግንኙነት መመስረቱን በምን ማወቅ ይችላል? በመጀመሪያ ግንኙነቱ መመስረት አለበት።

ማስታወስ ያለብን ትክክለኛው የሚባል ለአንድ ሰው የሚስማማ ግለሰብ ማግነት እጅግ ከባድ ነው። ስለዚህ የመሰረትነውን ግንኙነት ለማሳመር መሞከርና ጥሩ ጥሩውን ለመመልከት መሞከር አስፈላጊ ነው።

አንድ ሰው ጥሩ የሚሆነው ትክክለኛ ስለሆነ ወይም የሚሳሳተው ትክክለኛ ስላልሆነ ሳይሆን፤ ሰው በመሆኑ ነው።

ስለዚህ አንድ ሰው ሲሳሳት መራቅ፤ ጥሩ ሲሆን ደግሞ መቅረብ ተገቢ አይደለም።


@pclovee
@pclovee
​​ 🌺የባል አይነቶች🌺
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉

ከባለፈውየቀጠለ

5⃣💐ጥገኛ ተውሳክ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
ሰነፍ ነው። ሚስቱን የሚያፈቅረው ለገንዘብ ሲል ነው። የሚስቱን ብር ኢንቨስት የሚያደርገው ለሌሎች ሴቶች ነው። ሐሳብ የማመንጨት ችሎታው ተሰልቧል። በቤት
ውስጥ ያሉ የጋራ ኋላፊነቶችን በሙሉ ጠቅልሎ ያስረከበው ለሚስቱ ነው። እርሷን ማገዝ
የሚባል አይታሰብም። ተቀላቢ ወንበዴ ነው።

💐6⃣ህጻን ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
ኃላፊነት አይሰማውም። የጨቅላነት ባህሪ ያጠቃዋል። ቤተሰቦቹን አሊያም ዘመዶቹን
ሳያማክር በራሱ ውሳኔ መስጠት አይችልም። ልፍስፍስ ነው። ብዙውን ጊዜ ውሳኔ
ለመውሰድ የሚያማክረው ከሚስቱ ቤተሰቦች ይልቅ ቤተሰቦቹን ነው። ግና አላስፈላጊ
ችግር ሲፈጠር ሁሌም ጣቱን የሚቀስረው ወደ ሚስቱ ቤተሰቦች ነው።

💐7⃣እንግዳ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
ውሎው ሁሌም ከቤት ውጭ ነው። ወደ ቤት ሲመጣም እንደ እንግዳ ነው። ለቤተሰቦቹ
አስፈላጊውን ቁሳቁስ ያቀርባል። ግና ለነርሱ የሚሰጠው ሽራፊ ጊዜ የለውም። ቀኑን ሙሉ
ከተማውን ሰልሎ ለአዳር ወደ ጫካ እንደሚገባ ሽምቅ ተዋጊ ነው።

💐8⃣ተንከባካቢ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸🌸»̶̥✽̶┉┉
አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ነው። ለቤተሰቡ ጊዜ ይሰጣል። ከቁሳዊ አቅርቦት ባሻገር ስሜታዊ
ፍላጎቶችን ያሟላል። ቤቱን በመንፈሳዊ ስርዓት ይመራል። ኃላፊነቱን በጥንቃቄ ይወጣል።
ለሚስቱ ደጋፊ እና አጋርም ጭምር ነው።

🎴የባል አይነቶች በዚሁ ተጠናቀቀ አንተ ከየትኛው ነህ ወይም የአንቺ ባል ከየትኛው ነው @jaden_36 ላይ አድርሱኝ መልካም ውሎ💦
እነዚህ ሁሉ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሌላ ነገር ሳይሆኑ ሁሉም የጋብቻ ቀለበቶች ናቸው ፡፡እነዚ የጋብቻ ቀለበቶች በአንድ የቀለበት መሸጫ ሊሸጡ የተቀመጡ ቀለበቶች አይደሉም ! እነዚ ሁሉ ቀለበቶች የግለሰብ ንብረቶችም አይደሉም ! እነዚህ ነፍ ቀለበቶች በጣም በሚገርም ሁኔታ ከእ.አ.አ ከ1939-1945 በተደረገው በሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያት ከሟቾች ግለሰቦች ወታደሮች ጣት ላይ የተሰበሰቡ የጋብቻ ቀለበቶች ናቸው 🙁

አስቡት ለ6ት አመታት በተካሄደው 2ኛው የአለም ጦርነት ምክንያት በጊዜው በሰአቱ የስንቱ ቤት ትዳር ሊናጋ እና ሊፈርስ እንደቻለ 🤷‍♂ አሁንም ቢሆን ወደፊትም ቢሆን ከጦርነት ምንም አይገኝም !!

መልካም ቀን
🌹😘ይጠቅማልና 😘ለእህቶቻችን አድርሱልን ወደ በዋላ የወንዶችን እንመለስበታለን!!

💋ሴት ሆይ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?!"
:
➊.ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
:
➋.ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
:
➌.ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው
:
➍.ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና
ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ
:
➎.ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ ሄደሽም ባልሽን በቤተሰቦችሽ ፊት የምታሚ ከሆነ
:
➏.ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ
የማትንከባከቢ ከሆንሽ
:
➐.በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ጌታን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
:
➑.ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ
:
ከእንግዲህ እነዚህን ነገሮች ገታ አድርጊ ባልሽ ላንቺ
😘መታያሽ
😘መከታሽ
የሱ ድምቀት የሱ ግርማ ሞገስ ላንቺ ክብር ነውና በቻልሺው መጠን ባልሽን ከአጠገቡ ሆነሽ አበረታቺው!!

@pclovee
@pclovee
@pclovee
​​​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄
          
:¨·.·¨:
ወይ ሴቶች🌺
┈┈••◉❖◉●••┈

👨‍❤️‍👨ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ
አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡
መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ
መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡
ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ
ስብሰባ ለመታደም ወደዛ ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደሞ
ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው
ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው
ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት
መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ
ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት
ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ
አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡
ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ
በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ
አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም
ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት
ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ
ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፁፍ ተፅፎበታል፡፡

💓 ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡ ዝምታ አያታርቅም ዝምታ መቼም መፍትሔ ሁኖ አያውቅም፡፡

​​​​​​@pclovee
@pclovee
ስለሷ በደንብ ለማወቅ የሚረዱ ጥያቄዎች

1. “የምትወጂው መጽሐፍ ምንድነው እና ለምን?”

2. “ቤትሽ ቢቃጠል ቀድመሽ ምን ይዘሽ ትወጫለሽ?”

3. “የምትወጂው የልጅነት መጫወቻ ምን ነበር?”

4. “በጣም መጥፎ ሥራሽ ምንድነው?”

5. “ስምሽ ምን ማለት ነው?”

6. “ትርፍ ጊዜሽን እንዴት ታጠፊያለሽ ፣ እና የት ትሄጃለሽ?”

7. “የትኞቹን አርአያዎች በጣም ታከብሪዋቸዋለሽ?”

8. “የት ነው የተወለድሽው?”

9. “ከገበያ ዝርዝርሽ ውስጥ ለየት ያለ አንድ ነገር ምንድነው?”

10. “ችግር ፈጣሪ ነሽ?”

11. “የቅርብ ጓደኛህ ማን ነው እና ከእሱ / ከሷ ምን ትወጂያለሽ?”

12. “ቅጽል ስም አለሽ?”

13. "ለመጓዝ የምትፈለልጊበት አንድ ቦታ ምንድነው?"

14. “ምን ያስቆጣሻል? በተለይ ከሌሎች ሰዎች የሚያናድድሽ ነገር! ”

15. “ሞት የአንቺ ትልቁ ፍርሃት ነው ወይስ ሌላ ነገር አለ?”

16. “ለአንድ ቀን ወንድ ብትሆኚ መጀመሪያ የምታደርጊው ነገር ምንድነው?”

17. “ጠንካራ ሰው እንድትሆን ያደረገሽ አንድ ነገር ምንድነው?”

18. “የበለጠ ለማወቅ የምትወጂው ነገር ምንድነው?”

19. “በጣም የሚስማማሽ ቦታ የት ነው?”

20. “ምንጊዜም ማድረግ እየፈለግሽ አድርገሽ የማታውቂው ነገር ምንድነው?”

21. “ለማምለጥ የምትፈልጊበት ቦታ የት ነው?”

22. "በጣም ደስ ያለሽ ቀን መቼ ነው? ለምን?"

23. “ስለራስሽ አንድ ነገር መለወጥ ብችዪ ምን ሊሆን ይችላል?”

24. “ትልቁ ፍርሃሽ ምንድነው?”

25. “ወጣትነት ላንቺ ምንድነው?”

26. “በህይወትሽ ያደረግሽው የእብደት ተግባር ምንድነው?”

27. “ምስጋናዎችን በቀላሉ ትቀበያለሽ? ወይስ ምስጋናዎችን ትጠያለሽ? ”

28. “ማንኛውም እንስሳ መሆን ብትችዪ ምን እንስሳ ትሆኛለሽ?”

29. “ኮከብ ቆጠራዎችን ምን ያህል በቁም ነገር ትወስጃለሽ?”

30. “የሚቆጭሽ ነገር አለ? ትልቁ ምንድነው? ”

T.me/pclovee
😘ዛሬ ላይ የተለያዮ ሰዎች ናፍቆታቸው በተለያዮ መንገዶች ገልፀው ይሆናል
     እኔም ጋር አንድ የተደበቀ ስሜት አለ ……… ናፍቆት
     እኔም አንድ ሰው ናፍቆኛል መች ላግኘው? እንዴት ላግኘው? ከየት ላግኘው ብቻ ናፍቆኛል ናፍቆት ከውሀ ጥማት ከምግብ ረሀብ በላይ ስቃይ አለው። ሁላችንም ሰው ናፍቆናል ብዬ አምናለሁ አሁንም ላይ በናፍቆት ላይ ያለን ሰዎች አለን የራቀን ሰው እንናፍቃለን የማይመለስን ሰው እንናፍቃለን ዳግም እንደማንገናኝ እያወቅን እንናፍቃለን።
………በተቃራኒው አብረውን በአካል እያሉም እንናፍቃለን። ርቀው የሄዱ ሰዎችን መናፈቅ ከባድ ነው ልባችን ዝም ብሎ መቁሰል በትዝታ መኖር በትዝታ መራመድ በትዝታ መሰቃየት  ስቃዮ አያባራም ህመም አለው። ለመዳን በሞከርን ቁጥር ይባስ እንቆስላለን እንደማለን እንታመማለን።💋
T.me/pclovee
ፍቅር እና ሳቅ😂
🌹😘ይጠቅማልና 😘ለእህቶቻችን አድርሱልን ወደ በዋላ የወንዶችን እንመለስበታለን!! 💋ሴት ሆይ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?!" : ➊.ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ : ➋.ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ :…
🙍‍♂#ወንድ ሆይ ለትዳርህ ብቁ ነህ?
:
( ለወንድሞቻችሁ ላኩላቸው ይጠቅማቸዋልና)

➊.ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት
:
➋.ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን (ደግሞ ሃጢያት ነው በሉ 😂 #ሚስቱን ነው) እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ ።
:
➌.ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ
በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ
:
➍.ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ
:
➎.ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት
:
➏.ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ
:
➐.ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ
:
➑.ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም
እንደሷ ከተነጫነጭክ
:
➒.ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ
:
➓.ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።
:
የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን
አድንቅላት።
:
ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ ተመርመር 😊
➊➊.ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ
እንዚህን መምራት ካቃተህ
:
➊➋.ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት
:
➊➌.ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው
:
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን አስተካክል ወንድሜ

:
👉 ወንድሜ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት የተባለው ለእርሷ ጥቅም ብቻ መስሎህ ከታየህ ተሸውደሃል
#ዘውድ ውበቷ ነው #የሷ ውበት ያንተ ውበት ነው
#የሷ መታየት ያንተ በድምቀት መታየት ነውና እስቲ ዘውድነቷን አምነህ ተቀበል ክብርም ስጣት
😍ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ እና ሼር እንዳይረሱ💋

T.me/pclovee
​​Kiyaye😍😍😍aleme😍😍😍😍😍😍😍😍estnfase hiwete fkr mn mehonu yawekut banchi new hiwete takyalesh tkmt 7 yetewaweknbat ken betam new makebrat lyu kene nat lelte😍😍😍😍ke ehtoche belay new mwedsh hyabe 😍😍😍ne kiya
Ngste😍kmeme😍yene fkr mn lblesh bezi mdr lay endachi mwedat set yelechim😍 beyeseatu beyedekikaw beyesecondu tnafkignalesh hule eskagegnsh eguagualew aleme kiyaye yelbe ngst love u for ever😍😍😍👭👭👭ne mrt guadegna ne kiya 😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘
ke kiyash😘😘

እናንተም መላክ ከፈለጋቹሁ በዚህ ላኩልን @jaden_36

😘ስለምትከታተሉን እናመሰግናል😘

@pclovee
@pclovee
@pclovee
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እሁድን በመሳቅ በመደሰት እናሳልፍ መልካም እሁድ😘😘😘😘

@pclovee
@pclovee
@pclovee
መነበብ ያለበት 🌀እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ🌀

ስሜ #ሰብለ ይባላል፡፡
ተወልጄ ያደኩት ባህር ዳር ሲሆን የፍቅር ሕይወቴ የሚጀምረዉ የ9ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር፡፡

የማፈቅረዉ ልጅ ደሞ አብሮ አደጌ እና የትምሕርት ቤት ጓደኛዬም ጭምር ከነበረዉ ዳኒ ነበር፡፡

እኔ ዳኒን እንደ ወንድሜ ነበር የማየዉ እሡም እንደ እሕቱ ያየኝ ነበር በመሀል ግን ከሆነ ግዜ በሗላ እኔ እሡን በፍቅር አይን ማየት ጀመርኩ፡፡
ቀንም ለሊትም እሱን ማሠብ ማሠላሠል ጀመርኩ፡፡ከሱ ጋር ሆኜ በሀሣብ ጭልጥ ማለት ጀመርኩ ትምሕርቴን በአግባቡ መከታተል አቃተኝ፡፡
ዳኒም የሆነ ነገር ሆነሻል ፀባይሽም ተቀይሯል አለኝ፡፡ እኔም ደሕና እንደሆንኩ ነገርኩት፡፡
በጣም አጥብቆ ሢጠይቀኝ እንደምወደዉ ነገርኩት እሱም ፈርቼሽ ነዉ እንጂ በጣም እወድሻለሁ አለኝ፡፡
ተቃቅፈን ተለቃቀስን፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ የኔ እና የሡ ግንኙነት አሪፍ ሆነ ማታ ማታ walk ማድረግ ጀመርን፡፡ ቅዳሜና እሁድ አብረን መዋል ቀጠልን፡፡
ፍቅራችን በገሀድ ወጣ የሠፈር ሰዎችም አወቁ፡፡ ቤተሠቦቻችንም አወቁ፡፡ የኔ ቤተሠቦች በጣም ተቆጡኝ ትምሕርትሽን መማር አለብሽ ከሱ ልጅ ጋር እንዳናይሽ አሉኝ እኔ ግን መኝታ ቤት ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡

ቢቆጡኝም እኔ ከዳኒ ጋር ቀጠልኩኝ፡፡
የሆነቀን ማታ ላይ walk እያረግን እያለ ታላቅ ወንድሜ አግኝቶን ሁለታችንንም መታን በተለይ እኔን ከሡ ነጥሎ እቤት ወስዶ ያለማንም ገላጋይ ቀጠቀጠኝ፡፡ ጫናዉ በረታብኝ ዳኒን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ ስለዚሕ በንጋታዉ ከዳኒ ጋር ምን ማድረግ እንዳለብን መከርን በመጨረሻም እሱ ታላቅ እሕቱ አሜሪካ ነች እና የተወሰነ ዶላር ልካልኛለች ስለዚሕ ጠፍተን አዲስ አበባ እንሒድ አለኝ፡፡እኔም በሀሣቡ ተሥማማሁ፡፡
አዲስአበባ እንደገባን አልጋ ይዘን ለአንድ ሁለት ቀን አደርን ከዚሕ በሗላ ግን ገንዘብም ቶሎ ሥለሚያልቅብን የሆነች በጣም ድክም ያለች ቤት ተከራየን፡፡ኑሮ በጣም ከበደ ገንዘባችንም እየተመናመነ መጣ የሚላስ የሚቀመስ መጥፋት ጀመረ፡፡
ስለዚሕ ዳኒ የሆነ ሥራ መሥረት አለብኝ በማለት የጉልበት ሥራ ጀመረ፡፡እንደ ቤተሠቦቻችንም ባይሆንም፡፡ ያለችንን እየተቃመሥን መኖር ጀመርን፡፡እኔ ከምንም በላይ በደሣሣ ጎጆም ብኖርም በሕይወቴ ፍፁም ደስተኛ ነኝ፡፡
በመሀል አረገዝኩ፡፡በዚሕ ኑሮ ላይ አስቸጋሪ ቢሆንም ደስተኛ ሆንኩኝ፡፡
ዳኒ በመሀል ከስራ ወጣ፡፡በቀን አንዴ የምንበላበት ጊዜም ነበረ፡፡
እኛ ግን አሁንም በፍቅራችን ደስተኞች ነበርን፡፡
ዳኒ ስራ ፍለጋ ጠዋት ቁርሱን ሳይበላ ወቶ ማታ ይገባል፡፡ ቢርበንም ፍቅራችን ከምግብ በላይ ነበር፡፡
ዳኒ በድጋሚ አንድ ድርጅት ዉስጥ በጉልበት ስራ ተቀጠረ፡፡ከባዱን ኑሮ እየገፋነዉ ባለበት ሁኔታ ዳኒ ከቤት ጠፋ እኔ የአምስት ወር እርጉዝ ሆኛለሁ ምን ይዋጠኝ ቀን ከለሊት በለቅሶ መታጠብ ሆነ ሥራዬ፡፡
እቤት ከቀረ አምስት ቀን ሆነዉ፡፡የትአካባቢ እንደሚሠራ እና አብረዉት የሚሠሩትንም ሥለማላቅ መያዣ መጨበጫዉ ጠፋኝ፡፡
ከአምስተኘዉ ቀን በሗላ እቤት ሲመጣ የሆነዉን ሁላ ነገረኝ፡፡ ቤተሠቦቹ ይዘዉ ወስደዉት እንደነበረና አምልጦ እንደመጣ ነገረኝ፡፡
ተቃቅፈን ተለቃቀስን፡፡ቤት መቀየር አለብን ብለን ሌላ ቦታ አንድ ፍራሽ ብቻ የምታዘረጋ ቤት ተከራየን፡፡ዳኒዬ አሁንም ወጣ ገባ እያለ መሥራት ቀጠለ፡፡
የሆነ ቀን ሰርፕራይዝ አለ ነገ አሳይሻለሁ አለኝ ፡፡በንጋታዉ ከሆነች ልጅ ጋር ሆነዉ የሆነ ኮንዶሚንየም ቤት አካባቢ ወስደዉ ልጅቷ አንደኛዉ ቤት ወስዳ ይሕ የናንተ ቤት ነዉ እኔ የዳኒ እሕት ነኝ ከአሜሪካ ነዉ የመጣሁት አለችኝ፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡በርካታ ደቂቃዎች
እኔና ዳኒ ተቃቅፈን ተለቃቀስን፡፡ልጅቷ በመቀጠልም ስራ እንድትሰሩበት ብላም የታሸገ ብሮች ሰጠችን፡፡ወይ ጉድ
አልኩኝ ታሪካችን ተቀየረ በፍቅር መፅናት የመጨረሻዉ ዉጤት እንዴት ደስ ይላል፡፡እኔ ና ዳኒ ትንሽም ብትሆን የራሣችንን ስራ እየሠራን የአንድ ልጅ እናትና አባት ሆነን ጣፋጭ የትዳር ሕይወት እየመራን እንገኛለን፡፡

💓ለእናንተም እዉነተኛ አፍቃሪ እና ጣፋጭ የፍቅር ሕይወት ይስጣችሁ፡፡💓 Amen,,,,,,,በሉ !

#share በማድረግ ለወዳጅዎ ማድረስዎን አይርሱ፡፡

@pclovee
@pclovee
ውድ የፍቅር እና ሳቅ ቻናል ተከታታዮች እንደሚታወቀው የቻናላችን አባላቶች እየበዙ ስለሆነ እኛም አሪፍ አሪፍ የፍቅር ጥቅሶች
❤️የፍቅር ታሪኮች
❤️የፍቅር ግጥሞች እና ሌሎችንም መፃፍ እና ማቅረብ የሚችል አጋዥ ያስፈልገናል ስለሆነም ብቃቱ አለኝ የሚል ሰው ካለ በ @jaden_36 ያናግረኝ

❗️❗️ ማሳሰቢያ ስለ ሀይማኖት ስለ ዘር ስለ ፓለቲካ መፃፍ አይቻለም

የናነተው ቤተሰብ ፍቅር እና ሳቅ ቻናል
@pclovee
@pclovee
@pclovee
🌹....ጽጌረዳ አልኩሽ
ስያሜ ባጣልሽ፤ ውበትሽ በዝቶብኝ፣
ከሁሉ ሴት በልጠሽ ፤አምረሽ በትታይኝ።
ያ....ች የእጽዋት ዘር ፤ጽጌረዳ አበባም፣
ውበቷን እንደሷ ፤የሚያክላት የለም።
በእርሷ ተማርኮ ፤ሚቀጥፋት ሲጠጋ፣
የምታደማበት፤ አላት ሾህ ሚዋጋ።
አንችም ማራኪ ነሽ፤ እንደ ጽጌረዳ፣
እሾህ ልብ ስላለሽ ፤አላምዶ ሚከዳ።
እና ምልሽ ዉዴ ፦
ከስምሽ አብልጨ ፤ጽጌረዳ ምልሽ፣
ቅኔ ስቀኝ ነው ፤ለሌላ እንዳይመስልሽ...
ኧረ ሰዎች ምንድነው ? ወይ ሞራል ስጡን ወይ ደሞ የገጠማችሁት ነገር ካለ ላኩልን፡፡
ካልቻላቹ ደሞ በቃ Share አድርጉ፡፡
2025/07/01 02:21:39
Back to Top
HTML Embed Code: