Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሪፍ movie ነው ተመልከቱት
ቤተክርስቲያንን ከማሸነፍ

ፀሀይን ማጨለም ይቀላል

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
Forwarded from 💃እኔ መፃፍ ብችል (አዶኒስ የአቡካዬ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰው ልጅ ጠባይና ባሕርይ እጅጉን ይገርማል።
አንዳንዴ የምንፈልገው ነገር እውነትም የምንፈልገውን ነው? አንዳንዴ የምናሳድደው በእርግጥም መያዝ የምንሻውን ነው? ወይስ ከመያዝ ይልቅ በማሳደድ ውስጥ፣ ከማግኘት ይልቅም በመፈለግ ውስጥ ምሥጢር አለ?
.
.
አንዲትን ሴት አጥብቆ የሚፈልግ ሰው ገጥሞኝ ያውቃል። ሁሌም ቀልቧን ለመማረክ ጥረት ያደርጋል። በአፍላ ትውውቃቸው ወቅት እሷን ካገኘ ከዓለም ምንም እንደማይፈልግ ይነግረኝ ነበር። ያቺ ሴት በዚያ ወቅት ፍጹም ናት። ንጽሕት ናት።  መንፈሱንና ልቡን ሁሉ ሞልታ ነበር። ብዙ ደጅ ጠንቶ የራሱ አደረጋት። የራሱ ከሆነች ቀን ጀምሮ ግን ዋጋዋ ቀንሶ ታየው። ቀድሞ ያልተገለጠ ነጭናጫነቷ የታየው መሰለው። ንጽሕናዋ ፍጽምናዋ ሁሉ ጠፋበት። ውበቷ ሀሰት ሀሰት ሆነበት። “ምን ሆኜ ነበር?” “ምን አስነክታኝ ነበር?” እያለ ለኃጢአቱ ምክንያት ሰጠ።
.

ለውጡ ግን የምንም ሳይሆን የቦታ ለውጥ ነበር። ድሮ ሲያሳድዳት ከፊቱ ነበረች። አኹን ከእጅ መዳፉ ላይ ነች።
.

አንዳንድ ነገሮች መፈለግ ላይ ብቻ መቆም አለባቸው ? አንዳንድ ነገሮችን አሳድደን ባንይዛቸው ይሻላል? ስኬት የጥረትን ያኽል ጣዕም የለውም? የለውም ወይ?
.

ይህ ሰው ምክንያት ፈልጎ ራቃት። ምክንያት ፈልጋ በተራዋ ፈለገችው። የማግኘት ስካር ሲያፋንነው የእልኋን ተከተለችው። ድሮ የተለመነችው በተራዋ ለመነች። አስለመነች። ምናልባት እሷም የተመኘችው ፈልጎ የማግኘትን ጣዕም መቅመስ፣ ሮጦ የመድረስን ሕልም ማሳካት እንጂ እሱን አልነበረም። ሁለቱም በውስጣቸው ያለውን ዕረፍት አልባ ተቅበዝባዥ ሰይጣን ለማገልገል ታተሩ እንጂ በውስጣቸው ፍቅር የለም —ቅንጣት እንኳ።
.
.
ጠቢቡ ሶሎሞን የደረሰበት ይኽ ነው። “ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ” ለማለት ያበቃውን መሰልቸት ለመረዳት ሰሎሞን መኾንን ይጠይቃል። የመድረስ መከራ ኃያል ነውና ሰሎሞን በሎሌው ይቀና እንደኾነ ማን ያውቃል ? የሞላለት ከበርቴ ጌታ ለማኝ መኾን ይሻ እንደሆነ እንዴት ይታሰባል ?
.
.
እንደዚህ በነፍስ ፈልጌያቸው ሳገኛቸው እንደ ጉም የሆኑብኝ … ልኾን ተመኝቻቸው ስሆን ደም እንባ ያስለቀሱኝ … እድሜዬን፣ ገንዘቤን ፣ ጥረቴን ሁሉ ሰጥቻቸው ሲሳካ “ተሳካ የልቤ ሞላ” ከማለት ይልቅ በዓይኔ እንኳ ለማየት ያስጠሉኝ፣ ያንገሸገሹኝ፣ የቀፈፉኝ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰዎች እንደ ዕድለኛ በሚቆጥሩኝ ነገር፣ “ታድለህ”በሚሉኝ ነገር፣ እኔን መኾን በተመኙባቸው አንዳንድ ነገሮች እኔ ግን አጥንቴ ድረስ ታምሜ ዐውቃለኹ። ሰው ከእኔ የተመኘውን ነገር እንደ ልብስ አውልቄ ብሰጠው ተመኝቻለኹ።
.
.
የምፈልገውን ነገር እፈልገዋለኹ? መሄድ የምሻበት ሀገር መኖር እፈልጋለኹ ? ሰው የምኞቱ ባርያ የፍላጎቱም ሎሌ ነው። አንዳንዴ እርካታ ፍላጎትን፣ ማግኘትም ጣዕምን ያሳድዳሉ። መድረስ ዋጋውን የማይቀንሰው ደስታ ምንድነው ? ማግኘት የማያደበዝዘው መንገድ ምንድነው? በየቀኑ እንደ ዐዲስ በመገረም ሊሞላኝ የሚችል ነገር ምንድነው? ይህንን ደስታ ለራሴ እመኛለኹ። ይህንን እርካታ ለሰው ሁሉ እመኘዋለኹ። ካልኾነ ግን መንገዴን በእሾኽ ይጠረው፣ በጥርብ ድንጋይም ይዝጋው። አብረውኝ በማይከርሙ ደስታዎች ተሰላችቼያለኹ።

ይነጋል💚💛
🔑ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን እንዴት መክፈት እንችላለን?

አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡

Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡

Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡

Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot). በትክክል ይሰራል…


ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @ethiouniversity1bot

            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @pock_model  ♨️
♨️ ♦️ @pick_model  ♨️
♨️ ♦️ @pick_model ♨️
╚══════════ ╝
Forwarded from ℙ𝕚𝕔
10 years old me at ፎቶ ቤት
🤓
<))>
|\_
Photographer : ስታይል ቀይር

Me:
😎
<((>
_/|
#promise... 🙄
Forwarded from ሰውና ~ ፍልስፍናው (Ceku'aa)
🌿 ያለ ፍቅር የሚደረግ ወሲብና ያለ እዉነት የሚደረግ አምልኮ አንድ ናቸዉ።
ሁለቱም ከመንፈስ አጉድሎ ስጋን የሚያሞኙበት የመስገብገብ ስሜት ነዉ።"


Unknown /📚
2024/05/17 10:02:48
Back to Top
HTML Embed Code: