የምስራቅ ክ/ከ አስተዳደር ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በውቅሮ ቀበሌ የስንቅ ማዘጋጀት ተደረገ.....

ዛሬ 16/01/2015 ዓ.ም በዛ ጠዋት በዛ ብርድ እና ዝናብ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የውቅሮ ቀበሌ አስተዳደር አመራሮች የዉቅሮ ቀበሌ ነዋሪ ሴቶች እና የፕላስ የኪነ-ጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበር ወጣቶች በምስራቅ ክ/ከ አስተዳደር ውቅሮ ቀበሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የማዕድ ማዘጋጀት ተግባር አከናውነዋል።

በዚህም ተግባር ፕላስ የኪነ-ጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበር ከውቅሮ ቀበሌ አመራሮች ጋር በመሆን እንደ ወጣት ለሀገር መከላከያው ያለውን ፍቅር እና ድጋፍ እንደ ከዚህ ቀደሙ በተግባር አሳይቷል።

"ሀገር ማለት ሰው ነው ሰው ማለትም ሀገር"

ፕላስ የኪነ-ጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበር
ሀዋሳ
16/01/2015 ዓ.ም
2024/05/19 21:52:09
Back to Top
HTML Embed Code: