Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ

#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡

#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

✿በራስ መተማመን ማነስ

✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች

✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

©zepsychology

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ www.tg-me.com/Psychoet
👍488
#መልካም_የህዳር_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyabc
👍2120
የኑሮ ቀውስን ማሸነፍ |Overcoming Crisis|
በዶክተር ማይልስ ሞንሮ ተጽፎ በአማረኛ ተተርጉሞ የቀረበ

በአስቸጋሪ ጊዜ የማደግ ሚስጥር
📌ሕይወት ሲከፋ እንዴት እናመልጣለን?
📌በሌላ ሰው ስህተት ስንወድቅ ምን እናረጋለን?
📌በተለያዩ የሕይወት ቀውሶች ውስጥ ስንገባ እንዴት እናመልጣለን?


አስተማሪ የስነልቦናዊ ምክር ስለሆነ ጊዜ ሰታችሁ አድምጡት!
ክፍል 1 | Part 1
https://youtu.be/B7Q1GThhups
👍17
እንኳን ደስ አለን!
የ12 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሊጀምር ነው!

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን

ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰጣል፡፡ ሕዳር 17 ቅዳሜ እና 18 እሑድ ይጀምራል ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 3-6 ➋ቅዳሜ 8-11
እሑድ 3-6 ➍እሑድ 8-11

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet

አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
👍19
#መጀመር
ማንኛውም ነገር ካልጀመርነው ይከብዳል ስንጀምረው ተግዳሮት አለዉ ደጋግመን ስናደርገዉ ቀላል ነዉ።
ሳንጀምር ይከብዳል አንበል እንደሚከብድ በምን አወቅን?
1. እንጀምረው
2. እንቀጥለው
3. እንጨርሰው ።
#ሁሌ ከሁዋላ የሚሰበረው እስክንለምድ ነው!!!
©ሁንዴ

ይህን መልዕክት ለምትወዱአቸው #5 ታታሪ ጓደኞቻችሁ Forward አርጉልኝ !
#Join #Share
@psychoet
@psychoet
@psychoet
👍208
🔑🔑🔑12ኛ ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል!

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀት፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?

ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰጣል፡፡ ሕዳር 24 ቅዳሜ እና 25 እሑድ ይጀምራል ያሉን ፈረቃዎች
➊ ቅዳሜ 8-11 ወይም ➋እሑድ 3-6

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ባሉን ውስን ቦታዎች ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet

🏠አድራሻ:- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

🖼🎁ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
@psychoet
👍13
በሌለን ነገር ከማማረር ባለን ነገር ማመስገን ጤናማ ያደርጋል ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ፡፡
ሀሳቡን ለሌሎችም አጋሩ
@psychoet
22👍8👏2
ከወደ አርባምንጭ ሜሎሪና-ቴሎስ እየተነበበ ነው

‹‹ልጄ ያሬድ፣ የሰው ልጆችን መከራ ማሸነፊያ መሣሪያ ስለኾነው ነገር ልንገርህ፡፡ ችግሮችን ሁሉ የምናሸንፍበትና ከገባንበት አረንቋ የምንወጣበት አንድ ትልቅ መሰላል አለ፤ እሱም መልካም ተስፋ ነው፡፡ ተስፋ፣ ከምንኖርበት ቦታና ካለንበት አካባቢ አልፈንና ተሻግረን አርቀን እንድናስብ የሚረዳን ነው። ተስፋ አሳብ ነው፤ ተስፋ ምኞት ነው። ዛሬያችንን፣ ከተወረሰበት ጨለማ አራግፈን የምናወጣበት ነው፡፡ ይቺ ዓለምም ብትኾን ለተስፈኞች የተለየ ቦታ ያላት ትመስላለች፡፡ ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይታይ፣ ሳይሰማ፣ ሳይዳሰስና ሳይጨበጥ በፊት በአሳብ ደረጃ እያለ የማይታየውን እንዲታይ፣ ያልተጨበጠውን እንዲጨበጥ የሚያደርጉት ትላልቅ ተስፈኞች
ናቸው፡፡ ተስፋ በርግጥ የወደቀውን ያነሣል፤ የተሰበረውን ይጠግናል፡፡

‹‹ስለዚህ ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ መልካም ተስፋ አድርግ፡፡ ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው፤ ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው፡፡ ሕይወትህ መከራ፣ ችግር፣ ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ፣ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን፡፡ በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው፡፡ በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ሥራ በደስታም ኑር፡፡››

የናንተንም ፎቶ ከወደዳችሁት ከመጽሐፉ የወጣ አባባል ጋር ላኩልን
📸 Kibre-ab Elias ĸébå
👍18
ወዳጆቼ ኾይ፣ ከጠቀማችሁ ትንሽ ነገር ልበላችሁ

ኹላችንንም ወደዚህች ምድር የላከን ፈጣሪ ነው፡፡ አንዳችንም ወደን ፈቅደንና አስበንበት የመጣን የለንም፡፡ ታዲያ ለምን ይኾን ፈጣሪ ወደዚህች ምድር የላከን? በቃ በልተን ጠጥተን፣ ተምረን ሰርተን ፣ አግብተን ወልደን እንድንሞት ብቻ ነው? ወይስ ሌላ ምክኒያት ኖሮት ይኾን? ቆይ የሕይወት ሩጫችን የት ለመድረስ ነው? ከደረስንስ በኀላ? የሕይወትስ ትልቁ ነገር ምንድነው?
#ራሳችንን_እንጠይቅ
@Psychoet
👍30
በዛው መጠን የኛ የሆኑ ሰዎችንም እናውቅበታለን 😍 @psychoet
👍495
ሰው ነህ !
💧በሰጡህ ቦታ አትቅር ፣ ሰው እንጂ ድመት አይደለህምና።
💧ማንም ወደ ፈለገው አይቀይስህ፣ ሰው እንጂ የመስኖ ውኃ አይደለህምና።
💧በቁጣ የሠራኸውን አታፍርስ ፣ ሰው እንጂ ጎርፍ አይደለህምና።
💧በወደቅህበት አትቅር፣ ሰው እንጂ ዛፍ አይደለህምና።
🙏ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን::
የተባለው ከተስማማህ ሼር አድርግ

@Psychoet
👍539👏8
እውነት ከሚናገር ሰው በላይ የሚጠላ የለም፡፡
@psychoet
👍373
🔥👉 ጭንቀትን_ድብርትንና_አሉታዊ ስሜቶችን_ለመከላከል የሚረዱ_ዘዴዎች🔥👈

🎈ባለፈ ጥፋት ወይም ውድቀት ላይ በማተኮር #ፀፀት# ውስጥ አለመግባት። ከባለፈው ስህተት በመማርና አሁን/ዛሬ ላይ ማተኮር።

🎈 ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ማድረግ።

🎈 ከተለያዩ እፆችና አልኮል #ሱሰኝነት# መቆጠብ።

🎈 ግጭቶችን፣ ቅራኔዎችንና አለመግባባቶችን በአግባቡ መፍታት።

🎈 ውጥረትንና ጭንቀትን የሚፈጥሩብዎትን ነገሮችና ሁኔታዎችን መለየትና ከእነሱ መራቅ።

🎈 በጎ ማድረግና ምላሹን ከሰዎች አለመጠበቅ።

🎈ጭንቀትና ድብርት ሲሰማዎ ለቅርብ ወዳጅ፣ ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ማጋራት።

🎈ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥምዎ፤ ራስን ማረጋጋት።

🎈ሌሎች ሰዎች ስለእርስዎ በሚሰጡት ትችት እና አስተያየት አለመረበሽ።

🎈 የህይወትን ጥሩ ገፅታ ማየት።

🎈በአላማና በእቅድ መኖር ፤ ጊዜን በስራ ማሳለፍ።

🎈የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ንፅህናን መጠበቅ እና ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን መከተል።

🎈ለራስ ጊዜን መስጠትና እረፍት ማድረግ።

🎈ከሁሉም በላይ በፈጣሪ መታመንና እኛ ልንፈታ የማንችላቸውን ነገሮች ለእርሱ መተው።

መልእክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ Share & Like አይርሱ።

© Psych ጤና Fb ፔጅ
👉በመአዛ መንክር -ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
www.tg-me.com/psychoet
👍52👏94
በዓሉን ለምታከብሩ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ 🙏
21👍14
ሰው መሆን በቂ ነው!

አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀና መውጣትም አልቻለም፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ደክሞት በጉድጓዱ መካከል ቁጭ እንዳለ …

• ከንፈር መጣጭ ሰው አየውና - “ሁኔታህን ሳስበው በጣም በሃዘን እሞላለሁ” ብሎት ሄደ፡፡

• ተመራማሪ ሰው አየውና - “ይህ ጉድጓድ ከተማ መሃል ሆኖ ሰው መውደቁ አያስደንቅም” ብሎት ሄደ፡፡

• ፈራጅ ሰው አየውና- “ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው እንደዚህ ሊወድቁ የሚችሉት” ብሎት ሄደ፡፡

• ነጭናጫና አጉረምራሚ ሰው አየውና- “እኔ ወድቄ የነበረበትን ጉድጓድ አላየህ” ብሎት ሄደ፡፡

• አነቃቂ ንግግር አስተማሪው አየውና- “በራስህ ብታምን ከዚህ ትወጣለህ” ብሎት ሄደ፡፡

• ዘረኛ ሰው አየውና - “የምን ሃገር ሰው ነህ?” በማለት ከጠየቀው በኋላ የእርሱን ቋንቋ ስላልተናገረ ጥሎት ሄደ፡፡

•ውሸተኛ የሀይማኖት ሰው አየውና - " የኔ እምነት ተከታይ ብትሆን አወጣህ ነበር " ብሎት ሂደ፡፡

• በመጨረሻ ይህንን ሁሉ ድራማ ሲመለከት የነበረ አንድ ጨዋ ጎልማሳ ሰው ከብዙ ጥረት በኋላ እየሳበ አወጣው ፡፡

ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? በእርግጥ ሰውነት ከሁሉ ይበልጣል ፡፡

ምንጭ :- ከዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

በቅንነት ሼር ያድርጉ👇
http://www.tg-me.com/psychoet
👍39👏94👎3
2025/07/12 19:47:04
Back to Top
HTML Embed Code: