Telegram Web Link
ሜሎሪናን እያነበባችሁና አስተያየቶቻችሁኝ እየሰጣችሁን ስላለ እናመሠግናለን። 🙏
12👏2
‹‹..ምቀኝነት በመጀመሪያ የሚገለጸው በቀልድ ውስጥ ነው። ስለዚህ ሰዎች በቀልድ የሚሉህን ኹሉ ከመረዳትና ራስህን ከአደጋ ለመጠበቅ ቸል እንዳትል። … ሰው በውስጡ የሌለን ወይም ያልመሰለውን ነገር በአፉ አይተነፍስም።››

ሜሎሪና - ሕይወቴ
39👍15😁1
"ይቺ ዓለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነው፡፡ ባጠቃላይ ዓለም ራስ ወዳድ ናት - ነዋሪዎቿም እንደዛው። ይሳካልህ ብለው መርቀውህ ሲሳካልህ የማይወዱ፣ ሰላም ሁን ብለው ሸኝተውኽ ጥልን የሚመኙልህ፣ ይከናወንልህ ብለው ውድቀትን የሚያስቡልኽ፣ ራሳቸውን ለመጥቀም አንተን የሚጎዱ ሰዎች ብዙዎች ናቸው።"

መስፍን እንዳለው

ሜሎሪና - ሕይወቴ
👍519
ከቻናሉ ቤተሰቦች ምን ያህሎቻችሁ "ሜሎሪና-ሕይወቴ" ን እያነበባችሁ ነው? የመጀመሪያው ዕትም ጥቂት ስለቀረ በሚቀርባችሁ መደብር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ትችላላችሁ።
@psychoet
👍9
ሬድዮ ላይ ስለ ምን ጉዳዮች መስማት ያስደስታችኋል?
ሀሙስ 20

#ውሸት

ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

©Zepsychologist
@psychoet
👍3413😁1
በ"ሜሎሪና" ሦስቱም መጽሐፍት ላይ ያደረግነውን ውይይት እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ

https://youtu.be/VxBArnirP1I?si=AyhHYAfgMjNKcmkH
👍141
#3ቱ_የትኩረት_መንገዶች

ተግባራቶችን እየቀያየሩ አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዛ ከሚል በውጥረት የተሞላ የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ቀጣዩን ተግባርህን በጥንቃቄ ምረጥ፤

#1_እጅህ_ላይ_ባለው_ስራ_ላይ_አተኩር
ሌላውን ነገር ሁሉ ወዲያ በል እና በእጅህ የያዝከው ስራ ላይ ብቻ ትኩረትህን አድርገህ ስራ፡፡ በእጅህ የያዝከውን ስራ በጥድፊያ ጨርሰህ ወደሚጠብቅህ ቀጣይ ስራ መሄድ እንዳለብህ ከሚያሳስብህ ስሜት ውስጥ ወጥተህ በእጅህ ባለው ስራ ላይ ብቻ ተመሰጥ፡፡ ሁልጊዜም ቀጣይ የሚሰራ ስራ ይኖራል፤ ምክንያቱም የስራ ዝርዝሮች ባህሪያቸው እንዲህ ነው፣ ማብቂያ የላቸውም፡፡

#2_በኋላ_የሚሰሩትን_ስራዎች_ለበኋላ_አቆያቸው፡፡
ይህ መላው ዓለምህ እንደሆነ ቆጥረህ መቶ ፐርሰንት ትኩረትህን በእጅህ ላይ ባለው ስራ ላይ በማድረግ እርሱን ስራ፡፡ 

#3_አሁኑ_ቅጽበት_ላይ_ሁን
ሙሉ በሙሉ አትኩሮትህን አንድ ጊዜ አንድ ተግባርን መፈጸም ላይ አድርግ፡፡

#ቁም_ነገሩ - ዝግ በል፡፡ ተንፍስ፡፡ ተነሳሽነትህንና ግቦችህን ገምግም፡፡ መቅደም ያለበትን ነገር አስቀድም፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ተግባርን ብቻ ፈጽም፡፡ አሁን ጀምር፡፡ በየሰዓቱ የ5 ደቂቃ እረፍት አድርግ፡፡ እንደገና ደጋግመው፡፡ (እናም አስታውስ፤ ውጤት ውጤቱን ለማምጣት ከሚወስደውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው፡፡)


📗📒📕 © ድሬ

አስተማሪ መልእክቶችን፣  ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
👍246
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
✍️ የዚህ ድንቅ መምህር የህይወት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ፅፌዋለሁ፣የምር ግን አንድ 5 ፊልም ይወጣዋል 😲
👉 አባቴ ጥበቃ እየሰራ፣ጫማውን እየሰጠ ነው ያስተማረኝ፣8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ሳልፍ በጣም ደስ ብሎት አልጋ ላይ መተኛት ያለበት እሱ ነው ብሎ ከእናቴ ጋር መሬት እየተኙ እኔ አልጋ ላይ እተኛ ነበር።
👉 ዩንቨርስቲ ስገባ ነበር መበላሸት የጀመርኩት፣የመጀመሪያ አመት ጥሩ ውጤት ነበረኝ፣ሁለተኛ አመት ግን ከትምህርቱ ሱሱ ቀደመና ክላስም መግባት ተውኩኝ፣መማር አቃተኝ ከዛም ከዩንቨርሲቲው ተባረርኩ።
👉አባቴ ይሄን አያውቅም ህንድ ሀገር የጀመርኩት ፕሮሰስ ነበር ለሱ ስሮጥ ለዩንቨርሲቲ ዊዝድሮው ሞልቼ ነው ብየ ዋሸሁት፣በዚህ አላበቃም የህንዱም ፕሮሰስ እንደተበላሸ ዋሸሁት
👉 በጣም ስለሚያምነኝ ያሰብከው አይቀርም ብሎ ያለውን ዕቃ ሸጦ ቻይና ላከኝ
👉ቻይናም ሄጄ ሱሱ አላቆመም፣ ቀጠለ እዛም በሱስ ምክንያት ከአመት በኋላ ተባረርኩ፣ ኢትዮጵያ መጥቼ ለ2ኛ ጊዜ አባቴን ዋሸሁት፣እርሱም ለ2ኛ ጊዜ የቤት እቃውን ሸጦ ድጋሚ ላከኝ🤔
👉 በዚህ ዙር ተለውጬ አባቴን ለመካስ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር የሄድኩ፣ነገር ግን በሱስ ተተብትቤ ስለነበር አሁንም አልተሳካም 1 አመት ሙሉ ክላስ ሳልገባ ሱሱን ሳካሂድ ቆየሁ፣ ለ3ኛ ጊዜ ከዩንቨርሲቲ ተባረርኩ፣ለአባቴ ሳልናገር ተመልሼ መጣሁ፣አዲስ አበባ አልጋ ይዤ የነበረኝ ገንዘብ እስከሚያልቅ ቆየሁ፣ሱሱም ቀጥሎ ነበር
👉የነበረኝ ብር አለቀ፣በስተመጨረሻም ጎዳና ወጥቼ መኖር ጀመርኩ፣አባቴ ግን ቻይና እንዳለሁ ነበር የሚያውቀው
👉እናም ጎዳና ላይ ብዙ ጊዜያቶች አሳለፍኩ የረሀብና የጥማት ጊዜያቶች፣ለመተኛት ከ22 የካአባዶ ጫካ እሄድ ነበር፣ለሊት እቀመጣለሀ፣ቀን ነበር የምተኛው በጣም ከባድ ጊዜ ስለነበር
👉 አንድ ቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብዬ የሚያውቁኝ ልጆች በአጠገቤ ሲያልፉ አየሁ እነሱ በጣም ተጎሳቁየ ስለነበር አለዩኝም ነበር ግን ድንገት የሚያውቀኝ ሰው አይቶኝ ለአባቴ እንዳይናገር ፈርቼ ለምኜ ወደ ደብረዘይት ሄድኩ።
👉 እዛም መነሀሪያ አካባቢ የሚያድሩ ልጆች ጋር ጎዳና መኖር ጀመርኩ፣ከዛም የህይወቴን ከባዱን የመራብና የመጠማት ጊዜ አሳለፍኩ
👉 ከዛም ልሞት ስለመሰለኝ፣ከሞትኩም በቃ የሚያውቀኝ ሰው እንዲያገኘኝ አዲስ አበባ ሄጄ ልሙት ብየ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ጀመርኩ
👉 እኔ ደክሞኝ ተስፋ ቆርጬ በጨረስኩ ሰዓት እግዚአብሔር ጀመረ፣ የተሳፈርኩበት ሚኒባስ ውስጥ ታሪኬ እንዲቀየር ምክንያት የሆነችዋን ሴት አገኘሁ....................ይቀጥላል

©የእውነትመንገድ

@psychoet
👍4411👏1
https://www.tiktok.com/@nahutel/video/7490134803711315205

በጣም የማደንቀው የቢዝነስ ሰው 🙌
👍1
በ19 አመቱ በአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት ሰርጎ በመግባት እና ብዙ የሀገሩን ሚስጥሮች ሰርቋል በሚል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ 15 አመት ተፈርዶበት ህይወቱን በእስር ቤት እየመራ ይገኛል ።

አባቱ ብቻቸውን የሚኖሩ አዛውንት ነበሩ ። አንድ ቀን ድንች ለመትከል ፈልገው በእድሚያቸው መግፋት ምክንያት ጥንካሬ አልነበራቸውም :

ከዚያም ለታሰረው ልጃቸው እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ

::

"ውድ ልጄ የአትክልት ስፍራውን ለመቆፈር እና ድንች ለመትከል እንድትረዳኝ አሁን ከእኔ ጋር ብትሆን እመኝ ነበረ ። አሁን የሚረዳኝ የለኝም። "

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አባትየው ከልጃቸው ደብዳቤ ደረሳቸው።

"አባባ እባክህን አትቆፍር ፤ ምክንያቱም አንድ ጠቃሚ ነገርስለደበቅኩኝ ከእስር ቤት ስወጣ ምን እንደሆነ እነግርሃለሁ።"

የልጃቸው መልእክት በተጻፈ በአንድ ሰአት ውስጥ የምስጢርአገልግሎቱ እና ሰራዊቱ ቤቱን ከበቡ።

በደቂቃዎች ውስጥ የአትክልት ስፍራውን ቆፍረው ሁሉንም ነገር አስወግደው ምንም ነገር ሳያገኙ ቤቱን ለቀው ወጡ።

ከሳምንት በኋላ ከልጃቸው ሌላ ደብዳቤ ደረሳቸው ።

"አባዬ መሬቱ በፖሊስ በደንብ እንደታረሰ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ድንች መትከል ትችላለህ ። ሌላ ነገር ስትፈልግ ኣሳውቀኝ ፤ የእስር ጊዜን ጨርሼ እስክመጣ ድረስ ካንተ ጋርመሆን አልችልም ነገር ግን በምችለው መንገድ ለመደገፍ የተቻለኝን አደርጋለሁ። "
👍346👏6😁5
አርጀንቲናዊ ነው ፡ Jorge Mario Bergoglio ይባላል ፡
ይህ ወጣት የኬሚስትሪ መምህር ሆኖ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ፡ ይህንን ስራ በመተው ፡ በቦነስ አይረስ የምሽት ናይት ክለቦች የበር ላይ ጥበቃ ሆኖ ሰርቷል ።
ስራው በቀጥታ ናይት ክለቡን መጠበቅ ሳይሆን ፡ ወደ ክለቡ የሚገቡትን ሰወች መፈተሽ ፡ እድሜያቸው አጠራጣሪ የሆኑ ወጣቶችን መታወቂያ እያዩ ማስገባት. .
አንዳንዴም በናይት ክለቡ ውስጥ ግጭት ሲኖር ጣልቃ በመግባት ማስማማት የመሳሰሉ ስራዎችን ነበር የሚሰራው ።
..
Jorge Mario በሀያ አመት እድሜው ባጋጠመው አደገኛ ህመም ምክንያት አንድ ሳንባው ተቆርጦ እንዲወጣ ሲደረግ ብዙዎች ረጅም እድሜ እንደማይኖር ገምተው ነበር ። ሆኖም ያጋጠመው የጤና እክል ተጨማሪ 68 አመታትን ፡ በህይወት እንዳይኖር አላገደውም ።
...
ይህ ከላይ ያነሳነው ታሪክ ፡ በ88 አመት እድሜያቸው ዛሬ በሞት የተለዩት የካቶሊኩ ጳጳስ የፖፕ ፍራንሲስ የወጣትነት ታሪክ ነው ።
.......
ከናይት ክለብ ባውንሰርነት ፡ የካቶሊክ ጳጳስ እስከመሆን የደረሰ ስብእና ።
........
በአንድ ወቅት በምንም ሁኔታ ውስጥ ልታልፍ ፡ ትችላለህ ሆኖም አንድ ቀን የዛሬው ማንነትህ ተቀይሮ ታላቅ ደረጃ እንደምትደርስ ፡ የኚህ ጳጳስ ህይወት ከተራ ማነቃቂያ ያለፈ የህይወት ምስክርነት ነው ።
👍233
ከሥራ ደክሞኝ ነው የመጣሁት፣ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳልኩኝ ባለቤቴ በብርጭቆ ውሃ ሰጠችኝ ፣ ልጄ አንድ ወረቀት ሰጠኝ ወረቀቱ ላይ የተፃፈው እንዲህ ይነበባል ።

እንግሊዝኛ .......17 ከመቶ
ባዮሎጂ ...........35 ከመቶ
ሒሳብ ..............40 ከመቶ
ፊዚክስ .............37 ከመቶ
ኬሚስትሪ ..........42 ከመቶ
ኢኮኖሚክስ ........12 ከመቶ
እርሻ...................19 ከመቶ
ጂኦግራፊ ...........22 ከመቶ

ንዴቴን መቆጣጠር አቅቶኝ " ይሄ ምንድነው? ሁልግዜ ሞባይል እና ቴሌቪዥን ላይ ነህ። እንዴት ይህን ማርክ ውጤት ብለህ ለማሳየት ደፈርክ?" በጩኽት ልጄን ተቆጣውት።

ባለቤቴ " ትእግስት ይኑርህ አዳምጠኝ.... " ስትለኝ ።

ንግግሯን ሳትጨርስ "ዝም በይ ልጁን ያበላሸሽው አንቺ ነሽ! ከዚህ በኋላ መቼም ሰው አይሆንም " አልኳት ።

ሚስቴ"ይገርማል! አለች።

"በቤተሰባችን እንደዚህ አይነት የወረደ ውጤት ያመጣ የለም" በንዴት እና በጩኽት ተናገርኩኝ።

ልጄ አጠገቤ መጣና " አባዬ ንዴት ውስጥ እንድትገባ ስለአደረኩህ አዝናለሁ ፤ ቁምሳጥኑን ሳፀዳ በ1977 ዓ.ም የአንተ የፈተና ውጤት ሪፖርት ነው"አለኝ ።

ስሙን ሳየው የእኔ የድሮ የትምህርት ቤት ውጤት ካርድ ነው፣ ስሜ በትልቁ የትፃፈበትን የፊት ለፊት ካርዱን አላየሁትም ነበር።
@psychoet
😁17👍156
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
አንድ እስረኛ በስቅላት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል ነገር ግን የሳይንቲስቶች ቡድን የሰዎችን እምነት እና የአዕምሮ ጥንካሬን ለመፈተሽ ፈለጉና ከስቅላት ይልቅ በእባብ ንክሻ እንደሚገደል ነገሩት።
የበለጠ አሳማኝ ለማድረግ አንድ ትልቅ አስፈሪ እባብ አሳዩት። እስረኛው በፍርሃት ተሞልቶ ዓይኑን ታሰረ። ሳይንቲስቶቹ እስረኛው ሳያውቅ በእባብ ንክሻ በሚመስል መልኩ እጁን በስለታም መርፌ ተጠቅመው የእባብ ንክሻ አስመስለው ወጉት።
ከዚያም ራቅ ብለው ሲመለከቱ እስረኛው በእባቡ እንደተመረዘ በማመን በሰውነቱ ውስጥ የመርዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ምንም እንኳን ትክክለኛ መርዝ ባይኖርም ሰውዬው በእባቡ ንክሻ ላይ ያለው እምነት በፍጥነት አካላዊ ውድቀትን አስከትሎ በደቂቃዎች ውስጥ ሰውየው ወድቆ ሞተ።

ይህ ክስተት አስደንጋጭ ቢሆንም እምነት እና መጠበቅ እውነተኛ አካላዊ ውጤቶችን ሊያመጣ የሚችልበት (placebo effect) የፕላሴቦ ተጽእኖ በመባል ይታወቃል፡፡ አእምሮ ምን ያህል ኃይለኛ እንደሆነ ያሳያል።
አእምሮ የእኛን እውነታ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ሊቀይረው ይችላል። በዚህ ሁኔታ እስረኛው በእጣ ፈንታው ላይ ያለው እምነት በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ሰውነቱ ምንም እንኳንበእባቡ ባይነደፍም ንክሻው በእውነት የተከሰተ ያህል ምላሽ እንዲሰጥ አድርጓል።

ይህ ታሪክ ወሳኝ ትምህርት ያስተምረናል፡፡ ሀሳቦቻችን፣ እምነቶቻችን እና አመለካከቶቻችን በደህንነታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ስለራሳችን እና ስለ ህይወታችን የምናምነው ነገር ሊያነሳን ወይም ሊጥለን ይችላል።
ስለዚህ አእምሯችን እውነታዎቻችንን የመቅረጽ አቅም ስላለው አዎንታዊ አመለካከትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። የሃሳብህን ሃይል በፍፁም አቅልለህ አትመልከት። በጥንካሬዎ እና በችሎታዎ ማመንን ይምረጡ ምክንያቱም አእምሮዎ ፈተናዎችን ለማሸነፍ ትልቁ አጋርዎ ሊሆን ይችላልና፡፡

©️ከመፅሐፍት አለም
27👍4
የማያዛልቃችሁን ሰው ለዩ!

በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሼር አድርጉት

ከሚከተሉት ባህሪያት ቢያንስ አንዱን የምታዩባቸው ሰዎች ምናልባት ብዙም የማያዛልቋችሁና አንድ ቀን ለስሜት ጉዳት አጋልጠው የሚሰጧችሁ አይነት ሰዎች እንደሆኑ ጠርጥሩ፡፡

• ራሳችሁንም ሆነ ያላችሁን ነገር በነፃ ስላቀረባችሁላቸው፣ ልክ እንደ ርካሽ የሚቆጥሩና የማያመሰግኑ ሰዎች፡፡

• በዓላማችሁና ለማደግ በምታደርጉት የየእለት ጥረት የሚያላግጡና የሚያሾፉ ሰዎች፡፡

• እየጠፉና እየቆዩ ለአንድ ነገር አማራጭ ሲያጡና ያንን ነገር ከእናንተ ብቻ እንደሚያገኙ ሲያውቁ ብቻ የሚፈልጓችሁ ሰዎች፡፡

• እናንተንና ወዳጅነታችሁን ሳይሆን የእናንተንና ያላችሁን ነገር ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች፡፡

• በፍጹም የማያምኗችሁ ሰዎች፡፡

• ስህተታችሁን እየቆጠሩ የሚወቅሷችሁና በፍጹም ይቅር የማይሏችሁ ሰዎች፡፡

• ስህተታቸው እንዳይገኝባቸው እናንተን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች፡፡

• ሰዎችን ለእናንተ የሚያሙና ስለሰው ክፉን የሚያወሩላችሁ ሰዎች፡፡

• እናንተ የጀመራችሁትን ነገር እነሱ እንደጀመሩት አድርገው ለማሳየት የሚጣጣሩ ሰዎች፡፡

• ለእነሱ መኖር፣ መስጠትና መልካም ነገር ማድረግ፣ ልክ እንደ ግዴታችሁ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች፡፡

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
👍188
2025/07/09 15:48:44
Back to Top
HTML Embed Code: