ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷♂
Photo
✍️ የዚህ ድንቅ መምህር የህይወት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ፅፌዋለሁ፣የምር ግን አንድ 5 ፊልም ይወጣዋል 😲
👉 አባቴ ጥበቃ እየሰራ፣ጫማውን እየሰጠ ነው ያስተማረኝ፣8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ሳልፍ በጣም ደስ ብሎት አልጋ ላይ መተኛት ያለበት እሱ ነው ብሎ ከእናቴ ጋር መሬት እየተኙ እኔ አልጋ ላይ እተኛ ነበር።
👉 ዩንቨርስቲ ስገባ ነበር መበላሸት የጀመርኩት፣የመጀመሪያ አመት ጥሩ ውጤት ነበረኝ፣ሁለተኛ አመት ግን ከትምህርቱ ሱሱ ቀደመና ክላስም መግባት ተውኩኝ፣መማር አቃተኝ ከዛም ከዩንቨርሲቲው ተባረርኩ።
👉አባቴ ይሄን አያውቅም ህንድ ሀገር የጀመርኩት ፕሮሰስ ነበር ለሱ ስሮጥ ለዩንቨርሲቲ ዊዝድሮው ሞልቼ ነው ብየ ዋሸሁት፣በዚህ አላበቃም የህንዱም ፕሮሰስ እንደተበላሸ ዋሸሁት
👉 በጣም ስለሚያምነኝ ያሰብከው አይቀርም ብሎ ያለውን ዕቃ ሸጦ ቻይና ላከኝ
👉ቻይናም ሄጄ ሱሱ አላቆመም፣ ቀጠለ እዛም በሱስ ምክንያት ከአመት በኋላ ተባረርኩ፣ ኢትዮጵያ መጥቼ ለ2ኛ ጊዜ አባቴን ዋሸሁት፣እርሱም ለ2ኛ ጊዜ የቤት እቃውን ሸጦ ድጋሚ ላከኝ🤔
👉 በዚህ ዙር ተለውጬ አባቴን ለመካስ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር የሄድኩ፣ነገር ግን በሱስ ተተብትቤ ስለነበር አሁንም አልተሳካም 1 አመት ሙሉ ክላስ ሳልገባ ሱሱን ሳካሂድ ቆየሁ፣ ለ3ኛ ጊዜ ከዩንቨርሲቲ ተባረርኩ፣ለአባቴ ሳልናገር ተመልሼ መጣሁ፣አዲስ አበባ አልጋ ይዤ የነበረኝ ገንዘብ እስከሚያልቅ ቆየሁ፣ሱሱም ቀጥሎ ነበር
👉የነበረኝ ብር አለቀ፣በስተመጨረሻም ጎዳና ወጥቼ መኖር ጀመርኩ፣አባቴ ግን ቻይና እንዳለሁ ነበር የሚያውቀው
👉እናም ጎዳና ላይ ብዙ ጊዜያቶች አሳለፍኩ የረሀብና የጥማት ጊዜያቶች፣ለመተኛት ከ22 የካአባዶ ጫካ እሄድ ነበር፣ለሊት እቀመጣለሀ፣ቀን ነበር የምተኛው በጣም ከባድ ጊዜ ስለነበር
👉 አንድ ቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብዬ የሚያውቁኝ ልጆች በአጠገቤ ሲያልፉ አየሁ እነሱ በጣም ተጎሳቁየ ስለነበር አለዩኝም ነበር ግን ድንገት የሚያውቀኝ ሰው አይቶኝ ለአባቴ እንዳይናገር ፈርቼ ለምኜ ወደ ደብረዘይት ሄድኩ።
👉 እዛም መነሀሪያ አካባቢ የሚያድሩ ልጆች ጋር ጎዳና መኖር ጀመርኩ፣ከዛም የህይወቴን ከባዱን የመራብና የመጠማት ጊዜ አሳለፍኩ
👉 ከዛም ልሞት ስለመሰለኝ፣ከሞትኩም በቃ የሚያውቀኝ ሰው እንዲያገኘኝ አዲስ አበባ ሄጄ ልሙት ብየ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ጀመርኩ
👉 እኔ ደክሞኝ ተስፋ ቆርጬ በጨረስኩ ሰዓት እግዚአብሔር ጀመረ፣ የተሳፈርኩበት ሚኒባስ ውስጥ ታሪኬ እንዲቀየር ምክንያት የሆነችዋን ሴት አገኘሁ....................ይቀጥላል
።©የእውነትመንገድ
@psychoet

በ19 አመቱ በአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት ሰርጎ በመግባት እና ብዙ የሀገሩን ሚስጥሮች ሰርቋል በሚል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ 15 አመት ተፈርዶበት ህይወቱን በእስር ቤት እየመራ ይገኛል ።
አባቱ ብቻቸውን የሚኖሩ አዛውንት ነበሩ ። አንድ ቀን ድንች ለመትከል ፈልገው በእድሚያቸው መግፋት ምክንያት ጥንካሬ አልነበራቸውም :
ከዚያም ለታሰረው ልጃቸው እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ
::
"ውድ ልጄ የአትክልት ስፍራውን ለመቆፈር እና ድንች ለመትከል እንድትረዳኝ አሁን ከእኔ ጋር ብትሆን እመኝ ነበረ ። አሁን የሚረዳኝ የለኝም። "
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አባትየው ከልጃቸው ደብዳቤ ደረሳቸው።
"አባባ እባክህን አትቆፍር ፤ ምክንያቱም አንድ ጠቃሚ ነገርስለደበቅኩኝ ከእስር ቤት ስወጣ ምን እንደሆነ እነግርሃለሁ።"
የልጃቸው መልእክት በተጻፈ በአንድ ሰአት ውስጥ የምስጢርአገልግሎቱ እና ሰራዊቱ ቤቱን ከበቡ።
በደቂቃዎች ውስጥ የአትክልት ስፍራውን ቆፍረው ሁሉንም ነገር አስወግደው ምንም ነገር ሳያገኙ ቤቱን ለቀው ወጡ።
ከሳምንት በኋላ ከልጃቸው ሌላ ደብዳቤ ደረሳቸው ።
"አባዬ መሬቱ በፖሊስ በደንብ እንደታረሰ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ድንች መትከል ትችላለህ ። ሌላ ነገር ስትፈልግ ኣሳውቀኝ ፤ የእስር ጊዜን ጨርሼ እስክመጣ ድረስ ካንተ ጋርመሆን አልችልም ነገር ግን በምችለው መንገድ ለመደገፍ የተቻለኝን አደርጋለሁ። "

አርጀንቲናዊ ነው ፡ Jorge Mario Bergoglio ይባላል ፡
ይህ ወጣት የኬሚስትሪ መምህር ሆኖ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ፡ ይህንን ስራ በመተው ፡ በቦነስ አይረስ የምሽት ናይት ክለቦች የበር ላይ ጥበቃ ሆኖ ሰርቷል ።
ስራው በቀጥታ ናይት ክለቡን መጠበቅ ሳይሆን ፡ ወደ ክለቡ የሚገቡትን ሰወች መፈተሽ ፡ እድሜያቸው አጠራጣሪ የሆኑ ወጣቶችን መታወቂያ እያዩ ማስገባት. .
አንዳንዴም በናይት ክለቡ ውስጥ ግጭት ሲኖር ጣልቃ በመግባት ማስማማት የመሳሰሉ ስራዎችን ነበር የሚሰራው ።
..
Jorge Mario በሀያ አመት እድሜው ባጋጠመው አደገኛ ህመም ምክንያት አንድ ሳንባው ተቆርጦ እንዲወጣ ሲደረግ ብዙዎች ረጅም እድሜ እንደማይኖር ገምተው ነበር ። ሆኖም ያጋጠመው የጤና እክል ተጨማሪ 68 አመታትን ፡ በህይወት እንዳይኖር አላገደውም ።
...
ይህ ከላይ ያነሳነው ታሪክ ፡ በ88 አመት እድሜያቸው ዛሬ በሞት የተለዩት የካቶሊኩ ጳጳስ የፖፕ ፍራንሲስ የወጣትነት ታሪክ ነው ።
.......
ከናይት ክለብ ባውንሰርነት ፡ የካቶሊክ ጳጳስ እስከመሆን የደረሰ ስብእና ።
........
በአንድ ወቅት በምንም ሁኔታ ውስጥ ልታልፍ ፡ ትችላለህ ሆኖም አንድ ቀን የዛሬው ማንነትህ ተቀይሮ ታላቅ ደረጃ እንደምትደርስ ፡ የኚህ ጳጳስ ህይወት ከተራ ማነቃቂያ ያለፈ የህይወት ምስክርነት ነው ።

ከሥራ ደክሞኝ ነው የመጣሁት፣ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳልኩኝ ባለቤቴ በብርጭቆ ውሃ ሰጠችኝ ፣ ልጄ አንድ ወረቀት ሰጠኝ ወረቀቱ ላይ የተፃፈው እንዲህ ይነበባል ።
እንግሊዝኛ .......17 ከመቶ
ባዮሎጂ ...........35 ከመቶ
ሒሳብ ..............40 ከመቶ
ፊዚክስ .............37 ከመቶ
ኬሚስትሪ ..........42 ከመቶ
ኢኮኖሚክስ ........12 ከመቶ
እርሻ...................19 ከመቶ
ጂኦግራፊ ...........22 ከመቶ
ንዴቴን መቆጣጠር አቅቶኝ " ይሄ ምንድነው? ሁልግዜ ሞባይል እና ቴሌቪዥን ላይ ነህ። እንዴት ይህን ማርክ ውጤት ብለህ ለማሳየት ደፈርክ?" በጩኽት ልጄን ተቆጣውት።
ባለቤቴ " ትእግስት ይኑርህ አዳምጠኝ.... " ስትለኝ ።
ንግግሯን ሳትጨርስ "ዝም በይ ልጁን ያበላሸሽው አንቺ ነሽ! ከዚህ በኋላ መቼም ሰው አይሆንም " አልኳት ።
ሚስቴ"ይገርማል! አለች።
"በቤተሰባችን እንደዚህ አይነት የወረደ ውጤት ያመጣ የለም" በንዴት እና በጩኽት ተናገርኩኝ።
ልጄ አጠገቤ መጣና " አባዬ ንዴት ውስጥ እንድትገባ ስለአደረኩህ አዝናለሁ ፤ ቁምሳጥኑን ሳፀዳ በ1977 ዓ.ም የአንተ የፈተና ውጤት ሪፖርት ነው"አለኝ ።
ስሙን ሳየው የእኔ የድሮ የትምህርት ቤት ውጤት ካርድ ነው፣ ስሜ በትልቁ የትፃፈበትን የፊት ለፊት ካርዱን አላየሁትም ነበር።

አንድ እስረኛ በስቅላት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል ነገር ግን የሳይንቲስቶች ቡድን የሰዎችን እምነት እና የአዕምሮ ጥንካሬን ለመፈተሽ ፈለጉና ከስቅላት ይልቅ በእባብ ንክሻ እንደሚገደል ነገሩት።
የበለጠ አሳማኝ ለማድረግ አንድ ትልቅ አስፈሪ እባብ አሳዩት። እስረኛው በፍርሃት ተሞልቶ ዓይኑን ታሰረ። ሳይንቲስቶቹ እስረኛው ሳያውቅ በእባብ ንክሻ በሚመስል መልኩ እጁን በስለታም መርፌ ተጠቅመው የእባብ ንክሻ አስመስለው ወጉት።
ከዚያም ራቅ ብለው ሲመለከቱ እስረኛው በእባቡ እንደተመረዘ በማመን በሰውነቱ ውስጥ የመርዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ምንም እንኳን ትክክለኛ መርዝ ባይኖርም ሰውዬው በእባቡ ንክሻ ላይ ያለው እምነት በፍጥነት አካላዊ ውድቀትን አስከትሎ በደቂቃዎች ውስጥ ሰውየው ወድቆ ሞተ።
ይህ ክስተት አስደንጋጭ ቢሆንም እምነት እና መጠበቅ እውነተኛ አካላዊ ውጤቶችን ሊያመጣ የሚችልበት (placebo effect) የፕላሴቦ ተጽእኖ በመባል ይታወቃል፡፡ አእምሮ ምን ያህል ኃይለኛ እንደሆነ ያሳያል።
አእምሮ የእኛን እውነታ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ሊቀይረው ይችላል። በዚህ ሁኔታ እስረኛው በእጣ ፈንታው ላይ ያለው እምነት በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ሰውነቱ ምንም እንኳንበእባቡ ባይነደፍም ንክሻው በእውነት የተከሰተ ያህል ምላሽ እንዲሰጥ አድርጓል።
ይህ ታሪክ ወሳኝ ትምህርት ያስተምረናል፡፡ ሀሳቦቻችን፣ እምነቶቻችን እና አመለካከቶቻችን በደህንነታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ስለራሳችን እና ስለ ህይወታችን የምናምነው ነገር ሊያነሳን ወይም ሊጥለን ይችላል።
ስለዚህ አእምሯችን እውነታዎቻችንን የመቅረጽ አቅም ስላለው አዎንታዊ አመለካከትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። የሃሳብህን ሃይል በፍፁም አቅልለህ አትመልከት። በጥንካሬዎ እና በችሎታዎ ማመንን ይምረጡ ምክንያቱም አእምሮዎ ፈተናዎችን ለማሸነፍ ትልቁ አጋርዎ ሊሆን ይችላልና፡፡
©️ከመፅሐፍት አለም

የማያዛልቃችሁን ሰው ለዩ!
በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሼር አድርጉት
ከሚከተሉት ባህሪያት ቢያንስ አንዱን የምታዩባቸው ሰዎች ምናልባት ብዙም የማያዛልቋችሁና አንድ ቀን ለስሜት ጉዳት አጋልጠው የሚሰጧችሁ አይነት ሰዎች እንደሆኑ ጠርጥሩ፡፡
• ራሳችሁንም ሆነ ያላችሁን ነገር በነፃ ስላቀረባችሁላቸው፣ ልክ እንደ ርካሽ የሚቆጥሩና የማያመሰግኑ ሰዎች፡፡
• በዓላማችሁና ለማደግ በምታደርጉት የየእለት ጥረት የሚያላግጡና የሚያሾፉ ሰዎች፡፡
• እየጠፉና እየቆዩ ለአንድ ነገር አማራጭ ሲያጡና ያንን ነገር ከእናንተ ብቻ እንደሚያገኙ ሲያውቁ ብቻ የሚፈልጓችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተንና ወዳጅነታችሁን ሳይሆን የእናንተንና ያላችሁን ነገር ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች፡፡
• በፍጹም የማያምኗችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታችሁን እየቆጠሩ የሚወቅሷችሁና በፍጹም ይቅር የማይሏችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታቸው እንዳይገኝባቸው እናንተን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች፡፡
• ሰዎችን ለእናንተ የሚያሙና ስለሰው ክፉን የሚያወሩላችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተ የጀመራችሁትን ነገር እነሱ እንደጀመሩት አድርገው ለማሳየት የሚጣጣሩ ሰዎች፡፡
• ለእነሱ መኖር፣ መስጠትና መልካም ነገር ማድረግ፣ ልክ እንደ ግዴታችሁ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች፡፡
(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጨዋታ እንግዳ ላይ ከመዓዛ ብሩ ጋር በነበረው ቆይታ ላይ መዓዛ እንዲህ ስትል ጠየቀችው ፦ “ዶ/ር ዳዊት ላንተ የተሠጠህ ትልቁ ሥጦታ የቱ ነው ?" “ዶ/ር ዳዊት፦ ሁሌም ይህን ጥያቄ ስጠየቅ በተደጋጋሚ የምመልሰው መልስ ይሄንን ነው። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሬዝዳንት ሆኜ ስሠራ አንድ ምስኪን ገበሬ ከአምቦ አካባቢ ልጃቸው በጠና ታሞ ይዘው መጥተው እንከታተልላቸው ጀመር ልጁም ከቀን ወደ ቀን ለውጥና መሻሻል ማሳየት ጀመረ፡ አባትም ቢሮዬ ድረስ መጡ። “ዶክተር እንደው እባክህ ከድፍረት እንዳታይብኝ እባክህ ብለው ተጨናነቁ” ፤ ምንድነው አባቴ? አልኳቸው እሳቸውም ወጣ ብለው ማዳበሪያ ተሸክመው መጡ ። ማዳበሪያ ውስጥም በቆሎ እሸት ነበረ ። “ይሄ ነው የደረሰው ብለው” እሱን ሲሰጡኝ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር፡ ተርፏቸው ሳይሆን ካላቸው ላይ ነበረ ለኔ ሥጦታ ብለው ያመጡልኝ።”
አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦
“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።
ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።
ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት!።”
©ሞገስ ዘአምደ

ይህ የኢትዮጵያውያን ህክምና ባለሙያወች ታሪክ ነው ::
የአፍሪካ ዝቅተኛዋ ደሞዝ ከፋይ ሀገር
Specialist ሀኪም ወርሀዊ 120ዶላር
አጠቃላይ ሀኪም 84ዶላር
ነርስ 70ዶላር ወርሀዊ ክፍያ ምትከፍል ብቸኛ ሀገር ናት
ራሱን ለtb, hepatitis virus,hiv እና ሌሎች መሰል በሽታወች አጋልጦ ሚሰራው ሀኪም የጤና insurance የለውም።በትንሽ ክፍያ ሚሰራው የጤና ባለሙያ ለዚህ ሁሉ በሽታ ተጋልጦ እየሰራ ያለ insurance እየሰራ የጤና መድህን እንኳን ተጠቃሚ እንዲሆን አይፈቀድለትም?
ህይወት ሲያድኑ ኖረዋል አሁን ግን ህይወታቸውን ልናድን ይገባል!
ከሀኪሞች ጎን እቆማለሁ#
ሼር ይደረግ

ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
#Share
የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡
ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?
ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡
የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ
ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡
ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት
በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡
ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?
❖ተግባራዊ ግብ
በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡
❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ
ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡
❖ጽናት
ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡
❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም
ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡
❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል
እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡
(በአሸናፊ ካሳሁን)©Zepsychology

ማኔጅመንት እወቅ!
ምንም ትምህርት ብትማር ማኔጅመንት/አስተዳደር ልታውቅ ያስፈልግሃል።
ማኔጅመንት፣ አስተዳደር፣ አመራር፣ ቁጥጥር የተባሉት የትምህርት ወይም የእውቀት ዘርፎች አንድነትና ልዩነት አላቸው። መሠረታቸው ግን ማኔጅመንት ነው። ማኔጅመንት ሁሉን-አቀፍ ነው። ማኔጅመንት ውስጥ አመራር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ አስተዳደር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ መቆጣጠር አለ።
ማኔጅመንት ገሪነት ነው። ማኔጅመንት ሥራን፣ ሰውን፣ የአሠራር ባህልን ይገራል። ማኔጅመንት የገሪነት ሚናውን የሚጫወትበት ብዙ ሞዴሎች፣ ስልቶች እና ዘዴዎች አሉት።
የብዙ ችግሮች መፍትሔ ማኔጅመንት ውስጥ አለ። ህይወትህን በስርዓት ለመምራት ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ነው። ማኔጅመንት እውቀት ከሌለህ ችግር መዝዘህ እንኳን ሊተገበር ያልታለመ ችግር ውስጥ ትዘፈቃለህ። ግዴለም ማኔጅመንት እወቅ!
መጀመሪያ የተማርከው ምንድን ነው?
የተማርከው ምንም ይሁን ማኔጅመንት ብታውቅ ህይወትህ ለማቃናት ትልቅ እገዛ ያደርግልሃል። ማኔጅመንት ካላወቅህ ግን ሌሎች ይጫወቱብሃል። አንተም ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ ታባክናለህ። ችግርህን ለመፍታት የሚችል ሲስተም ያጥርህና ትግል እና ግጭት ውስጥ ትገባለህ።
ልብ በል! ከዚህ ቀደም እንዳልነው
SYSTEM = Save Your Self Time, Energy Money ማለት ነው።
ለራስህ ይሁን ለሀገርህ ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ የሚቆጥብ ወይም የሚያባዛ ስርዓት ካልፈጠርህ ከንቱ ድካም እና የችግር አዙሪት ቀለበት ውስጥ ነህ።
የተማርከው ህክምና ይሁን ምህንድስና፣ ህግ ይሁን ፍልስፍና ለውጥ የለውም። ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ይልሃል።
ማኔጅመንት ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ እና መቆጣጠር የሚሉ ዋና ተግባራት አሉት።
ለማቀድ ግብን እና የትኩረት አቅጣጫን መምረጥ ይጠይቃል። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ያገኘው ጦርነት ውስጥ ነጠላዬን አቀብሉኝ ብሎ ዘው ብሎ አይገባም። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ጦርና ጋሻ በእጁ ስላለ፣ ስልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጠ፣ ህግ ስለሚደግፈው ያየውን ችግር ሁሉ በህግና በጉልበት ልፍታ አይልም። ይህ የሚገባህ ማኔጅመንት ስታውቅ ነው። ማኔጅመንት በጠርሙስ ታሽጎ ያለን ጂኒ ክዳኑን ከፍቶ ራሱን ችግር ውስጥ አይጥልም።
ማኔጅመንት ስታውቅ ዋናውን እና ቀላሉን፣ ጠቃሚና ገለባውን፣ ግንድ እና ቅርንጫፉን ለይተህ የምታተኩርበትን ትመርጣለህ፤ ብራንድህን በፈለግኸውና ጠቃሚ በሆነ መስመር ትገነባለህ፤ ለሥራና አገልግሎትህ በቂ ክፍያ የሚያስከፍል ስርዓት ትዘረጋለህ፤ የመቆጣጠሪያ ዘዴ ትዘረጋና አካሄድህን እየለካህ በመገምገም ማስተካከያ ታደርጋለህ።
ማኔጅመንት ከታች ጀምሮ በየትምህርት ሳይክሉ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ቢሰጥ ጠቃሚ ነው። በኮሌጅ ደረጃ ላሉም የትምህርት መስኩ ቢያንስ 2 የማኔጅመንት ኮርስ ሊሰጥ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ። ማኔጅመንት የማያውቅ "አዋቂ" ስራው ስርዝ-ድልዝ ዓይነት ነው።
በነገራችን ላይ በደረጃዎች የተከፋፈለ Mini-MBA የሚባል ስልጠና አለን። ይህ ስልጠና ለብዙዎች አስፈላጊ ነው።
የህግ ሰው ብትሆን፣ ሀኪም ብትሆን፣ መሃንዲስ ብትሆን፣ ኢኮኖሚስት ብትሆን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህር ብትሆን፣ ፖለቲከኛ ብትሆን፣ የታክሲ ሾፌር ብትሆን፣ የኳስ አሰልጣኝ ብትሆን፣ ባል ብትሆን፣ ሚስት ብትሆኚ፣ ሚኒስትር ብትሆን፣ ፓስተር ብትሆን፣ ... ማኔጅመንት ካላወቅህ ችግር ውስጥ ነህ። ማኔጅመንት እወቅ!
ችግር የሚፈጠረው ማኔጅመንት ባለማወቅ ነው። ችግር የሚፈታውም የማኔጅመንት ስልት በማወቅ ነው።
የሀገራችን ህዝብ የማኔጅመንት እውቀት ከፍ ሊል የተገባ ነው።
የህዝባችን የማኔጅመንት እውቀትና ልምድ ሲዳብር የመነጋገሪያ አጀንዳችን ይቀየራል፣ የጠራ ግብ ይኖረናል፣ የትኩረታችን አቅጣጫ ይቀየራል፣ ችግርን ለመፍታት ሚና ሚናችንን ለይተን እንደራጃለን፣ አካሄዳችንን ከግባችን አንጻር እየለካን፣ እየገመገምን እና እያስተካከልን ወደ ግባችን እንገሰግሳለን።
ማኔጅመንት የእውቀት ሁሉ መቋጠሪያ ነው።
የማኔጅመንት ትምህርት ስለሲስተም ነው።
ማኔጅመንት ሳይንስም ጥበብም ነው።
እስኪ በዚህ የማኔጅመንት መነጽር ሰሞኑን አየር ላይ የናኙትን የአስጌ ደንዴሾን የመክሰስ ሀሳብ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሀኪሞችን Enough is Enough የሚል የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ፣ የኢሠማኮ የደሞዝ ወለል ይደንገግልኝ ጥያቄ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የሰይፉ እና ኩኩ ኢንተርቪው፣ የቴዲ ኮንሰርት እና ሌሎችም ሰፊ ሽፋን ያገኙ የሀገራችን ጉዳዮች ፈትሹት።
የቱ ለዓቅመ-አጀንዳነት ይበቃል? የቱ በየትኛው ስልትና ዘዴ ሊኬድበት ይገባል? የቱ ሰፊ ጊዜ ይፈልጋል? የቱ ሀገራዊ አጀንዳ ነው? የሁሉም ችግር ስረ-መሠረትስ ምንድን ነው?
በጨዋነት እንወያይ።
#Focus!
Get Toughe Zer

መለወጥ መፈለግ ጥሩ ጅምር ነው። ግን በቂ አይደለም። እውነታው ግን ህልሞች ያለድርጊት ህልም ሆነው ይቀራሉ:: ሁሉንም መጽሃፍቶች ማንበብ፣ ሁሉንም አነቃቂ ቪዲዮዎች መመልከት እና ፍጹም የወደፊት ዕጣህን በጭንቅላትህ ማቀድ ትችላለህ። ነገር ግን አንድ እርምጃ ካልወሰድክ እና ትንሽም እንኳን እንቅስቃሴ ከሌለ ምንም ነገር አይለወጥም::
ዝግጁ አንደሆንክ ስለተሰማህ ብቻ ለውጥ አይመጣም። ለውጥ የሚመጣው ያለሁበት ቦታ መቆየት ሰለቸኝ ብለህ ቆርጠህ የተነሳህ ጊዜ ነው። እንደ መብረቅ የሚያነሳሳህን ነገር መጠበቅ አቁም። ለራስህ 'ነገ' ማለትን አቁም:: የተሳካላቸው ሰዎች ሁልጊዜ የተነሳሱ አይደሉም ነገር ግን ስሜታቸው ባይሆኑም እንኳ የሚንቀሳቀሱ ናቸው:: ስለዚህ ጀምር። የተመሰቃቀለ፣ ዘገምተኛ፣ የማይመች ቢሆንም ለማንኛውም ጀምረዉ። ምክንያቱም ባለህበት ቦታ መቆየትም ይጎዳል ነገር ግን ልዩነቱ - አንዱ ወደ ፀፀት ሌላኛው ደግሞ ወደ እድገት ይመራል::
©Dani

#ስንፍና_ማሸነፊያ_8ቱ_የጃፓን_ዘዴዎች
1- ኢኪጋይ፦ በጠዋት ከአልጋህ በደስታ የምትነሳበትን የሕይወትህን ዓላማ ፈልግ።
2- ካይዘን፦ ትልቅ ውጤትን ከመጠበቅ በየቀኑ ትንንሽ መሻሻሎች ላይ አተኩር።
3-ሾሺን፦ ሁልጊዜ የትኛውንም ስራ የጀማሪነት አስተሳሰብ ይዘህ ቅረብ።
4-ሃራ ሃቺ ቡ፦ ሆድህ 80% ሲሞላ መብላትህን አቁም።
5-ሽንሪን ዮኩ፦ የተፈጥሮ ሻወር ማለት ነው። ተፈጥሮ ውስጥ ጊዜ ማሳለፍን ልመድ።
6- ዋቢ ሳቢ፦ ሁሉም ነገር ፍጹም አይሆንም። ፍጹም ያልሆነው ነገር ውስጥም
ውበትን እይ።
7-ጋንባሩ፦ በየትኛውም ትግዳሮት ውስጥ የምትችለውን ያህል ጥረት በማድረግ ስራ።
8-ጋማን፦ ነገሮች ሲከብዱና ሲከፉ ትዕግስትና ጽናት ይኑርህ።

አንብቡና አትርፉ!!!!
አንድ የሳይኮሎጂ መምህር ተማሪዎቹ የዉሳኔ እና ተግባርን ልዩነት እንዲረዱ በማሰብ አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ጥያቄዉም ...... "በአንድ ዛፍ ላይ የተቀመጡ ስምንት ወፎች አሉ ብላችሁ አስቡ፤ከነዚህ ስምንት ወፎች መሃል ስድስቱ ለመብረር ቢወስኑ ስንት ወፎች በዛፉ ላይ ይቀራሉ???" የሚል ነበር።
አብዛኞቹ ተማሪዎች "ሁለት ወፎች ብቻ ናቸዉ የሚቀሩት!!" ሲሉ ይመልሳሉ።
አንድ ተማሪ ግን "በዛፉ ላይ የሚቀሩት ወፎች ስምንት ናቸዉ።" በማለት ይመልሳል።
መምህሩም እንዴት ስምንት ወፎች ሊቀሩ እንደሚችሉ እንዲያብራራ ይጠይቁታል...
ተማሪዉም "ጥያቄዉ ወፎቹ ለመብረር መወሰናቸዉን እንጂ መብረራቸዉን አይገልፅም!!!ዉሳኔ እና ተግባር ፍፁም የተለያዩ ናቸዉ!!!!"ሲል ያብራራል
መምህሩም ትክክለኛው መልስ ልጁ የመለሰዉ እንደሆነ በመግለፅ ....."ብዙዎች ይህን አደርጋለሁ፣ይህን አላደርግም ሲሉ በተዋቡ ቃላት መወሰናቸውን ሲገልፁ ይሰማሉ፤ይሁን እንጂ ኑሯቸዉን ስትመለከቱ ተናገረዋቸዉ የነበሩ ዉቡ ቃላቶችን አታገኟቸዉም።ብዙዎች ያወራሉ ጥቂቶች ብቻ ይተገብራሉ፤ዉሳኔ አንድ ነገር ነዉ ተግባር ግን መገለጫ ነዉ።
ከጠቀማችሁ,ሌሎችም እንዲያነቡ አድርጉ,,,