Telegram Web Link
Forwarded from Book center📚👥
-💙🦋

〖 ልብ ብለው ያንብቡት ራሳችንን የምናይበት አስገራሚ ታሪክ〗

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች።
አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ
ካሉት ሱቆች ኩኪስና መጽሐፍ ገዛች።

ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት)
ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር
አመራች። ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች።

አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል። በሁለት መደገፊያ
ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል መተከዢያ
ሆኗታል።

ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት።
ሳያስፈቅዳት መውሰዱ አስደነቃት። ግን ዝም አለች። ቀጥላ
እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ አሁን ተበሳጨች።
ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።

በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ
አይደለም በኩኪስ ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር አልፈለገችም።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች።

" ይሄ የተረገመ ሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል አሰበችና
በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰውየው ኩኪሷን ሁለት
ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት።
ከልክ ያለፈ ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

ሰዓቱ ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን ማመን
አልቻለችም። ያልተከፈተው የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ
ውስጥ አለ። በጣም አፈረች ተሸማቀቀች።

ለካስ የራስዋን ኩኪስ ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም ያጸጸታት ሰውየው
እስከ መጨረሻው አንዲት ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት
የነበረው ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ ስትበሳጭበት
በመቆየቷ እጅግ አፈረች። አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን
ጊዜው አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ ሐገሩ
አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳን
የላትም።

ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣
ግን ሁሉም እሷው ጋ ቀሩ አልፏል።

አራት የማይጠገኑ ነገሮችን አሰበች፦
🔶 ️ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
🔶️ ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
🔶️ ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
🔶️ ጊዜ ካለፈ በኋላ ዋጋ እንደሌለው

እኛም ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን በፊት መጀመሪያ
ራሳችንን እንይ ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው ልናከብራቸው
የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ
እናመስግናቸው።ጊዜ ካለፈ በኋላ እድሉ አይገኝምና ዋጋ የለውም።

የውጭ ምንዛሪ ዋጋ የሚመነዘረው በወቅቱ በቀኑ በተሰጠው
የምንዛሬ ዋጋ ብቻ ነው። በትናንት የምንዛሪ ዋጋ ዛሬ መመንዘር አይቻልም።

ስለዚህ ለገጠመን መልካም ነገር ዋጋ መስጠት ያለብን ቀን ሲሆን ደስ ይላል ካለፈ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በነበረበት አይቀጥልምና
ደስ አይልም።

ለዚህ አይደል በሕጉ ዓለም " የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል።" የሚባለው
«አስተዋይ ልብ መልካምነትን ይመራል»

📚

#begena_mezmur
______________________________________________
@books_centerr
@books_centerr
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Watch "Treat people with kindness!!" on YouTube
https://youtube.com/shorts/tQ86xTu8Aqg?feature=share
Watch "YOU THINK YOU'RE IN LOVE ? #SHORTS" on YouTube
https://youtube.com/shorts/fBgN_GSrjxQ?feature=share
🌧

Life isn't about waiting for the storm to pass It's about learning to dance in the rain.

💦
________
@realitysensation
@realitysensation
💜

A 14 year girl ask 20 year old brother what is love?

Brother replied...
I know you eat chocolate from my bag everyday. And I still keep it there.

#Tag_ur_brother
________
@realitysensation
@realitysensation
Forwarded from Henok (Tesla ∞)
When we see the Earth from space, we see ourselves as a whole. We see the unity, and not the divisions. It is such a simple image with a compelling message; one planet, one human race.
~Stephen Hawking
@science_of_cosmos
2025/07/08 15:43:51
Back to Top
HTML Embed Code: