Telegram Web Link
-💞🦋

BE WITH SOMEONE WHO WILL TAKE CARE OF YOU,NOT MATERIALISTICALLY,BUT TAKE CARE OF YOUR SOUL,YOUR WELL - BEING,YOUR HEART,AND EVERY THING THAT'S YOU.
___________________________________________________
@REALITYSENSATION
@REALITYSENEATION
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Book center📚👥
🍂 አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም
ብልህ ሁን ማለት እንጂ

🍁 ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም
ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!

🍂 ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም
በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!

🍁 አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም
ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!

🍂 ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም
በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!

🍁 ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!

🍂 ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!

🍁 ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት
አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ
ማለት እንጂ!

🍂 ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም
ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!

🍁 ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም
ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!

🍂 ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም
ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ
ሁን ማለት እንጂ!

🍁 እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት
አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!

🍂 አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም
ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!

🍁ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም
ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!

🍂 ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም
አምሮብሃል ማለት እንጂ!

🍁 ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም
ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!

ምርጥ መጣጥፎች
#begenamezmur
_____________________________________________
@books_centerr
@books_centerr
⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉

S et goals
E xercise
L ove yourself
F ocus on fitness

R elax
E at right
S mile
P ositive attitude
E njoy life
C are for others
T hink about others

@realitysensation
Forwarded from Book center📚👥
-💙🦋

〖 ልብ ብለው ያንብቡት ራሳችንን የምናይበት አስገራሚ ታሪክ〗

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች።
አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ
ካሉት ሱቆች ኩኪስና መጽሐፍ ገዛች።

ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት)
ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር
አመራች። ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች።

አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል። በሁለት መደገፊያ
ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል መተከዢያ
ሆኗታል።

ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት።
ሳያስፈቅዳት መውሰዱ አስደነቃት። ግን ዝም አለች። ቀጥላ
እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ አሁን ተበሳጨች።
ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።

በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ
አይደለም በኩኪስ ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር አልፈለገችም።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች።

" ይሄ የተረገመ ሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል አሰበችና
በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰውየው ኩኪሷን ሁለት
ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት።
ከልክ ያለፈ ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

ሰዓቱ ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን ማመን
አልቻለችም። ያልተከፈተው የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ
ውስጥ አለ። በጣም አፈረች ተሸማቀቀች።

ለካስ የራስዋን ኩኪስ ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም ያጸጸታት ሰውየው
እስከ መጨረሻው አንዲት ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት
የነበረው ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ ስትበሳጭበት
በመቆየቷ እጅግ አፈረች። አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን
ጊዜው አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ ሐገሩ
አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳን
የላትም።

ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣
ግን ሁሉም እሷው ጋ ቀሩ አልፏል።

አራት የማይጠገኑ ነገሮችን አሰበች፦
🔶 ️ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
🔶️ ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
🔶️ ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
🔶️ ጊዜ ካለፈ በኋላ ዋጋ እንደሌለው

እኛም ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን በፊት መጀመሪያ
ራሳችንን እንይ ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው ልናከብራቸው
የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ
እናመስግናቸው።ጊዜ ካለፈ በኋላ እድሉ አይገኝምና ዋጋ የለውም።

የውጭ ምንዛሪ ዋጋ የሚመነዘረው በወቅቱ በቀኑ በተሰጠው
የምንዛሬ ዋጋ ብቻ ነው። በትናንት የምንዛሪ ዋጋ ዛሬ መመንዘር አይቻልም።

ስለዚህ ለገጠመን መልካም ነገር ዋጋ መስጠት ያለብን ቀን ሲሆን ደስ ይላል ካለፈ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በነበረበት አይቀጥልምና
ደስ አይልም።

ለዚህ አይደል በሕጉ ዓለም " የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል።" የሚባለው
«አስተዋይ ልብ መልካምነትን ይመራል»

📚

#begena_mezmur
______________________________________________
@books_centerr
@books_centerr
2025/07/03 23:36:33
Back to Top
HTML Embed Code: