Forwarded from ወንጌሉ አገልግሎት | Wongelu Ministries
ሞትን መለማመድ | ጳጉሜ 5
ለእኔ የዓመት መጨረሻ እንደ ሕይወቴ መጨረሻ ነው። የዓመቱ የመጨረሻ ቀን፣ የመጨረሻ ሰዓት የሆነው ጳጉሜ 5 ከምሽቱ 11፡59 ሲል፣ ልክ እንደ ሞቴ ቅጽበት እቆጥረዋለሁ።
የዓመቱን 365 ቀናት እንደ አንድ የህይወት ዘመን ናሙና እመለከታቸዋለሁ። የዓመቱን የመጨረሻ ቀን ደግሞ የምመለከተው ልክ ዶክተሩ መጨረሻው በጣም እንደቀረበ ከነገረኝ በኋላ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዳሉኝ የመጨረሻዎቹ ቀናት ነው። በእነዚህ የመጨረሻ ሰዓታት ውስጥ፣ የዚህ ዓመት የህይወት ዘመን በዓይኔ ፊት ያልፋል፤ እናም አንድ የማይቀር ጥያቄ እጋፈጣለሁ፤ ይህን ሕይወት በሚገባ ኖሬዋለሁ? ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ” ይለኝ ይሆን (ማቴዎስ 25፥21)?
ዓመቴን የምጨርሰው በዚህ መንገድ በመሆኑ በጣም እድለኛ ነኝ። ለእናንተም የዓመቱ መጨረሻ ተመሳሳይ ትርጉም እንዲኖረው እጸልያለሁ።
እድለኛ እንደሆንኩ የሚሰማኝ ሞቴን መለማመዴ ትልቅ ጥቅም አለው ብዬ ስለማስብ ነው። ለሕይወታችን የመጨረሻው ትዕይንት ለመዘጋጀት በዓመት አንድ ጊዜ መለማመዱ ፋይዳው ቀላል አይደለም። ምክንያቱም መስከረም 1 ማለዳ አብዛኞቻችን በህይወት እንነቃለን፤ በአዲስ የህይወት ዘመን አፋፍ ላይ፣ እንደገና እንደ አዲስ መጀመር እንችላለን።
እንዲህ ያለው ልምምድ ትልቁ ጥቅም ድክመቶቻችን የት እንዳሉና ያልተዘጋጀንባቸው ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ ስለሚያሳየን ነው። በዋናው የግጥሚያ ዕለት በትክክለኛ ተመልካቾች ፊት እውነተኛውን ፍልሚያ ከመፋለማችን በፊት ለመለወጥ፣ ለማደግና ለመሻሻል ጊዜ ይሰጠናል።
ለአንዳንዶቻችሁ ስለሞት ማሰብ በጣም ከባድ ነው። አስፈሪ፣ አደንዛዥ፣ ጭልምልም ያለ፣ በሀዘንና በጭንቀት የተሞላ በመሆኑ በተለይ በበዓላት ወቅት ከአእምሯችሁ ለማስወጣት የተቻላችሁን ጥረት ታደርጋላችሁ። ይህ ግን ልክ አይመስለኝም። ስለ ሞት በጥበብ ማሰብ ይቻላል። ማሰቡ ደግሞ ጠቀሜታ አለው። በሕይወቴ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ሃሳቦች መካከል ስለ ራሴ ሞት በየሆነ ጊዜ ማሰብ ነው።
ምርጡን ኑሮ መኖር የሚቻልበትን ዘዴ ለማወቅ የሚያስችለውን ጠቢብ ልብ እንዴት ታገኛለህ? ዘማሪው እንዲህ ይመልሳል፦
“እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤ እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤ ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል….. ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።” (መዝ 90:5-6፣ 12)
ዕድሜን መቁጠር ማለት ህይወታችን አጭር እንደሆነ እና ሞታችን በቅርቡ እንደሚሆን ማስታወስ ማለት ነው። የሕይወትን አቅጣጫ የሚለውጥ ታላቅ ጥበብ የሚገኘው እነዚህን ነገሮች በየጊዜው በማሰላሰል ውስጥ ነው።
ጳውሎስ ሕይወቱን ለመለካት የተጠቀመበት የስኬት መስፈርት፣ “እምነቴን ጠብቄ ነበር ወይ?” የሚል ነው። “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።” (2 ጢሞ 4:7-8)። ይህ በየዓመቱ ማለቂያ ሕይወታችንን የምንለካበት ቱንቢና የምንመዝንበት ሚዛናችን ይሁንልን።
በዚህ በሚያልፈው ዓመት በእምነታችን እንዳልጠነከርን ወይም ማደግ ያለብንን ያክል እንዳላደግን ከተገነዘብን ደስ ሊለን ይገባል፤ ምክንያቱም ይህ አመት የመጨረሻው ሞት ልምምድ ብቻ ነው። ማንቂያ ደውላችን ነው። ከነገ ጀምሮ እምነታችንን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ለመፈጸም የምንችልበት ሙሉ ህይወት ከፊታችን አለ። ይህ አዲሱ ዓመት፣ እግዚአብሔርን የበለጠ የምናውቅበት፣ የምንወድድበትና የምንመስልበት ዓመት ይሁንልን!
Telegram | YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website
#ለዛሬ
“እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤ እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤ ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል። ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን” (መዝሙር 90፥5-6፣ 12)።

❤5👍1
ጊዜን መረዳት በሚል ርዕስ እሁድ ለት የተሰበክነው ምርጥ ትምህርት አለ።
ዘፍጥረት 1 ላይም ማየት እንደምንችለው አስቀድሞም እግዚአብሔር ቀንና ለሊትንና አመታት የሚጀምሩበትንም ወቅት እንዲያመለክቱ ብሎ መፍጠሩ የወቅትን መፈራረቅ ትርጉም እንድንሰጠው ያደርገናል። (I used to think that new year didn't really mean anything. I'm still not sure what exactly it means but I know it means something.)
መዝሙር 90 ላይ የተማርናቸው 3 ነጥቦች
1-2
"እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።"
1, ሙሴ እግዚአብሔርን refer የሚያደርገው በአዶናይነቱ ነው። ስለሰው ልጅ ህይወትና ጊዜ ስናስብ ሁልጊዜ መጀመር ያለብን ከጊዜ ውጪ በሆነው ዘለዓለማዊ አምላክ እንደሆነ ያስተምረናል።
2, እግዚአብሔር መጠጊያ፣ መኖርያ፣ ዘለቄታ ያለው ማደርያ ፣our dwelling place ነው። ይህንንም በታሪክ ውስጥ በትውልዶች መሀከል አይተናል።
3, የእግዚአብሔር ዘላለማዊነት ውስጥ ፈጣሪነቱ አለ። (ከሁሉ በፊት ስለነበረ) እንደነተራራና ምድር የገዘፉም ቢሆን ከእርሱ ውጪ ያሉ ነገሮች ሁሉ ፍጥረታት ናቸው። There is a categorical difference. ብቻውን ቀድሞ ስለነበረ እርሱ ማንም ላይ ጥገኛ አይደለም ፍጥረት ሁሉ ግን እርሱ ላይ ጥገኛ ነው። He is also transcendent from His creation. He's not confined to time, space and matter. በዚህ ውስጥ ቅድስናውን ፣ ሉዓላዊነቱን፣ አስተዳዳሪነቱን ፣ መጋቢነቱን ሁሉ መረዳት እንችላለን።
3-6
"ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ “የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤ ሺህ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣ እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና። እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበናሉ፤ እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤ ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።"
ሰው ሰው ነው። ከhumanity ጋር አብሮ የሚመጣውን limitation መገንዘብ አለብን። Its easy to forget that we can't be in control. ጊዜያዊ ነን። ዘፍጥረት 2 እንደሚናገረው ከአፈር (አስቀድሞ ከተፈጠረ ፍጡር) ተበጅተን የፍጥረት ቁንጮ መሆናችን የሚያስገርም ነው (መዝሙር 8)። ስለዚህ ወደተገኘንበት አፈር የምንመለስበትን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ይወስናል። ጊዜውን ሲወስን ደግሞ ለእኛ መረዳት ትርጉም ላይሰጥ ይችል ይሆናል። ረጅም እድሜን ከመፈለግ አንፃር የሰዎች መሞቻ እድሜ ግር ሊለን ይችላል። ግን በእግዚአብሔር perspective ልክ እኛ አንድ ቀንን ወይ እርቦ (4 ሰዓት) እንደምናሳጥር ሺህ አመት ትንሽ ነው። ስለዚህ በወደደው ጊዜ ሰዎችን ወደአፈር ይጠራቸዋል።
7-12
"በቊጣህ አልቀናልና፤ በመዓትህም ደንግጠናል። በደላችንን በፊትህ፣ የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ። ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤ ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን። የዕድሜአችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጒዳለን። የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው። ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።
Life is filled with suffering and toil. በሀጥያትና በእግዚአብሔር ቁጣ ስር ያለች ምድር ስለሆነች ከምድር መከራና ሰቆቃን አናመልጥም። እድሜያችንን በመቃተት እንድንጨርስ የሚያደርግ በቂ ህመም አለ። ስለዚህ 70 ና 80 አመት በቂ (ከበቂ በላይ) ነው። ከዚያ በላይ ለመኖር መጓጓትና ሞትን መፍራት ከንቱ ነው። እንደነማቱሳላ የተጋነነ ርዝመት ያለው ህይወት ለመኖር የሚፈልግ ሰው የሚኖርበትን ዘመን ያልተረዳ፣ የቁጣውን ሀይል ያላወቀ፣ የመዓቱን አስፈሪነት ያላስተዋለ ሰው ነው። (I also think only self absorbed people can ignore the suffering around them and desire immortality.)
ስለዚህ
ጥበብ የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ እድሜያችንን መቁጠር እንማር። ዘመናችንን value እንድናደርግና እያንዳንዱን ቀን ዋጋ እንድንሰጠው መማር አለብን። እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ።ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ። (ኤፌ 5:15)
13-17
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው። በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን። መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣ ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን። ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ። የጌታ የአምላካችን ሞገስ በላያችን ይሁን፤ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤ አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።

❤13👍2
I've been asked by some of you for a bible in a year calendar and this schedule allows you to go through the Old testament once and the New testament and the psalms twice by reading 4 chapters a day. Have a good one guys 😊
❤8
Forwarded from ወንጌሉ አገልግሎት | Wongelu Ministries
ኩራቴ ኢየሱስ ነው || All My Boast Is in Jesus
— ገላትያ 6፥14
መዝሙሩን ለማድመጥ 👇
YouTube link:- https://youtu.be/NiVU4eMiaJw
...ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
— ገላትያ 6፥14
መዝሙሩን ለማድመጥ 👇
YouTube link:- https://youtu.be/NiVU4eMiaJw
👍2❤1
Audio
You are my strength when I am weak
You are the treasure that I seek
You are my all in all
Seeking you as the precious jewel
Lord to give up I'd be a fool
You are my all in all
Jesus, Lamb of God
Worthy is Your name.
Taking my sins, my cross, my shame
Rising again, I bless your name
You are my all in all
When I fall down, You pick me up
When I am dry, You fill my cup
You are my all in all
Jesus, Lamb of God
Worthy is Your name!
You are the treasure that I seek
You are my all in all
Seeking you as the precious jewel
Lord to give up I'd be a fool
You are my all in all
Jesus, Lamb of God
Worthy is Your name.
Taking my sins, my cross, my shame
Rising again, I bless your name
You are my all in all
When I fall down, You pick me up
When I am dry, You fill my cup
You are my all in all
Jesus, Lamb of God
Worthy is Your name!
❤10
"Consider Christ so that He might become more central for you, that you may know Him better and treasure Him more and enter into His joy.
That is just how we will most honor the Father! By sharing His own everlasting delight in His son (John 5:23). Its also the secret of how to become like the Lord of love. (2 Cor 3:18). As we consider Him we will look at how He is our life, our righteousness , our holiness, our hope."
በህይወታችሁ ማዕከል ይሆን ዘንድ፣ በጥልቀት እንድታውቁት፣ እንደውድ ዕንቁ ይበልጥ እንድትሳሱለትና ወደፍስሀው እንድትገቡ ክርስቶስን አስቡት።
አብን የምናከብርበት ዋና መንገድ ይህ ብቻ ነው። አባት በልጁ ያለውን ዘላቂ ደስታ መጋራት። የፍቅርን አምላክ ለመምሰልም ሚስጥር ከዚህ ውጪ አይደለም። አተኩረን ባስተዋልነው ቁጥር እርሱ ህይወታችን፣ ፅድቃችን፣ ቅድስናችንና ተስፋችን መሆኑን እንረዳለን።
From the Memoirs and Remains of Rev Robert Murray M'Cheyne

❤7
Pursuing Holiness
የህግ ሚና ለአማኞች ከህግ በታች እንዳልሆንን የሮሜ መፅሀፍ በተለይም በምዕራፍ 6, 7 ያስረዳናል። በምሳሌው መሰረት አሁን ላይ we're not married to it. ለህጉ በመሞት ከቀንበሩ ነፃ ወጥተናል። ከፀጋ በታች ነን። ህጉን ጌታ ኢየሱስ ጠንቅቆ ፈፅሞልናል። ድነናል የምንለው በእርሱ ውስጥ ተሸሽገን ነው። ሀጥያታችንን ከድኖታል። በልጁ በኩል ስለሚያየን we are justified/right with…
I think its time to do a series on the 10 commandments. It will give me an excuse to study the practical implications and to make a case on why they (should) matter to us.
❤7👍3
ትዕዛዝ 1
“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።” ዘጸ 20፥3
ዋናው ነገር የእምነታቸው ጥንካሬ ወይ ትልቅነት ሳይሆን የምናምንበት አካል ነው። በተለይም ደግሞ ሀበሻ በግርድፉ ሀይማኖተኛ ስለሆነ ምናልባትም ስሜታዊ ሆኖ የሚያወራለት እምነት ይኖረዋል። ይበቃኛል በሚለው አቅም የሚተጋበት sincere አምልኮ አለው። የእግዚአብሔር demand ደግሞ ከሌሎቹ ጣዖታት በተለየ መልኩ ለብቻው መመለክን demand ያደርጋል። Only He has divine rights over all. ይህ ለእኛ 3 ዋና ዋና implications አሉት
1, እግዚአብሔርን ብቻ ማምለክ አለብን
ከእግዚአብሔር በቀር አምልኮ የተገባው የለም። Henotheism ወይንም ደግሞ ካሉት አማራጮች መሀከል እግዚአብሔርን መምረጥ አይደለም የሚበቅብን። Monotheism begins by acknowledging that all the other "gods" have no ontological existence.
ከእስራኤል የጀመረ syncretism የሚባል ቅዱሱን የእግዚአብሔር ሀይማኖት ከሀሰተኛ ጣዖታት ጋር የመቀየጥ ልምድ አለ። (ኢያሱ 24:14, 1 ነገስት 18:21, ማቲ 6:24) ይሄ ዛሬ ላይም የቀጠለ ልምምድ ነው። ብዙዎቻችን እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ በመኖሩ ደስተኞች ነን። የህይወታችንን የሆነ ክፍል በመስጠታችን አይደብረንም። የምንሰጥበትን መጠን የምንወስነው እኛው ነን። ደፍረን አንለውም እንጂ managable የሆነ በሰጠነው ክፍል ብቻ የሚመለክ አምላክ ነው የምንፈልገው።
Calvin commented on "You shall have no other gods before me" as God forbidding us from showcasing our idols before his face just as a husband would never want to see his wife bringing the guy she is cheating with.
ከካልቪን ጋር በዚህ አተረጓጎም ባንግባባ እንኳ ለአምልኮ ትዳር ጥሩ analogy ነው። ማንም ሚስቱን እወድሻለው ካለ በኋላ ሌላ የምወዳትን ልጅ ስላገኘው ከእርሷም ጋር የተወሰነ ጊዜ አሳልፋለው። ግን አንቺም ለኔ ቦታ አለሽ። ሁለታቹም ለኔ ዋጋ አላቹ ቢል ምላሿን መገመት አይከብድም።
If she's gracious she will rightfully give him an ultimatum to leave her or the new woman he is interested in. Who would condemn her for being cruel, emotional, jealous, intolerant or unfair? ትዳር የሚጠይቀውን መሰጠት የሚረዳ ሰው ታድያ አምልኮን ከዚያ አብልጦ መገንዘብ አለበት። እግዚአብሔርን እንወዳለን ካለን በእርሱ ልክ የምንወደው ነገር መኖር የለበትም። ስለፍቅር ስናወራ ደግሞ ከስሜታዊነቱ በስቲያ ያለውንም ውሳኔና ድርጊት ዳራ መገንዘብ አለብን።( ዘዳግም 6:4-5)
2, ጣዖታትን አስወግዱ
የምንወደው የheidelberg ካታኪዝም ጣዖትን ሲያብራራ "having or inventing something in which one trusts in place of alongside of the only true God who has revealed himself in his word." በማለት ነው። በቃሉ ውስጥ ከምናውቀው ያህዌ ውጪ ያሉ መታመኛዎቻችን ሁሉ ጣዖታት ናቸው። እዚህ ላይ ከሰው ባህሪ የማይገባኝ ነገር ነበር። አንድ rational የሆነ ሰው እንዴት በራሱ እጅ የሰራውን ቁስ ወይ ደግሞ ሰው ሰራሽ እንደሆነ በሚረዳው ነገር ለመታመን ይፈተናል? Doug Stuart በዚህ ጉዳይ ላይ ጣዖታት offer የሚያደርጉትን መሳቢያቸውን ያብራራል።
1, ዋስትና ይሰጣሉ: የተቀመጠውን ቀመር ተከትለን ከታዘዝን እና መስዋዕቱን በትክክል ካቀረብን ይሰራልናል የሚል እርግጠኛነት
2, ራስ ወዳድ motivation: አማልክቱ መስዋዕት ካልበሉ ይጠፋሉ። ስለዚህ ሰውን የሚተባበሩት ለራሳቸው በማሰብ መሆኑ አምልኮውን mutually beneficial ውል ያደርገዋል።
3, ቀላል ነው : ምንም አይነት moral code ወዮ ቅድስና አይጠይቅም። መስዋዕቱን እና የተቀመጠውን ritual የተገበረ ሁሉ ተቀባይነት አለው።
4 Convenient ነው: ከእዮርባም ጀምሮ የተዘረጋው system ጣዖታትን ማምለክ የተመቸና ድካም አልባ እንዲሆን አስችሏል። God restricted sacrifice to the tabernacle and later in the temple. አሁን ደግሞ አምልኳችን በእውነትና በመንፈስ መሆን አለበት የሚል መለኪያ አለው። አብዛኞቹ የአምልኮ ቀን መርሀግብሮች በቃሉ define ተደርገዋል።
5, Culturally normal ነበር: በዙርያቸው የነበሩ ሀገራት ሁሉ በስም ለየት ላሉ ጣዖታት ተመሳሳይ አምልኮን ያቀርቡ ነበር። ስለዚህ ከጎረቤቶቻቸው ጋር fit እንዲያደርጉና እንዲቀላቀሉ፣ እንዲጋቡ በር ይከፍታል። በዛን ጊዜ monotheist መሆን ከባድ ነበር።
6, logical ይመስላል: ለተፈጥሯዊው አዕምሮ አንድ አሞላክ አንድን ነገር ብቻ ይቆጣጠራል የሚለው ሀሳብ ትርጉም ይሰጣል።
7, ስጋን ደስ ያሰኛል: የሚታዩ ብዙ ቆንጆ እና አጓጊ ነገሮች ነበሩት።
8, indulgent ያደርጋል : በዘወትር ህይወቱ እያረደ የማይበላውን ሰው የመስዋዕቱን ድግስ እንዲበላ እድል ይሰጣል። ምርጥ ምርጡን ምግብና ወይን እንዲለምዱ ያደርጋል።
9, erotic ነበር: አማልክቱ ሀሰተኛ በመሆናቸውና በዘመናችንም ስለተለያዩ cults እንደምናውቀው ሁሉም አይነት ወሲባዊ ሀጥያትን ከመጠን በላይ promote የሚያደርግ ነው።
ትልቁ ጣዖት አምልኮተ ራስ ይመስለኛል። ከላይ ያለውን ዘጠኙንም motivation ያሟላል። በዛ ላይ ደግሞ እኛው ለእኛው እንዲመች አድርገን የፈጠርነው ጣዖት ነው። በራስ መተማመንና በራስ መታመን መሀል ያለው ቀጭን መስመር ብዙዎችን ወደዚህ አምልኮ ከቷል። ለስጋው የሚያዝናናን የሚያስደስትን ነገር፣ የማያጉላላና ብዙ ዋጋ (ራስን መካድን) የማይጠይቅ፣ አፋጣኝና predictable የሆነ practical እርዳታ ሌላ ከየትም አናገኝም።
3, እግዚአብሄርን በክርስቶስ በኩል ማምለክ
አስርቱ ትዕዛዛት የተሻሩ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ትዕዛዞቹ ግን kevin በሙዚቃዊ መንገድ እንደሚያብራራው አልተሻሩም። But they have transposed። ማለትም አሁንም እንጠብቃቸዋለን ግን የምንታዘዛቸው ለየት ባለ መንገድ ነው።( In a different key.)እኔን ብቻ አምልኩኝ ያለው እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን ላይ ኢየሱስን እንድንሰማ ነግሮናል። ማቲ 17:5 ክርስቶስ አምልኳችን እንደሚገባው የተለያዩ ክፍሎች ይነግሩናል።
“እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራ ቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።”ዕብ 1:3
“ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣” ፊልጵስዩስ 2፥10
“እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።” ዮሐንስ 14፥7
የዚህ አንድምታ ምንድነው? እግዚአብሔርን የምናውቀውም ሆነ የሞናመልከው በክርስቶስ በኩል ካልሆነ የምናመልከው ያህዌን አይደለም።

❤9👍1
ካልቪን ለዚህ የሚሆን ጥሩ መለኪያ አለው። (Worship የሚለው ትልቅ ሀሳብ በውስጡ Adoration, Trust, Invocation and Thanks giving አሉት።)
1, የምንደመመው፣ ትልቁን ውዳሴ የምንሰጠው ለማን ነው?
2, የምንታመንበት፣ በሞት ሸለቆ ስንሆን እንደማይተወን እርግጠኛ የምንሆንበት ማን ነው?
3, ችግር ውስጥ ስንሆን የምንጣራው ማንን ነው?መልስ መፍትሄ ወይ ምሪት ስንሻ ወዴት እንሄዳለን?
4,ነገሮች እንዳሰብነው፣ ካሰብነውም በላይ መልካም ሲሆኑ የምናመሰግነውና credit የምንሰጠው ለማን ነው?

❤20👍2
Pursuing Holiness
<unknown> – 08_Tenager___ተናገር___Meskerem_Getu(256k)
The amount of times I've heard this song... its one of those songs that I might hear after 10 years and remember exactly the season of life I was in when I first heard it.
❤5
ፈልጌህ መጥቻለው ፈልጌህ
ላገኝህ መጥቻለሁ ኢየሱስ ላገኝህ
ናፍቀኸኝ መጥቻለሁ ልሰማህ ልሰማህ
ፈልጌህ መጥቻለው ኢየሱስ ላደምጥህ
አንተ ብቻህን እንድትደመጥ
የስጋዬ ጩኸቱ ረጭ ይበል ፀጥ
ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው ይኸው በለኝ
የልብህን ሀሳብ እስቲ አጫውተኛ
ሁንልኝ የህይወቴ መካከለኛ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች
በኔም ላይ እንድትሆን ለሀሳብህ ልመች ለአንተ ልመች
ብቸኛ አቅሜ 'ምታደርገኝ ቀና
በአንተ ካልሆነ ከቶ አልድንምና
ምትለኝን ሁሉ ላደምጥ ፈልጌ
በፊትህ ሆናለው ራሴን ባዶ አድርጌ
ላገኝህ መጥቻለሁ ኢየሱስ ላገኝህ
ናፍቀኸኝ መጥቻለሁ ልሰማህ ልሰማህ
ፈልጌህ መጥቻለው ኢየሱስ ላደምጥህ
አንተ ብቻህን እንድትደመጥ
የስጋዬ ጩኸቱ ረጭ ይበል ፀጥ
ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው ይኸው በለኝ
የልብህን ሀሳብ እስቲ አጫውተኛ
ሁንልኝ የህይወቴ መካከለኛ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች
በኔም ላይ እንድትሆን ለሀሳብህ ልመች ለአንተ ልመች
ብቸኛ አቅሜ 'ምታደርገኝ ቀና
በአንተ ካልሆነ ከቶ አልድንምና
ምትለኝን ሁሉ ላደምጥ ፈልጌ
በፊትህ ሆናለው ራሴን ባዶ አድርጌ
❤20👍3
ኢየሱስ : ስንደክም ተስፋችን
(Repost)
“የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።” ኢሳይያስ 42፥3

ለራሴ ከተውከኝማ እንደሸንበቆ እንኳ ረዘም ብዬ አልታይም። እንደተቀጠቀጠ ሸንበቆ እንኳን ሰው ላስደግፍ ለራሴም የማላስተማምን ድኩም ነኝና እንደሰው ስልቹ ብትሆን ሰብረህ ትጥለኝ ነበር ፤ አልጠቅምህምና።
ጧፍ ነዶ ነዶ እያለቀ ሲመጣ ይጤሳል። የዛኔ የሰሙ ክርፋት መከራ ነው ፤በዛ ላይ ብርሀንም አይኖረውም። ጌታዬ እንደሰው ብትሆን ጭላንጭሉን ብርሀን ታጠፋው ነበር።
የቃልህ መዶሻ ሲያደቀኝ የሀጥያቴን ሀያልነት ተመልክቼ ስለኔ የተሰቀለው ኢየሱስ ወንጌል ሲበራልኝ ድህነት በጭራሽ እንደማይገባኝ ተረድቼ ነበር። የተዘፈቅሁበትን ሀጥያት እያወቅሁት በየትኛው ፅድቄ እመካለሁ? በአመፅ የምቅበዘበዘዋን ፈልገህ ባዳንከኝ ሰሞን ላስደስትህ ታትር ነበር።
የሚያሳዝንህን ሀጥያት ተጸይፌ ላሸንፍ እታገል ነበር። ክቡር ቃልህን ማንበብ በፀሎት የልብ መሻትህን መፈለግ ስላንተ ማውራት አንተን ማዋራት ቀንበር አይመስለኝም ነበር ። ዛሬ የጉልበቴ መታሰርና የልቤ ዝለት ያኔ ከተፀየፍኩት ሀጥያት ጋር በድርድር የመወዳጀቴ ውጤት መሆኑንም አውቃለሁ።
ታድያ እኔ ራሴ ባለችኝ ትንሽዬ እውቀት መሳቴን ተረድቼ ድካሜን ከጠላሁ ነውርና እንከን ፈፅሞ የሌለብህ ቅዱሱ እግዚያብሄር ደግሞ ይብሱኑ እንዴት ሀጥያቴን ትጠላው ይሆን? ደክሜ ከስጋ ጋር እንደወትሮ መታገል ሲያቅተኝም የኔ ደግ መሲህ አትሰብረኝም ፤ አታጠፋኝም!
ከሀይማኖተኞቹ ፈሪሳውያን ይልቅ በሀጥያቱ ለሚሸማቀቀው ትራራለህ። የኔ መልካም! የኔ ብርቱ! ደካማውን ጥለህ ሀይልህን ከመግለጥ ይልቅ አፅንተኸኝ የምህረት ማሳያ ታደርገኛለህ። ሰላሜ ተናግቶ እምነቴ ሲላላ ከምንም በላይ የምወደው ቃልህን ለማንበብ ከእስትንፋሴ ይልቅ የምትቀርበኝን አባቴን ለማዋራት ተስኖኝ እንዲሁ ስምህን ስጠራ ታዝንልኛለህ።
በሀጥያት ደክሜ ፤ ንስሀ መግባት ሲያታክተኝ ማድረግ የምፈልገውን ፅድቅ ማድረግያ አቅም ያጣሁ ቀን አያጠፋኝም። የፀጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ እስከፍፃሜው ያፀናኛል። ሀያሉ ድካሜን ያግዛል።
አዲስ ፍጥረት መሆኔን እስክጠራጠር እንኳን ብደክም.. በበረቱ ሰዎች ምን ያህል ብቀና..በርትቼ እሮጥ የነበረበትን ጊዜ እያሰብኩ አሁን መንፏቀቅ እንኳን እንደተሳነኝ አይቼ ባነባ ድካሜን አይቶ የሚራራልኝ ደግ ካህን አለኝ።
ምህረቱ የበዛ! የሀጥያተኛውን ጥፋት የማይወድድ አባት አለኝ። ዘይቱን ሲጨምርልኝ ዳግም ብርሀኔ ይታደሳል። የደከሙትን ልጆቹን በፀጋው ደግፎ ያቆማል እንጂ እንደሰው ሸንበቆ አይሰብርም። እንደሰው ከብርቱዎቹ ጋር ወግኖ በሀጥያቴ ዝዬ ሳዝን አያጠፋኝም። ጠወልጋለች ብሎ አይሰብረኝም በፀጋው ባለጠግነት ያፀናኛል እንጂ!
ሸክሜ ሲከብድብኝ ወደኔ ነይ ይለኛል። አባት ነውና ሳይጠየፍ ቁስል ማከም እረፍትን መስጠት ያውቅበታል! ባርያህ ልሆን እንኳ አይገባኝም ብዬ እግሩ ስር ስደፋ ሙት የነበረች ልጄ መጣች ብሎ ቀለበቱን አድርጎልኝ ድግስ ያዘጋጃል።
❤16👍6🙏3
Forwarded from Mahlet Mesfin
we have a God who has chosen to be known as the God of Abraham, Isaac, and Jacob. oh how each of these three figures embodies distinct characteristics that reflect different aspects of faith and human experience! Abraham stands out as an exceptional figure of unwavering faith, a true giant in faith. Isaac, on the other hand, exemplifies obedience and innocence…… he accepted his father's will without question when he was bound for sacrifice ( he is old enough to say no or cry out for help but he didnt), he lived harmoniously with those around him, avoiding conflict, and receiving a wife as a divine gift. In contrast, Jacob's life was marked by disobedience and cunning; he often relied on his flawed intellect to navigate challenges. And yet, despite his flaws, he was embraced and redeemed by the Lord. This is a powerful reminder that God is not only the God of the relatively faithful Abraham and the obedient Isaac but also of Jacob, who represents the flawed and the redeemed like me. I love God!
❤18👍3😢1🙏1