Telegram Web Link
Yared-Maru-Ethiopian-Protestant-Old-Gospel-Song
<unknown>
ለጊዜው ከሚገኝ ፡ ከኃጢአት ደስታ
የዓለምን ትርፍ ፡ ንቆ ራሱን የገታ
እንደመርደክዮስ ፡ በደጁ የተጋ
ከጌታው ሚቀበለው ፡ አለ ብዙ ዋጋ

አርቆ ዋጋውን ተምኖ
ብድራቱን ያየ ትኩር ብሎ
ተጥሎ አይቀርም ፤ በአምላኩ ይታሰባል
እንዳለፈ ውሃ
መከራውን ይረሳል..
25
እግዚአብሔርን የምትወድዱ ክፋትን ጥሉ ፤ እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል። ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።

መዝሙር 97:10-12
29👏3👍1
Pursuing Holiness
መክብብ 5:1-7 (Part 9) ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። የእግዚአብሔር ቤት በራሱ ሰፊ የሆነ ሀሳብን የተሸከመ ሀረግ ቢሆንም በዚህ አውድ የአምልኮ ስፍራን የሚወክል ይመስለኛል። ሰባኪው አምልኮን ለማቅረብ ስንሄድ / ስናቀርብ behave እንድናደርግ እያስጠነቀቀ ነው። እግር ደግሞ ስብዕናን የሚመስል ቃል ነው። Creatureliness or humanity የሚል ሀሳብን በውስጡ ያዘለ…
ወደአድራሻህ ላለመቅረብ ሰበብ የሚያበዛ ሰው መች እግሩን ይጠብቃል? እዚም እዛም ስንት አልባሌ ቦታን የረገጠ እግር በንስሀ እንባ ሳይነፃ እየተንፏቀቀ እፊትህ ሲያደርሰኝ ከሰነፍ መስዋዕት ውጪ ምን ላቀርብልህ እችላለሁ? ለነገስታት ንጉስ አምልኮን ማቅረብ እንዴት እንደቀለለብኝ እንጃ። አንተው ባዘዝከው መንገድ ብቻ የሚገባህን ባለኝ አቅም ሁሉ ልሰጥበት የሚገባ ስፍራ ነው። ወደሀልዎትህ casually ከመግባት ጠብቀኝ። ለአንተ የማደርገውን ነገር ሁሉ with intention እንዳደርገው አሰልጥነኝ። በእርግጥ ሰው ብቻ ነኝ። Thats how you made me. ወደአንተ ስመጣ እንደመልዓክ አልሆንም። ስለዚህ ብዙ እንከን ያለብኝ ልጅህ እንደሆንኩ act ማድረግ እንድችል እርዳኝ። መብረር በሚያቃጣኝ ሰዓት አካሄዴን ጠብቅ።

እውነታውን ስናዘዝ በነዚያ ወቅቶች የቀረብኩህ ራሱ ልሰማህ ሳይሆን የማያባራውን ብሶቴን ሰምተህ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ነው፡፡ ራሴን ከእኔው ክፋት ፤ አረማመዴን ከወደቀችው አለም ፈተና ሳልጠብቅ.. ቅዱሳን መላዕክት ፊታቸውን ሳይሸፍኑ የማይቀርቡትን ሀልዎት በስልቹ ሽምደዳ ፀሎት ዘው ብዬ መግባቴን ስንቴ ከፅድቅ ቆጥሬው ይሆን? በምድር ላይ ካሉ ፍስሀዎች ሁሉ አንተን ከማምለክ ጋር የሚስተካከል የለም። ይሄ እውነት ነው። አንተንም ደስ የሚያሰኝህና የሚያከብርህ ተግባር ነው። ነገርግን ትክክለኛውን ነገር ለነሳሳተ ምክኒያት ወይንም በተሳሳተ መንገድ ከማድረግ ጠብቀኝ።

ስንፍና ከመስዋዕቴ ይወገድ። ይልቁንም አንተን ለመስማት መጓጓት እንድችል እርዳኝ። ቃልህ እንደሚል የስንፍናን መስዋዕት አቅራቢ በፊትህ ክፉን እንደሚሰራ አያውቅምና ተላላ ነው፡፡ የራሱን ትከሻ እየመታ በደሉን እያበረታታ መኖሩን ማን ደፍሮ ይነግረዋል (ከቃልህ ውጪ..)  ሰይፍ በሆነው ቃልህ ስንፍናዬን ገስፅልኝና አንተን ለመስማት ልቅረብህ! አንተ እኮ የህይወት ቃል አለህ!

ከሰማሁህም በኀላ ምላሽ ስሰጥ ስሜታዊነት በችኮላ ያንደረደረው ድንፋታዬ አሸማቆኛል! መልካምነትህን ስሰማ እኔም ልመስልህ ወድጄ ስንቱን ሸጋ ነገር አደርጋለሁ ለማለት ልቤ እንደሚቸኩል ታውቃለህ.. አንደበቴም ያልተብላላን ምኞት ሲተፋ አይሰክንም ለመደመጥ ይፈጥናል እንጂ፡፡

ድፍረቱን ከየት አመጣሁት ቆይ? አንተ በሰማይ ምትኖር አምላክ እኔ ደግሞ በምድር ያለው ፍጡር ነኝ.. ምናልባት "ሩቅ" ስለሆንኩ ቃልአባይነቴ consequence የለውም ብዬ ይሆናል.. ተላላነቴን ይቅር በል፡፡ ለሰው እንኳን ቃል ገብቶ መካድ ያስጠይቅ የለ? አንተ ደግሞ በሰማይ ነህ..ገና ሽለላዬን ስደነፋ የልቤን ቆራጥነት ፣ የውሳኔዬን intention፣ የችኮላዬን ምክኒያት እንዳትረዳ የፉከራዬ ድምፅ መች ይከልልሀል? ታውቀኝ የለ? እራሴን ከምረዳው በላይ የምታነበኝ በሰማይ ከፍ ብለህ አለህ፡፡
ሰው ከመሆን ጋር አብረው ያሉትን ውስንነቶች እንዳስብ እርዳኝ። የሆነ ነገር ለማግኘት እንደቸኮለ ሰው ያልተገናዘበን ምላሽ ወደሀልዎትህ እያቀረብኩ እንዳልዘባርቅ እርዳኝ።  አንተ በልጅህ ስም የሚፀለይን ፀሎት በሙሉ እኔደምትሰማ አምናለሁ። በእርግጥ ፀሎቴ ሁልጊዜ inperfect ኘው። እያረምክ ስለምትሰማኝ እንጂ ብዙ ስህተት አለው። ምን እንደምለምን አላውቅም። የሚበጀኝን የምታውቀው አንተ.. እንደአንተ ሁሉን ባውቅ የምፀልየውን ፀሎት እንደምትመልስልኝ ምስክሮቼ ሳልለምን የሰጠኸኝ በረከቶች ናቸው። አሁንም አባት ሆይ አንተን መፍራት አስተምረኝ።  ትክክለኛ ቦታዬን ልወቅ። እግዚአብሔር በሰማይ ነህ። እኔ በምድር ነኝ። እይታዬ፣ እውቀቴ፣ ሀይሌ ውስን መሆኑን እንዳልረሳ አደራ።

ስለዚህ ቃሌን ጥቂት አድርግልኝና ውርደቴን ማርልኝ፡፡ በምድር እንደሚኖር ሰው መማልን አስተምረኝ.. ህልምን የሚገልጠው ስራ ነው.. የኔ ስራ የሚያሳብቀው ደሞ ህልሜ ነው ብዬ የምፎክረው ቅዱስ ህይወት አይደለምና ብዙ ልፈፋዬ "የሞኝ ንግግር" ብቻ ሆኗል፡፡
Afterall what I do matters more than the promises I make. Good intention ብቻውን ጥቅም የለውም። በስራ ያልተገለጡ ንግግሮቼ ሁሉ ያሸማቅቁኛል። በትጋት የሚሰሩ ሰዎች የሚያገኙትን ክብር እሰራለው ብሎ በመፎከር ብቻ ማግኘት ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ቃልአባይነት ነው። ምህረትህ ይብዛልኝ።

ሁለት ነገር ልለምንህ.. የተሳልኩትን ስዕለት ለመፈፀም ስንፍና እንዳያዘገየኝ እርዳኝ.. የማልፈፅመውን ነገር አደርጋለሁ ብሎ ከመሳል ጠብቀኝ፡፡ በእርጥም አንተን ለመዋሸት ከመሞከር ቃል አለመግባት ብልህነት ነው፡፡ የልብን ስለምታይ አንደበት ልብ ያላመነበትንና እሰራለው ብሎ ያላቀደበትን ነገር በችኮላ እንዳይለፍፍ ልጓም አበጅለት፡፡

አንደበቴ ወደ ሀጥያት ለመራኝ እልፍ ጊዜያት ሁሉ የሚያኖረኝ ምህረትህ ይግነንልኝ ፤ ከቁጣህም አድነኝ፡፡ የወደፊቱን አላውቅም። ብሳል እንኳን ሳልዘገይ፣ ሰበብ ሳላበዛ እንድፈፀም እርዳኝ። አንደበቴን ከከንቱ ፉከራ መከልከል አስተምረኝ። እንደማላደርግ የማውቀውን ነገር አደርጋለው ከማለት ጠብቀኝ። አንተ እግዚአብሔር አትሸነገልም። ለእንደኔ ያለ ደካማ ብዙ ቃል ከንቱ ነው። ይልቅ ጆሮዬን አንተን ለመስማት የፈጠነ ይሁንልኝ፡፡

The fact that you see my heart is both comforting and terrifying. Its comforting cause you understand me completely. All the good, the bad and the ugly. You see it all. Its terrifying cause I can't fool you. I can't impress you with my convincing performance. Rid me of any religious pretense and hypocrisy.

ከሆንኩት ነገር ውጪ ምንም ነገርን መስዬ አልታይ። አምልኮ ህይወት አይደል? እውነተኛ ህይወት፣ እውነተኛ አምልኮ ይኑረኝ።  አንተ የምትቀበለው ደስ የሚያሰኝህ መስዋዕት ይሁንልኝ። የየዕለት to-do ሊስቴ ላይ የማይቀር ተግባር እሱ ይሁን። ከትህትናህና የተነሳ እንዳትቀልብኝ .. ወደ አንተ ስመጣም ደግሞ "ባልተጠበቀ እግር" ባልተገራ እኔነት እንዳይሆን ፈሪሀ እግዚአብሄርን አስተምረኝ፡፡ The concept of fearing you, በኑሮ ነው የሚገለጠው። አንተ የሚገባህን ቦታ ስትይዝ ሁሉ ይስተካከላል። ሁሉን የምታውቀውን አንተን መፎገር አለመቻል ውስጥ ያለው በረከት ብዙ ነው። ራሴን በመሆን የምህረትህን ኪዳን የጌታዬን ደም ታምኜ ድካሜን እንድናዘዝ ድፍረት ይሆነኛል። ስለዚህም አመሰግንሃለሁ።
26👍3
በምድር ያሉ ውድ ሀብቶች ሁሉ "ህይወትህን ስጥና ግዛኝ" ይላሉ። ህይወቱን ሰጥቶ የገዛን ብቸኛው ውድ ሀብት ኢየሱስ ነው።
47👏3
Track 05 Filegaw Aderege...
Aster Abebe Official
እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ
ማን ይችል ነበረ የጌታ ደጅ ሊረግጥ
እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው
እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው
ስንቱን ቤት ይቁጠረው

ደጋግሞ የተፈተነ እምነቴ
እንዳይንኮታኮት አልቆለት እንዳይወድቅ
እንደስንዴ ሊያበጥረኝ የወጣውን ፈታኝ
በ ‘አይቻልም’ ሲሰድ

የአንደበቴን ሳይሆን ያወቀ የልቤን
እንደተመኘሁት ልሆን ያለመቻሌን
እስኪቆሙ እግሮቼ በብዙ አገዘኝ
ሃይልን እስክቀበል አይዞሽ በርቺ እያለኝ
ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላት
ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት

ክህደት መሃላዬን አላውቀውም ማለቴን
ዶሮ ሶስቴ እስኪጮህ አልፎ መጨመሬን
ከትንሳኤው ማግስት ብርቱዎች እያሉ
ከሰነፎች ተርታ እንደኔ ያልዋሉ
ፍለጋው አረገኝ መጣ ወዳለሁበት
ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት

በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
በማለዳ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ለተቤዠኝ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ሳላቋርጥ ምስጋናዬ ይኸው

በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር
ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር
አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን
እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን
ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ
አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ
የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ
አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ

አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ
አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ
ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ
መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ
29👍4😁1
📌
👏63
የመንፈስ ድህነት

ፓይፐር ከስብከቱ በኋላ አንድ ተማሪ መጥቶ
Isn’t Christianity a crutch for people who can’t make it on their own?” ሲለው በአጭሩ አዎ ብሎ መመለሱን ይናገራል። ማንም ለአካላዊ አንካሳነት የተሰሩ ክራንቾችን አይነቅፍም። ክርስትናን ግን እንደዛ ለድጋፍ እንደሚሆን መንገድ ማሰብ የማይፈለግበት ምክኒያት ያ አማኞችን አንካሳና ደካማ ማድረጉ ነው።

በራሴ ብቁ ነኝ ብሎ ለሚመካ ሰው offensive ነው። ኢየሱስ ደግሞ ለህመምተኞች እንጂ ለጤነኞች እንዳልመጣ ተናግሯል። ይህ ማለት ጌታን የሚያገኙት መንፈሳዊ በሽታቸውን የተረዱ ብቻ ናቸው።  ይሄንን ታድያ ሰው ለምን መቀበል አይፈልግም? እውነተኛ ፍስሀና እርካታ በራስ ከመደገፍ፣ በራስ በመተማመን የሚመጣ ስለሚመስለን ነው። We're so obsessed with self-esteem.  በራሳችን ከመደገፍ ይልቅ እንደህፃናት በሆነ ትሁት ልብ እግዚአብሔር ላይ መደገፍን አንፈልግም። Unworthy ሆነን የወደደንን ከማድነቅ ይልቅ ተወዳጅ የመሆንን self esteem እናሳድዳለን።

እነ አዳምን የጣላቸውም ይሄው ነው። እንደእግዚአብሔር በመሆን ውስጥ ያዩት ነፃነት አለ። ጌታ ደግሞ በተራራው ስብከቱ "በመንፈስ ድሀ የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግስተ ሰማይ የእነርሱ ናትና" ሲል የምንጠላውን ምስኪንነት፣ ጎስቋላነት፣ ረድኤት አልባነት ወስዶ የመንግስቱ መግቢያ መዳረሻ ያደርገዋል።

ቃሉም ይህን ያስረግጥልናል። እግዚአብሔር የሚቀበለው መስዋዕት የተሰበረን ልብ ነው።
ይህን ስንል ደግሞ እንደዳዊት በሀጥያት ፀፀት ስለመሰበር ብቻ አይደለም። በመልካሙም ጊዜ አማኝ የልቡ ቅኝት መሆን ያለበት “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ?...”(1 ዜና 29፥14) Who is qualified for this?

አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ኢዮብ፣ ኢሳይያስ ታላላቅ አባቶች እና ታላላቅ ነብያቶች ሁሉ የሚያመሳስላቸው ነገር ይህ ነው። የእግዚአብሔርን ዋጋ በመረዳት ለራሳቸው ትልቅ ግምት ከመስጠት የተፈወሱ ትሁታን ነበሩ። ሲስቱም ይታደሳሉ ፤ በስኬታቸውም አይታበዩም ነበር። They don't base their identity on their success or failures.

ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚልቅ የተባለው መጥምቁ ዩሃንስ ማንም አይሁዳዊ የማያደርገውን እንደባርያ የኢየሱስን ጫማ ለመፍታት እንኳ ብቁ አይደለሁም ሲል እናገኘዋለን። He is saying that he is not worthy to be a slave. እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ሲል በቁጭት አይደለም። የራሱን ዋጋ የሚያስረሳ ዕንቁነትን ጌታ ላይ ስላየ ነው።

ምናልባትም ከተፃፉልን ብዙ ፀሎቶች አጭሩና በአስፈላጊነቱ ሁልጊዜ relevant የሆነው ፀሎት የምንሰማው ከቀረጥ ሰብሳቢው ነው። "ጌታ ሆይ፤ እኔን ሀጥያተኛውን ማረኝ።" አለ። ፀደቀ። Its so simple that we often miss it. እግዚአብሔር እንደሚመልስ እርግጠኛ መሆን የምንችለው ፀሎት ይህ ነው። በተገላቢጦሹ እራሱ ጴጥሮስ ከእኔ ተለይ እኔ ሀጥያተኛ ነኝ ሲል እያለ ያለው ምን እንደሆነ አውቆ  (as tim keller says God often corrects our prayers and answers what we should've asked for if we knew what he knows) ጠላት ሊፈትነው ብዙ እየጣረም ultimately ግን እንዳይወድቅ እምነቱን በመጠበቅና አብሮት በመሆን መልሶለታል።

የሀጥያተኞች ዋና ብሎ ራሱን የሚጠራው ጳውሎስም የከበረውን መዝገብ የተቀበለ ሸክላ አድርጎ ነው ራሱን የሚቆጥረው። ለበጎ ትጋቱ ሁሉ "በእኔ የሚሰራው ክርስቶስ ነው" እያለ credit ሲሰጥና በድካሙ ሲመካ እናገኘዋለን።

This is how piper defines spiritual poverty
• It is a sense of powerlessness in ourselves.
• It is a sense of spiritual bankruptcy and helplessness before God.
• It is a sense of moral uncleanness and personal unworthiness before God.
• It is a sense that if there is to be any life or joy or usefulness, it will have to be all of God and all of grace.

ከሁሉም በፊት "Sense" የሚል ቃል ያስገባበት ምክኒያት ፣ እንደዚህ ተሰማንም አልተሰማንም በእግዚአብሔር ፊት ግን እውነታው ያ ስለሆነ ነው። ከክርስቶስ ውጪ ሁላችንን የሚገልጥ መገለጫ ነው መንፈሳዊ ድህነት።

"Blessed are the poor in spirit who mourn. Blessed are the people who feel keenly their inadequacies and their guilt and their failures and their helplessness and their unworthiness and their emptiness — who don’t try to hide these things under a cloak of self-sufficiency, but who are honest about them and grieved and driven to the grace of God."
29👍6👏1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤ አንተ ዝም ካልኸኝ፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ። ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣ እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣ የልመናዬን ቃል ስማ።


ፀሎት በእግዚአብሔር ላይ ያለንን ጥገኝነት የምናሳይበት መንገድ ነው። በመጀመርያ እግዚአብሔርን በኪዳን ስሙ ያህዌ ሆይ ብሎ ሲጠራ የዘመኑ ቅዱሳን የሚሰሙት "to you, my Father" አይነት ነገር ነው። Personal/ Intimate ነው። የሚፀልየው ደግሞ ሁለተኛው ስንኝ ላይ እንደምናየው በተቀደሰ ማደርያው ወዳለው እግዚአብሔር ነው። ይሄም በኪዳኑ መሰረት እግዚአብሔር ስለሚቸረው መገኘቱ/ አብሮነቱ ያስታውሰናል። So God is a personal God. He is in His Holy Sanctuary. And He is our rock. እግዚአብሔር ዐለቱ የሆነ ሰው አስተማማኝ ጠንካራና ፅኑ መደገፊያ አለው።

ልመናው ደግሞ አስቸኳይ የሆነ ረድኤትና ምህረትን ፍለጋ ነው። ምናልባትም በመከራ የሰነበተ ሰው ሆኖ የእግዚአብሔርን ጣልቃገብነት ማፋጠን የፈለገ ይመስላል። ለዚህም ነው ፀሎቴን ቸል አትበል ለማለት እግዚአብሔርን በሰውኛ ቋንቋ ባልሰማ ዝም አትበለኝ እያለ የሚማፀነው። በእርግጥም በመከራ ለሚያልፍ ሰው ከእግዚአብሔር ዝምታ በላይ ከባድ ነገር የለም። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አይነት ነገር ነው። ግዴታ ችግሩ ለሞት የሚያደርስ ላይሆን ይችላል የመቃብሩን expression የተጠቀመው። He can be saying መከራዬ ልጋፈጠው፣ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ከመሆኑ በፊት እርዳኝ። He is actively pleading for mercy. እግዚአብሔር ደግሞ በባህሪው መሀሪ ነው (ዘፀ 34:6) ስለዚህ ጥገኝነቱንና፣ መጠባበቁን ለማመልከት እጆቹን ወደ መሀሪው ይዘረጋል።

በልባቸው ተንኰል እያለ፣ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣ከክፉ አድራጊዎችናከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ። እንደ ሥራቸው፣ እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤ እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤ አጸፋውን መልስላቸው። ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይገነባቸውም



የዘማሪው concern የፍትህ ጥያቄ ነው።ልባቸው በክፋት ተሞልቶ በአንደበት ከሚሸነግሉት ጋር አብሮ መዳኘት አይፈልግም። እግዚአብሔር ክፋትን እንዲቀጣ መፀለይ እንዳለብን ይሄ ያስተምረናል። በቀልን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትንም። እነዚህ አመፀኞች የመመለስ ተስፋ የነበራቸውም ይመስላል። They just didn't care about God and His works. Which can only mean that they were preoccupied with themselves and their works. የተጠቀሱበት መገለጫ ደግሞ አመፅ ስለሆነ ይህ ስራቸው በቀጥታ ከእግዚአብሔር ስራ ጋር የሚቃረን እንደሆነ እንረዳለን። ስለዚህ ፍፃሜያቸው ጥፋት ነው።

የልመናዬን ቃል ሰምቷልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን። እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤
ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤
ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

በእግዚአብሔር መታመን አመስጋኝ ያደርጋል። ምስጋናዎቹን ካስተዋልን ከተነሳበት ልመና ጋር በተጓዳኝ መነበብ የሚችል ነው። He cried out for mercy and he thanks God for showing him mercy. እግዚአብሔር አብሮን እንዳለና ስንፀልይም እንደሚሰማን በሀሳብ ደረጃ ብናምን እንኳ.. actually ግን እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሲመልስ ብቸኛው ሞላሽ ምስጋና ነው። We won't feel entitled to it. Its one of the most humbling things እንደውም። እግዚአብሔር ከሚያደርግልን ነገር እኩል ይህ መዝሙር የሚያስታውሰን its who God is to us..

ሲጀምር ዓለት በማለት ይጠራዋል። ከዚያም ብርታትና ጋሻ በማለት ተመሳሳይ ምስልን ይሰጠናል። አስቀድሞ ሞትን እንደ worst case scenario አይቶ የተማፀነ ሰው አሁን በእግዚአብሔር ላይ ባለው መታመን ሲታመን እናያለን። He is boasting on His confidence because God proved to be his helper. በእርግጥም በእግዚአብሔር ታምኖ የተከዳ፣ ያልታገዘ፣ ያፈረ የለም። በዓለቱ ተደግፈን ዛሬን ያየን ሁላችን ቆም ብለን ብናስታውስ እንዲህ ያለ መዝሙር አይጠፋንም። Who is more reliable than our God? None more faithful. ይሄንን ደግሞ ከግል ምስክርነት ባለፈ ለህዝቡ ባለው የኪዳን ታማኝነት እንረዳለን። እግዚአብሔር ለህዝቡ ብርታት ነው።

ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤
እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።


It ends the same way it begins.. reminding himself of who God is.
እግዚአብሔር የህዝቡ አዳኝ ነው። ህዝቡን እንደርስቱ treasure ያደርጋቸዋል። የበረከት አምላክ ነው። Tender የሆነ መልካም እረኛ ነው። እቅፉ ዘለዓለማዊ ነው። አያሰጋም።
Psalms 28
14👍5🙏2
CityAlight - My God is A...
CityAlight
Dark, dark is the valley
Faint, the light at my feet
But whatever may face me
My God is all I need.

Bright, bright are the treasures
Life may offer to me
But whatever the pleasure
My God is all I need.

He is my strength, when I cannot go on
Peace, when all my power is gone
Hope, although the night is long and deep


He is my song, for He has rescued me
Joy, now He has set me free
Praise, praise to my Father be
My God is all I need
.

Brief, brief are my days here
Soon my journey complete
But I look to my Savior
Where God has met my need
Yes, He has met my need.

My God is so big,
So strong, and so mighty
There's nothing my God cannot do.
The mountains are His,
The valleys are His,
The stars are His handiwork too.
15👍2
📌
17👍1
Melt the clouds of sin and sadness
Drive the dark of doubt away
Giver of immortal gladness
Fill us with light of day

Henry Van Dyke (1907)
26👍1
Pursuing Holiness
ኑዛዜ... ጌታ ሆይ እኔን ሀጥያተኛዋን ማረኝ "....የሚያመካኙትን አጡ" የተባሉት ሰዎች እጅግ ያሳዝኑኝ ነበረ። ምክንያቱም እድሜዬን ሙሉ ለራሴ ጥብቅና በመቆምና በመከራከር ስላሳለፍኩ ማመካኛ ሰበብና defence ያላቸውን ሚና አበክሬ አውቀዋለሁ... I try to rationalize my actions and why I do what I do...to a point where selfcriticism swallows…
..ቀረጥ ሰብሳቢው ግን በርቀት ቆሞ፣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ማየት እንኳ አልፈለገም፤ ነገር ግን ደረቱን እየደቃ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ’ ይል ነበር...እላችኋለሁ፤ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይህኛው በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ጻድቅ ተቈጥሮ ወደ ቤቱ ተመለሰ። Luke 18፥13
23👍2
...ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ" ዮናስ 2:7
65😢4
Therefore, to you who believe, He is precious.. እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው..(1 Peter 2:7)
39
📌
29🙏1
2025/10/29 08:00:05
Back to Top
HTML Embed Code: