Therefore, to you who believe, He is precious.. እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው..(1 Peter 2:7)
📌
ብዙ ብዙ ፍቅሩ
ብዙ ብዙ ምህረቱ
ብዙ ብዙ ቸርነቱ
አቆመኝ በቤቱ

ጌታ ብዬ ምጠራው
አዲስ ቅኔ ምቀኘው
እግሬም ፀንቶ የቆመው
በእኔ አይደለም በእርሱ ነው።
ምህረቱ ብዙ ነው!

በብርቱ ሰልፍ ያቆመኝ
በውጊያ ድል የሰጠኝ
ሀጥያት ስትከበኝ
በድካሜ እያገዘኝ
ፍቅሩን እያሳየኝ!

በጠላቴ ፊት ለፊት
ራሴን ሲቀባ ዘይት
ሲያስተናግደኝ ተግቶ
ገበታን አዘጋጅቶ
ቸርነቱ በዝቶ።

መድሀኒቴን ሳስከፋ
ገበታውን ስደፋ
ማረኝ ብዬ ግን ሳለቅስ
በእጆቹ በመዳሰስ
እንባዬን በማበስ።

እግዚአብሔር አባቴ
ይክበር ይንገስ በህይወቴ
ይህንን አይቻለው
ጌትነቱ የፍቅር ነው
ፍጥረት ሁሉ ያንግሰው።

ብዙ ብዙ ፍቅሩ
ብዙ ብዙ ምህረቱ
ብዙ ብዙ ቸርነቱ
አቆመኝ በቤቱ።
አልተወውም..

"So much of the Christian life is just hanging on. Yes, we should have a theology of flourishing, growing, riding the wave. But as I age and talk with other Christians, earnest but embattled, I'm learning that much of the Christian life is simply not giving up. Often, hanging on IS riding the wave." Pastor Dane Ortlund

ለሁሉ ጊዜ አለው። ለመሮጥ፣ በህይወት ለመበርታት፣ ለማደግ፣ ከክብር ወደ ክብር ከፍ ለማለት ፣ ብዙ ለማፍራት..ሁሉ። That was what the "መጋቢዬ መብሌ" piece was all about. ከውጪ ለሚያይ ሰው ግልፅ በሆነ መንገድ ሊለካ የሚችል ለውጥና ፍሬያማነት ሊኖር ይችላል።

And yet.. I 100% agree with this quote by Dane. ስለ ክርስትና ህይወት እየገባኝ ካለው ነገር ትልቁ ይሄ ነው። What we don't do matter just as much as what we do. መስቀሉን የሙጥኝ ይዞ አለመልቀቅ የክርስትናን ሰፊውን ህይወት ይወክላል።ብዙዎቻችን የሚዘከርለትን ጀብዱ ስለክርስቶስ አንሰራም። ስለስሙ አልተሰደድንም። ለወንጌል ዋጋ አልከፈልንም። በአጭሩ ቢቀመጥ ክርስትናን አለመተዋችን ሊሆን ይችላል ትልቁ ስኬታችን።

Hanging on/not giving up is not a particularly glamorous life. ጋሽ ስዩም በዘመረበት ልክ "አልተወውም" ብሎ የከተበው ያለም አይመስለኝም። ብዙ ሲሰበክም አንሰማም። ብዙ ለመፃፍም አይመችም።" ምንም ወጀብ ቢያይል የያዛችሁትን ዕርፍ አትልቀቁ። ወደኋላ አትዩ። Just hang on" seems to be something you tell weak and feeble people. ለደካከሙት የሚሆን ማበረታቻ ፣ ማስተዛዘኛና ማፅናኛ ቃላት እንጂ ለሁላችንም ሁልጊዜ የሚያስፈልገን ማስታወሻ አይመስለንም።

ስለዚህም ህይወታችን በመውጣትና በመውረድ ውስጥ constantly ይዋዥቃል። የማንይዘው የማንጨብጠው አዙሪት ውስጥ ራሳችንን often እናገኘዋለን። እግዜር ራርቶልን ቆም ብለን ራሳችንን ቃሉ እንደሚል በእምነት ስለመኖራችን መፈተን ብናስብና ቃሉን እንደመመዘኛ ብንጠቀም የምንረዳው ትልቁ ነገር ችግራችን  እስራኤል በተደጋጋሚ ወደጣዖት አምልኮና ወደአመጿ ከምትመለስበት ችግር ጋር ብዙ አይራራቅም።

We forget easily. I used to think that it was for my own good that I forget so quick. "የኋላዬን እየረሳሁ" ብዬ ያለአውዱ አጣቅስም ይሆናል። ነገርግን እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ያደረገልንን ነገር፣ በኖርንበት ዘመን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ታሪክ ፣ በህይወታችን ያለውን የእግዚአብሔር አሻራ፣ Objectively በኑሯችን የሆኑትን መንፈሳዊ እውነታዎች መዘንጋት is the beginning of every fall, every delay in holiness and growth, every fruitlessness, every exhaustion and despair. You think I'm exaggerating? Think about it እስቲ..

አልተወውም አልለቀውም መድሀኒቴን
የሰላሜን ጌታ እረፍት የሰጠኝን ፤ጌታ ኢየሱሰን

መግቢያ መውጫ አጥቼ ስንከራተት በአለም
አፅናናኝ ኢየሱስ ነይ የኔ ነሽ አለኝ
ጥሪውንም ሰማሁ ህይወቴም ረካች
መቅበዝበዜ ቀረ ነፍሴም ተደሰተች

ሀያሉ አምላክ ነው ለእኔ የደረሰ
ማቄን የቀደደ እንባዬን አበሰ
ሰላም እረፍት ሰጥቶ መድሀኒት የሆነኝ
ተስፋዬን አድሶ በቃሉ ያፅናናኝ

አለም አሽቀንጥራ ገፍትራ ስትጥለኝ
ደረሰልኝ ጌታ እኔ አለሁሽ አለኝ
በቀኝ በግራዬ ቆመልኝ አምላኬ
በአፍቃሪዬ ፀናሁ ቀረ መብረክረኬ

ለነፍሴ እረፍት ሆነኝ ቀለለኝ ሸክሜ
መጨነቄ ቀረ ፈሰሰ ሰላሜ
ፀጋን አለበሰኝ ነውሬንም ሸፈነው
ልገዛለት እንጂ እርሱን እንዴት ልተው?

ይሄ የነፍሳችን የዘወትር መዝሙር ሆኖ ከላይ ወደተጠቀሰው አመፅ፣ ፍሬአልባነት፣ ትካዜና ይህ ነው የማይባል ዝለት ውስጥ መሰንበት ይቻላል? I highly doubt it. At the end of the day, its not our grip thats the decisive factor in our salvation. Meditating and enjoying the soul thrilling truth about the gloriousness of our redemption is what gets us to a point where we rededicate our devotions and order our priorities until everything in us gets to a point of clinging to Jesus tightly enough that we genuinely ask "ልገዛለት እንጂ እርሱን እንዴት ልተው?.. አልተወውም!..
And.. out of His compassion He calls : "እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤
እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ ወደ ውሆች
ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣ የወይን ጠጅና ወተት ግዙ
ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ?
በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጒልበታችሁን ትጨርሳላችሁ?

ስሙ፤ እኔን ስሙኝመልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች
ጆሮአችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ።
ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
....እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት
ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው
ወደ እግዚአብሔር ይመለስ
እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤
ወደ አምላካችን ይመለስ፤
ይቅርታው ብዙ ነውና። (ኢሳይያስ 55:1-7)
አድራሻ፦
1) በጃዕፈር መጽሐፍት መደብር (ለገሃር እና 4 ኪሎ ቅርንጫፍ)
2) አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ መጽሐፍት መደብር (ስቴዲየም ዙሪያ ቀይ መስቀል ፊት ለፊት)
2) ጉርድ ሾላ፣ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት፣ ሜርሲ ፕላዛ 13ኛ ፎቅ ላይ ያገኙታል።
ከአዲስ አበባ ውጪና በብዛት ለሚፈልጉ ከታች በዚህ ስልክ ይደውሉ።
+251 90 574 6765
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
There on the cross, Jesus redefined glory.
Michael Reeves 🖤
ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይበብርሃንህ ተገለጥ። በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይኀይልህን አንቀሳቅስመጥተህም አድነን። አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤ እንድንም ዘንድ፣ ፊትህን አብራልን።

የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነድደው፣ እስከ መቼ ድረስ ነው? የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው። ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብንየሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን ፤ እንድንም ዘንድ፣ ፊትህን አብራልን።

ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት። መሬቱን መነጠርህላት፤ እርሷም ሥር ሰድዳ አገሩን ሞላች። ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ። ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ ቍጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች። ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣
ለምን ቅጥሯን አፈረስህ? ዕርያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤ በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል። የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤

ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤ ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት። እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤ የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል። ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣ በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን። ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም ፤ ሕያዋን አድርገን ፤ እኛም ስምህን እንጠራለን። የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤
እንድንም ዘንድ፣ ፊትህን አብራልን።


መዝሙር 80
ለእስራኤል ተሐድሶ የቀረበ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ የአሳፍ መዝሙር።
💯💯💯
Audio
እውር ነበርኩ አሁን ግን አያለው
ሙት ነበርኩ አሁን በህይወት አለው
ስወድቅ አንተግን ተቤዠኸኝ
በእጥፍ ህይወት ባረከኝ።

ጠፍቼ ነበር አባቴ አገኘኸኝ
ከጥፋት ወደንብረት ቀየርከኝ
ብሩህ ተስፋ ሙሉ ህይወት ሰጠኸኝ
በብዙ እጥፍ ባረከኝ።

ባርኮቴን ሁሉ እቆጥራለው፤ ሁሉን እቆጥራለሁ
በማላየው ነገር ባንተ እታመናለው።
በረከቴን እቆጥራለው፤ ሁሉን እቆጥራለው
መልካምነትህን በዘመኔ አያለው።

በድቅድቁ ሸለቆ ውስጥ ነበርክ
በሀዘኔ ጥልቀት አልተለየህ
ለነገ ተስፋ ጉልበቴ ነህ
በብዙ ተስፋ ባረከኝ።

ደግነትህ ይፈልገኛል
ሙሉ ልብህ አግኝቶኛል
በወጀብ በአውሎ ንፋስ ውስጥ
ምህረትህን አስበዋለው።
ቅጠሎች ረግፈውም ህይወት ይቀጥላል። እግዚአብሔር በነፍስ ውስጥ የሚሰራው ስራ በውርጭ ወቅት አይጠፋም። ምንም እንኳን አማኝ የመከነ ቢመስል በዚያ በረጋው ዝምታም ውስጥ የሚቀጥል ፀጋ አለ።ስለዚህም በጊዜው ያብባል። ይፈካል።
CH Spurgeon
Need of Grace
Prayer from The Valley of Vision

O Lord, You know my great unfitness for service, my present deadness, my inability to do anything for your glory and my distressing coldness of heart. I am weak, ignorant, unprofitable and loathe and abhor myself.

I am at a loss to know what you would have me do, for I feel amazingly deserted by you and sense your presence so little. You make me possess the sins of my youth and the dreadful sin of my nature so that I feel all sin. I cannot think or act but every motion is sin.

Return again with showers of converting grace to a poor gospel-abusing sinner. Help my soul to breath after holiness, after a constant devotedness to thee, after growth in grace more abundantly everyday.

O Lord, I am lost in the pursuit of this blessedness, and am ready to sink because I fall short of my desire. Help me to hold out a little longer until the happy hour of deliverance comes for I cannot lift my soul to you if you don't bring me in your goodness.

Help me to be diffident, watchful , tender, lest I offend my blessed Friend in thought and behavior. I confide in you and lean upon you and need you at all times to assist and lead me.

O that all my distress and apprehension might prove but Christ's school to make me fit for greater service by teaching me the great lesson of humility!

ጌታ ሆይ፥ ለአገልግሎት ፈፅሞ እንዳልበቃሁ ፣ አንዳች ነገር ለክብርህ ማድረግ እንደማልችልና ስለአሳሳቢው የልቤ ቅዝቃዜ አንተ ታውቃለህ። ደካማ፣ ጭፍንና የማልረባ በመሆኔ ራሴን እጠየፋለው።

አብሮነትህን ብዙ ስለማላጣጥመውና በአንተ እንደተረሳውና እንደተተውኩ ስለሚሰማኝ ምን እንዳደርግልህ እንደምትፈልግ አይገባኝም። ከፍጥረቴ የተሸኸምኩት በደል ላይ የለጋነቴን መተላለፍ እንዳነግብ አድርገኸኝ ሀሳብ ሆነ ድርጊቴ..እንቅስቃሴዎቼ ሁሉ ውስጥ ያለው ሀጥያት ይታወቀኛል።

ወንጌልህን አላግባብ ለምትበድለው ምስኪን ሀጥያተኛ በሚለውጠው የፀጋህ ማዕበል ናላት። ነፍሴ ቅድስናን፣ ለአንተ ቋሚ የሆነ መሰጠትንና በየዕለቱ በፀጋህ ብልጥግና ማደግን አነፍንፋ እንድትከታተል አግዛት።

ጌታ ሆይ ፥ ይሄንን ብፅዕና ፍለጋ ጠፍቻለሁ። መሻቴንም መኖር አቅቶኝ ልሰጥም እየተንደፋደፍኩ ታየኛለህ። ነፃ የምወጣበት አስደሳች የአርነት ሰዓት እስኪደርስ ትንሽ እንድታገስ እርዳኝ። በቸርነትህ ካላቀረብከኝ የገዛ ነፍሴን ወደአንተ ማቅናት እንኳን አቅቶኛል።

በሀሳብ ባህሪዬ ብሩኩን ወዳጄን እንዳላሳዝን በራሴ የማልደገፍ፣ ንቁ እና ሩህሩህ አድርገኝ።  ሚስጥሬን ለአንተ እነግራለሁ። ሁልጊዜ እደገፍብሀለውና ታስፈልገኛለህ። ምሪትህንና እገዛህን ያለማቋረጥ እሻለው።

ጭንቀቴና ፍርሀቴ ሁሉ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውዱን የትህትና ትምህርት አስተምሮኝ ለከበረ አገልግሎት ብቁ እንዲያደርገኝ ፀሎቴ ነው።
2025/07/05 21:38:58
Back to Top
HTML Embed Code: