Telegram Web Link
Our Dear Kids and Parents,

On behalf of Safari Academy, I extend warm wishes to you and your families on the occasion of EID-AL-FITR.

As we mark the end of Ramadan, I extend my heartfelt wishes to you and your families for a blessed and joyous Eid al-Fitr.

May this special occasion be filled with love, peace, and happiness.

Eid Mubarak to all!

Warm regards,
Eyob Ayele
The School President
Forwarded from Safari Academy Grade 2
ይህ ልጅ ካሌብ ይባላል። ዛሬ ጠዋት ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ ጠፍቶ ወላጆቹ ፍለጋ ላይ ናቸው።

ልዩ ፍላጎት ስላለው ነገሮችን በቀላሉ ስለማያገናዝብ አደጋ ላይ ነውና ካያችሁት ወይም መረጃ ከደረሳችሁ እባካችሁ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ደውላችሁ በማሳወቅ ተባበሩን።
         0923814703
         0924909305
ውድ ቤተሰቦች:-

ከሰዓታት በፊት አፋልጉን ብለን የጠየቅናችሁ ልጃችን ህፃን ካሌብ ገ/ህይወት የተገኘ መሆኑን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

ሁላችሁም ባላችሁበት መረጃው እንዲዳረስ ላደረጋችሁት ታላቅ አስተዋፅኦ ምስጋናችን ከልብ ነው።🙏
የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል

📢 12 ወሳኝ ነጥቦች

📖➊ ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።
ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።

📖❷ መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተው
ን እያስተካከሉ ይጓዛሉ።

📖➌ ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

📖➍ አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ....

📖➎ ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።

📖❻ ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::

📖❼ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

📖❽ ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡

📖❾ ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡

📖❿ ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

📖⓫ ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡

📖⓬ እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡


መልካም ንባብ

                  ካነበብነው
2024/06/16 12:45:08
Back to Top
HTML Embed Code: