Telegram Web Link
ጀግኖች የ12ኛ ክፍል ልጆቻችን እንደተለመደው እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አኩርተውናል!
እንኳን ደስ አለን/ አላችሁ
Exceptional Appreciation and Thank you Message from Safari President

My dear heroes, our Grade 12 Senior Kids— thank you for lifting our spirits and filling us with pride through your outstanding results on the EAES! Your success is a shining example of hard work, perseverance, discipline and determination. We are truly proud of you and wish you every success in your future endeavors.

I also extend my respect and warmest congratulations to your parents and to our entire community, who have supported and believed in you and in us throughout this journey.

Last but certainly not least, my deepest appreciation goes to our esteemed teachers and management team. Your dedication, commitment, and love for our Kids have made this remarkable achievement possible. You are truly blessed, and your efforts will forever be remembered.

Eyob Ayele
Safari Academy
President
የምንወዳችሁና የምናከብራችሁ ልጆቻችን፣ ወላጆች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች

ውድ ጀግኖቻችን፣ የ12ኛ ክፍል ልጆቻችን ባስመዘገባችሁት የዮኒቨርሲቲ መግቢያ (EAES) ድንቅ ውጤት በጣም ኮርተናል፣ መንፈሳችንን ከፍ አድርጋችሁታል፣ እጅግ ደስተኞች ስላደረጋችሁን ከልብ እናመሰግናለን!

የእናንተ ስኬት የጠንካራ ስራ፣ የትግል መንፈስ፣ የዲሲፕሊን እና የቆራጥነት ውጤት ነው። በጣም እንወዳችኃለን።

ልጆቼ ፈጣሪ በህይወታችሁ ሁሉ ብርሃን ይሁናችሁ፤ አሸናፊ ያድርጋችሁ፤ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ፤ ስኬታማ ያድርጋችሁ!

በተጨማሪም በዚህ ጉዞ ውስጥ እናንተን እና እኛንም የደገፉና ያመኑ ሳፋሪን ምርጫቸው ያደረጉትን በብዙ ያገዙንን ወላጆቻችሁን እና አጠቃላይ ቤተሰቦቻችሁን
ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።

በመጨረሻ የዚህ ውጤት ዋና መሰረት የሳፋሪ ስኬት ምሰሶ የሆናችሁትን፤ ደከመኝ ሳትሉ ለልጆቻችን ዕድገት የለፋችሁ አሁንም የምትለፉ ጀግኖች ወንድም እህቶቼ የማከብራችሁ መምህራንና የአመራር ቡድናችንን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የእናንተ ጥረት፣ ቁርጠኝነት እና ለልጆቻችን ያላችሁ ፍቅር ይህንን አስደናቂ ስኬት እንዲሳካ አስችሏል። በእውነት ፈጣሪ ድካማችሁን ይቁጠር፤ ጉልበትና ብርታት ይሁናችሁ። ከልቤ እወዳችኃለሁ!

ኢዮብ አየለ
ሳፋሪ አካዳሚ
ፕሬዚዳንት
2025/09/16 10:17:03
Back to Top
HTML Embed Code: