በኦሮሚያ ምዕራብ ሸዋ በኖኖ ወረዳ 12 ነዋሪዎች እና 22 ታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳደር ገለፀ!
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ከጉራጌ ዞን የተነሱ ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን እና የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ 22 መግደላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።በኖኖ ወረዳ ሀሎ ዲኒቂ መንደር ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 8/2018 ዓ. ም. ምሽት ላይ በተፈጸመው ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ሲናገሩ የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ ግን የተገደሉት 12 ሰዎች መሆናቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጸዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ተሰማርተው እርምጃ መውሰዳቸውን የገለፁት የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወንዳፍራሽ ሉሌሳ "የተገደሉት 22 ናቸው የሚባለው ውሸት ነው።12 ናቸው የተገደሉት። ከ22 በላይ የተገደሉት ከታጣቂዎቹ ወገን ነው" ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት መንደር ነዋሪዎች ጥቃት "ከጉራጌ ዞን ተሻግረው የመጡ በፋኖ ታጣቂዎች" ቅዳሜ ምሽት ላይ "አሰቃቂ ጥቃት" ፈጽመዋል ሲሉ ከስሰዋል።ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ እንደገለጹት፤ ታጣቂዎቹ "ከጉራጌ ዞን በመነሳት በፈጸሙት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ንጹኃን ዜጎች ላይ" ጥቃት ፈጽመዋል።
ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጸምበት በነበረው ኖኖ ወረዳ አሁን በተፈጸመው ጥቃት "ቤታቸው ውስጥ እና ከቤት ውጪም የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 22 ደርሷል" በማለት ነዋሪው ገልጸዋል።

❤9🤔8👏3👍2👎1
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል እንደሚሸፍን ተገለፀ፤ ፈተናው ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሆነ
የትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮው 2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል እንደሚሸፍን እና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች እንደሚፈተኑ አስታውቋል።
በተጨማሪም ፈተናው ከ10 እስከ 12ኛ ክፍል የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት እንደሚያደርግ ገልጿል።በመሆኑም ተማሪዎች፣ መምህራንና ባላድርሻ አካላት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ለሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ለሁለቱ ከተማ አስስተዳደር ት/ቢሮዎችና ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ ነው።
ሚኒስቴሩ በደብዳቤው፤ የዘንድሮውን የ12ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅትን አስመልክቶ ጥቅምት 6/2018 ዓ/ም ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በበይነ መረብ በተደረገ ስብሰባ ፈተናው ከ9 -12 እንዲሸፍን ከስምምነት መድረሱን ገልጿል።
በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
በተያያዘ ዜና የ2018 የሀገር አቀፍ 12 ክፍል ተፈተኝ የብሔራዊ መታወቂያ ከሌለው መመዝገብም ሆነ መፈተን እንደማይችል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቋል። የብሔራዊ መታወቂያን ከፈተናው ምዝገባ ቀደም ብሎ ማውጣት እና መያዝ እንደሚገባም አሳስቧል።
የተማሪ ቤተሠብ፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራሮች እና አካላትም እገዛ እንዲያቀርቡ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ጥሪ አቅርቧል።

❤19🤔2
Sheger Press️️
Photo
“ገዳማዊ ልማት ለቤተ ክርስቲያን ትሩፋት”
ገዳማት በነፍስ መንገድ የሚጓዙ መነኮሳት መገኛ ናቸው፡፡
በስራ ተግተውና በርትተው የሚታዩት መነኮሳቱ፣ የሚያጋጥማቸውን ፈተና በጾም ፣ በጸሎት በስግደት ያልፉታል፡፡
እኛም በጠንካራ ስራቸው ላይ አንዲት ጠጠር ብንጥል፣ከትጋታቸው ጋር ተደምራ ተአምር ትሰራለች፡፡
ገዳማቱን ስናለማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የሃይማኖት መሠረቷንም እናጸናለን፡፡
በመሆኑም ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ፣ በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡
በጉባኤው ሊቃነ ጳጳሳት፣ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያን፣ መምህራንና ዘማሪያን የሚገኙ ሲሆን፣ እርስዎም በጉባኤው ተሳታፊ እንዲሆኑ መንፈሳዊ ጥሪ ቀርቦሎዎታል፡፡
አዘጋጅ :- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
መግቢያ 100 ብር ብቻ
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
👉የመግቢያ ትኬቱን በእለቱም በዛው በሚሊኒየም አዳራሽም ማግኘት ይችላሉ።

❤6👍3
አሜሪካ በሩሲያ የኃይል ግዙፍ ኩባንያዎች የሆኑት በሮስኔፍት እና በሉኮይል ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች
የአሜሪካ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ "ያለ አንዳች ምክንያት ጦርነትን ለማስቆም ቭላድሚር ፑቲን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው" ብሏል።
ከዚያም ዶናልድ ትራምፕ "ከፑቲን ጋር የነበረኝን ስብሰባ ሰርዣለሁ። አሁን ጊዜው አይደለም። ወደፊት እናደርገዋለን" ብለው አስታውቀዋል።
ትራምፕ ይህንን የተናገሩት የኔቶ ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ማርክ ሩተ ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው። "ትክክል መስሎ አልታየኝም፤ መሄድ ባለብን አቅጣጫ እየሄድን ያለ አይመስልም ነበር" በማለት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ለውሳኔያቸው ምክንያቱን አብራርተዋል።

❤13👎5🥴1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
የምርጫ ውጤት ለህዝብ ማሳወቂያ ቀን ደግሞ ሰኔ 3 ቀን እንደሚሆንም ቦርዱ አስታውቋል።
ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ የጦፈ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳን ለፓርቲዎች ለውይይት አቅርቧል።
ለውይይት በቀረበው የጊዜ ሰሌዳው መሰረትም ህዳር ወር ውስጥ በምርጫ መወዳደር የሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ይመዘገባሉ ተብሏል።
የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለህዝብ ይፋ ማድረግ፤ ህዳር 19 ተጀምሮ በጥር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ለማጠናቀቅ ታስቧል።
የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ ደግሞ ከታህሳስ መጀመሪያ እስከ ጥር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ እንዲመዘገቡ በእቅዱ ላይ ተጠቅሷል።
እንዲሁም የምረጡኝ ቅስቀሳ ከታህሳስ 10 እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲከወን የታቀደ ሲሆን ከግንቦት 20 እስከ 23 ያሉት ሶስት ቀናት ደግሞ ቅስቀሳ የማይደረግባቸው ወይም የጽሞና ጊዜ እንዲሆኑ በሚል ቦርዱ ማሳወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
ግንቦት 24 ቀን መራጮች ድምጽ የሚሰጡበት ቀን ይሆናል የተባለ ሲሆ ከግንቦት 25 ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ደግሞ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።
በውይይቱ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ አመቺ እንዳልሆነ እና የሰላም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል ተብሏል።
@sheger_press

❤15👎4🤔1
Sheger Press️️
Photo
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ አለባቸው፡፡
ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸውን የይዘት አካባቢዎች ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ለፈተና ዝግጅት የሚደረግባቸውን የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ባዮሎጂ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ እና ኢኮኖሚክስ ናቸው ብለዋል፡፡
ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል ነው ያሉት፡፡
ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርት እና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን እንደሚሰጥ ጠቁመው ÷ አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ስለሆነም ተፈታኞች ፈተናውን በበይነ መረብ ለመፈተን እራሳቸውን ከወዲሁ ሊያዘጋጁ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

❤8🤔3👍2🥰1
Sheger Press️️
Video
ጥቅምት 16/2018 ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲመጡ እነዚህ መረጃዎች ላይ ግንዛቤ ይኑርዎት🙏
በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ውስጥ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ''ገዳማዊ ልማት ለቤተክርስቲያን ትሩፋት ''በሚል ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በዕለተ እሁድ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት ወደ አየር መንገድ በሚወሰደው መንገድ በኩል ያለው የክብር እንግዳ መግቢያ ጥሪ ለተደረገላቸው ፡እንግዶች ብቻ ሲሆን ጥሪ ከተደረገላቸው ውጪ በዚህ በር መጠቀም የተከለከለ ነው።
በእንግዶች የአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተቀኝ አቅጣጫ የመኪና ማቆሚያ ሲሆን ከዋናው መግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ፡ ቦታ በቀኝ በኩል የገዳሙ ምርቶች መሸጫ በግራ በኩል የመረጃ ዴስክ እና ቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ይገኛል። ወደ ዋናው መግቢያ በር በሁለት የተከፈለ ሲሆን ወንዶች በግራ አቅጣጫ ሴቶች በቀኝ አቅጣጫ ያሉትን በሮች ወደ አዳራሹ ለመግባት መጠቀም ይኖርባቸዋል።
በስናፕ ፕላዛ በኩል ያለው ሌላኛው መደበኛ መግቢያ ለምዕመናን ክፍት ሲሆን በመግቢያው በቀኝ አቅጣጫ የደህንነት የፍተሻ ጣቢያ ይገኛል። ምዕመናን ለፍተሻ በመተባበር ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ፡ በግራ አቅጣጫ የምመዕናን መኪና ማቆሚያ ተዘጋጅቷል። በቀኝ በኩል ያለው የደህነነት ጣቢያ እንዳለፉ በቀኝ እና በግራ በኩል የመጸዳጃ ቤቶች ይገኛሉ።
በአዳራሽ ፡ መግቢያ ፡ በር ፡ በቀኝ ፡ አቅጣጫ ፡ የመጀመሪያ ፡ የህክምና ፡ ፡ ዕርዳታ ፡ መስጫ ፡ ጊዜያዊ ፡ ክሊኒክ ፡ እና አምቡላንስ ፡ ይገኛሉ። በአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተግራ የመረጃ መስጫ ዴስክ እና የቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ፣ በስተቀኝ የገዳም ምርቶች መሸጫ ለምዕመናን ክፍት ናቸው።
የመጀመሪያ፡ የአዳራሽ ዋና መግቢያ እንዳለፉ ጸበል ጻድቅ ሲኖር ወደ አዳራሹ ለመግባት፡ ሁለት በሮች ሲኖሩ በግራ በኩል የወንዶች መግቢያ በቀኝ በኩል የሴቶች መግቢያ በመሆኑ ምዕመናን በመማሪያው መሰረት ይግቡ። ለአካል ፡ ጉዳተኞች ፡ ብቻ ፡ የተዘጋጁ ፡ መቀመጫዎች ይገኛሉ። ከመድረኩ ፊት ለፊት ያሉ መቀመጫዎች የአገልጋዮች ማረፊያ ቦታዎች ናቸው። አዳራሹ፡ 10,000 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ እንደመቻሉ በአስተባባሪዎች በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ምዕመናን በተዘጋጁ ወንበሮች መቀመጥ ይችላሉ።
መዝሙር 24:6 ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ። እንዳለ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
በዚህ ጉባኤ ላይ የገዳማውያኑን ጥሪ ተቀብላችሁ ለምትገኙ ሁሉ ክብርን ይስጥልን።
በቃሉ በረከት ፍሬ የምናፈራበት ይሁንልን።

❤15👍3
በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሠዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፣ 7ቱ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው‼️
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሠት ወረዳ ትላንት ምሽት በደረሠ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሠዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የቦሰት ወረዳ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር ሀላፊ ኢንስፔክተር ስለሺ በላይ አደጋው የተከሠተው መነሻውን ከአዳማ ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከአንድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በአደጋው ከሞቱት ሠዎች ውስጥ 7ቱ የ ህክምና ባለሙያዎች መሆናቸውንም የክልሉ ጤና ቢሮ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ አስታውቋል። ቢሮው በተጨማሪም ባለሙያዎቹ በአርሲ ዞን በአገልግሎት ላይ የነበሩ እና ለሞያ አቅም ማሻሻያ እና ፈተና ወደ ሀሮማያ ዩንቨርስቲ ሲጓዙ አደጋዎ መድረሱን ገልጿል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሠዎች በቦሰት ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እያገኙ መሆኑን የተነገረ ሲሆን የአደጋው መንስኤም በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑ ተጠቁሟል።
የወረዳው የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር ሀላፊው አክለውም አካባቢው በተለይም የወለንጪቲ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

❤31😢8😱1
ባለቤቱን “ድንቡሽቡሽ” ብሎ የጠራው ግለሰብ ለቅጣት ተዳረገ‼
የባለቤቱን ስልክ ‘በቁልምጫ’ ስም መዝግቦ የያዘው ቱርካዊው ግለሰብ ለቅጣት ተዳርጓል።
ስማቸው ያልተጠቀሰው ጥንዶች በቱርኳ ኡሳክ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፥ ሚስት ወፈር ባለው ሰውነቷ ሳቢያ ባል “ድንቡሽቡሽ” ብሎ መጥራቱን ተከትሎ ምቾት አልሰጠኝም በሚል ፍቺ ፈጽመዋል።
ከዚህ አልፎም ባለቤቷ ስልክ ቁጥሯን ተንቀሳቃሽ ስልኩ ላይ “ድንቡሽቡሽ” ብሎ መዝግቦ መያዙ ምቾት ያልሰጣት ሚስት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤተ ወስዳ ባለቤቷን ከሳዋለች።
ግለሰቧ የቀድሞ ባለቤቴ በሰውነት አቋሜ ተሳልቋል በሚል ፍርድ ቤት የመሰረተችው ክስ ተቀባይነት አግኝቷል።
በዚህም የቀድሞ ባለቤትህን የስልክ ቁጥር “ድንቡሽቡሽ” በሚል መጠሪያ በመመዝገብ በተክለ ሰውነቷ በመሳለቅ የሞራል ጉዳት አድርሰሃልና ለዚህ ቅጣት ይገባሃል ብለውታል ዳኛው።
ይህን ተከትሎም መጠኑ ያልተጠቀሰ የገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሁም የሞራል ካሳ ለቀድሞ ባለቤትህ ክፈል በሚል ተበይኖበታል።
ጉዳዩ በቱርክ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ገሚሱ የቁልምጫና የፍቅር መጠሪያ በመሆኑ ይህ አይገባውም ሲሉ፥ በርካቶች ደግሞ ጥቃቅን የቤተሰብ ጉዳዮች አደባባይ ወጥተው የፍርድ ቤት ቅጣት ማስከተላቸው አስገራሚም አሳዛኝ ነው ብለውታል ሲል ከራዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

🥴15❤12👍5🤔1
Sheger Press️️
Photo
ጥቅምት 16/2018 ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲመጡ እነዚህ መረጃዎች ላይ ግንዛቤ ይኑርዎት🙏
በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ውስጥ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ''ገዳማዊ ልማት ለቤተክርስቲያን ትሩፋት ''በሚል ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በዕለተ እሁድ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት ወደ አየር መንገድ በሚወሰደው መንገድ በኩል ያለው የክብር እንግዳ መግቢያ ጥሪ ለተደረገላቸው ፡እንግዶች ብቻ ሲሆን ጥሪ ከተደረገላቸው ውጪ በዚህ በር መጠቀም የተከለከለ ነው።
በእንግዶች የአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተቀኝ አቅጣጫ የመኪና ማቆሚያ ሲሆን ከዋናው መግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ፡ ቦታ በቀኝ በኩል የገዳሙ ምርቶች መሸጫ በግራ በኩል የመረጃ ዴስክ እና ቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ይገኛል። ወደ ዋናው መግቢያ በር በሁለት የተከፈለ ሲሆን ወንዶች በግራ አቅጣጫ ሴቶች በቀኝ አቅጣጫ ያሉትን በሮች ወደ አዳራሹ ለመግባት መጠቀም ይኖርባቸዋል።
በስናፕ ፕላዛ በኩል ያለው ሌላኛው መደበኛ መግቢያ ለምዕመናን ክፍት ሲሆን በመግቢያው በቀኝ አቅጣጫ የደህንነት የፍተሻ ጣቢያ ይገኛል። ምዕመናን ለፍተሻ በመተባበር ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ፡ በግራ አቅጣጫ የምመዕናን መኪና ማቆሚያ ተዘጋጅቷል። በቀኝ በኩል ያለው የደህነነት ጣቢያ እንዳለፉ በቀኝ እና በግራ በኩል የመጸዳጃ ቤቶች ይገኛሉ።
በአዳራሽ ፡ መግቢያ ፡ በር ፡ በቀኝ ፡ አቅጣጫ ፡ የመጀመሪያ ፡ የህክምና ፡ ፡ ዕርዳታ ፡ መስጫ ፡ ጊዜያዊ ፡ ክሊኒክ ፡ እና አምቡላንስ ፡ ይገኛሉ። በአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተግራ የመረጃ መስጫ ዴስክ እና የቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ፣ በስተቀኝ የገዳም ምርቶች መሸጫ ለምዕመናን ክፍት ናቸው።
የመጀመሪያ፡ የአዳራሽ ዋና መግቢያ እንዳለፉ ጸበል ጻድቅ ሲኖር ወደ አዳራሹ ለመግባት፡ ሁለት በሮች ሲኖሩ በግራ በኩል የወንዶች መግቢያ በቀኝ በኩል የሴቶች መግቢያ በመሆኑ ምዕመናን በመማሪያው መሰረት ይግቡ። ለአካል ፡ ጉዳተኞች ፡ ብቻ ፡ የተዘጋጁ ፡ መቀመጫዎች ይገኛሉ። ከመድረኩ ፊት ለፊት ያሉ መቀመጫዎች የአገልጋዮች ማረፊያ ቦታዎች ናቸው። አዳራሹ፡ 10,000 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ እንደመቻሉ በአስተባባሪዎች በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ምዕመናን በተዘጋጁ ወንበሮች መቀመጥ ይችላሉ።
መዝሙር 24:6 ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ። እንዳለ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
በዚህ ጉባኤ ላይ የገዳማውያኑን ጥሪ ተቀብላችሁ ለምትገኙ ሁሉ ክብርን ይስጥልን።
በቃሉ በረከት ፍሬ የምናፈራበት ይሁንልን።
መግቢያ 100 ብር ብቻ
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44
👉የመግቢያ ትኬቱን በእለቱም በዛው በሚሊኒየም አዳራሽም ማግኘት ይችላሉ።
በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ውስጥ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ''ገዳማዊ ልማት ለቤተክርስቲያን ትሩፋት ''በሚል ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በዕለተ እሁድ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት ወደ አየር መንገድ በሚወሰደው መንገድ በኩል ያለው የክብር እንግዳ መግቢያ ጥሪ ለተደረገላቸው ፡እንግዶች ብቻ ሲሆን ጥሪ ከተደረገላቸው ውጪ በዚህ በር መጠቀም የተከለከለ ነው።
በእንግዶች የአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተቀኝ አቅጣጫ የመኪና ማቆሚያ ሲሆን ከዋናው መግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ፡ ቦታ በቀኝ በኩል የገዳሙ ምርቶች መሸጫ በግራ በኩል የመረጃ ዴስክ እና ቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ይገኛል። ወደ ዋናው መግቢያ በር በሁለት የተከፈለ ሲሆን ወንዶች በግራ አቅጣጫ ሴቶች በቀኝ አቅጣጫ ያሉትን በሮች ወደ አዳራሹ ለመግባት መጠቀም ይኖርባቸዋል።
በስናፕ ፕላዛ በኩል ያለው ሌላኛው መደበኛ መግቢያ ለምዕመናን ክፍት ሲሆን በመግቢያው በቀኝ አቅጣጫ የደህንነት የፍተሻ ጣቢያ ይገኛል። ምዕመናን ለፍተሻ በመተባበር ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ፡ በግራ አቅጣጫ የምመዕናን መኪና ማቆሚያ ተዘጋጅቷል። በቀኝ በኩል ያለው የደህነነት ጣቢያ እንዳለፉ በቀኝ እና በግራ በኩል የመጸዳጃ ቤቶች ይገኛሉ።
በአዳራሽ ፡ መግቢያ ፡ በር ፡ በቀኝ ፡ አቅጣጫ ፡ የመጀመሪያ ፡ የህክምና ፡ ፡ ዕርዳታ ፡ መስጫ ፡ ጊዜያዊ ፡ ክሊኒክ ፡ እና አምቡላንስ ፡ ይገኛሉ። በአዳራሽ ዋና መግቢያ በስተግራ የመረጃ መስጫ ዴስክ እና የቅሬታ ማቅረቢያ ዴስክ ፣ በስተቀኝ የገዳም ምርቶች መሸጫ ለምዕመናን ክፍት ናቸው።
የመጀመሪያ፡ የአዳራሽ ዋና መግቢያ እንዳለፉ ጸበል ጻድቅ ሲኖር ወደ አዳራሹ ለመግባት፡ ሁለት በሮች ሲኖሩ በግራ በኩል የወንዶች መግቢያ በቀኝ በኩል የሴቶች መግቢያ በመሆኑ ምዕመናን በመማሪያው መሰረት ይግቡ። ለአካል ፡ ጉዳተኞች ፡ ብቻ ፡ የተዘጋጁ ፡ መቀመጫዎች ይገኛሉ። ከመድረኩ ፊት ለፊት ያሉ መቀመጫዎች የአገልጋዮች ማረፊያ ቦታዎች ናቸው። አዳራሹ፡ 10,000 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ እንደመቻሉ በአስተባባሪዎች በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ምዕመናን በተዘጋጁ ወንበሮች መቀመጥ ይችላሉ።
መዝሙር 24:6 ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ። እንዳለ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
በዚህ ጉባኤ ላይ የገዳማውያኑን ጥሪ ተቀብላችሁ ለምትገኙ ሁሉ ክብርን ይስጥልን።
በቃሉ በረከት ፍሬ የምናፈራበት ይሁንልን።
መግቢያ 100 ብር ብቻ
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44
👉የመግቢያ ትኬቱን በእለቱም በዛው በሚሊኒየም አዳራሽም ማግኘት ይችላሉ።
❤26
"ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለ #ዶቸ_ቬለ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳይሰሩ መታገዳቸውን" ተቋሙ አስታወቀ
"ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለዶቸ ቬለ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳይሰሩ ለጊዜዉ መታገዳቸውን" ሚዲያው አስታወቀ።
ዶቼ ቬለ ማምሻውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ በፃፈዉ ደብዳቤዉ ዶቼ ቬለና ወኪሎቹን የኢትዮጵያን ሕግና ደንብ ጥሰዋል፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አያከብሩም በማለት ወቅሷል" ሲል አስታውቋል።
የሚዲያ ተቋሙ በመግለጫው ከ1980ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ ዘጋቢዎች አማካይነት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊና ማሕበራዊ ጉዳዮችን እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ አካባቢያዊ፣ አሐጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ተቋማትና ማሕበራትን እንቅስቃሴና ክንዋኔዎችን ሲዘግብ መቆየቱን አስታውሷል።
እንዲሁም "ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የወኪሎቹን ቁጥር በማሳደግ መቀሌ፣ ባሕርዳር፣ ደሴ፣ አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋና አሶሳ በሚገኙ 9 ወኪሎቹ አማካይነት መረጃዎችን በማሰባሰብ ገለልተኛ፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ ዘገባዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያሰራጭ መቆየቱን" መግለጫው አመልክቷል።
ይሁንና "የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ በፃፈዉ ደብዳቤዉ ዶቼ ቬለና ወኪሎቹን የኢትዮጵያን ሕግና ደንብ ጥሰዋል፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አያከብሩም በማለት ወቅሷል" ሲል መግለጫው ገልጧል።
በመሆኑም "ከዛሬ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚገኙ የዶቸ ቬለ ዘጋቢዎችን የሥራ ፈቃድ ለጊዜዉ ማገዱን" የገለፀው መግለጫው "ባለሥልጣኑ ጊዚያዊ ያለዉ እግዳ ሥለሚቆይበት ጊዜ የገለፀዉ ነገር አለመኖሩን" አክሏል።

❤12👎10👍2🤔1🤬1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው ለተለያዩ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ምደባ አከናውኗል።
በዚህ መሠረት
ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ኬሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ።
ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ
ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ በሁለተኛ ቀን የጉባኤው ውሎው ወስኗል።

❤18👍3