Telegram Web Link
Sheger Press️️
Photo
ዘ አፍሪካ ማሪታይም ኮንፈረንስ 2025 ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2018ዓ.ም ይካሄዳል

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የባህር አጠቃቀም መሰረት የሚጥል ዘ አፍሪካ ማሪታይም 2025 ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ እንደሆነ ተገልጿል

ዘ አፍሪካ ማሪታይም ኮንፈረንስ 2025 የመላው አፍሪካ መሪዎች እና በአለም አቀፍ የባህር ላይ ጭነት ማጓጓዣ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ መሪዎችን የሚያሳትፈው ይህ ኮንፈረንስ "አፍሪካ- ቀጣይ የአለም አቀፍ የመርከበኞች ግንባር" በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተነግሯል፡፡

ዋይ ሲ ኤፍ ማኒንግ ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ጋር በአጋርነት የሚያዘጋጀው ይህ  የሶስት ቀናት ዝግጅት፣ አፍሪካ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን ያካተተ የባሕር ላይ የሰው ኃይል ለመገንባት በጋራ በምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍን መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

ጉባኤው ሚኒስትሮችን፣ የቁጥጥር አካላትን፣ የመርከብ አስተዳደር ኃላፊዎችን፣ የባሕር ላይ አካዳሚዎችንና የልማት አጋሮችን የሚያሰባስብ ሲሆን፣ ኮንፈረንሱ ራዕይ ፖሊሲ እና አጋርነትን ለማቀራረብ አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የባሕር ላይ ኢኮኖሚ ቋሚ አበርክቶ እንዳላት ለማሳየት ያለመ እንደሆነ በመግለጫው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ፌይሳ ጉባኤውን እንደሚከፍቱ የተገለፀ ሲሆን፣ መንግሥታት የሥልጠና፣ የሥራ ዕድልና ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚያገናኝ ዘላቂ የባሕር ላይ ሥነ-ምህዳር ለመገንባት ያለውን ስትራቴጂያዊ ቁርጠኝነት ያቀርባሉ፡፡

የጉባኤው መርሐ ግብር ከራዕይ ወደ ተግባር እና ወደ ፖሊሲ ለመሸጋገር በሚያስችል መልኩ የተዋቀረ ሲሆን፦
በቀን 1 – ራዕይን ማስቀመጥ:- አፍሪካ በባሕር ላይ ያላትን ፍላጎት መቅረጽ እና ለአኅጉራዊ የመርከበኞች አጀንዳ መሠረት መጣልን

በቀን 2 - የኢንዱስትሪ እና የአካዳሚ የውይይት መድረክ:- ዓለም አቀፍ ቀጣሪዎች ከአፍሪካ የባሕር ላይ አካዳሚዎች ጋር የሚገናኙበት እድሎችን እና አቅም የሚገናኙበት መድረክ መፍጠር።

በቀን 3 – ፖሊሲና አስተዳደር:- ህብረት የለው የአፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት ዕጣ ለማምጣት ብሔራዊ ማዕቀፎችን፣ ደንቦችን እና ዲፕሎማሲን ማጣጣም ይካሄዳል ።

የአፍሪካ የባሕር ላይ ጉባኤ ሰብሳቢና የዋይ ሲ ኤፍ ማኒንግ ሊሚትድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ፍራንስ ጆበርት እንዳሉት "የአፍሪካ ታላቅ የባሕር ላይ ሀብት ሕዝቦቿ ናቸው። ይህ ጉባኤ እምቅ አቅምን ወደ ዕድል በመቀየር አፍሪካውያን መርከበኞች በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ በልበ ሙሉነት እና በተወዳዳሪነት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን በመገንባት ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

በመግለጫው ኢትዮጵያ የአስተናጋጅነት ሚና መውሰዷ በአፍሪካ የባሕር ላይ የሥልጠና ተቋም (EMTI) እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ላይ የልህቀት ማዕከል በኩል በባሕር ላይ ትምህርት ላይ እያደረገች ያለችውን እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት እንደሚያንፀባርቅ ተገልጿል።

የዘንድሮው የአፍሪካ የባሕር ጉዳይ ጉባኤ 2025 ከጉባኤው ባሻገር በመንግሥታት፣ በኢንዱስትሪና በአካዳሚዎች መካከል ያለውን ተሳትፎና አጋርነት ለማስቀጠል ያለመ መድረክ የሆነውን የአፍሪካ የባሕር ላይ ትብብር መረብ በመመስረት ይጠናቀቃል።
17👎1
የእስራኤልና የሐማስ የሰላም ዕቅድ በግብፅ ተፈረመ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከበርካታ የዓለም መሪዎች ጋር በመሆን በጋዛ ሰርጥ የሚካሄደውን ግጭት በአንዴ ለማቆም ያለመውን እና በእስራኤልና በሐማስ ታጣቂ ቡድን መካከል ዘላቂ ሰላም የሚፈጥረውን ዕቅድ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በይፋ ፈርመዋል።

ይህ ስምምነት በሁለቱ ወገኖች መካከል የቆየውን ውጥረት ሙሉ በሙሉ ለማብቃት እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምን ለማስፈን እንደ ትልቅ ምዕራፍ የሚታይ ታሪካዊ እርምጃ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

ፊርማው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሰላም የወሰደውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ዕቅዱም የረጅም ጊዜ መፍትሔዎችን እንደሚይዝ ይጠበቃል።

@sheger_press
@sheger_press
18👏4🤯1
9🙏7
Sheger Press️️
Photo
ዘወትር አርብ በዘውዱ ፋንታ የእሾህ አክሊል ይደፋ ነበር

ሀገራችን ከ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ሃይማኖታዊ አስተዳደር ጐልቶ የሚታይባት ነበረች። በተለይ 11ኛውና 12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ እጅግ የሚገርም ሃይማኖታዊ መንግስት የመሰረተችበት ወቅት ነበር።

በዘመናቱ የነበሩት የዛጉዌ ስርወ መንግስት አስተዳዳሪች ፍፁም ክርስቲያናዊ ከመሆናቸውም በላይ የሀገሪቱ መሪዎች ካህናት ነበሩ። ከእነዚህ አንዱ ገናናው የኢትዮጵያ መሪ ቅዱስ ላሊበላ ንግስናን ከቅስና ጋር አጣምሮ የያዘ ሰው ነበር። ንጉስ ሆኖ አገርና ህዝብ ይመራል፤ ቄስ ሆኖ ደግሞ በአብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ ያገለግላል። ከቅዱስ ላሊበላ በፊት የነበሩት ቅዱስ ሐርቤይ፣ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስና ከእርሱ በኋላ የነገሠው ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ቅስናና ንግስናን አስተባብረው ይዘው ነበር። እነዚህ መሪዎች በሃይማኖታዊ ሰውነታቸው ሰርተዋቸው ካለፉ ነገሮች መካከል ድንቅ ኪነ-ሕንፃ ያላቸው አቢያተ ክርስቲያናትና መልካም አስተዳደር ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ ታሪካቸው ያወሳል።

በዛግዌ ሥርወ መንግስት የዓፄ ላሊበላ ተከታይ ንጉስ ነአኩቶ ለአብ ለቅዱስ ላሊበላ የወንድሙ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ሐርቤይ እናቱ መርኬዛ ይባላሉ። ጻድቁ፤ ንጉስ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥታና ጽላት ቀርጻ ቤተክርስቲያን አሳንጻ ከምታከብራቸው አራት የዛጉዌ ነገስታት አንዱ። ለ40 ዓመታት የነገሰው ነአኩቶ አሁን ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ ባለበት ስፍራ ሁሌም አርብ አርብ ቀን የክርስቶስን ህማም እያሰበ በዘውዱ ፋንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ፤ 5 ጦር ዙሪያውን ተክሎ እየደማ እያለቀሰ ሲጸልይ ሲሰግድ ይውል ነበር። አንድ ቀንም ጌታችን ተገለጾለት ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ እኔ ለዓለም ደሜን ያፈሰስኩት አንድ ቀን ነው፤ አንተ ግን 40 ዓመት ሙሉ ደምህንንና እንባህን ስታፈስ ኖርክ ይበቃሃል፤ አሁን ወደ እኔ ልወስድህ ነው አለው፡፡

ነአኩቶ ለአብም ጌታዬ ሆይ እዚህ ቦታ እኔን ብለው የሚመጡትን ወገኖቹን ሁሉ ማርልኝ ሲል ጠየቀው፡፡ ጌታም እውነት እልሃለው ቦታህን ባይረግጥ ዝክርህን ባያዘክር እንኳን ዝናህን ሰምቶ ያሰበህን ኃጢያቱ ምን ቢበዛ እምርልሃለው፤ ዳግመኛም እልሃለው 40 ዓመት ሙሉ እንባህን ያፈሰስክባት ይህች ድንጋይ እስከ እለተ ምጽአት እያነባች ትኖራለች ከዚህ ለሚጠጡ ለሚጠመቁ ድህነት ይሁናቸው ብሎታል። ዛሬም ድረስ በነአኩቶ ለአብ ቤተክርስቲያን ከጣራው ስር ባሉ ጎድጓዳ ድንጋዮች ውስጥ እየቆየ ክረምት ከበጋ ጠብ የሚለው ጸበል አይቋረጥም እንዲያውም በበጋ መጠኑ ይጨምራል። ምን ቢሞላም በፍጹም ሞልቶ ተርፎ አይፈስም፡፡ ከላሊበላ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 6 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኘው ቤተርክስቲያኑ በመጠን አነስተኛ ሲሆን ከተሰራ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ከበላዩ ዋሻ ሳይደርቅ በሚፈስ የምንጭ ውሃው ይታወቃል።

በቤተርክስቲያኑ ጥንታዊ መጻሕፍት፣ መስቀሎችና ሙዳዮችን ጨምሮ ድንቅ ቅርሶች ይገኛሉ። ገድሉ እንደሚነግረን፣ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አሸተን ማርያምን አንጾ ከጨረሰ በኃላ በካሕን ሥርዓት ቤተክርስቲያኑን ሲያጥን በርካታ ቅዱሳን እጣኑን አሽትተው በቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቅጥቅ ብለው ቆሙ፤ እርሱም በመገረም እናንተ ደግሞ እንዴት መጣችሁ አላቸው እነርሱም እጣኑን አሽትተን አሉት በዚህም የተነሳ “አሸተን ማርያም” ተብላለች። በቅድስና ሲያገለግል ኖሮም በ70 ዓመቱ ህዳር 3 ቀን አርፏል ቢልም ገድሉ፣ እንደ ሄኖክ ማረጉን ይናገራል። በተሰጠው ቃልኪዳን የሚታመኑ ገዳማውያን እንደርሱ እንዲያጸናቸው ይማጸኑታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
22🥰5🤯1
በአፍሪካዊቷ ሀገር ማዳጋስካር ምን ተፈጠረ?

- ከ15 ቀን ገደማ በፊት የማዳጋስካር ወጣቶች የመሩት ተቃውሞ ይቀሰቀሳል። ይኸው ተቃውሞው በዋና ከተማዋ አንታናናሪቮ ካለ የኃይል መቆራረጥ እና የውሃ እጥረት ጋር የሚያያዝ ነበር። የወጣቶቹ ተቃውሞ ' Gen Z Madagascar ' የሚል ስያሜ ነበረው።

- በኃላ የወጣቶቹ ተቃውሞ ቁጣ የታከለበትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ ሙስና እንዲያበቃ ፣ የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል ወደመጠየቅ ተሸጋገረ።

- የመንግሥት ምላሽ የነበረው ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ መበተን፣ የሰዓት እላፊ መጣል፣ ሰልፈኞች ላይ መተኮስ ሆነ። በተቃውሞ 22 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ተጎድተዋል።

- የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆኤሊና መንግስታቸውን በትነው ወታደራዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ፣ ጄነራል ሩፊን ፎርቱናት የሚባሉ። ግን አለመረጋጋቱ ለሚቆም አልቻለም።

- አንድ የማዳጋስካር የጦር ክንፍ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀቀለ። ከፕሬዜዳንቱ ትእዛዝ ማቀበል አቆመ። ይኸው ኃይል ወደ ተቃዋሚዎች ምንም እንዳይተኮስ አዘዘ። ፕሬዚዳንቱም ሁኔታውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ ገለጹ።

- ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ የት እንዳሉ ባይታወቅም ፤ አንዳንድ ሪፖርቶች ግን በፈረንሳይ ወታደራዊ አውሮፕላን በሞሪሺየስ አድርገው ወደ ዱባይ ሄደዋል ብለዋል።

መረጃው tikbah ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበው ነው።

@sheger_press
@sheger_press
30👏7
ትራዎሬ ከ 23ተኛ የግድያ ሙከራ ተረፈ

የቡርኪናፋሶው ጥቁር አልማዝ ካፒቴን ኢብራሂም ትራዎሬ ከ22ተኛ የግድያ ሙከራ በተዓምረኛ የደህንነት መዋቅሩ በህይወት መትረፍ ችሏል።

የቡርኪና ፋሶን ማዕድናት ያለከልካይ በመቦጥቦጥ ሀገሪቷ ላይ እንደ ጥገኛ ፓራሳይት ተጣብተው ደሟን ሲመጡ የነበሩት ምዕራባውያንን  እርዳታችሁንም ድጋፋችሁንም አንፈልግም፣ እናንተ ካልሰረቃችሁን የሀገሬ ቡርኪና ማዕድን ከህዝቧ አልፎ ለመላ አፍሪካውያን ይተርፋል፣ ፊታችሁን ሳታዞሩ ሀገሬን ለቃችሁ ውጡ ብሎ  በቀጭን ትዕዛዝ ጠራረጎ ባባረራቸው ትራዎሬ ጥርስ ነክሰው በሳለፍነው ሳምንት 22ኛቸው የሆነውን ኦፕሬሽን ለመፈጸም በቅድመ ዝግጅት ላይ የነበሩ ቅጥረኛ ሰላዮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ የሆላንድ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በአስተዳዳሪውና በምክትሉ እንዲሁም በሰራተኞቹ በኩል ትራዎሬን ማስገደልና ከስልጣን ለመገርሰስ ሲንቀሳቀሱ በደህንነት ተቋሙ መያዛቸውን ተከትሎ  የቡርኪናፋሶ የደህንነት ተቋም በምርመራው ያገኘው መረጃ እጅግ አስገራሚና በእርግጥም ትራዎሬ ከምዕራቦቹ አቅም በላይ የሆነ የዚህ ትውልድ ቶማስ ሳንካራ ነው አስብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
77🥰12
#ETHIOPIA🇪🇹

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባዉ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።

ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ በይፋ ታትሞ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ልማት የመጠቀም ጥረቷን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል።

ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ማዕቀፎች መሰረት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች የመጠቀም ሀገራዊ ጥረትን የመምራትና የማስተባበር ዋነኛ ኃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል።

ትኩረት አድርጎ የሚሠራባቸው ቁልፍ ዘርፎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ሳይንስና ምርምር መሆናቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።


@sheger_press
@sheger_press
28👏5👍1
"አሁን መልሶ ግንባታ እንጀምራለን"- ዶናልድ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።

በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።

ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።

"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።

በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።

ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።
"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።

"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።

ትራምፕ የሰላም ዕቅዱ ሁለተኛ ክፍል ተጀምሯል ብለዋል።

ትራምፕ በግብፁ ውይይት ላይ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው። እዚህ ለመድረስ 3,000 ዓመታት መውሰዱን ታምናላችሁ? ብለዋል።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፋታሕ አል-ሲሲ በአገራቸው ትልቁ የሆነውን 'ኦርደር ኦፍ ዘ ናይል' ሽልማት ለትራምፕ ሰጥተዋል።
አል-ሲሲ "አስከፊው ጊዜ ያከተመበት ታሪካዊ እርምጃ ነው" ሲሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ገልጸዋል።

@sheger_press
@sheger_press
14👍4
14
Sheger Press️️
Photo
ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ቢሆንም እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው፡፡

የትውልድ ሃገሩ ሶርያ ውስጥ ሮሃ አካባቢ ነው፡፡ ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው፣ ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት፣ ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ፡፡ ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ፣ ከአዳም እስከ ኖኅ፣ ከአብርሃም እስከ ሙሴና ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አገናኘችው፡፡ ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች፡፡ ይህም በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት ምሥጢራትን የተመለከተ እየተባለ እንዲጠራ አድርጎታል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በሰማይ በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል፡፡

በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት፣ ከሰማይ ንግሥት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል፡፡ "የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል፡፡ የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ 7 እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ፡፡ አንድ አረጋዊ፣ ጽሕሙ ተንዠርግጐ፣ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ፣ በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን በበገናው ሊያመሰግን ጀመረ፡፡ "አቤቱ ጌታችን በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ" ሲል መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት፡፡ በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ፡፡

ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ፡፡ ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ አምላካችን እግዚአብሔር እንደልቤ ያለው በርካታ ሀብትም የሰጠው ልበ-አምላክ፣ ጻድቅ፣ የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ ዳዊት ነበር፡፡ አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሰምቷልና፡፡ በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል፡፡ እመ-ብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጎርጎርዮስን አመስግናዋለች፡፡ ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች:: "ልጆቼ ሆይ! ከብርሃን ጨለማን፣ ከደግነት ክፋትን፣ ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን ምነው መምረጣችሁ? እኔ ስለ እናንተ በየቀኑ እየለመንሁ እነሆ አለሁ:: ወደ ጨለማ ገሃነም እንዳትወርዱ እባካችሁ ንስሐ ግቡ!" ስትል መልዕክቷን አስተላለፈች፡፡

ድንግል በክልኤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ለቅዱሱ ሰው ነግራው፣ ቅዱስ ዳዊትን አስከትላ በግሩማን መላእክት ታጅባ የእሳት መጋረጃዎች ወደ ተተከሉበት ድንኳን ገባች፡፡ በዚያም ተመሰገነች፡፡ ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫም "ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት፣ ወይብልዋ፣ በሐኪ ማርያም ሐዳሲሁ ጣዕዋ"፤ “መላእክት ማርያምን በመጋረጃዎች ውስጥ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል እያሉ አመሰገኗት” የሚለውም ለዚህ ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከሰማይ ቆይታው መልስ ያየውን ሁሉ ጽፎ ለአበው ሰጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አባቶቻችን ረዓዬ ኅቡዓት “ምሥጢራትን ያየ” አባት ይሉታል፡፡ ቅዱሱ ተረፈ ዘመኑን በተጋድሎ ፈጽሞ መጋቢት ሁለት ቀን አርፏል፡፡

የቅዱሳን እናታቸው ድንግል እመ ብርሃን መዓዛ ፍቅሯን ታብዛልን፡፡ በቅድስና ሕይወት፣ በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን ቅዱሳንና ገዳማውያን እደግፍ በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
40🤬2👍1
አንድ ዶላር 148 ብር ተሸጠ‼️

አንድ የአሜሪካ ዶላር በ148 ብር ጨረታ ተሸጠ‼️
ብሔራዊ ባንክ የ150 ሚሊዮን ዶላር ውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል።

ባንኩ መሰል ጨረታ ሲያወጣ ለ10ኛው ዙር ሲሆን በዚህ ዙር 150 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ለመሸጥ አቅርቧል።

በጨረታው የአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148.1007 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። / 1 ዶላር በ148.1007 ተሽጧል /

ይህ አዲስ አማካኝ ዋጋ ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 138.2 ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር፣ የ9 ብር ከ90 ሳንቲም ወይም የ 7.16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ዛሬ በተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ድልድል 31 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ጨረታው ላይ ተሳትፈው በሽያጩ ተሳትፈዋል ተብሏል።

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በሚፈቅደው ጊዜ ተመሳሳይ ጨረታዎችን እቀጥላለሁ ብሏል።
13😱8👌4
2025/10/19 01:23:51
Back to Top
HTML Embed Code: