Telegram Web Link
🙏155
Sheger Press️️
Photo
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምልጃ እና በረከት አይለየን🙏

ጥቅምት 5 ቀንም ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው

ዓይናችን በገለጽንበት ቅጽበት ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፈው ሁሉ አባታችን በተወለዱ ጊዜ አንደበታቸው ከምስጋና የተገኘ፣ ስለሀገራችን መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው የጸለዩ፣ ገና በ3 ዓመታቸው በገዳም መኖር የጀመሩና ከማሕጸን ጀምሮ ለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የተለዩ፣ ከተወለዱ ጀምሮ እህል ያልቀመሱ፣ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩ፣ ከጌታችን ጋር መሞት አይገባኝም ብለው የተከራከሩ ታላቅ ቋድቅ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ሠላሳ ሦስት ዓመት በትዳር ሲቆዩ በሩካቤ ስጋ የተዋወቁት ልጅ እንዲሰጣቸው ለሦስት ቀናት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ መጋቢት 29 ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡

ወዲያውም ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገዶ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን “ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው” አለውና ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ከአዳም ጀምሮ ያሉ ቅዱሳንም ሁሉ ባረኩት፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ላሉበት ገዳም ሰጣቸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔርም አጸናው አበረታው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደውና ሕፃኑን ከበር ላይ አስቀምጦ ምግቡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ነገረው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን አስገብቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ አሳደገው፡፡ ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ተቀብሎ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሥራው የተቃና ሆነ፡፡

አባ ዘመድ ብርሃንም እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸው፡፡ እግዚአብሔርም ከባረካቸው በኋላም ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር እንዲኖሩ፣ እንስሳቱም የእግራቸውን ትቢያ እየላሱ እንደሚኖሩ ነገራቸው፡፡ ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም ከኖሩ በኋላ በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለ ኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጸሎታቸውም ብዙ እልፍ ነፍሳትን አስምረዋል፡፡

ሦስት መቶ ዓመት ከኖሩ በኋላም ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ደብር ቅዱስ የሚባለው ዝቋላንም አሳያቸው፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመሥታወት እንደሚያይ አባታችንም የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአታቸውን በግልጽ በተመለከቱ ጊዜ ተወርውረው ወደ ባሕሩ በመግባት የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየዋል፡፡ ጌታችንም መጥቶ ኢትዮጵያን ምሬልሀለሁ ውጣ አላቸው፡፡ ሲወጡም ሰውነታቸውን ዳሶ አደሳቸው፡፡ ጥቅምት 5 ቀንም ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በሀገራችን 262 ዓመታት በጸሎትና በትምህር እየቀዱሱዋት፣ አጋንንትን እያሳደዱ ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው መጋቢት አምስት አርፈዋል፡፡

በቅዱሳኑ ምልጃ ያመንን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
🙏267👍5
የብር የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል መጨረሻው እስከ የት ድረስ ነው?

"የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ እንዲመራ" ከመደረጉ ጥቂት ቀናት በፊት የአንድ ዶላር ዋጋ Jan 1,2024 ላይ ብር 56.4777 የነበር ሲሆን፣ ከ7 ወር በኋላ July 30,2024 ላይ የአንድ ዶላር ዋጋ ብር 57.8338 ሆኗል።

የአንድ ዶላር ዋጋ በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ ያሳየው ጭማሪ በብር 1.3561 ሲሆን፣ በመቶኛ 2.40% ብቻ ነው።

July 31 2024 ላይ "የውጭ ምንዛሪ በገበያ" እንዲመራ ከተደረገ ከሁለት ቀን በኋላ የአንድ ዶላር ዋጋ በብር 17.59 በመቶኛ ደግሞ 31.15 % እንዲጨምር ተደርጓል።

Octobe 14, 2025 በተደረገው ጨረታ የአንድ ዶላር ዋጋ ብር 148.1007 የደረሰ ሲሆን፣ ከJuly 30,2024 በኋላ ማለትም "የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ" እንዲመራ ከተደረገ ከ1 ዓመት ከ2 ወር ከ15 ቀን በኋላ 162.23 % ወይም በብር 91.62 ጨምሯል።

ካለፈው ጨረታ June 5, 2025 ላይ ከተደረገው ጋር ሲነጻጸርም በ5 ወር ውስጥ ብር 13.1488 ወይም 9.74% ጨምሯል" ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያው ሙሸ ሰሙ ገልጸዋል።
(ቀሪ ማጣቀሻና ገለጻቸው ከላይ ተያይዟል
13😢13👍3😱1
ያለፈቃድ ደመወዝ መቁረጥ‼️

የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ።

ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል።
ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው።
ተቋሙ ከህግ ውጪ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው የሚቆረጥባቸው ገንዘብ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበልኝ ነው ብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ከደመወዛቸው ላይ ገንዘብ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነግረውኛል ብሏል።

በተመሳሳይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞንም በተለያዩ ወረዳዎች የሚሰሩ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተነግሯል።

ይህም የችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል ብሏል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫ።

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ስምምነቱን በፅሁፍ ሲገልፅ፣በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይንም በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ ደሞዙን መቁረጥም ሆነ መያዝ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

ችግሩ አለ ተብሎ ቅሬታ በቀረበባቸው አካባቢዎችም አስቸኳይ እርምት ሊደረግ ይገባል ሲል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳስቧል።
ሸገር

@sheger_press
@sheger_press
24🔥1
መኪናውን አቁሞ ኮሪደር ልማቱ ላይ ሽንት
ሲሸና የነበረ ግለሰብ ተያዘ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተማዋን ውብና ፅዱ የማድረግ ዕቅድን ለማሳካት፣ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ ልዩ ስሙ ወሎ ሰፈር አካባቢ ከዋናው አየር መንገድ አጠገብ ባለው የኮሪደር ልማት አካባቢ መኪናውን አቁሞ ሽንት ሲሸና የነበረ ግለሰብ ተይዟል።

* ተግባር፡
ግለሰቡን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር አውሏል።

* ቅጣት፡
በፈፀመው የደንብ መተላለፍ መሰረት 2,000 (ሁለት ሺህ) ብር እንዲቀጣ ተደርጓል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣኑ፣ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም፣ ማንኛውም ደንብ ተላላፊ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ባለስልጣኑ፣ ማንኛውም የደንብ መተላለፍ ሲመለከት ኅብረተሰቡ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

@sheger_press
@sheger_press
10🥴6😱4
ከሰሞኑ ተዋቂዉ ሙዚቀኛ አንዶለም ጎሳ በዱባይ ኮንሰርት ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል ፡፡
ታዲያ ብዙዎች ጉዳዩን ከቀድሞ ባለቤቱ ቀነኒ አዱኛ አሞሞት ጋር ተያይዞ ጥያቄዎችን እያነሱ ነዉ ፡፡
አንድ ሰሞን ለልጃቸዉ ፍትህን ሲጠይቁ የነበሩ ቤተሰቦች እና አንዶለም ጎሳ ከምን ደርሰዉ ዝምታን መረጡ?
አባገዳዎች የገቡበት ሚስጥራዊ ሽምግልና
👇👇👇 ዝርዝር ይዘናል
https://youtu.be/YiHXeS7Vsm8?si=ahj7qfEFK0hnwphd
8👎4🤔1
Sheger Press️️
Photo
የማይታየው አምላክ ቢወርድ በምቀኝነት ገደሉት

በዘመነ ሐዋርያት ከነበሩና አስደናቂ ታሪክ ከነበራቸው ቅዱሳን አንዱ ይህ አባት ነው:: ትውልዱ ግሪካዊ ሲሆነ ከነአሪስቶትል ሲያያዝ የመጣውን ፍልስፍና ጨርሶ በማጥናቱ የፈላስፎች አለቃ የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር:: በግሪክ አቴንስ ለነበሩ ፈላስፎችም ሁሉ የበላይ ሲሆን በአርዮስፋጐስ ታላቁ ሰው እርሱ ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እድሜው ገና ወጣት ነበር ቅዱስ ዲዮናስዮስ፡፡ በግሪክ ምድር ከሚመለኩ 250 አማልክት መካከል ቁም ነገር አላገኘምና ፈላስፋ ስለ ሆነ ሁሌ ይመራመር ይልቁንም ስለ እውነተኛው አምላክ ያስብ ነበር፡፡ ዓለም በተፈጠረች በ5,534 ዓመት መጋቢት 27 ቀን በዕለተ ዓርብ ስቅለት 6 ሰዓት ላይ ምድር ተናወጠች፡፡ ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ፡፡ በዚህ የተደናገጡ የአቴና ነዋሪዎችና ፈላስፎች ወደ ዲዮናስዮስ ተሰብስበው የተፈጠረውን ነገር መርምረህ አስረዳን አሉት፡፡

ባለው ጥበብ ባሕሩን፣ የብሱን፣ ፀሐይ፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን ቢመረመራቸው በቀደመ ቦታቸው አገኛቸው፡፡ ግራ ቢገባው እንቅልፍ ራቀው፤ ከዚያም ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ መጻሕፍትን ሲያገላብጥ "አርስጣላባ" በሚባል ግዙፍ መጽሐፍ ውስጥ "እልመክኑን" የሚል ጽሑፍ አገኘ:: ወደ ውጪ ወጥቶ በሕዝቡና ጠቢባኑ ፊት ልብሱን ቀድዶ አለቀሰ:: እነርሱም ደንግጠው "ምነው መምሕራችን? ምን ሆንህ?" ቢሉት "የማይታየው አምላክ ቢወርድ በምቀኝነት ገደሉት የሚል ጽሑፍ አገኘሁ" አላቸው:: "እልመክኑን" ማለት "የማይታይ አምላክ" ማለት ነውና:: ከዚህ በሁዋላ ተማሪዎቹን ጠርቶ "እልመክኑን" የሚለውን ስም ከቤተ ጣዖቱ በር ላይ ለጥፉት አላቸው፡፡ ከ14 ዓመታት በኋላ ቅዱስ ዻውሎስ ወንጌልን እየሰበከ አቴና ደረሰ፡፡ ዘመኑም በ48 ዓ.ም ነበር፡፡ ወደ ከተማዋ ሲገባ በጣዖት ቤቱ በር ላይ የተለጠፈውን ጽሑፍ ተመለከተና ያስተምራቸው ያዘ፡፡ ትምሕርቱን የሰሙ ጠቢባኑና ሕዝቡ ሐዋርያውን ይዘው ወደ ዲዮናስዮስ ፊት አቀረቡት፡፡

አዲስ አምላክን ሲያስተምር አግኝተነዋል ሲሉትም ቅዱስ ዻውሎስ እኔ አዲስ አምላክን የምሰብክላችሁ አይደለሁም፤ ይልቁኑ ከቀድሞም የፈጠራችሁ ቀጥሎም የሞተላችሁ እናንተም “እልመክኑን ብላችሁ ሳታውቁት ታመልኩት የነበረውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” አላቸው፡፡ ዲዮናስዮስም ቅዱስ ዻውሎስን "ለዚህ ምን ምልክት አለህ?" ቢለው የዛሬ 14 ዓመት መጋቢት 27 ቀን በዕለተ ዓርብ 6 ሰዓት ላይ ታላላቅ ተአምራት ተደርጎ አይደለምን! እነዚህ ሁሉ የተደረጉት በስቅለቱ ጊዜ ነው" ሲል መለሰለት፡፡ ዲዮናስዮስም ፈጥኖ በክርስቶስ አመነ፤ የአካባቢው ጠቢባንና ሕዝቡም አምነው ከመሪያቸው ጋር ተጠመቁ፡፡ ቅዱስ ዻውሎስም ቅዱስ ዲዮናስዮስን አስተምሮ የአቴና የመጀመሪያው ዻዻስ አደረገው፡፡

ቅዱሱም ክርስቲያኖችን ያበዛ፣ መንጋውንም ያጸና ዘንድ ብዙ ተጋ፡፡ በተለይ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ታዋቂ ደራስያን አንዱ ሆነ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ በርካታ ድርሰቶችን ደረሰ፡፡ ዛሬም ድረስ ሃይማኖተ አበው ውስጥ የሚገኘው ድርሰቱ ጣዕሙ ልዩ ነው:: ቅዱሱ ለብዙ ዘመናት ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ በዚህች ቀን የአካባቢው አገረ ገዥ አንገቱን አስቆርጦት ሰማዕት ሆኗል፡፡ የሚገርመው ግን ሲገድሉት በቦታው ሰው ስላልነበረ ቅዱሱ ተነስቶ፤ ተቆርጣ የወደቀች ራሱን አነሳት፡፡ በጐኑ አቅፎም ደቀ መዛሙርቱ እስካሉበት ሒዶ በፊታቸው ዘንበል አለ፡፡ ምዕመናንም እያለቀሱና እየዘመሩ ከተሰየፉት አርድእቱ ኡሲፎስና ኡርያኖስ ጋር ቀብረውታል፡፡ የቅዱሳንን ተጋድሎ አብነት አድርገው ገዳማውያን ይጋደላሉ፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
27🥰3
የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

በአፋር ኪብላቲ ረሱ ዞን ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከምሽት 2:00 ጀምሮ አስፈሪ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከጥቅምት 1 ቀን ጀምሮ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነው ብለዋል።
በራህሌ እና በኮናባ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ቤቶችን፣ የውሃ ጉድጓዶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን እና መስጊዶችን አፍርሷል።
ከተያያዙት ምስሎች ውስጥ ሁለተኛው በቡሬ ቀበሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተራራው ሲናድ የሚታይ አቧራ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
15😱2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የበረራ አገልግሎት ዳግም ጀመረ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የሚያደርገውን በረራ ከጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳግም ማስጀመሩን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ከጥቅምት 5 ቀን  ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ገልጾ በቀጣይ ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግን በረራዎቹን በቀን ወደ ሁለት ጊዜ እንደሚያሳድግ ጠቁሟል።

በሱዳን ጦር ሰራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ሚያዚያ 2015 ወዲህ የሱዳን መንግሥት ዋና ከተማዋን ካርቱምን በመልቀቅ አገሪቱን ሲያስተዳድር የቆየው በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ፖርት ሱዳን ከሚገኝ ጊዜያዊ መቀመጫው እንደነበር ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ተከታታይ በረራዎችን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ከወራት በፊት በሀገሪቱ እንደገና ባገረሸው ግጭት ሳቢያ ወደ ፖርት ሱዳን ሲያደርግ የነበረውነ በረራ ለማቋረጥ ተገዶ ቆይቷል።

@sheger_press
@sheger_press
11👍1
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ መሥራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።

የምክር ቤት አባላቱ እንደገለፁት የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት መረጋገጥ ለኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሕይወት ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።

የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕዝብ አጀንዳ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ ሀገራት እንዲሁም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ዘንድ ድጋፍ ማግኘቱ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ጥያቄው የተመራበትና አሁንም እየሄደበት ያለው መንገድ የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ፤ ተገቢውን ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም ሊሠራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

#ጋዜጣፕላስ

@sheger_press
@sheger_press
8👎3👏2
የገንዘብ ሚኒስትሩ ለዓለም ባንክና ለአይኤምኤፍ ተጨማሪ የብድር ጥያቄ አቀረቡ‼️

የልዑካን ቡድናቸውን ይዘው በዓለም ባንክና በዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ (አይኤምኤፍ) ስብሰባ እየተሳተፉ የሚገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተጨማሪ የብድር ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ከጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ ስብሰባ የገንዘብ ሚኒስትሩ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ተክለወልድ አጥናፉና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድና ልዑካቸው ከዓለም ባንክ ምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ኒዲያሜ ዲኦፕ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ሚኒስትሩ በግብርና ምርታማነት፣ በኢነርጂ፣ በሰው ሀብት ልማት፣ በቀጣናዊ ትስስርና መሠረተ ልማት ከፍ ያለ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መጠየቃቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡

አቶ አህመድ የዓለም ባንክ ላደረገው ከፍተኛ ቴክኒካዊና የፋይናንስ ድጋፍ እንዳመሠገኑ፣ መንግሥት እያካሄዳቸው ያሉ ደሃ ተኮር ሪፎርሞችን በተመለከተ ማብራራታቸውንና ሪፎርሙን ለማስቀጠል የዓለም ባንክ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸውን አክሏል፡፡

የዓለም ባንክ የምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለኃይል ማስፋፊያ፣ ለአነሰተኛ አርሶ አደሮች ምርታማነት ፋይናንስና ትሰሰር ለመጨመር፣ ጥራት ያለው የሰው ኃይል ወደ ሥራ እንዲገባ፣ አነሰተኛ አምራቾችን ለመደገፍ ሥራዎች ይከናወናሉ ማለታቸው ተገልጿል፡፡ (Reporter)
13😱3😢3👎1
2025/10/25 18:18:20
Back to Top
HTML Embed Code: