Telegram Web Link
"የኢንዱስትሪ መንደር" ከተባለችው ኮምቦልቻ የወንዝ ውሃ በፋብሪካ ኬሚካል ወደ መርዝነት ተቀይሯል!

ኮምቦልቻ፣ ኢትዮጵያ— የ"ኢንዱስትሪ መንደር" ተብላ የምትሞካሸው ኮምቦልቻ ከተማ ውስጥ ካሉ ፋብሪካዎች የሚለቀቅ አደገኛ ኬሚካሎችን የያዘ ተረፈ ምርት፣ የወንዙን ውሃ ደም የመሰለ ቀለም እንዲይዝ በማድረግ የአካባቢውን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል።

የኮምቦልቻና የቃሉ አርሶአደሮች በኢንቨስትመንት ስም መሬታቸውን በዝቅተኛ ዋጋ ከተቀሙ በኋላ፣ የተረፋቸውንም እርሻ ከዚህ ከባድ የኬሚካል ፍሳሽ የሚመጣ መርዝ ተንከባክበው እንዳያለሙት ስጋት ላይ ወድቀዋል።

ይህ ደም የመሰለ ፈሳሽ ወንዝ የተረፈ ምርት የኮምቦልቻ እና የቃሉ አርሶአደሮች የሰብል ምርትንና የመሬቱን ለምነት በመግደል ላይ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎችና አርሶአደሮች ይህ መርዝ የአካባቢ ስነ-ምህዳር ላይ እያሳደረ ያለውን ከባድ ተፅዕኖ ገልጸዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ድምጹን ቢያሰማም፣ "የራሱን ምቾት የሚጠብቅ አመራር እንጂ ለሕዝብ ደህንነት ደንታ የሌለው ነው" በማለት በሕዝብ ደህንነት ጉዳይ ላይ የኃላፊነት ስሜት የጎደለው አመራር መኖሩን ይወተወታሉ። እስካሁን ለቅሬታቸው የሚሰማ ኃላፊ ማጣታቸው ነገሩን ይበልጥ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ጥሪ ለሚመለከተው አካል!
የኮምቦልቻ እና የአካባቢው ወንዞች በዚህ አሰቃቂ የፋብሪካ ኬሚካል ተረፈ ምርት መበከሉ የአርሶአደሩን ኑሮ ከመናድ ባሻገር፣ ለወደፊት የጤና ቀውስና የአካባቢ ጥፋት ሊዳርግ ይችላል።

ፌዴራልና ክልላዊ የመንግስት አካላት ለሕዝብ ደህንነትና ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

Via አሊ ወሎ

@sheger_press
@sheger_press
19🤔3👍1
የ 4 ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ፤ የ 2 ሚሊዮን ብር ሎተሪ አሸነፉ

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ዓለምፀሐይ በላቸው በ39ኛ ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛ ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር / ሁለት ሚሊየን ብር / ዕድለኛ በመሆን ቼካቸውን ተረከቡ ፡፡

ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ባለትዳርና የ4ልጆች እናት ሲሆኑ በደረሳቸውም ገንዘብ ወደንግድ ለመሰማራት እንዳሰቡ ተናግረዋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
👍233🥰2👏2
አረቄ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ሊዘጉ ነው‼️

ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም. (E.C.) : ቢንጎ እና አረቄ ቤቶች በአዲስ አበባ አይኖሩም ተባለ! አስተዳደሩ ቆራጥ ውሳኔ አስተላለፈ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ እና የአረቄ መሸጫ ቤቶችን በተመለከተ አስቸኳይ እና ቆራጥ ውሳኔ አሳለፈ።

ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድም የቢንጎ ማጫወቻም ሆነ የአረቄ መሸጫ ቤት መኖር የለበትም!

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት፦
"እነዚህ ቤቶች (የቢንጎ ማጫወቻ እና በየመንደሩ ያሉ አረቄ ቤቶች) የከተማው ወንጀል መፈልፈያ ቦታዎች ናቸው።"

መመሪያውም ቤቶቹ የወንጀል ምክንያት በመሆናቸው ምክንያት ከከተማው እንዲጠፉ ታስቦ ነው።

ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መመሪያ ተሰጥቶ እንደነበር ቢታወቅም፣ ቤቶቹ አሁንም በስራ ላይ መሆናቸው ታውቋል። አስተዳደሩ ግን አሁን ባጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባን ከእነዚህ ቤቶች ነፃ ያደርጋታል ብሏል።

ትዕዛዙን ላለማስፈፀም የሚከፈል ዋጋ፦
ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ትዕዛዙን ተፈጻሚ የማያደርጉ ኃላፊዎች ላይም ማስጠንቀቂያ "ይህንን ማስፈፀም ያልቻሉ ኃላፊዎችም በቦታቸው አይቀጥሉም!"

Via ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@sheger_press
@sheger_press
41👏9👎4🤯1
የ12 አመት የእንጀራ ልጁን ደጋግሞ የደፈረው ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ በከሚሴ ከተማ በመድፈር ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ገለፀ።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ እንድሪስ አሊ እንደገለፁት በቀን 07/01/2018 በዋለው ችሎት ተከሳሽ መኪን የሱፍ ሙህዬ የተባለ ግለሰብ የከሚሴ ከተማ የ04 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው እስከ ሚታወቅበት ቀን 28/01/2018 አ.ም ከቀኑ 9:00 ድረስ የግል ተበዳይ የእንጀራ ልጁ የሆነችውን ራህመት አሊ ጫኔ እድሜዋ 12 አመት የሆችውን በተደጋጋሚ በመድፈር ክብረ ንፅህናዋን በመውሰድና የአራት ወር ነብሰጡር እንድትሆን ማድረጉን ገልፀዋል።

በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ በከተማው ፓሊስ ምርመራ ተጣርቶ መዝገቡ የደረሰው የከሚሴ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት እድሜዋ ከ12 የሆናት ህፃን አስገድዶ መድፈር ወንጀል 1996 በወጣው በወንጀል መቅጫ ህግ መሰረት ለደዋ ጨፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ በቀን 07/01/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ላይ ተከሳሹ ወንጀለኛ ሁኖ በመገኘቱ ተከሳሽን ያርማል ሌሎቹን ያስተምራል በማለት የ 25 አመት ፅኑ እስራት እንዲፈረድበት መደረጉን የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ሀላፊ ገልፀዋል።

@sheger_press
@sheger_press
🤬1815😢3
ቅጣት‼️

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት ላይ ዳንስ ቤት የተገኙ ሴቶች የገንዘብ ቅጣት መቀጣታቸውን ተሰማ።

ከማህበረሰቡ ባህል ያፈነገጠ አለባበስ ለብሰው ዳንስ ቤት የተገኙ 13 ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በገንዘብ እንዲቀጡ መደረጉን የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ::

የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ኚካሃ አኳይ ለወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት ሴቶቹ ሰሞኑን በዲማ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ ከባህል ውጪ አለባበስ ለብሰው ከምሽቱ 4:ዐዐ ላይ ዳንስ ቤት በመገኘታቸው ጽ/ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ውሎው እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር በአጠቃላይ 65 ሺህ ብር እንዲቀጡ መደረጉን ተናግሯል ::

በመጨረሻም ጽህፈት ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የጀመረው የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

@sheger_press
@sheger_press
22👍8🤔4👏3
ለክልል አቃቢ ህጎች ከተላከው አዲሱ የደመወዝ ስኬል ውስጥ የአፋር፣የሲዳማ፣የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዓቃቤ ሕግ የደመወዝ ስኬልን ከላይ አያይዘነዋል።

@sheger_press
@sheger_press
👍54
💥🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿Everton visits Etihad

City has lost to the Toffees just once in the last 18 meetings, but now the teams are neck and neck in the table.

Bet on Premier League and catch every moment with Melbet!

⬇️
Promo - PRESSSH
Link - https://bit.ly/423Tlea
3
በወላይታ ዞን፣ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በአደጋ ምክንያት የደረሰ ጉዳት!

በወላይታ ዞን፣ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፣ በሌ አዋሳ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቁልቁለት መንገድ ላይ አደጋ መድረሱ ተዘግቧል።

ነዳጅ የጫነ አንድ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ሲጓዝ፣ ብሬክ (ፍሬን) ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ ምክንያት መንገድ ስቶ ወጥቷል።

ተሽከርካሪው በከፊል መኖሪያ ቤት ደርምሶ የወደቀ ሲሆን፣ በሰዎች ሕይወት ላይ ከባድ ጉዳት ሳይደርስ መቅረቱ ታውቋል።

ሆኖም በደረሰው አደጋ በሹፌሩ እና በአንዲት ትንሽ ህፃን ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

ለአሽከርካሪዎች የተላለፈ መልዕክት፦

ወደዚህ አካባቢ የምትጓዙ አሽከርካሪዎች!

መንገዱ ከባድ ቁልቁለት የሚጠብቅ በመሆኑ፣ ሲያሽከረክሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

@sheger_press
@sheger_press
12😢8🤔1🙏1
6
Sheger Press️️
Photo
የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት እየታሰበ ከቅዳሜ ምሽት አራት ሰዓት ጀምሮ ካህናት አባቶች በማሕሌተ ጽጌው እመቤታችን ትመሰገናለች፡፡

የዓለሙን ሁሉ ፈጣሪ ይዛ በበረሃው የደረሰባት መከራ የገጠማት ውሃ ጥምና ረሃብ ይዘከራል፡፡

ልጇን ይዛ የተሰደደችው ንግስተ ሰማያት ወምድር የደረሰባትን መከራ አብነት ሆኗቸው ነፍሳቸውን ለማዳን ስጋቸውን ለክርስቶስ ፍቅር በማስገዛት በረሃብና በውሃ ጥም የሚቸገሩትን ገዳማውያን ለማሰብ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ከቶ ከየት ይመጣል?

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያን ስጋዊና መንፈሳዊ ውጊያ በበረታበት አካባቢ በብዙ መከራ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

ይህን መከራቸውን ለማስታገስ፣ ውሃ ጥማቸውን ለመቁረጥ፣ ረሃባቸውንም ለማስታገስ የእመቤታችን መከራ በሚታሰብበት ዘመነ ጽጌ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከ 5፡00 ጀምሮ  በሜሊኒየም አዳራሽ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡ በአንድ መቶ ብር ብቻ ቲኬቱን በመግዛት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
29
2025/10/19 20:49:34
Back to Top
HTML Embed Code: