Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Audio
سورة الكهف🌺

بصوت الشيخ رعد محمد الكردي
https://www.tg-me.com/slmatawahi
እረዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 ያቺንም አሏህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ቁርኣን ሙሉ ለሙሉ የአምላካችን የአሏህ ንግግር ነው፥ በቁርኣን ላይ አሏህ "ሰውን እረዱ" ያለበት ቃል በቀጥታ ሆነ በተዋዋሪ አናገኝም። ከዚያ በተቃራኒው ባይብል ስለ ሰው መታረድ የሚናገር መጽሐፍ ነው፦
1 ነገሥት 18፥40 ኤልያስም፦ ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ፡ አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ "አሳረዳቸው"። וַיֹּאמֶר֩ אֵלִיָּ֨הוּ לָהֶ֜ם תִּפְשׂ֣וּ ׀ אֶת־נְבִיאֵ֣י הַבַּ֗עַל אִ֛ישׁ אַל־יִמָּלֵ֥ט מֵהֶ֖ם וַֽיִּתְפְּשׂ֑וּם וַיֹּורִדֵ֤ם אֵלִיָּ֙הוּ֙ אֶל־נַ֣חַל קִישֹׁ֔ון וַיִּשְׁחָטֵ֖ם שָֽׁם׃

"አሳረዳቸው" ለሚለው የገባው ቃል "ዪሻተም" יִּשְׁחָטֵ֖ם ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ሻሃት" שָׁחַט ነው፥ "ሻሃት" שָׁחַט ማለት "አረደ" ማለት ነው። ኤልያስ ነቢይ ሆኖ የበአል ነቢያትን 450 ሰዎች ማሳረዱ ከቄራ ባለቤት ልዩነቱን ትነግሩኝ? ሲያሳርድ በውስጠ ታዋቂነት "እረዱ" የሚል መርሕ አለ። እንቀጥል! የያዕቆብ ልጆች ገለዓዳውያን የአፍሬምን ሰው ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገሪያ አረዱት፦
መሳፍንት 12፥6 እነርሱ፦ አሁን ሺቦሌት፡ በል አሉት፤ እርሱም አጥርቶ መናገር አልቻለምና፦ ሲቦሌት፡ አለ፤ ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገሪያ "አረዱት"፥ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።

የቄራው ሥርዓት በዚህ አላበቃም። የሰማርያ ሽማግሌዎች የኢዩን ልጆች እና ሰባ ሰዎች አርደዋል፦
2ኛ ነገሥት 10፥7 ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው "አረዷቸው"፤ ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ። וַיְהִ֗י כְּבֹ֤א הַסֵּ֙פֶר֙ אֲלֵיהֶ֔ם וַיִּקְחוּ֙ אֶת־בְּנֵ֣י הַמֶּ֔לֶךְ וַֽיִּשְׁחֲט֖וּ שִׁבְעִ֣ים אִ֑ישׁ וַיָּשִׂ֤ימוּ אֶת־רָֽאשֵׁיהֶם֙ בַּדּוּדִ֔ים וַיִּשְׁלְח֥וּ אֵלָ֖יו יִזְרְעֶֽאלָה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "ገደሏቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዪሻቱ" יִּשְׁחֲט֖וּ ሲሆን "አረዱ" ማለት እንጂ "ገደሉ" ማለት አይደለም። ንጉሥ ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል ቦታ አረዳቸው አሳረዳቸው፦
2ኛ ነገሥት 10፥11 ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል "አረዳቸው"። וַיַּ֣ךְ יֵה֗וּא אֵ֣ת כָּל־הַנִּשְׁאָרִ֤ים לְבֵית־אַחְאָב֙ בְּיִזְרְעֶ֔אל וְכָל־גְּדֹלָ֖יו וּמְיֻדָּעָ֣יו וְכֹהֲנָ֑יו עַד־בִּלְתִּ֥י הִשְׁאִֽיר־לֹ֖ו שָׂרִֽיד׃
2ኛ ነገሥት 10፥14 እርሱም፦ በሕይወታቸው ያዙአቸው፡ አለ። ያዙአቸውም፥ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች "አረዷቸው"፤ ማንንም አላስቀረም። וַיֹּ֙אמֶר֙ תִּפְשׂ֣וּם חַיִּ֔ים וַֽיִּתְפְּשׂ֖וּם חַיִּ֑ים וַֽיִּשְׁחָט֞וּם אֶל־בֹּ֣ור בֵּֽית־עֵ֗קֶד אַרְבָּעִ֤ים וּשְׁנַ֙יִם֙ אִ֔ישׁ וְלֹֽא־הִשְׁאִ֥יר אִ֖ישׁ מֵהֶֽם׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "ገደሏቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዪሻቱም" יִּשְׁחָט֞וּם ሲሆን "አረዷቸው" ማለት እንጂ "ገደሏቸው" ማለት አይደለም። ዳዊት ነቢይ እና ንጉሥ ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድን አንገቱን ከማረድም አልፎ ቆርጦታል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥51 ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ "ራሱንም ቈረጠው"።

ባሻዬ "በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ "ሃይማኖቴ ተነካብኝ" ብሎ ሊያርድ ሰይፍ የመዘዘ ግለሰብ የለም" ላልክበት ዐላዋቂነት በቁና ከላይ ተቀምጦልካል። ቁርኣን ስለ መግደል ምን ይላል? ለሚለው ከዚህ በፊት የጻፍኩት ስላለ ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://www.tg-me.com/Wahidcom/2708

አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ትምህርት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት ▯●

- "ነገረ ኢየሱስ ወመቅደላዊት ማርያም"
- "አላህ የት ነው?"


◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ሳላህ
🅅🅂
◍ ወገኖቻችን
ቁርአን የልብ ብርሃን አስታውሱ
🌹እውነተኛ ደስታህ የማንንም ደስታ ሳትገድል
የማንንም ልብ ሳትጎዳ የማንንም ነውር ሳታጋልጥ
የማንንም ስጋ በሀሜት ሳትበላ
ቀንህን መጨረስ ነው!!

🌹. @slmatawahi
ላስቸግራችሁ @followers በገንዘብ አይደለም እንተባበረው በሃሳብ እና ድጋፍን በመስጠት
ብዙ አፕሊኬሽኖችን በመስራት ዩቱብ ቴሌ ግራም ላይ ትልቅ ውለታ የዋለልን ወንድማችን ነው ዶክተር Hussen Oumer አሁን ይህንን ውድድር እንዳሸንፍ እኛ እናግዘው
ሸር አድርጉለት ሁላችሁም ታግ ያደረጋችሁ ተባበሩት

የሞባይል አፕሊኬሽን አዘገጃጀት ስልጠና - ዶ/ር ሁሴን ኡመር ውድድሩን ለመመልከት
https://youtube.com/watch?v=cXpe0y3SDk4&si=GkXyPTeQYEEjht7n
NG 5 የሚል ፅሁፍ ወደ 800 በSMS ደጋግማችሁ በመላክ ነጋድራስ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ወደ ቀጣይ ዙር እንዳልፍ ድምፅ መስጠት ትችላላችሁ አመሰግናለሁ ።
ውጭ ያላችሁት ስለማይቻል ይህንን ፖስት ሼር በማድረግ አግዙኝ

በአንድ ሲም ደጋግማችሁ መላክ ይቻላል
በሳፋሪኮም አይቻልም
በፓኬጅ አይቻልም
ከውጭ ሐገር ሆናችሁ አይቻልም
ስላከበራችሁኝ ከልቤ አመሰግናለሁ ባሸንፍም ባላሸንፍም የህዝቡን ፍቅር አይቸበታለሁ ክበሩልኝ
ነቢዩ ኢብራሂም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥69 «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡ قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ

ኩሽ የኖሕ ልጅ ሲሆን ናምሩድን ወለደ፥ ናምሩድ በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። እንስሳት የሚያድን አዳኝ"hunter" ነበረ፦
ዘፍጥረት 10፥8 ኩሽም ናምሩድን ወለደ፥ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። וְכ֖וּשׁ יָלַ֣ד אֶת־נִמְרֹ֑ד ה֣וּא הֵחֵ֔ל לִֽהְיֹ֥ות גִּבֹּ֖ר בָּאָֽרֶץ׃
ዘፍጥረት 10፥9 እርሱም በያህዌህ ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፥ ስለዚህም፦ “በአምላክ ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ" ተባለ። הֽוּא־הָיָ֥ה גִבֹּֽר־צַ֖יִד לִפְנֵ֣י יְהוָ֑ה עַל־כֵּן֙ יֵֽאָמַ֔ר כְּנִמְרֹ֛ד גִּבֹּ֥ור צַ֖יִד לִפְנֵ֥י יְהוָֽה׃

"ኒምሩድ" נִמְרוֹד ማለት "አመጸኛ" ማለት ሲሆን "ኒምሩድ" የሚለው ስም በኃላ ላይ ልክ እንደ አጼ፣ ሄሮድስ፣ ፈርዖን፣ ቄሳር የባቢሎን ነገሥታት ስም ሆነ፥ ይህ ስም በዋነኝነት የባቢሎን የመጀመሪያው ንጉሥ ስም ነበረ፦
ዘፍጥረት 10፥10 የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር "ባብኤል፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው። וַתְּהִ֨י רֵאשִׁ֤ית מַמְלַכְתֹּו֙ בָּבֶ֔ל וְאֶ֖רֶךְ וְאַכַּ֣ד וְכַלְנֵ֑ה בְּאֶ֖רֶץ שִׁנְעָֽר׃

"ባብ-ኤል" בָּבֶ֔ל ማለት "የአምላክ በር" ማለት ነው፥ ቦታውን ወደ አምላክ የሚያስገባ በር እንደሆነ አስበው ወደ ሰማይ ወደ አምላክ የሚደርስ ግንብ ለመሥራት ሲያስቡ ያኔ በቋንቋ ተበታተኑ። ሙሐመድ ኢብኑ ጀሪር አጥ ጦበሪይ "ታሪኹ አር ረሡል ወል ሙልክ" تاريخ الرسل والملوك በተባለ መጽሐፋቸው ላይ "ኑምሩድ" نُمْرُود የተባለው የመጀመሪያ የባቢል ንጉሥ ግንብ እንደገነባ እና አሏህ ያንን እንዳፈረሰ እንዲሁ ቀደም ሲል የሰዎች ቋንቋ ሲሪያኪኛ(ዐረማይስጥ) እንደነበር እና በኃላ በመዘበራረቅ ሰባ ሁለት ቋንቋዎች እንደሆኑ ዘግቧል።
ይህ ባብኤል የተባለው አገር የናምሩድ አገር ይባላል፦
ሚክያስ 6፥6 የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ "የናምሩድንም አገር" በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ። וְרָע֞וּ אֶת־אֶ֤רֶץ אַשּׁוּר֙ בַּחֶ֔רֶב וְאֶת־אֶ֥רֶץ נִמְרֹ֖ד בִּפְתָחֶ֑יהָ

ነቢዩ ኢብራሂም በተነሳበት ዘመን ደግሞ ሌላ የባቤል ንጉሥ የነበረው አሏህ ንግሥናን የሰጠው ሲሆን ኢብራሂም ለእርሱ፦ "ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው" ሲል ንጉሡም "እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም" አለው፦
2፥258 ወደዚያ አሏህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን? ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም» አለ፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ

ማሞት እና ሕያው ማድረግ ጋይብ ነውና በሚታይ ነገር ኢብራሂም፦ "አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት" አለው፡፡ ያም የካደው ንጉሥ መልስ አጣ፦
2፥258 ኢብራሂም፡- «አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው መልስ አጣ፥ አሏህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

ለእነዚህን ጣዖታውያን ኢብራሂም "ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁን እና የማይጎዳችሁን ነገር ከአሏህ ሌላ ታመልካላችሁን? ሲላቸው እነርሱም ደግሞ ኢብራሂምን "አቃጥሉት" በማለት በእሳት ላይ ጣሉት፥ አሏህም፦ "እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አለ፦
21፥69 «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡ قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
ሚሽነሪዎች፦"አብርሃም በእሳት እንደተጣለ ባይብል ላይ የለም፥ ስለዚህ ቁርኣኑ ከየት አመጣው" ብለው ይተቻሉ።
፨ሲጀመር አንድ ታሪክ ባይብል ላይ አልተዘገበም ማለት ታሪኩ ነባራዊ ሳይሆን ምናባዊ ነው አያሰኝም።
፨ሲቀጥል አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው፥ ቁርኣን ላይ ታሪኩን የተረከልን እራሱ የዓለማቱ ጌታ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል።
፨ሢሰልስ በታልሙድ ውስጥ ኢብራሂም ጣዖት አላመልክም በማለቱ እሳት ውስጥ እንደተጣለ ይናገራል፦
ታልሙድ ፐሳቺም 118 A ቁጥር 20
ክፉው ናምሩድ አባታችን አብርሃምን ወደ እሳት እቶን ውስጥ በጣለ ጊዜ ገብርኤል በቅዱሱ እና በተባረከው ፊት እንዲህ አለ፡- የዓለማት ጌታ ሆይ! እኔ ወርጄ እቶን አቀዘቅዛለው፥ በዚህም ጻድቁን አብርሃምን ከእሳት እቶን አድናለሁ"። בְּשָׁעָה שֶׁהִפִּיל נִמְרוֹד הָרָשָׁע אֶת אַבְרָהָם אָבִינוּ לְתוֹךְ כִּבְשַׁן הָאֵשׁ אָמַר גַּבְרִיאֵל לִפְנֵי הַקָּדוֹשׁ בָּרוּךְ הוּא: רִבּוֹנוֹ שֶׁל עוֹלָם, אֵרֵד וַאֲצַנֵּן וְאַצִּיל אֶת הַצַּדִּיק מִכִּבְשַׁן הָאֵשׁ.

ይህንን ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ወይስ እንደተለመደው "ተኮርጆ ነው" የሚል ዲስኩራችሁ ትደሰኩሩ ይሆን?
፨ሲያረብብ በዕብራይስጥ "ዑር" אוּר ማለት "የእሳት እቶን" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "እሳት" እና "እቶን" ለሚል ቃል "ዑር" אוּר በሚል ይመጣል፦
ኢሳይያስ 31፥9 አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፥ ይላል እሳቱ በጽዮን እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ ያህዌህ። וְסַלְעֹו֙ מִמָּגֹ֣ור יַֽעֲבֹ֔ור וְחַתּ֥וּ מִנֵּ֖ס שָׂרָ֑יו נְאֻם־יְהוָ֗ה אֲשֶׁר־א֥וּר לֹו֙ בְּצִיֹּ֔ון וְתַנּ֥וּר לֹ֖ו בִּירוּשָׁלִָֽם׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ "እሳት" እና "እቶን" ለሚል የገባው ቃል "ዑር" אוּר እንደሆነ አስተውል! እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ፈጣሪ አብርሃምን ያወጣው ከከለዳውያን የእሳት እቶን ነው፦
ዘፍጥረት 15፥7 "ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን "ዑር" ያወጣሁህ ያህዌህ እኔ ነኝ" አለው። וַיֹּ֖אמֶר אֵלָ֑יו אֲנִ֣י יְהוָ֗ה אֲשֶׁ֤ר הֹוצֵאתִ֙יךָ֙ מֵא֣וּר כַּשְׂדִּ֔ים לָ֧תֶת לְךָ֛ אֶת־הָאָ֥רֶץ הַזֹּ֖את לְרִשְׁתָּֽהּ׃

"ዑር" אוּר ማለት "የእሳት እቶን" "የእሳት ነበልባል" ማለት ነው፥ "ዑር" אוּר በሚል ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው ቃል "ሜ" מֵ ደግሞ "ከ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው። ስለዚህ ኢብራሂም በእሳት ውስጥ ተጥሎ አሏህ ከእሳት እንዳዳነው መናገሩ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ እንዲህ ይገኛል፥ በማታውቁት ነገር መዘላበድ እንዲህ ዋጋ ያስከፍላችኃል። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰይጣን በክርስትና
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
- "ቁርዓን ከአላህ ለመውረዱ ማስረጃ"
- "ሰይጣን በክርስትና አስተምህሮ"
- "የገድላት ቅሌት"


◍ ወንድም ሳላህ
◍ ወንድም አቡ ሳላህ
◍ እኅት ዛህራ
#ሰላት ለረሳ ሰው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐

“ረስቶ ወይም ተኝቶ ሰላት ያልሰገደ ማካካሻው ባስታወሰ ግዜ መስገድ ነው።”

📚 ቡኻሪ (597) ሙስሊም (684) ዘግበውታል
አስካሪ መጠጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

"ኸምር" خَمْرየሚለው ቃል "ኸመረ" خَمَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ "የሚሸፍን" "የሚደብቅ" "የሚሰውር" ማለት ነው፥ እኅቶቻችን ከሚሰተሩበት ሒጃብ መካከል "ጉፍታ" እራሱ በቁርኣን "ኺማር" خِمَار ይባላል፦
24፥31 ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ። وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም አስካሪ መጠጥ”alcohol" ሁሉ “ኸምር” خَمْر ይባላል፦
2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ስለሆነ ለሰዎች ጥቅም አለው፥ አስካሪ መጠጥ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው፥ አስካሪ መጠጥ ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ዑመር በአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ ”ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የሚሰውር” ለሚለው የገባው ቃል “ኻመረ” خَامَرَ መሆኑ ልብ አድርግ! አስካሪ መጠጥ አእምሮን የሚያስት እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ”፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው” ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ ‏”‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው”። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ ‏”‏

“ሙሥኪር” مُسْكِر የሚለው ቃል “ሠኪረ” سَكِرَ
ማለትም "ሰከረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሚያሰክር" "የሚያነፍዝ" ማለት ነው፥ “ሠከር” سَكَر እራሱ “አስካሪ”intoxicant” ማለት ሲሆን “ሡክር” سُكْر ደግሞ “አስካሪነት”intoxication” ማለት ነው። ኸምር ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚሠራ ጠጅ ነው፦
16፥67 ከዘምባባዎች እና ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፡፡ ከእርሱ ጠጅን እና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ፡፡ وَمِن ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

አሏህ ከዘንባባ እና ከወይን ፍሬ ማብቀሉ በእርግጥ ታምር አለበት፥ ከዚህም ሰው በሠናይ መልካም ምግብ ማለትም ጭማቂ ሲሠራ በተቃራኒው እኩይ የሆነውን አስካሪ ጠጅን ይሠራል። "ዛሊከ" ذَٰلِكَ ማለትም "በዚህም" የተባለው ኢሥሙል ኢሻራህ ከበፊቱ ያለው "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የተባለው ዶሚሩል ሙንተሲል የሚያመለክት ነው፥ ይህም "እርሱ" የተባለው ፍራፍሬው ነው፦
16፥11 "በ"-"እርሱ" ለእናንተ አዝመራን፣ ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ። يُنبِتُ لَكُم بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ የተባለው የአዝመራን፣ የወይራንም፣ የዘምባባዎችንም፣ የወይኖችንም ፍራፍሬ ነው። ተጨማሪ አናቅጽ፦ 6፥99 13፥3 ይመልከቱ!
ፍራፍሬ ሲቆይ ስኳርነቱ ወደ አሲድ ይቀየርና ቆምጣጣነት"Fermentation" ሢሠራ ወይም ጌሾና ብቅል ሲቀላቀልበት ፓስቸራዜሽን”Pasteurization” እና ኒዩትራላይዜሽን”Neutralization” በመሆን ያሰክራል፥ ቢራ ፣ ቮድካ፣ ውስኪ የመሳሰሉት የዛ ውጤት ናቸው። አስካሪ መጠጥ አዕምሮን የሚያደንዝ እና ለጥል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለጣዖት አምልኮ የሚዳርግ፣ ከሶላት እና አሏህ ከማውሳት የሚያዘናጋ እኩይ ነገር ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥91 ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፤ አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን ተከልከሉ፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ

"ነቢዝ" نَّبِيذ ማለት ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚጠጣ ጭማቂ"juice" ነው፥ እርሱን መጠጣት ሐላል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 81
ዐብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህ አባቱ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ "በኮዳ በስተቀር ከነቢዝ የሚዘጋጅ ነገር እንዳትጠጡ ከልክያችሁ ነበር፥ ግን አሁን በሁሉም ሰፍነግ መጠጣት ትችላላችሁ። ነገር ግን አስካሪ መጠጥ እንዳትጠጡ። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُرَيْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَهَيْتُكُمْ عَنِ النَّبِيذِ إِلاَّ فِي سِقَاءٍ فَاشْرَبُوا فِي الأَسْقِيَةِ كُلِّهَا وَلاَ تَشْرَبُوا مُسْكِرًا ‏”‏

ይህ ጭማቂ ከሁለት ቀናት አሊያም ከሦስት ቀናት በኃላ ስለሚቆመጥጥ ሙሥኪር ይሆናል፥ ሙሥኪር መጠጣት ሐራም ነው። አይደለም ኸምር ጠጪው ይቅርና ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፦
ሡነንን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 6:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ ኸምርን ጠጪውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ረግሟቸዋል"። أَنَّهُمَا سَمِعَا ابْنَ عُمَرَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَعَنَ اللَّهُ الْخَمْرَ وَشَارِبَهَا وَسَاقِيَهَا وَبَائِعَهَا وَمُبْتَاعَهَا وَعَاصِرَهَا وَمُعْتَصِرَهَا وَحَامِلَهَا وَالْمَحْمُولَةَ إِلَيْهِ ‏”‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 1:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "የሚያሰክር ነገር ሁሉ ኸምር ነው፤ የሚያሰክር ነገር ሁሉ ሐራም ነው፡፡ በዱኒያህ ኸምርን የጠጣ እና በእሷም ላይ ዘውትሮ ሳይቶብት የሞተ ሰው በአኺራ የጀነቷን አይጠጣትም"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ شَرِبَ الْخَمْرَ فِي الدُّنْيَا، ثُمَّ لَمْ يَتُبْ مِنْهَا، حُرِمَهَا فِي الآخِرَةِ ‏”‌‏.‏

አሏህ ከአስካሪ መጠጥ እና በአስካሪ መጠጥ ከሚመጣ ጥፋት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Audio
سورة الكهف (كاملة) تلاوة حصرية ومميزة 🎧❤️ القارئ أحمد خضر

ውብ ቲላዋ ሱረቱል ካሕፍ"
https://www.tg-me.com/slmatawahi
ኡማህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥120 ኢብራሂም ለአሏህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

አልምጥ እና አልግጥ የሆኑ ሚሽነሪዎች፦ "ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ያለ አግባብ ሁለት ቦታ ገብቷል፥ አንደኛው እንስሳትን ሕዝብ ሲል ሁለተኛው ደግሞ ኢብራሂምን ሕዝብ ይላል" እያሉ ያለ ዕውቀት ሲቦተረፉ ግርም ይላል። ሐቅን አጥልቆ እና ታጥቆ ለተነሳ ሙሥሊም ይህ አንኮላ እና እንኩቶ ትችት ከመጤፉ ነው፥ ለዚህ ቅሪላ እና አለሌ ትችት መልስ እንስጥ!
"ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል "አመመ" أَمَّمَ ማለትም "ሐዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሕዝብ" ማለት ነው፥ የኡማህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኡመም" أُمَم ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው፦
6፥38 ከተንቀሳቃሽም በምድር የሚኼድ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم

"ዳባህ" دَابَّة ማለት "እንስሳ" ማለት ነው፥ እንስሳት የየራሳቸው ስብስብ ስላላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው "ሕዝብ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሐዘበ" ማለትም "ሰበሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስብስብ" ማለት ነው፥ እንስሳት እኮ "ስብስብ" አላቸው፦
ምሳሌ 30፥25 ገብረ ጕንዳን ኃይል የሌላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። הַ֭נְּמָלִים עַ֣ם לֹא־עָ֑ז וַיָּכִ֖ינוּ בַקַּ֣יִץ לַחְמָֽם׃
ምሳሌ 30፥25 ሽኮኮዎች ያልበረቱ "ሕዝቦች ናቸው። פַנִּים עַ֣ם לֹא־עָצ֑וּם וַיָּשִׂ֖ימוּ בַסֶּ֣לַע בֵּיתָֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አም" עַ֣ם ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን ገብረ ጕንዳን እና ሽኮኮዎች "ሕዝብ" መባላቸው ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ሁለተኛውን ትችት እስቲ እንመልከት፦
16፥120 ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ "ሕዝብ" ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ኢብራሂም "ሕዝብ" የተባለው በመውለድ እና በመክበድ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት፣ ቅም አያት፣ ቅማንት፣ ሽማት፣ ምንዥላት፣ እንጅላት፣ ፍናጅ እና ቅናጅ በመሆን መባዛቱን የሚያሳይ ነው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው አብርሃም "ሕዝብ" እንደሚሆን ይናገራል፦
ዘፍጥረት 17፥6 እጅግም አበዛሃለሁ፥ "ሕዝብ" አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። וְהִפְרֵתִ֤י אֹֽתְךָ֙ בִּמְאֹ֣ד מְאֹ֔ד וּנְתַתִּ֖יךָ לְגֹויִ֑ם וּמְלָכִ֖ים מִמְּךָ֥ יֵצֵֽאוּ׃

አብርሃም ሲወልድ እና ሲዋለድ በመብዛት ሕዝብ መሆኑን ካየን ዘንዳ ሕዝብ ከሆነ በኃላ አምላካችን አሏህ ቁርኣን ላይ "ኢብራሂም "ሕዝብ" ነበር" ቢለን እንዴት ያለ ዕውቀት ለትችት ትሮጣላችሁ? አሏህ የህዲኩም ወዩሠቢትና! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሴቶች ሩቅያ አድርጉልን ቅሩልን እያላቹሁ ወደ ቀልብ ዶክተር እንድሁም ወደ አጅነብይ ወንድ የምትሄዱ ሴቶች የሼኹን ምክር አድምጥጣቹሁ ተግብሩ


ሼኹ ሲመልሱ

ሴቶች ራሳቸዉን ሩቅያ ያድርጉ ይቅሩ

የሰዉ ልጅ ከቻለ ራሱ ላይ ሩቅያ መቅራት ማድረጉ የተሻለ የበለጠ የለም

አዎ
ምናልባትም በድግምት ወይም በጅን ተፈትኖ ይሆናል በራሱ ላይ ለመቅራት ይከለክለዉ ይሆናል

ሌላ ሰዉ ሊፈልግ ይችላል

ነገር ግን
በላጩ ሩቅያ አንድ ሰዉ ራሱ ሩቅያ ማድረጉ መቅራቱ ነዉ በላጩ

ሴት ልጅ ሩቅያ ከፈለገች ሴት ልጅ ትቅራባት

ሴት ልጅ ትቅራባት

ከቤቸሰቦቿ ቢሆን እንኳ

ወንድሞቼ ለሩቅያ የምስክር ወረቀት የለም

ሩቅያ በአሏህ ንግግግር ነዉ

ራቂ የተለየ የምስክር ወረቀት የተሰጠዉ የለም ከሌሎች የሚለይበት

ሩቅያ እርግጠኛ ሁኖ በአሏህ ንግግር ነዉ የሚደረገዉ

ሴት የምትቀራ ካልተገኘ ወንድ ቢቀራባት መስፈርቱ ከተማላ ችግር የለም

የመጀመሪያው ሸርጥ

1ኛ, የሚቀራባት ሴት እና የሚቀራባት ወንድ ለብቻቸዉ ላይገለሉ ነዉ( ለብቻቸዉ ላይሆኑ ነዉ

ይልቁንም ከቅርብ ዘመዷቿጋ መሆን የተሻለ በላጭ ነዉ ወይም ከሴቶችጋ


2ኛ, ሴቷ የተሸፈነች መሆን አለባት

ወደ ራቂ ከገባች ቡኋላ ፊቷን የምትገለጥ መሆን የለባትም

ፊቷን መገለጥ አያስፈልግም

እሷ ተሸፍና ይቅራባት

3ኛ ላይነካት ነዉ

በቀጥታም ይሁን በዋሲጧ


ለሩቅያ መንካት አያስፈልግም(አይጠበቅም


አንዳድ ራቂዎች ጉሮሮ ጡት ይይዛሉ አይፈቀድም

አንዳዶቹ ደግሞ ከራሷ ላይ ሚህፈዝ ካደረጉ ቡኋላ እላዩ ላይ እጁን ያስቀምጣል አይፈቀድም

እነዚህን ሳያደርግ ዝምብሎ ይቅራባት
👇👇👇
ሀገራችን በአለንጋ ወይም በሙስበሀ ልቀቅ ልቀቅ እያሉ የሚመቱ ራቂዎች አሉ
ይሄም ስህተት ነዉ
👇👇👇
https://www.tg-me.com/HuzeyfaAhmed
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዚህች አይነቷ ሴት መግቢያዋ ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም ረሱልﷺ | ኡስታዝ አህመድ አደም | hadis Amharic | Ustaz ahmed adem |
2024/05/29 11:15:17
Back to Top
HTML Embed Code: