Telegram Web Link
068 Al-Qalam
Abu Bakr Al-Shatri
🍂የጧት ግብዣ
🍃በጣም ደስ በሚለኝ ቃሪእ
🎙አቡ በክር አሽ-ሻጢሪይ
🍁 ሱረቱል አል ቀለም
ተጋበዙልኝ🌺
ሸረሪት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

ከሦስቱ ሡራዎች ከሡረቱል ፋቲሓህ፣ ከሡረቱል አንቢያእ እና ከሡረቱል ኢኽላስ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ የተሰየመው በውስጡ በያዘው ይዘት እና ጭብጥ ነው፥ የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ ”ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ “ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ “ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ “እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር”። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا

ስማቸው በውስጣቸው ከያዙ ሡራዎች አንዱ ሡረቱል አንከቡት ነው፥ ስለ አንከቡት ትንሽ እንበል። ጋጥመ-ብዙ"Arthropoda" የእንስሳ ክፍለ-ስፍን"phylum" ሲሆን ሸረሪት ክፍለ ምድቡ ከጋጥመ-ብዙ ነው። "አንከብ" عَنْكَب‎ ማለት "ወንድ ሸረሪት" ማለት ሲሆን "አንከባህ" عَنْكَبَة‎ ደግሞ "ሴት ሸረሪት" ማለት ነው፥ "ዐንከቡት" عَنكَبُوت የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም ፆታ ያገለግላል። ድርን በማድራት ቤት የምትሠራው ግን ሴቷ ሸረሪት ናት፦
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا

እዚህ አንቀጽ ላይ በድሯ ቤት የምትሠራዋ ሴት ሸረሪት እንደሆነች ለማመልከት የገባው ቃል በሙዘከር "ኢተኸዘ" اتَّخَذَ ሳይሆን በሙአነስ "ኢተኸዘት" اتَّخَذَتْ ነው፥ አምላካችን አሏህ ግን ሁሉም ዐዋቂ ስለሆነ በቁርኣኑ ነግሮናል። የሥነ-ሕይወት ጥናት እንደሚያትተው የሸረሪት ሐር"silk" ተፈጥሯዊ ፕሮቲን ሲሆን የምትፈትለው ሴቷ ሸረሪት መሆኗ የታወቀው በ1984 ድኅረ-ልደት ነው፥ የሸረሪት ሐር እየተጠላለፈ "ድር"web" ይሆንና እራሷን መከላከያ፣ መሸሸጊያ፣ መጠለያ ይሆናል። "ቤተ-ሰብእ" ማለት "የሰዎች ቤት" ማለት ነው፥ "ቤት" የሚለው ጣሪያ እና ግድግዳውን ብቻ ሳይሆን ስብስቡን ያመለክታል። እሩቅ ሳንሄድ፦ "እዚህ ቤት" ስንል ከውስጥ "አቤት" ወይም "እመት" የሚሉን "ቤት" የተባለው ፍካሬአዊ እንጂ እማሬአዊ እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፥ በቁርኣን "ቤተ-ሰብእ" የሚለው ቃል "አህለል በይት" أَهْلَ الْبَيْت ነው፦
33፥33 *"የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድ እና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ الرِّجْسَ أَهْلَ الْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا

"እመ-ቤት" ማለት "የቤት እናት" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "ቤት" የሚለው ጣራ እና ግድግዳ ማለት አይደለም፥ አንድ ሰው ትዳሩ ሲበተን "ቤቱ ፈረሰ" ይባል የለ እንዴ? እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ ሸረሪት ለመከላከል፣ ለመሸሸግ እና ለመጠለል የምታደራውን ድሯን "በይት" بَيْت ማለቱ የሚደንቅ ነው። ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው ሸረሪት በድሯ ያደራችው ቤት ነው፦
29፥41 ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ

የሸረሪት ድር ዝናብ ሆነ ሙቀት መቋቋም የማይችል ደካማ ቤት ነው፥ እነዚያ ከአሏህ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶችን አድርገው የያዙ ሰዎች ልክ እንደሸረሪት ቤት እጅግ በጣም ደካማ ናቸው። ይህንን ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፦
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

አምላካችን አሏህ ይህንን ቡሩክ መጽሐፍ ያወረደው የአእምሮዎች ባለቤቶች አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ ነው፦
38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ቡሩክ መጽሐፍ ነው፥ የአእምሮዎች ባለቤቶች አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

አሏህ የቁርኣንን አንቀጽ አስተንትነው ከሚገሰጹት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት ትንቢቶች
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
▯▩ ወይይት ▩▯

"ትንቢት ለኢየሱስ በብሉይ ኪዳን"

◍ ወንድም ሳላህ
🅥🅢
◍ ወገናችን ጌርሣም
تلاوة بديعة لـ سورة الذاريات
للقارئ: عبدالإله العجيري
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብዙ ሚስት በባይብል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

ባይብል ላይ "አንድ ብቻ አግቡ" የሚል መመሪያ የለም፥ ከዚያም ባሻገር ከአንድ በላይ ማግባት የተከለከለበት አንድ ጥቅስ የለም፥ ከዚያ ይልቅ ከአንድ በላይ ያገቡ የአምላክ ባሮች ብዙ ሰዎች በቁና ናቸው። ለናሙና ያክል፦
1. ያዕቆብ
ዘፍጥረት 31፥17 ያዕቆብም ተነሣ፥ ልጆቹንና “ሚስቶቹንም” በግመሎች ላይ አስቀመጠ።

2. ጌዴዎን
መሣፍንት 8፥30 ለጌዴዎንም “ብዙ ሚስቶች” ነበሩትና ከወገቡ የወጡ ሰባ ልጆች ነበሩት።

3. ሕልቃና
1ኛ ሳሙኤል 1፥2 ሕልቃና ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ።

4. ዳዊት
1ኛ ሳሙኤል 25፥43 ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፤ "ሁለቱም ሚስቶች" ሆኑለት።
1ኛ ዜና መዋዕል 14፥3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም “ሚስቶችን” ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ።

5. ሰሎሞን
1ኛ ነገሥት 11፥3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ "ሰባት መቶ ሚስቶች" ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት።

6. አሽሑር
1ኛ ዜና መዋዕል 4፥5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ "ሁለት ሚስቶች" ነበሩት።

"አይ ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ብዙ አገቡ እንጂ ፈጣሪ ብዙ እንዲያገቡ አልፈቀደላቸውም" ከተባለ ፈጣሪ አለመከልከሉ በራሱ መፍቀዱን ያሳያል። ሲቀጥል አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ካሉት እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የተናገረው ፈቅዶ ነው፦
ዘዳግም 21፥15 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ”ሁለት ሚስቶች” ቢኖሩት፥

ፈጣሪ ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት ምን ዓይነት እንክብካቤ ማድረግ እንዳለበት ሕግ ያወጣ ነበርን? ፈጣሪ ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ ለዳዊት ለዛውን የሰውን ሚስቶችን ይሰጠው ነበርን? ፈጣሪ የዳዊት ጌታ ተብሌ የተጠቀሰውን የሳኦን ሚስቶች ሰቶት ነበር፥ ከዚያ የበለጠም ካስፈለገ እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶለታል፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥8 "የጌታህንም "ሚስቶች" በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።

ፈጣሪ ለዳዊት የሳኦን ሚስቶች ካልበቃው ሊጨምርለት እንደሚችል መናገሩ በራሱ ከአንድ በላይ ማግባት ሐላል መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
የአዲስ ኪዳን ነብይ ኢየሱስ ነው፥ ኢየሱስ፦ "ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው" አላለም። እርሱ በብሉይ የነበረውን ሕግ አልሻረም።
ሌላው እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ነው፥ ሲጀመር ጳውሎስ ነብይ አይደለም። ሲቀጥል የሚናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ አዞት አይደለም፥ ንግግሩ የራሱ እንጂ የጌታ አይደለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥12 ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም።
2ኛ ቆሮ 11፥17 እንደዚህ ታምኜ ስመካ “የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም”።

ሢሰልስ ጳውሎስ፦ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ወይም ለእያንዳንዲቱ ባል ይኑራት" አለ እንጂ ለእያንዳንዱ ለራሱ አንዲት ሚስት ትኑረው አሊያም ለእያንዳንዲቱ ለራሷ አንድ ባል ይኑራት አላለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።

ለእያንዳንድህ እና ለእያንዳንሽ ብር እሰጣችኃለው ማለት የብሩ መጠን ስላልተገለጸ አንድ ብር ብቻ ተብሎ እንደማይተረጎም ሁሉ ባል እና ሚስት መባሉ የቁጥሩን መጠን በፍጹም አያሳይም፦
መዝሙር 62፥12 አንተ "ለእያንዳንዱ" እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለህና።
ሮሜ 2፥6 እርሱ "ለእያንዳንዱ" እንደ ሥራው ያስረክበዋል።

"እያንዳንድ"every" የሚለውን ቃል "አንድ"one" ብሎ መረዳት የተንሸዋረረ መረዳት ነው። "ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው" ያሉት ምዕራባውያን እንጂ ባይብል አይደለም። ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክሉም ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ የአንድ ሰው መብቱ እና ነፃነቱ ነው የሚል መርሕ አላቸው፥ ምዕራባውያን በ 17ኛው ክፍለ-ዘመን ሰው እንዲዋለድ እና እንዲባዛ ስላልፈለጉ እንጂ የመጡበትን ዳራ የክርስትናን መሠረት አድርገው አይደለም። ለዛ ነው ግብረ-ሰዶም እንዲስፋፋ የተፈለገው፥ ይህንን እንደ ሥልጣኔ የምዕራቧ ቤተክርስቲያን ግብረ-ሰዶም ታጋባለች። ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ዝሙት ሲፈቅዱ ኢሥላም ደግሞ ከአንድ በላይ በሐላል ኒካሕ ማድረግ ይፈቅዳል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
"ቅሌተ - ገድላት ወድርሳናት"

◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ሳላህ
◍ ወንድም ዊስፐር
◍ ወንድም አቡ ሳላህ
عبدالعزيز_التركي
ቁርአን የልብ ብርሀን ነዉ !
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Surah Kahf By Shaykh Abdullah Matrood سورة الكهف عبد الله مطرود
የነቢያችን"ﷺ" ሐያእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

68፥5 *"አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ"*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ

"ሐያእ" حَيَاء ማለት "ጨዋነት" "እፍረት" "ዓይነ-አፋርነት" ማለት ነው፤ ሐያእ የኢማን አንዱ ቅርንጫፍ ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 59
አቢ ሁራይራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ኢማን ከሰባ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ شُعْبَةً وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ዓይነ-አፋ ነበሩ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 20
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአንሷር ሴት ለነብዩ"ﷺ" "ከሐይድ መጨረስ በኃላ እንዴት ነው የምንተጣጠበው? ብላ ጠየቀች፤ እርሳቸውም፦ "ሽቶዋማ ቁራጭ ጨርቅ ከመስክ ጋር ውሰጂና ሦስት ጊዜ ሃፍረተ-ስጋን መታጠብ ነው" አሏት። ከዚያም ነቢዩ"ﷺ" አፍረው ፊታቸውን መለሱ፤ ስለዚህ እኔ ወደ እኔ አመጣኃትና ነብዩ"ﷺ" ምን እንዳሉ አስረዳኃት"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ امْرَأَةً، مِنَ الأَنْصَارِ قَالَتْ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَيْفَ أَغْتَسِلُ مِنَ الْمَحِيضِ قَالَ ‏"‏ خُذِي فِرْصَةً مُمَسَّكَةً، فَتَوَضَّئِي ثَلاَثًا ‏"‌‏.‏ ثُمَّ إِنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم اسْتَحْيَا فَأَعْرَضَ بِوَجْهِهِ أَوْ قَالَ ‏"‏ تَوَضَّئِي بِهَا ‏"‏ فَأَخَذْتُهَا فَجَذَبْتُهَا فَأَخْبَرْتُهَا بِمَا يُرِيدُ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم‏.‏

ነቢያችን"ﷺ" ይህ ታላቅ ሥነ-ምግባር ሐያእ ያላቸው ነቢይ እና በሐያአቸውም ተከታዮቻቸው መልካም መከተል አላቸው፦
68፥5 *"አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ"*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
33፥21 ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ *በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

”ጠባይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ኹሉቅ” خُلُق ሲሆን “አኽላቅ” أخلاق ማለት ደግሞ ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት ነው። ብልግና የሚመጣው ከኩፍር አሊያም ከኢማን መቀነስ ነው። ይህንን ነጥብ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ነቢያችንን"ﷺ" ባለጌ ለማስባል የሚጠቀስ ሐዲስ አለ፤ እዚህ ሐዲስ ላይ ነቢያችን"ﷺ" "የእናትህን ሐፍረተ-ስጋ ላስ" ወይም "የአባትህን ሐፍረተ-ስጋ ጥባ" ብለዋል ተብሎ እልም ያለ ቅጥፈት ሲቀጠፍ እናያለን፤ ለቃላቱ ይቅርታ እጠይቃለው፤ ግን መልስ መሰጠት አለበት፤ እነርሱ እንደውም ለስብእና በማይመጥን መልኩ በብልግና ቃላት ነበር ያስቀመጡት፤ ለማንኛውም ሐዲሱን እስቲ እንመልከት፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 12
ዑተያህ ኢብኑ ደምራህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው ከአባቴ ጋር ሌላው ሰው በዘመነ-ጃህሊያህ ሰዎች እርስ በእርሳቸው በሚወቃቀሱበት ወቀሰው፤ አባቴም አስቆጨው እና በኩኒያ አልጠራውም፤ ባልደረቦቹም አባቴን ሲመለከቱት፤ እርሱም፦ "ይህንን አልተቀበላችሁም መሰለኝ፤ በዚህ እኔ አክብሮት የለኝም። ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ማንም ሰው ሰዎችን በዘመነ-ጃህሊያህ ሰዎች እርስ በእርሳቸው በሚወቃቀሱበት ከወቀሰ አስቆጩት፤ በኩኒያ አትጥሩት"*። عَنْ عُتَيِّ بْنِ ضَمْرَةَ قَالَ‏:‏ رَأَيْتُ عِنْدَ أُبَيٍّ رَجُلاً تَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ، فَأَعَضَّهُ أُبَيٌّ وَلَمْ يُكْنِهِ، فَنَظَرَ إِلَيْهِ أَصْحَابُهُ، قَالَ‏:‏ كَأَنَّكُمْ أَنْكَرْتُمُوهُ‏؟‏ فَقَالَ‏:‏ إِنِّي لاَ أَهَابُ فِي هَذَا أَحَدًا أَبَدًا، إِنِّي سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ‏:‏ مَنْ تَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ فَأَعِضُّوهُ وَلا تَكْنُوهُ‏.‏

"ኩኒያህ" كنية ማለት በበኩር ልጅ አባት ወይም እናት መጠራት ነው፤ ለምሳሌ ሰሚራህ ከማለት ይልቅ በማዕረግ "ኡሙ ኢኽላስ" ወይም ወሒድ ከማለት ይልቅ በማዕረግ "አቡ ኢኽላስ" በማለት መጥራት ነው፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 26
አቢ ሁራይራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ስሜን(ሙሐመድ) ተጠቀሙ፤ ግን የኩንያህ ስሜን አትጠቀሙ፤ እኔ አቡ ቃሢም ነኝ"*። سَمِعْتُ أَبَا هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ تَسَمُّوا بِاسْمِي، وَلاَ تُكَنُّوا بِكُنْيَتِي، فَإِنِّي أَنَا أَبُو الْقَاسِم

ነቢያችን"ﷺ" "ቃሢም" የሚባል ልጅ የበኩር ልጅ ነበራቸው፤ በእርሱ "አቡ ቃሢም" ይባላሉ።
እንግዲህ ዛሬ በማህበራዊ ሚድያ ልክ በዘመነ-ጃህሊያህ ሰዎች እርስ በእርሳቸው በሚወቃቀሱበት በዘረኝነት ወቀሳ የሚወቃቀሰውን ሰው ነው "በኩንያ ስም አትጥሩት" ያሉት እንጂ እንኳን "ላስ" "ጥባ" ይቅርና ስለ አባት ሆነ እናት ሐፍረተ-ስጋ ሽታው የለውም። "ኩንየቲይ" كُنْيَتِي እና "ተክኑ" تَكْنُو የግስ መደብ ሲሆን የስም መደቡ "ኩኒያህ" كنية ነው። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንጂ እውነት አይደለም። በዋትሳፕ፣ በቴሌ ግራም እና በፌስ ቡክ የሚራገበው ቅጥፈት በእውነት ፊት መቆም አይችልም፦
17፥18 በልም፦ *"እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና"*፡፡ وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا
34፥49 *«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም ተወገደ»* በላቸው፡፡ قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ
21፥18 *በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው*፡፡ ለእናንተም ከዚያ ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፡፡ بَلْ نَقْذِفُ بِالْحَقِّ عَلَى الْبَاطِلِ فَيَدْمَغُهُ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌ ۚ وَلَكُمُ الْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢልቲፋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት በዓረፍተ ነገር በማዋቀር ረገድ “ነሕው” نَحْو ጉልኅ ሚና ሲኖረው “በላጋህ” بَلَاغَة ደግሞ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት የዓረፍተ ነገሩን መልእክት በመግለጽ ጉልኅ ሚና አለው፥ “በላጋህ” بَلَاغَة ማለት “የንግግር ስልት”rhetoric” ማለት ነው። ቅዱስ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፥ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው አሏህ ዘንድ የተወረደ ነው፦
11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

በበላጋህ ደርሥ ውስጥ ኢልቲፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። "ኢልቲፋት" اِلتِفَت የሚለው ቃል "ለፈተ" لَفَتَ ማለትም "ዞረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መዞር" ማለት ነው፥ በቁርኣን ውስጥ ያሉት ሰዋሰዋዊ ዙረት"grammatical shift" በጥቅሉ "ኢልቲፋት" اِلتِفَت ይባላሉ። አምላካችን አሏህ ሰዋሰዋዊ ዙረት የሚጠቀመው የቁርኣንን መልእክት ትኩረት እንድንሰጥ እና በቃላቱ እንድናሰላስል ነው፥ ለምሳሌ በሙተከለም ደረጃ ከሙፍረድ አነጋገር ወደ ተዐዚም አነጋገር ይዞራል፦
70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ

"እምላለው" በሚል ነጠላ ንግግር ጀምሮ "እኛ" በሚል የግነት እኛነት ይዞራል፥ በተመሳሳይ "አርሠልና" أَرْسَلْنَا በሚል ተዐዚም አነጋገር ጀምሮ "አና" أَنَا በሚል ሙፍረድ አነጋገር ይዞራል፦
21፥25 ከአንተ በፊትም፦ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

በተጨማሪም በሦስተኛ መደብ "አርሠለ" أَرْسَلَ ብሎ ተናግሮ በሦስተኛ መደብ የሚናገርለት ማንነት እራሱ እንደሆነ ለማሳየት በመጀመርያ መደብ "ሡቅና" سُقْنَا በማለት ያዞረዋል፦
35፥9 አላህም ያ ነፋሶችን የላከ ነው፥ ደመናዎችንም ትቀሰቅሳለች፤ ወደ ሙት አገርም እንነዳዋለን፡፡ وَاللَّهُ الَّذِي أَرْسَلَ الرِّيَاحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَسُقْنَاهُ إِلَىٰ بَلَدٍ مَّيِّتٍ

እንዲሁ በመጀመሪያ መደብ "ቁልና" قُلْنَا ብሎ ተናግሮ በመጀመሪያ መደብ የሚናገርለት ማንነት እራሱ እንደሆነ ለማሳየት በሦስተኛ መደብ "አሏህ" اللَّهُ በማለት ያዞረዋል፦
2፥73 «በድኑን በከፊሏም ምቱት» አልን፥ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡ فَقُلْنَا اضْرِبُوهُ بِبَعْضِهَا ۚ كَذَٰلِكَ يُحْيِي اللَّهُ الْمَوْتَىٰ وَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" "በል" በሚል ትእዛዛዊ ቃል ሲልካቸው፦ "እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ" በሚል በመጀመሪያ መደብ እንዲናገሩ በተናገረበት አንቀጽ ላይ "የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ" በማለት በሦስተኛ መደብ ያዞረዋል፦
7፥158 በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ እና በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡» قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

እንደዚህ የማዞር ሰዋስው በባይብል ውስጥም በጥቂቱ አለ፥ ለምሳሌ ያህዌህ በመጀመሪያ መደብ፦ "ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ! ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና" ብሎ ይናገራል፦
ዘጸአት 20፥2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ።
ዘጸአት 20፥7 የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ! ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።

ያዕቆብ በመጀመሪያ መደብ፦ "እንድነግራችሁ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ" ብሎ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 49፥1 ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ "በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ።
ዘፍጥረት 49፥2 እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ።

ኢየሱስ በመጀመሪያ መደብ፦ "በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ" ካለ በኃላ እራሱን በሦስተኛ መደብ፦ "የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል" ብሎ ይናገራል፦
ሉቃስ 12፥8 እላችሁማለሁ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል።

ትልም እና ሕልም ለይተው የማያውቁ ሚሽነሪዎች ቁርኣንን የጦስ ዶሮ ለማድረግ ከመቸኮል መጽሐፋቸውን በቅጡ ቢያነቡ መልካም ነው፥ እንዲህ ሲነጻጸር "የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ" ማለታቸው አይቀሬ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቃልም ስጋ ሆነ
husu negn ሁሱ ነኝ
◁▮ወይይት▮▷

"ቃልም ሥጋ ሆነ?"

◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
🅅🅂
◍ ወገናችን መሰሞ
Ismail Annuri
ሌላን አትገዙ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፥ "በ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" የሚለውን ሐረግ "ለ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" በሚል እያንሸዋረሩ ይረዳሉ ያስረዳሉ። ነገር ግን ጳውሎስ ያስቀመጠው በዚህ መልኩ አይደለም፥ እስቲ ከኢሳይያስ ኃይለ-ቃል እንጀምር! ፈጣሪ፦ "ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል" እያለ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል።

"ለእኔ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ለ" እና "በ" ሁለት የተለያዩ መስተዋድዶች ናቸው፦
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ።

"በ" የሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ ያለ መስተዋድድ በኢየሱስ ስም ለአብ መንበርከክን ያሳያል እንጂ ለኢየሱስ መንበርከክን አያሳይም። ለምሳሌ፦
ኤፌሶን 5፥20 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።

አምላክና አባት የተባለው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ይመሰገናል፥ አሁንም ኢየሱስ "በ" በሚል መስተዋድድ አስመላኪ እንጂ "ለ" በሚል መስተዋድድ ተመላኪ አይደለም፦
ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን "በ"-እርሱ እያመሰገናችሁ።

የሚመሰገነው አብ በማን ነው? ስንል "በ"-ኢየሱስ ነው። "በ" የሚለው መስተዋድድ አስምሩበት! እግዚአብሔር አብ "በ"-ኢየሱስ ይመሰገናል፦
ሮሜ 1፥8 አምላኬን "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።

ጳውሎስ አምላኩን እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመሰግናል። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የምስጋናን መሥዋዕት የሚቀርበው "ለ"እግዚአብሔር "በ"ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል፦
ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር "ለ"-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ "በ"-እርሱ እናቅርብለት።

"በ" አስመላኪ ሲሆን "ለ" ደግሞ ተመላኪ ነው። ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር ክብር የሚሰጠው "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፦
ሮሜ 7፥25 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን "ለ"-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን።

"በ" የሚለውን "ለ" ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ "በ"-ጽዮን" የሚለውን "ለ"-ጽዮን" ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ "በ"-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ።
ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም።

ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው። እናንተም እንደ ኢየሱስ አሏህን እንጂ ሌላን አትገዙ፦
11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሳማ ሥጋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ

"ኺንዚር" خِنزِير ማለት "አሳማ" ማለት ሲሆን የአሳማ አስተኔ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ጉንደ እንስሳ "እሪያ" እና "ከርከሮ" ናቸው፥ አሳማ ሴረም ፕሮቲኖችን ስለያዘ ሥጋው በሰውነት ውስጥ የአለርጂን ሂደት የሚያነቃቁ አልቡሚን እና ኢሚውኖ ግሎቡሊን አላቸው። በዚህም ግልጽ ምክንያት አካላችንን በጣም ብዙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ይይዛል፥ በአሳማ የጡንቻ ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ሰው የአሳማ ሥጋ ሲበላ ወደ ልቡ ጡንቻ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ይራቡና በዚህም ለሕይወቱ አስጊ ሁኔታን ያስከትላል። አምላካችን አሏህም ሰውን የሚጎዳው ይህንን የአሳማ ሥጋ መብላት ክልክሏል፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋን እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ
6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደምን፣ ወይም የአሳማ ሥጋን እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ

"ሐርረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውጪ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የአሳማ ሥጋ መብላትን ሐላል አርገዋል፥ ቅሉ ግን በባይብልም ቢሆን የአሳማ ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
ዘሌዋውያን 11፥7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ዘዳግም 14፥8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፥ ሥጋውን አትብሉ! በድኑንም አትንኩ።

"ሥጋውን አትብሉ" የሚለው ክልከላ ይሰመርበት! የእሪያን ሥጋ የሚበሉ ግን በጀሃነም በአንድነት ይጠፋሉ፦
ኢሳይያስ 66፥17 "የእሪያን ሥጋ፣ አስጸያፊ ነገርን፣ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ" ይላል ያህዌህ።

የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አናቅጽ ስንሰጣቸው፦ "የእሪያን ሥጋ በአዲስ ኪዳን ተፈቅዷል" ይላሉ፥ ነገር ግን መፈቀዱን የሚያሳይ አንድም ጥቅስ አያመጡም፦
ማቴዎስ 15፥11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው" አላቸው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም"።

እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ አንጻራዊ ንግግር እንጂ ወደ አፍ የሚገባ የሚያረክሱ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ ሐራም ናቸው፦
1 ቆሮ 10፥28 ማንም ግን፦ "ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው" ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ"።
ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
የሐዋርያት ሥራ 15፥20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰት፣ ከዝሙት ከታነቀም፣ ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
የሐዋርያት ሥራ 21፥25 አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል።

ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ አያካትትምን? ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ የሚጣል የለምን? አይ፦ "ኢየሱስ አያረክስም ያለው እጅ ሳይታጠቡ መብላትን እንጂ እርኩስ ነው የተባሉትን ምግብ አይደለም፥ ጳውሎስ የሚጣል የለም ያለው መልካም ምግብን ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ የአሳማ ሥጋ የተፈቀደበት አንድም ጥቅስ መቼም ልታመጡ አትችሉም። የማታውቁትን ነገር መናገር ዳፋው እና ጦሱ ለራስ ነው፥ ስለዚህ ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ የአሳማ ሥጋ ሐራም መሆኑን ብትቀበሉ ይሻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግድያ በባይብል
husu negn ሁሱ ነኝ
"ግድያ በባይብል"

◁ አቅራቢ

◍ ወንድም ሳላህ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
◆▮ነቢያት በባይብል▮◆

"ዳዊት (ዳውድ) ጨፋሪ ነበርን?"

◍እኅት ዘሐራ ሙስጥፋ
Forwarded from 💞فاطمة إمام 💞 Tqwa Habesha
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📣       📢      📣       📢       📣       📢

አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ ሙስሊሞች ሆይ!

እነሆ የአል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ "አል ሙኒር በገጠር" ለተሰኘው ፕሮጀክት አለም-አቀፍ  የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በ MAY 18/2024 በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት (ከኢሻ ሰላት በኋላ) እንደሚከናወን እያበሰርን ለፕሮግራሙ መሳካት በያላችሁበት ዱዐ እንድታደርጉና ከዚህ በታች የምንለጥፋቸዉን ማስታወቂያዎች እና በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶች ለዘመድ ወዳጆቻችሁ ታጋሩ ዘንድ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እንጠይቃለን።

የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ( Facebook, Telegram, WhatsApp, ወዘተ) በመጠቀም በርካታ እህትና ወንድሞች በዚህ ኸይር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ሰበብ እንሁን።

ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን!

አል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ።

ዋትስ አፕ ግሩፕ 👇👇👇

https://chat.whatsapp.com/BeWTXzCakK8C7A1BKaQqAr

ቴሌግራም ሊንክ 👇👇👇

https://www.tg-me.com/almuniracademy1


የዞም ሊንክ 👇👇👇

Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/6138373158?pwd=bFo5ZVFrcUpWbFV5YVNZMDlwZ2piQT09

ሜይ 18 እንገናኝ ሼር ሼር ሼር አድርጉ ባረከላሁ ፊኩም አዳል ለልኸይር ከፋኢሊሂ ነው
2024/05/15 03:03:17
Back to Top
HTML Embed Code: