Telegram Web Link
ይመሰክራሉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ

አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን እንዲመሰክሩ የሚያደርጋቸው ፍጡራን በዱንያህ ውስጥ መናገር የማይችሉ ፍጥረታትን ነው፥ ለምሳሌ የሰው ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ አሁን ላይ የማይናገር ሲሆን የትንሳኤ ቀን ግን አሏህ እንዲናገሩ በማድረግ ይመሰክራሉ፦
24፥24 በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡ يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
41፥20 በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸው እና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡ حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ

በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው፥ ከሓዲ መሆኑን በራሱ ላይ በራሱ ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ ይመሰክራል፦
75፥14 በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው። بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ
6፥130 "በራሳቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ"፡፡ وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِينَ
7፥37 "እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ"፡፡ وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ

በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 2775
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና በሦስት ሰዎች ላይ ተወክያለው፥ እነርሱም፦ በእያንዳንዱ አረመኔ አንባገነን ላይ፣ ከአሏህ ሌላ አምላክን የሚጣራ ሁሉ እና ቀራፆች ናቸው" ብሎ የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَخْرُجُ عُنُقٌ مِنَ النَّارِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ تُبْصِرَانِ وَأُذُنَانِ تَسْمَعَانِ وَلِسَانٌ يَنْطِقُ يَقُولُ إِنِّي وُكِّلْتُ بِثَلاَثَةٍ بِكُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ وَبِكُلِّ مَنْ دَعَا مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ وَبِالْمُصَوِّرِينَ ‏"‏ ‏

“ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት “ሓጅ” حَاجّ ሲባል የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ “ሓጃህ” حَاجَّة‎ ትባላለች፥ የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሑጇጅ” حُجَّاج‎ ይባላሉ። እሳት ለቅጣት የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት እንደሚኖረው ሁሉ በሐጅ ሥርዓት ላይ ሐጀሩል አሥወድ በነኩት ሑጇጅ ላይ መልካም ምስክር ይመሰክራል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 155
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስለ ሐጀሩል አሥወድ እንዲህ አሉ፦ "ወሏሂ! አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት ጋር ያስነሳዋል"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فِي الْحَجَرِ ‏"‏ وَاللَّهِ لَيَبْعَثَنَّهُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ يُبْصِرُ بِهِمَا وَلِسَانٌ يَنْطِقُ بِهِ يَشْهَدُ عَلَى مَنِ اسْتَلَمَهُ بِحَقٍّ ‏"‏ ‏

አንድ የማይናገርን ግዑዝ ነገር አሏህ እንዲናገር ማድረግ ምንም አይሳነውም፥ ምክንያቱም አሏህ ከግዑዝ አፈር ሰውን ፈጥሮ እንዲናገር ማረጉ በራሱ የእርሱ ችሎታ ነው። እሩቅ ስንሄድ በባይብል ኢያሱ ታላቁን ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው፥ ከዚያም ለሕዝቡ፦ "እነሆ፥ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው፦
ኢያሱ 24፥26-27 ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው። ኢያሱም ለሕዝቡ፦ እነሆ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው።

"ሰምቶአልና" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ታላቁ ድንጋይ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ የሚሰማበት ጆሮ አለውን? ሰምቶስ የሚመሰክርበት አንበት አለውን? ምን ያስደንቃል? ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል እኮ፥ የሚያጅበው ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ሲጮኽ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ሰምቶ ይመልስለታል፦
ዕንባቆም 2፥11 ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል።

የድንጋይ እና የእንጨት መናገር እና መስማት ለመቀበል ፍልስፍና ካላስፈለገ አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት መኖሩን ለመቀበል ፍልስፍና መስፈርት አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ጶታ
የነቢያት መንገድ | طريق الأنبياء
◆▮ውይይት▮◆

◍ ወንድም ናይ ሐቅ ሚዛን
◍ ወንድም አቡ ሙሐመድ
◍ ወንድም ራስ ምታት
🆅🆂
◍ ወገናችን Scorpio
◍ ወገናችን Nobi
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትክክለኛ የአላህ ባርያ ናችሁ?

◍እኅት ዝሀራ ሙሥጠፍ🎤📜
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
▪️ኢብኑ ረጀብ (رحمه الله) እንዲህ አሉ :-

"አላህ ጭንቀትንና ትካዜን ከሚያስወግድበት ትልልቅ ምክንያቶች ውስጥ :-
① - አላህን አብዝቶ ማውሳት (ዚክር ማድረግ)።
- በመልክተኛው (ﷺ( ላይ ሰለዋት ማውረድ
③ - ቁርአን መቅራትን ማብዛት ናቸው።"

اللهم صل على نببينا محمد وعلى آله وصحه أجمعين.

✍️ እኅት ዛህራ ሙስጠፋ
አህዛብ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አንዱ ክርስቲያን በውይይት ላይ ሲናደድ አህዛብ ብሎ ተናገረኝ፤ እኔም አህዛብ ምን ማለትና ምን እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ይቺን ቃል አትደፍራትም ነበር ብዬ ምላሽ ሰጠሁት፤ "አህዛብ" ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤትኒኮስ" ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አህዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦

ነጥብ አንድ
"ርኵሰት"
በመፅሐፍ ቅዱስ "የአሕዛብን ርኵሰት" ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦
ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ ""አሕዛብ"" የሚያደርጉትን "ርኵሰት" ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ታዲያ ይህ በኢስላም ትልቁ ሽርክ ነው፤ ከኢስላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙስሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው?

ነጥብ ሁለት
"ግብረ-ሰዶም"
አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ"hetro-sexual" እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም"homo-sexual" ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦
1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ "ሰዶማውያን" ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን ""የአሕዛብን ርኵሰት" ሁሉ ያደርጉ ነበር።

ታዲያ ይህ በኢስላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ።

ነጥብ ሶስት
"የተቀረፀ ምስል"
ነቢያት "የአሕዛብ ልማድ" ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦
2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም "አሕዛብ" እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም "የተቀረጹ ምስሎቻቸውን" ያመልኩ ነበር፤
2ኛ ዜና 16፥26 "የአሕዛብ አማልክት" ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች "የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ" ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ "ከአሕዛብ" ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ "የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት" የሚሸከሙና ያድን ዘንድ "ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ" እውቀት የላቸውም።
ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። "የአሕዛብ ልማድ" ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።

ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ኅሊና እያለ ምን ይኮናል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ጶታ
የነቢያት መንገድ | طريق الأنبياء
◆▮ውይይት▮◆

◍ ወንድም ናይ ሐቅ ሚዛን
◍ ወንድም አቡ ሙሐመድ
◍ ወንድም ራስ ምታት
🆅🆂
◍ ወገናችን Scorpio
◍ ወገናችን Nobi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
من روائع سلسلة سورة الكهف | الشيخ الزين محمد أحمد | Al Zine MOhammed Ahmed | surat al kahf
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ወንጀላችሁ እንድታበስለት የሚፈልግ ይችን ዚክር ይሐፍዝ"

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما على الأرضِ أحدٌ يقولُ لا إله إلا اللهُ واللهُ أكبرُ ولا حولَ ولا قوةِ إلا باللهِ إلا كفّرتْ عنهُ خطاياهُ ولو كانتْ مثلَ زبدِ البحرِ﴾

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል: 3460

እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በድብቅ አላህን ማመጽ💧

«ሰዎች እንዲያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህንም ስትሆን አትስራው !!»

(አስሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 1055)

◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
ሃሩን ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا

ሚሽነሪዎች፦ ቁርኣን ከባይብል ታሪክ ጋር ይጣረሳል" ብለው ሱሪ ባንገት ሊያስገቡ ሲቃጣቸው ይታያል፣ ከሚተቹበት መወዛገብ አንዱ፦ "ቁርአን የሙሴን ወንድ አሮንን የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ያደርጋል" የሚል ግራጫ ውሸት ይዋሻሉ፥ ይለቃሉ። በኢስላም ላይ ስትቀጥፉ ህሊናን ከሚያሳድድ ጥያቄ አታመልጡም።
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ "የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ነው" ይለናል። ሚሽነሪ ሃያሲ ሂስ ከመስጠት በፊት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ተነግሮ ከማያልቅ ታፍሶ ከማይዘለቅ ከዲነል ኢስላም ዕውቀት መማር ነው። መዋተቱና መቃተቱን ትታችሁ ጓዛችሁን ሸክፋችሁ ለመማር ኑ። መቆዘም አያዋጣም። ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተወዛገባችሁ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናያለን፣ "ሃሩን" هَارُونَ ማለት በአማርኛችን "አሮን" ተብሎ በቁርአን የተጠቀሱ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፣ እነርሱም አንዱ የሙሴ ወንድም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም፣ ይህን ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦

ነጥብ አንድ
"የሙሳ ወንድም ሃሩን"
ሙሳ አንደበተ ኮልታፋ እና ተብታባ ስለነበር ወንድሙ በእርሱ ፋንታ እንዲናገር ወደ አላህ ዱዓ አደረገ፦
20፥29 «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي
20፥30 *«ሃሩንን ወንድሜን*፡፡ هَارُونَ أَخِي
20፥32 *«በነገሬም አጋራው*፡፡ وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي
28፥34 *«ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና*፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ

ሙሳ መልእክተኛ ነው፤ ሃሩን ደግሞ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን "በነገሬም አጋራው" ብሎ በጠየቀው መሰረት ተውራት የተባለውን ሪሳላ ስለተጋራ መልእክተኛ ተባለ፤ "ከእኔ ጋር ላከው" የሚለው ይሰመርበት፤ ለዛ ነው አላህ ተውራትን ለሙሳ እና ለሃሩን ሰጠናቸው ያለው፦
21፥48 *ለሙሳ እና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ሃሩን በራሱ መልእክተኛ አይደለም፤ ግን ነቢይ ሆኖ ሙሳን በመልእክቱ በማስተላለፍ ይረዳዋል፤ አላህ ወደ ሕዝባቸው በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላካቸው፦
19፥53 *ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا
25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا
23፥45 *ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን*፡፡ ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ

ስለ ነቢዩ ሃሩን በጥቅሉ ይህንን ይመስላል። የሙሳ እና የሃሩን እናት እና አባት አሊያም የቤተሰብ ዝርዝር ስም ሆነ ማንነት ቁርኣን ላይ አልተጠቀሰም።
ነጥብ ሁለት
"የሃሩን እኅት"
አምላካችን አላህ በዒሣ እናት በመርየም ዘመን የነበሩት የመርየም ዘመዶች የዒሣን እናት መርየምን "የሃሩን እኅት" እንዳሏት ተርኮልናል፦
19፥28 *«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት*፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا

"አሏት" የሚለው ይሰመርበት፤ ባዮቹ የመርየም ዘመዶች ቢሆኑም አላህ ይህንን ተርኮልናል። የኢሳን እናት መርየም የአባቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "ኢያቂም" יְהוֹיָקִים በቁርኣን ደግሞ "ዒምራን" عمران ነው፤ የእናቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "አና" חַנָּה በተፍሲር ደግሞ "ሐናህ" حنة ነው፣ ኢያቄም የማርያም አባት ስለመሆኑ ከቁርአን ማየት ይቻላል፦
3፥35 *የዒምራን ባለቤት (ሐና)* «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን ፅንስ ከሥራ ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
66፥12 *የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ*፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِين

ቁርኣን ላይ የመርየም እናት ስሟ ባይጠቀስም ማንነቷ ተገልጻል። ነገር ግን ባይብል ላይ የመርየም እናት እና አባት ስም ሆነ ማንነት አልተገለጸም።
ስለዚህ ከመነሻው በሌለ ነገር ሁለት የተለያዩ ታሪካትን አዛብቶ ግጭት መፍጠር አይቻልም፣ ታዲያ ዒሣ እናት የመርየም ወንድም ሃሩን ማነው? ስንል የስም ሞክሼ እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ይህንን ከነብያችን"ﷺ" መረዳት ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38, ሐዲስ 13
አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ እንደተረከው፦ *"ወደ ነጅራን በመጣው ጊዜ የነጅራን ክርስቲያኖች፦"የሃሩን እኅት ሆይ! የሚል ቀርተክልናል፤ ሙሳ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት የነበረ ነው" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስመለስ ስለዚህ ጉዳይ ጠየኳቸው፣ እሳቸውም አሉ፦ "የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር*። عَنِ الْمُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ، قَالَ لَمَّا قَدِمْتُ نَجْرَانَ سَأَلُونِي فَقَالُوا إِنَّكُمْ تَقْرَءُونَ يَا أُخْتَ هَارُونَ وَمُوسَى قَبْلَ عِيسَى بِكَذَا وَكَذَا ‏.‏ فَلَمَّا قَدِمْتُ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلْتُهُ عَنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَمُّونَ بِأَنْبِيَائِهِمْ وَالصَّالِحِينَ قَبْلَهُمْ

ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር የምንረዳው የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የዒሳ እናት የመርየም ወንድም ኃሩን የስም መመሳሰል እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ናቸው፣ የእሳቸው ዘመድና ባልደረባም ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ይህን አንቀጽ ሲፈስረው፦ "አሮን የማርያም ግማሽ ወንድምና የአባቷ ልጅ ነው" በማለት አስቀምጦታል።

ነጥብ ሦስት
"ኢኽዋህ"
“ኢኽዋህ” إِخْوَة ማለት “ወንድማማች እና እህትማማችነት" ማለት ነው፤ አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው፦
49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው*፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

በነብያችን"ﷺ" ሐዲስ የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ ሁለት የስም ሞክሼ መሆኑ ተሰምሮበታል፤ ነገር ግን የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ አንድ ማንነት ናቸው ቢባል እንኳን አሁንም ችግር የለውም። ምክንያቱም አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል።
በትውፊት መርየም የሌዊ ዘር ናት፤ ሃሩንም የሌዊ ዘር ነው፤ ስለዚህ ሁለቱም ወንድምና እህት መሆን ይችላሉ፤ "አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን እና "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፤ ቃሉ የግድ አብራካዊ ወንድምና እህት ብቻ አያመለክትም። ምክንያቱም "ኡኽት" أُخْت የሚለው ቃል "ሚስል" مِثْل ማለትም "ቢጤ" በሚል ይመጣል፦
43፥48 ከተዓምርም አንዲትንም አናሳያቸውም እርሷ *ከብጤዋ* በጣም የበለጠች ብትኾን እንጅ፡፡ ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው፡፡ وَمَا نُرِيهِم مِّنْ آيَةٍ إِلَّا هِيَ أَكْبَرُ مِنْ أُخْتِهَا ۖ وَأَخَذْنَاهُم بِالْعَذَابِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
7፥38 አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን *ብጤዋን* ትረግማለች፡፡ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا

"ብጤዋ" ለሚለው የገባውን ቃል "ኡኽቲሃ" أُخْتِهَا አንዳንድ የኢንግሊሽ ትርጉም "እህትዋን"its sister" በማለት አስቀምጠውታል፦
43፥48 And We showed them not a sign except that it was greater than *its sister*, and We seized them with affliction that perhaps they might return [to faith]. Sahih International

ማጠቃለያ
ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ በዐረቢኛ “መርየም” مَرْيَم‎ ፣ በዐረማይክ “ማርአም” ܡܪܝܡ‎ ፣ በግሪክ “ማርያ” mαρία ሲሆን የስሙ መሰረት የዕብራይስጡ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ነው፤ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “መር” מר ማለት “ጠብታ” ማለት ሲሆን “የም” ים ደግሞ “ባህር” ማለት ነው፤ በጥቅሉ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ማለት “የባህር ጠብታ” ማለት ነው።
በባይብል ማርያም በሚል ስም የሚጠሩ ሴቶች ስምንት ሲሆኑ እነርሱም፦
1ኛ. የሙሴ እህት፦ ዘጸአት 15፥21
2ኛ. የዕዝራ ልጅ፦ 1ኛ ዜና 4፥17
3ኛ. የኢየሱስ እናት፦ ማቴዎስ 1፥18
4ኛ. መቅደላዊት፦ ሉቃስ 8፥2
5ኛ. የአልዓዛር እህት፦ ዮሐንስ 11፥1
6ኛ. የቀለዮጳም ሚስት፦ ዮሐንስ 19፥25
7ኛ. የማርቆስ እናት፦ 12፥12 እና
8ኛ. የሮሜ ማርያም፦ ሮሜ 16፥6 ናቸው።
የኢየሱስ እናት መርየም ለእናቷ አንድና የስለት ልጅ ብትሆንም በአባቷ ግን ወንድምና እህት እንዳላት ነገረ-ማርያም"Marylogy" ይነግረናል፣ ባይብልም ማርያም እህት እንዳላት ይናገራል፦
ዮሐንስ 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ፦ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ *የእናቱም እኅት*፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።

በታሪክ፣ በፔንታተች ሆነ በታልሙድ መጻሕፍት የሙሴና የአሮን አባት "እንበረም" עַמְרָם ሲሆን እናታቸው ደግሞ "ዮከብድ" יוֹכֶ֤בֶד ናት፣ ይህን ከራሳችሁ መጽሐፍ ቅሪት ማየት ይቻላል፦
ዘጸአት 6፥20 *እንበረምም עַמְרָם የአጎቱን ልጅ ዮካብድን יוֹכֶ֤בֶד አገባ፥ “አሮንና ሙሴንም” ወለደችለት*፤

ነገር ግን የሙሴ እህት ማርያም እና የኢየሱስ እናት ማርያም ሁለት የተለያዩ ሴቶች ናቸው። ይህ በቀላለ እንድትረዱት አንድ ናሙና ከባይብል ልስጣችሁ፣ "የጌት ሰው ጎልያድን" የገደለው ማን ነው ዳዊት ወይስ ይሽቢብኖብ?
እዚህ አንቀጽ ላይ የጌት ሰው ጎልያድን ዳዊት እንደገደለው ይናገራል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥4 ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር *የጌት ሰው ጎልያድ*፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ።
1ኛ ሳሙኤል 17፥50 *ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ*፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም።

እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ የጌት ሰው ጎልያድን ይሽቢብኖብ እንደገደለው ይናገራል፦
2ኛ ሳሙኤል 21፥19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የቤተ ልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን *የጌት ሰው ጎልያድን* ገደለ።

አንዱን ክርስቲያን ተወያይ ይህን ጥያቄ ሳቀርብለት "ወሒድ ምን ነካህ ደህና ሰው አልነበርክም እንዴ? ዳዊት የገደለው ጎልያድ እና ይሽቢብኖብ የገደለው ጎልያድ እኮ በተለያየ ዘመን የኖሩ ሁለት ግለሰቦች ናቸው" አለኝ፣ እውነት ነው የአይሁድ ሆነ የክርስቲያን ስመ-ጥርና ዝነኛ ኮሜንታተሮች በተለያዩ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ግን በአንድ ቦታ በጌት ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፣ ታዲያ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው ነገሩ፣ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ይሉሃል እንደዚህ ነው።
ሲቀጥል ወንድምና እህት የግድ የአብራክ ክፋይ የሚለውን አያሲዝም። ሉጥ የኢብራሂም የወንሙ ልጅ ሲሆን ኢብራሂም ለሉጥ ደግሞ አጎት ነው፣ ነገር ግን ሉጥ ለኢብራሂም ወንድም ተብሏል፣ ያ ማለት የአንድ ቤተሰብ መሆንን ካሳየ የሙሳ ወንድም አሮንና መርየም የሌዊ ቤተሰብ ስለሆኑ ወንድም አሊያም እህት ቢባሉ ችግር የለውም፦
ዘፍጥረት14፥12 በሰዶም ይኖር የነበረውን *የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን* ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።
ዘፍጥረት14፥14 አብራምም *ወንድሙ* እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሳትሳደቡ በማስረጃ መልሱ

1ኛ ነገሥት 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም።
⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ።
⁶ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም።

ደሞ ሌሎችንም ጣኦት ያስመልክ ነበር

“በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ።”
— 1ኛ ነገሥት 11፥7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የታመማችሁ ሰዎች ብስራት🌹💧

አንድ ሙስሊም ቢታመም እሳት ከወርቅና ከብር ቆሻሻን እንደሚያስወግድ ሁሉ በበሽታው የተነሳ አላህ ኃጢአቱን ያስወግድለታል።”

«አስ–ሲልሲለቱ አስ– ሰሒሃ –714»

◍እኅት ዛህራ ሙስጠፋ🎤📜
የአሏህ መታየት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

የትንሣኤ ቀን ምእመናን በጀነት ውስጥ ይሆናሉ፥ ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ በጀነት ውስጥ ያለው ተጨማሪ መንፈሳዊ ጸጋ አሏህን ማየት ነው፦
50፥35 ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ”እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ”፡፡ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌۭ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 354
ሱሀይብ እንደተረከው፦ "ነቢዩም’ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ የጀናህ ባለቤቶች ጀናህ በሚገቡ ጊዜ የተከበረው እና ከፍ ያለው አሏህ፦ "ጭማሪ እንድሰጣችሁ ትፍልጋላችሁን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ ፊታችንን አላበራህምን? ጀናትንስ አላስገባከንምን? ከእሳትስ አላዳንከንምን? ይላሉ። ከዚያ እርሱ ግርዶሹን ያነሳል፥ ለእነርሱ የወደደው አሸናፊው እና ክብራማ የሆነውን ከጌታቸውን ፊት በስተቀር ለእነርሱ ምንም ነገር በእነርሱ ዘንድ የለም"። عَنْ صُهَيْبٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا دَخَلَ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْجَنَّةَ - قَالَ - يَقُولُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى تُرِيدُونَ شَيْئًا أَزِيدُكُمْ فَيَقُولُونَ أَلَمْ تُبَيِّضْ وُجُوهَنَا أَلَمْ تُدْخِلْنَا الْجَنَّةَ وَتُنَجِّنَا مِنَ النَّارِ - قَالَ - فَيَكْشِفُ الْحِجَابَ فَمَا أُعْطُوا شَيْئًا أَحَبَّ إِلَيْهِمْ مِنَ النَّظَرِ إِلَى رَبِّهِمْ عَزَّ وَجَلَّ ‏"‏ ‏.‏

የምእመናን ፊቶች በትንሣኤ ቀን አብሪዎች ናቸው፥ ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፦
75፥22 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ
75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ
10፥26 ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገር እና ”ጭማሪም አላቸው"። ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፥ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ ٱلْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌۭ ۖ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌۭ وَلَا ذِلَّةٌ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

በተቃራኒው የከሓዲያን ፊቶች በትንሣኤ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፥ ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። ምክንያቱም እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፦
75፥24 ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ
80፥40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አለባቸው። وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ
80፥41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ
80፥42 እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ

እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነቸው በኋላ የካዱ እና ይክዱ በነበሩት ነገር ቅጣትን የሚቀምሱ ናቸው፥ እነርሱ በትንሣኤ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፦
3፥106 ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን አስታውስ፡፡ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ» ይባላሉ፡፡ يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ
84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

አምላካችን አሏህ በዛቱ ከፍጥረት ውጪ ቢሆንም ምእመናን በጀነት በዓይናቸው ሳያካብቡት እርሱ በሚፈልገው መልኩ ያዩታል። ፍጡራን እርሱን በማየት አያካብቡትም፥ እርሱ ግን ሁሉን ተመልካች ስለሆነ ሁሉንም ያካብባል፦
6፥103 ዓይኖች አያካብቡትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያካብባል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

"አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለት "ረቂቁ" ማለት ሲሆን አሏህ በፍጡራኑ ዓይን የማይከበብ ረቂቅ ነው፥ እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ነገር፣ ለማየት ብርሃን፣ ለመስማት ድምፅ፣ ለመታየት አካል ያስፈልገኛል። አሏህ ግን ከማንም ከምንም ፍጥረት ጋር ስለማይመሳሰል ፍጥረት ሳይኖር ፍጥረቱን የሚያውቅ፣ በጨለማ ውስጥ ያሉትን የሚያይ፣ በልብ የሚንሾካሸኩትን የሚሰማ፣ ለምእመናን በትንሳኤ ቀን ስይካበብ በመገለጥ የሚታይ ነው፦
42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አንዱን አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፥ እርሱም፦ "ፊቴን ማየት አይቻልህም" ብሏል፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው "ለማይታየውም" ለዘመናት ንጉሥ ምስጋና እና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን! አሜን።
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ "ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም" አለ።

አንዱን አምላክ አንድ ሰው እንኳ ባያየው እና ሊያይ ባይቻለው ባሮቹ ግን በትንሣኤ ቀን በትንሣኤያዊ ዓይን ፊቱን ያያሉ፦
ኢዮብ 19፥27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል።
ራእይ 22፥3 ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ።

አምላካችን አሏህን በትንሳኤ ቀን እርሱን ከሚያዩት ምእመናን ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምልጃ የሌለበት ቀን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ

"ምልጃ" ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፥ እነርሱም፦
፨አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣
፨ሁለተኛው የሚማልደው አማላጅ እና
፨ሦስተኛ የሚማለድለት ተመላጅ ናቸው።
አሏህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፥ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱት አማላጆች ደግሞ መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው፦
2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

"ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም" የሚለው ይሰመርበት! ዐውደ ንባቡ ስለ መላእክት እያወራ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚማለድላቸው ተመላጆች ደግሞ አሏህ ዘንድ ቃል ኪዳን የያዙት አማንያን ናቸው፦
34፥23 ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ
19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
20፥109 በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا

"በዚያ ቀን" የሚለው የፍርዱ ቀን ሲሆን በዚያን ቀን አሏህ የፈቀደላቸው መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለምዕመናን ያማልዳሉ። ነገር ግን ለኩፋሮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፦
40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع
2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ

"ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን" የፍርዱ ቀን ሲሆን ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለው ለኩፋሮች ስለሆነ ዐውዱ ላይ "ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው" በማለት ይናገራል። ያ የፍርዱ ቀን እነርሱም ከአሏህ እርዳታ የማይረዱበትን እና ምልጃን የማይቀበሉባት ቀን ነው፦
2፥48 ነፍስም ከነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፣ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፣ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝበትን፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡ وَاتَّقُوا يَوْمًا لَّا تَجْزِي نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْئًا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَاعَةٌ وَلَا يُؤْخَذُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ

"የማይቀበሉ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በግስ መደብ የተጠቀሱት እና "እነርሱ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በስም መደብ የተጠቀሱት በዳዮቹ ከሓዲዎች እንጂ ምእመናንን አይጨምርም፥ በፍርዱ ቀን አሏህ የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሙእሚን ቢኾን እንጅ ለከሓዲ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም። ኩፋሮች የትንሳኤ ቀን፦ "በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ? ተብለው ሲጠየቁ፦ "ከሰጋጆቹ አልነበርንም፣ ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፣ ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፣ በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን" ይላሉ። የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፦
74፥48 የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ

"ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" የተባለው አሁንም ለኩፋሮች እንጂ ለሙእሚን በፍጹም አይደለም። "ሑላህ" خُلَّة ማለት "ወዳጅነት" ማለት ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ማለት ደግሞ "ወዳጅ" ማለት ነው፥ በዚያ ቀን ኩፋሮች አንዱ ለሌላው ጠላት ነው፦
43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

"ወዳጆች" ለሚለው የገባው ቃል "አኺላእ" أَخِلَّاء ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ" የሚለው ይሰመርበት! አሏህን ፈሪዎች ምእመናንማ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይወዳጃሉ፡፡ የእነዚያም ወዳጅነት አማረ፦
4፥69 አላህን እና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا

ስለዚህ "ምልጃም የሌለበት ቀን" የተባለው "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" በተባለበት ዐውድ ከሆነ እና ለምእመናን ምልጃ ሆነ ወዳጅነት ካላቸው ምልጃ እና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ለኩፋሮች ነው፥ የፍርዱ ቀን ለኩፋሮች ቤዛ የሌለበት ቀን ነው። ሙጅሪም ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፥ ቅሉ ግን ለእነርሱ ቤዛ የሌለበት ቀን ስለሆነ ከእሳት ቅጣት አይቤዥም፦
70፥11 ዘመዶቻቸውን ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
ምእመናን ግን በጀነት ስላሉ ከዚያ ቀን ስቃይ ተቤዥተዋል። ከእነዚያ ከካዱት ግን ቤዛ አይወሰድም፥ ለእነዚያም ለበደሉት ከሐድያን በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፦
57፥15 «ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፥ ከእነዚያ ከካዱትም አይወሰድም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፥ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» ይሏቸዋል፡፡ فَالْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ مَأْوَاكُمُ النَّارُ ۖ هِيَ مَوْلَاكُمْ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ
39፥47 ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፡፡ وَلَوْ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ مِن سُوءِ الْعَذَابِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

ይህቺ የካፊር ነፍስ ከነፍስ ምንንም ቤዛ የማይያዝበትን ቀን ተጠንቀቁ! እንግዲህ ቤዛ፣ ምልጃ፣ ወዳጅነት የሌለበት ቀን የተባለው ከዐውድ እና አጠቃላይ ከቁርኣን መልእክት አንጻር ለከሓዲ በዳዮች ብቻ ነው። የፍርዱ ቀን ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ምልጃ ያረጋል፥ የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ሰው ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 402
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው የአሏህ ነቢይም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ጸሎት ያረጋል፥ በትንሳኤ ቀን የእኔ ጸሎት ለኡመቴ ምልጃ ነው*። عَنْ قَتَادَةَ، حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ دَعَاهَا لأُمَّتِهِ وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏”‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
2024/05/29 05:38:47
Back to Top
HTML Embed Code: