Telegram Web Link
ሙስሊሞችን ሰልቅጠው ሊበሉ አሰፍስፈዋ። በሙስሊሞች ከተማ መግቢያ በራፍ ላይ ጦራቸውን ሰብቀው ቆመዋል። ሰራዊቱ ተቀዳሚ ከፊል ጦሩን ወደፊት ለፊት አስጠግቷል። አንድ ሽማግሌ ከትንታጉ ጨቅላ ልጃቸው ጋር በመጥረቢያ እንጨት እየፈለጡ ነበር የመስቀላዊያኑ የጦር መሪ የተመለከታቸው። ሶስት ወታደሮቹን ይዞ ወደ እነርሱ ተጠጋ። "ስለ ሀገራችሁ መረጃን እንድትሰጡን እጠይቃችኋለው ስንት ሰራዊት እንዳለ የከተማዋንም መግቢያና መውጫ እንድትጠቁሙን" እንፈልጋለን አለ።

ሽማግሌው መጥረቢያቸውን በትከሻቸው ላይ እንደሸከፉ ካቀረቀሩበት ተነሱ
"ሁሉንም ነገር ከመንገሬ በፊት ምስክር እንዳይሆንብኝ ይህ ከአጠገቤ የቆመውን ልጅ ግደ*ሉል*ኝ" ሲሉ ተናገሩ።
ከመካከላቸው አንዱ ሠይፉን መዞ የልጁን አንገት በጠሰው። ደ*ሙ የምድሩን አፈር አራሰ። የብላቴናውን ታዳጊ ነፍስ ወደመጠጠችው መሬት ሸኹ ተመለከቱና እንዲህ አሉ
"ይህ እንድትገድሉት ያዘዝኳችሁ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?"
"ስለ እሱ ከኛ የበለጠ አንተ ታውቃለህ" ሲሉ መለሱላቸው።
"አዎ በእርግጥም ይህ ልጄ ነው። እኔን ገድላችሁ ከሱ መረጃን እንዳታገኙ ፈርቼ ቀድሜ ልጄን ሰዋሁት። ሀገሬን ወራችሁ ሙስሊም ወንድሞቼን እንድትገድሉ የሚረዳችሁን አንድ መረጃ ከምናገር ሞቴን እመርጣለሁ። ይሄው ፊታችሁ ቆሜያለሁ ቢሻችሁ በገመድ ቢሻችሁም በሰይፍ ነፍሴን ከሩሔ ጋር ነጥሏት እንጂ አንድ መረጃ ከኔ አታገኙም" አሏቸው።

ወታደሮቹ የልጁን ጀናዛ ተሸክመው ወደ ንጉሳቸው ይዘውት አቀኑ። ክስተቱንም አወጉት።
ንጉሡም እንዲህ አለ:-
"ሙስሊሞች ልጆቻቸውን የሚሠውባትን ከተማ በእርግጥም መቆጣጠር አንችልም። ብንወራቸው እንኳ ድልን አንጎናፀፍምና ሠራዊቱን ይይዛችሁ ወደ ኋላ ተመለሱ" ሲል አዘዘ።

በእርግጥም ንጉሱ እውነትን ተናገረ
#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
على هامان يا فرعون؟؟
ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ…

«ፊርዓውን ከነበረበት ድንበር ያለፈ ጥመት ጋ ጅል (ፋራ) ነገር ነበር አሉ። አማካሪው ሃማን ደግሞ እንደ የትኛውም የንጉሶች አማካሪ ብልጣብልጥ ነበር አሉ። እናም ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት በፊርዓው “የጌትነት ሙገታ” ያመነች አሮጊት ፍየልዋ ይሞትባትና ወደ ፊርዓውን ቤት ትመጣለች።

ስትመጣ ፊርዓውን አልነበረም ሃማንን አገኘችው።
"ጉዳይሽ ምን ነበር?" ሲላት
"ፍየሌ ሞታብኝ ፊርዓውን ሕያው እንዲያደርጋት ነበር የመጣሁት።" ትለዋለች

ሃማን ብልጥ ነበር;  ብለን የለ?
"ነይ በቃ ፊርዓውን አሁን ግመል እየፈጠረ ስለ ሆነ ይቆይብሻል። ስለዚህ ሌላ ፍየል ልስጥሽ።" ይላትና ሌላ ፍየል ሰጥቷት ትሄዳለች።

ፊርዓውን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሃማን "አንዷ አሮጊት ፍየሏ ሙቶባት ሕያው እንድታደርግላት መጥታ ነበር።" ሲለው ፊርዓውን ደነገጠ።

ሃማን "አይዞህ! ፊርዓውን ግመል እየፈጠረ ነው። ብያት ሌላ ፍየል ሰጥቻት ሄዳለች። አትመጣም።" አለው።

በዚህ ጊዜ ፊርዓውን እንደ መረጋጋት አለና በረጅሙ ተንፍሶ…………
  «ግመል መፍጠር እኮ እንዴት እንደ ሚያደክም ብታይ» አለው።


ሃማን ፈገግ አለና… …
     على هامان يا فرعون
ኧረ ፊርዓውን! በሃማን ላይአለው

በሃማን ላይ ሙድ ትይዛለህ ወይ እንዴ ጭራሽ ልትሸውደኝ ያምርሃል ማለቱ ነው።

ከዛኔ ጀምሮ ሰዎች በሚያውቁት ነገር ላይ  ሊሸውዳቸው ለሞከረ ሰው
على هامان يا فرعون
ኧረ ፊርዓውን! በሃማን ላይአለው

እያሉ አባባል አድርገው ይዘውታል።»

@smithhk
የአገር መሪ ናቸው። ፍትህን ያነገሱ የሐቅ ሰው። በእውነት ብርሀን ስር የዳኙ መሪ። አንድ ምሽት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው በሻማ ብርሃን እየታገዙ የአስተዳደራቸውን የግምጃ ቤት የገቢና ወጪ ሂሳብ በመስራት ላይ ናቸው። በር ተንኳኳ። እሳቸውን ለማነጋገር የሚፈልጉ ሁለት ሰዎች ነበሩ። በአስተዳደሩ ስልጣን ውስጥ ሁነኛ ቦታ የማግኘት ምኞት ነበራቸው። የመጡትም ይህንን ህልማቸውን ያሳካልናል ያሉትን አንድ ሃሳብ ይዘው ነው። ይህንን ሃሳባቸውን በመቀበል በመንግስታቸው ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚስጧቸው ከሆነ እነርሱ በፊናቸው ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል እንደሚገቡ በመግለፅ ለመደራደር ነበር።

ሰዎቹ እንደተቀመጡ የበራው ሻማ ጠፋና ሌላ ሻማ ተለኮሰ። በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በመገረም ሰሜት እርስ በእርሳቸው ተያዩ። ምክንያቱን ለማወቅ የበለጠ ጉጉት ያደረበት አንደኛው ሰው የመጣበትን ጉዳይ ከማንሳቱ ቀደም ብሎ የሚበራውን ሻማ አጥፍተው ሌላ ሻማ የለኮሱበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቀ። እሳቸውም "እናንተ ወደቤት ስትገቡ ይበራ የነበረውን ሻማ ከመንግስት ግምጃ ቤት ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የተገዛ የህዝብ ሀብት ነው። ይህ የምትመለከቱትን የግምጃ ቤት የወጪና ገቢ ሂሳብ ለመስራት ስል ነበር ያበራሁት አሁን እናንተ የመጣችሁበት ጉዳይ የግል ጉዳያችሁ በመሆኑ የበፊቱን ሻማ በማጥፋት ይህንን ከራሴ ገንዘብ ወጪ አድርጌ የገዛሁትን ሻማ ለኮስኩት" በማለት ለቀረበው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጡ። በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት እርስ በእርሳቸው ተያዩ የመጡበትን ዓላማ ማንሳት ቀርቶ አንዲት ሌላ ቃል እንኳ መተንፈስ ተሰኗቸው ወጥተው ሄዱ። ሰውየው አሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ነበሩ። አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው።

ኢስላም አለምን ሲመራ እንዲህ ነበር ፍትህ የነገሰው

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
عن أبي هريرة رضي الله عنه ،
عن النبي ﷺ قال :

((يَجِيءُ القُرْآنُ يَوْمَ القِيَامَةِ فَيَقُولُ : يَا رَبِّ حَلِّهِ. فَيُلْبَسُ تَاجَ الكَرَامَةِ ،
ثُمَّ يَقُولُ : يَا رَبِّ زِدْهُ. فَيُلْبَسُ حُلَّةَ الكَرَامَةِ ،
ثُمَّ يَقُولُ : يَا رَبِّ ارْضَ عَنْهُ. فَيَرْضَى عَنْهُ ،
فَيُقَالُ لَهُ : اقْرَأ وَارْقَ ، وَتُزَادُ بِكُلِّ آيَةٍ حَسَنَةً))

رواه الترمذي.
🌑የጀሀነም በሮች 7 ናቸው።
▰▰▰▰▰▰▰▰
1ኛው የጀሀነም በር (ሀነም) ይባላል፣
ሀነም ስያሜውን ያገኘው ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ ስለሚቃጠሉበት እና ስጋዎችን ስለሚትበላ ነው በሌሎች
የጀሀነም በሮች አንጻር አነስተኛ ቅጣት የሚስተናገድበት ነው።

2ኛው የጀሀነም በር (ለዛ) ይባላል፣
ለዛ ሁለት እጆችንና እግሮች በመብላት ትታወቃለች ለተውሂድ ጀርባ የሰጡ ሰዎችና የመልእክተኛውን ጥሪ
ያልተቀበሉ ሰዎች መኖሪያ ነች

3ኛው የጀሀነም በር (ሰቀር ) ይባላል፣ ሰቀር ያገኘውን ሁሉ አያስቀርም ወደ ብናኝ አመድነት ይቀይራል

4ኛው የጀሀነም በር (ሁጠማ ) ይባላል ።
ሁጥማ አጥንት፣ ከአጥንት በማጣበቅ ትታወቃለች ልብ ውስጥ
ዘልቆ የሚገባ ቅጣት የሚስተናገድባት የጀሀነም በር ነች በውስጧ የገቡ ይረዱ ዘንድ ደም፣በደም በሆነ እንባ የታጀበ
ለቅሶ ያለቅሳሉ ነገር ግን የሚረዳቸው አያገኙም።

5ኛው የጀሀነም በር ( ጀሂም) ይባላል፣
ጀሂም በትላልቅ የእሳት ፍሞች የተሞልቷል በጀሂም ውስጥ ያለው
አንዱፍም ትልቀቱ ብቻ ይቺን አለም ያክላል።

6ኛው የጀሀነም በር (ሰኢር) ይባላል፣
በሰኢር ውስጥ "300" ( ሶስት መቶ ) የእሳት ህንጻወች አሉ፣በያንዳዱ ህንጻዎች "300" (ሶስት መቶ) ቤቶች አሉ። በያንዳዱ ክፍል ውስጥ "300" (ሶስት መቶ) የቅጣት አይነቶች ይስተናገዱበታል
በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ እባቦችና ጊንጦች በብዛት ይገኙበታል።

7ኛው (ሀዊያ ይባላል)፣ ሀዊያ ውስጥ የገባ ዝንትአለም አይወጣም!!! ሀዊያ በውስጧ ሀባባ የተባለ እንደ ወንዝ ጅረት የሚፈስ እሳት የሆነ ወንዝ አለ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስድስትቱ የጀሀነም በሮች ሁሉ ሳይቀሩ ከዚህ ወንዝ አላህ ይጠብቃቸው ዘንድ ይማጸናሉ #ሰኡዳ የተባለ ተራራ በውስጧ የአላህ ጠላቶች እጆቻቸውና እግሮቻቸው ከፊቶቻቸው ጋር ታስሮ ከተራራው ጫፍ ላይ በአፍጡማቸው እንዲደፉ ይደረጋሉ !

የጀሀነም ዘበኞችም እነዚህን የአላህ ጠላቶች በከፍተኛ ሁኔታ ያሰቃዮቸዋል።

አላህ ከሁሉም የጀሀነም በሮች ቅጣት ይጠብቀን 🤲

@smithhk
#ኳታር አልተቻለችም! ለምዕራባዊያን ቆምጠጥ ያለ ህግ አውጥታለች

በመጭው ህዳር ወር በኳታር አስተናጋጅነት የአለም ዋንጫ ይካሄዳል።ኳታርም #አጃኢብ የሚያሰኙ ህጎችን እያፀደቀች ትገኛለች።

1.ማንኛውም ተጫዋችም ሆነ ደጋፊ አሊያም አሰልጣኝ ወደ ሀገር ኳታር ሲገባ የኒካህ ወይም የጋብቻ የምስክር ወረቀት ከሌላው ከሴት ጋር አልጋ መያዝ አይችልም እንቢኝ ብሎ ይዞ ከተገኘ ወህኒ ይወረወራል።

2.የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚደግፍ መለያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ አይቻልም።በተለይ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ከተያዙ የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል።

3.የትኛውንም አይነት አልኮል መጠጥ መጣጣት አይታሰብም።በተለይ አንደዛዥ እፆችን ይዞ የተገኘ ሰው እስከ ሰባት አመት እስራት ይጠብቀዋል። እና መሰል ህጎችን ኳታር ያወጣች ሲሆን ህጎቹን ፊፋም አፅድቆታል።

"ለ28 ቀናት ብለን እምነታችንን አንፃረርም" ሲሉም ነው የኳታር እግርኳስ ፌደሬሺን ፕሬዘዳንት ጄነራል አብዱልአዚዝ አብደላ የተናገሩት።

#ኳታር 👏🙏
በአላህ ፈጣሪነት፤ በእስልምና ሀይማኖት፤ በሙሐመድ(ﷺ)ነብይነት እና መልእክተኛነት የተደሰተ ሰዉ የኢማንን ጥፍጥና ቀምሷል። ረሱል(ﷺ)

#ሼር #share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
አንብቧትማ..!

ሁለት የሚዋደዱ ጓደሞች ቁጭ ብለው ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛዉ ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን አለው። ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው...

ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን ? ከዚያም የታመመ ሰው በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።

ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ሕይወት ምንድን ነው ? ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:

*1. ሆስፒታል *2. እስር ቤት *3. መቃበር
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ። በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ። በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ።

የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን። ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን አልሀምዱ ሊላህ!!

#ሼር #share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
www.tg-me.com/Quran_Mp3_Collection

1 @mishary_rashid_al_afasi
2 @Yassen_Al_Jazairi
3 @Sheikh_Abu_Bakr_Al_Shatri
4 @Sheikh_Muhammad_Al_Luhaidan
5 @Abdulbasit_Abdussamed1
6 @Sheikh_Abdul_Rahman_Al_Sudais
7 Ali_Al_Huzaifi
8 @Khalifah_At_Tonaeijy
9 Ahmad_Al_Ajmy
10 @Sheikh_Saad_Al_Gamidi
11 Emad_Al_Mansary
12 @Abdullah_ibn_Al_Basfar
13 @Sheikh_Nasser_Al_Qatami
14 @Abdulhadi_Kanakeri
15 @Sheikh_Maher_Al_Muaiqly
16 @Sheikh_Adel_Rayan
17 @Khalil_Al_Hussary
18 @Sheikh_Muhammad_Ayyub
19 @Abdullah_Awad_Al_Juhany
20 @Abdul_Rashid_Ali_Sufi
21 @Mohamed_Siddiq_El_Minshawi
22 @Abdul_Rahman_Al_Ossi
23 @Sheikh_Saud_Al_Shuraim
24 @Yasser_Al_Dosarii
25 @Muhammad_Al_Kurdi1
26 @Fares_Abbad1
27 @Sheikh_Salah_Bukhatir
28 @Imad_Zuhair_Hafez
29 @Muhammad_AbdulKareem
30 Ahmad_Misbahi
31 @Abdulaziz_Az_Zahrani
32 @Ibrahim_Al_Asirii
33 @Abdulbosit_Qobilov1
34 @Abdullah_al_Matrood1
35 @Afzal_Rafiqov1
36  Hani_Ar_Rifai
37 @Abdullah_Ali_Jaber
38 @Sheikh_Muhammad_Jibril
39 Jazza_Alswaileh
40 Bandar_Balila
41 @Mohammad_Al_Tablawi
42 Wadee_Al_Yamani
43 @Ghassan_Al_Shorbajyi
44 Zaki_Dagistan
45 Ahmad_Al_Lahdan
46 @Abdullah_Xalif
47 @Yasser_Al_Qureshi
48  Nabil_Al_Rifai
49 Salah_Al_Hashem
50 Shirazad_Taher
51 @Tawfeeq_As_Sayeghh
52 Rashid_Al_Arkani
53 @Sheikh_Mustafa_Ismail
54 Ali_Yakupov
55 Abdullah_Kamel
56 @Mahmud_Ali_Albanna
57 @Sheikh_Idris_Abkar
58 Hassen_Saleh
59 Moeedh_Al_Harthi
60 Ahmed_Naina
61 Waleed_Al_Naehi
62 Saber_AbdulHakam
63 @Mohammad_Saleh_Shah
64 @AbdulMuhsin_Qasim
65 Salah_Al_Budair
66 Akram_Alalaqimy
67 Jamaan_Alosaimii
68 @Abdulmohsen_Harty
69 @Abdul_Wadood_Haneef
70 @Mohammad_Al_Abdullah
71 Yahya_Hawwa
72 @Hasanxon_Yahyo_Abdulmajid
73 Khalid_Al_Jaleel
74 @Noreen_Muhammad_Siddique
75 @Ahmad_Al_Shalabii
76 @Alzain_Muhammad_Ahmad
77 @Abdulmohsin_Al_Obeikan
78 @Ibrahim_AlAkhdar

© @Quran_Mp3_Collection
Audio
😭የኛ ወንጀል እዚ ደርሰዋል!!😭
🙏ያረበል አለሚን ማረን የአላህ 🙏
በሼህ ኻሊድ አራሺድ
ሁላችንም ለምናውቀው ሼር እናድርግ
አላህ ወንጀላችንን ይማረን
አሚንን
#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ሙስሊሞች_በሰላታቸው_ላይ_በሶስት_ይከፈላሉ(360p)-0
<unknown>
ሙስሊሞች በሰላታቸው ላይ ተዘናግትዋል 😭😭

😍 በ ሼህ ኻሊድ አል ራሺድ 😍
#share #ሼር
#join
👇👇👇
Https://www.tg-me.com/smithhk
🔉 በነፃ

በቤትዎ ሆነው ኪታብ መቅራት ኢልምን መማር ይፈልጋሉ?
በ ሸህ ሰዒድ አሊ ሀቢብ ከ ሰኞ እስከ እሁድ ከ ጁመዐ ውጪ ኪታቦች በመቀራት ላይ ይገኛሉ ከእርስዎ የሚጠበቀው ቻናላችንን መቀላለቀል ብቻ ነው አሁኑኑ JOIN ብለው በ ቀጥታ ስርጭት ( LIVE ) ይከታተሉ
በ አካል መቅራት የምትፈልጉ አዲስ አበባ ቤተል መስጂድ
ሰአት ከ መግሪብ እስከ ኢሻ
📚 እስከ አሁን የተቀሩ ኪታቦች
📖አሱለል ፊቂህ
📖ሰፊና
📖ሹጅዐ
📖ባፈድል
📖ኡምደቱ ሳሊክ አሁን በመቀራት ላይ ያለ እና ሌሎችም
አሁኑኑ ይቀላቀሉ

https://www.tg-me.com/Al_Usmani
10) የሱብሂ ሰላት ጥቅሞች

በእስልምና ህግጋት ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ሰላት ነው። ሰላት አንድ ባሪያ ወደ ጌታው የሚቃረብበት መንገድ ነው። በ24 ሰዓት ክፍለ ጊዜ 5 (አምስት) የተለያዩ ወቅቶችን ወደጌታው የሚሰግድበት ሶስቱ በጨለማው ጊዜ የሚሰገዱ ሲሆን የተቀሩት ሁለት ሰላቶች በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይሰገዳሉ። የቀኑ የመጀመሪያው ሰላት በቀኑ የንጋት ክፍለጊዜ ላይ የሚገኘው የሱብሂ ሰላት ሲሆን ስለሱብሂ ሰላት ጠቀሜታዎች እንዳስስ። የሱብሂ ሰላት ሌላኛው መጠሪያው ፈጅር በመባል ይታወቃል።
በርካታ ኡለሞች ከሀዲስና ከቁርአን በመነሳት አስር ጠቀሜታዎችን ያስቀምጣሉ። የሱብሂ ሰላትን በጀመአ መስገድ ለአንድ ሰው በህይወቱ ላይ የሚፈጥረውን ጠቀሜታ እንመልከታለን።

1. ቀኑን በሙሉ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል
ጁንዱብ ቢን አብደላህ ቢን ሱፍያን በጅሊ አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው አሉ ነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አሉ “ሱብሂን ሰላት በጀምአ የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል …….”
“የሱብሂን ሰላት በጀመአ መስገድ በቀኑ ክፍለጊዜ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል ፣የሰው ልጆች ከሰዎች ጠባቂ ተላቀው በጌታቸው እንዲብቃቁና እንዲጠበቁ የሚደርግ ሰላት ነው፣……..” ሙስሊም ወአህመድ

2. አጅሩ(ምንዳው) ለሊቱን እንደቆመ ይቆጠርለታል
አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“የኢሻን ሰላት በጀመአ የሰገደ ግማሹን ለሊት እንደቆመ ሲሆን ሱብሂን በጀመአ የሰገደ ሙሉውን ለሊት እንደቆመ ይቆጠራል።” ሙስሊም

3. ከሙናፊቅነት ነጃ ይባላል
አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“በመናፍቃን ላይ ከባድ ሰላቶች የሱብሂና የኢሻ ሰላቶች ናቸው የእነዚህን ሰላቶች ጥቅም ቢያውቁ ኖሮ በዳዴም ቢሆን ወደሰላቱ ይመጡ ነበር።”  አህመድ፣ቡኻሪ እና ሙስሊም

4. ሙሉ የሆነን ኑር (ብርሃንን) ይለብሳል፤ በቂያም ቀን (በትንሳኤ ቀን)
ከቡረይዳ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ተይዞ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በጨለማ መስጂዶችን የሚጓዙ በየውመል ቂያማ (በትንሳኤ ቀን ) በሙሉ ኑር (ብርሃን) ይሆናሉ።” አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚ

5. መልአክቶች ይመሰክሩለታል፤ ያወድሱታልም
አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ  “በሰው ልጆች ላይ የተመደቡት መልአክቶች ይቀያየራሉ። በቀኑና በምሽቱ ክፍለ ጊዜ የሚቀያየሩበት ሰአት የሱብሂ ወቅት ላይ እና የአስር ወቅት ላይ ሲሆን ከዛም የ24 ሰአት ውሎአቸውን አላህ እያወቀ ለመልእክተኞቹ ይጠይቃቸዋል። ባሮቼን እንዴት ትታችኃቸው መጣችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው፤ እነሱም እንዲህ ይመልሳሉ። እየሰገዱ ትተናቸው መጣን። ስንመጣም እየሰገዱ አገኘናቸው።” ቡኻሪ ወሙስሊም

6. አጅራቸውን ልክ ሀጅ እና ኡምራ አድርገው እንደመጡ ማስመዝገብ ይችላሉ
አነስ ቢን ማሊክ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“የሱብሂን ሰላት በጀመአ የሰገደ ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ በዚክር ቁርአን በመቅራት እና መሰል ኢባዳዎች ሲሰራ ቆይቶ ሁለት ረካአን የሰገደ ከሀጅ እና ከኡምራ ጋር የሚስተካከል አጅርን አገኘ ሙሉ መሉ አጅርን ሸመተ” ቲርሚዚ

7. ዱንያ ላይ አከፋፍሎ የማይጨርሰውን ምርኮ ያገኛል
ኡመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በስተላለፉት ሀዲስ ላይ “ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይዞ በዘገበው ስለምርኮ እና ውርስ እያወሩ በነሩበት አጋጣሚ ብዙዎቹ በዚህ ምርኮ ላይ ፈጥነው ውሳኔን የሚወስኑ ፈጣኖች ሲሆኑ አንድ ምንም የለሌለው ሰው እንዲህ አላቸው ምን አይነት ነገር ላይ እንፍጠን ውሳኔያችንስ ምን ላይ ይሁን ስለበላጩ ምርኮ ከዚህ በሚበልጠው ሲላቸው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ “ልምከራችሁን? (ልጠቁማችሁን) ከህዝቦች በላይ ስለተደረጉት በምርኮ ላይ ፈጥነው ከሚሽቀዳደሙት?ህዝቦች ናቸው የሰላተ ሱብሂን ሰላት በጀምአ የተካፈሉት ናቸው ከዚያም ፀሀይ እስኪወጣ  አላህን የሚዘክሩ የሆኑት እነዚህ ናቸው ወደእውነተኛው ምርኮ በፍጥነት የሚሽቀዳደሙት።” ቲርሚዚ

8. ከሱብሂ ሰላት በፊት የሚገኘውን  ትልቅ እድል ይገጥማቸዋል
አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፈችው ሀዲስ ላይ  ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“ከሱብሂ በፊት የምትሰገደው ሁለት ረከአ ሰላት ዱንያና ዱንያ ከያዘቻቸው ነገሮች በሙሉ ትበልጥለታለች” ሙስሊም

9. ከእሳት ነፃ ይባላል በጀነትም ይበሰራል
ኡማራህ ቢን ሩወይባ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ “ፀሀይ ከመግባቷ በፊት እና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ሰላትን የሰገደ ሰው እሳት አያገኘውም” ይህም ማለት  “የሱብሂ እና የአስር ሰላቶች ናቸው።” ሙስሊም

10. በቂያማ ቀን (በትንሳኤ ቀን)ጌታውን ለማየት ይታደላል
ጀሪር ቢን አብድላህ በጀሊይ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላል “ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ተቀምጠን የለይለተ በድርን (ከረመዳን ለሊት) ጨረቃ በተመለክትን ጊዜ እንዲህ አሉ “ልክ ይችን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ማይት ትሻላችሁ እንግዲያውስ ፀሃይ ከመውጣቷ በፊት እና ከመግባቷ በፊት ያሉትን ሰላቶች እራሳችሁን አሸንፉ” ቡኻሪ እና ሙስሊም
ሙእሚን አላህን እውነት ብሎ ላመነ አንዱም ሀዲስ በቂ ነበር። የሰው ልጆች ግን ዝንጉና ረሺ በመሆናቸው በርካታ አስታዋሽ ሀዲሶች ሊቀርብ ችሏልና የሱብሂን ሰላት በጀምአ ለመስገድ ከምንግዜው በላይ መጠናከር ይኖርብናል።
መቼስ በቂያማ ቀን የአላህ ፊት ማየት የማይሻ የለም እና ይህን ለማግኘት በእነዚህ ሰላቶች መበራታት አለብን  እስቲ ይህን የቁርአን አንቀፅ አንብበው
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ
﴿٢٢﴾
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ
﴿٢٣﴾
“ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው። ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው።”
ይህን ከባድ ቀን እንደዋዛ ልታሳልፈው ነው ወንድሜ? ይህን ታላቅ ብስራት እንደቀልድ ልታባክነው አሰብክን? የተጫነብንን አብዋራ አራግፈን ከቸልተኝነት እና ከአላዋቂነት ለመንቃት ይህች ቁርአን። ይህች አለም ደሞ ጠፊ መሆኗን ባወቅን ጊዜ ምነኛ በባነንን ነበር!
ነፍስህ በዚያ በውድቅት ለሊት ተኛ ብላ በትወሰውስህ ሙአዚኑ እንዲህ ሲል ንቃ! “አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች” ብሎ ሲጠራክ ጌታክን ለማየት እንደምትቻኮል አትጠራጠር! ያን ጊዜ የሰላተ ሱብሂን ጥፍጥና ታገኝና ዱንያ አሉ በሚባሉ ማናቸውም ነገሮች የማትተካውን ደስታ እና ከአላህ ጋር ከባድ ፍቅርን ትላበሳለክ።

#share #ሼር
#join
👇👇👇
Https://www.tg-me.com/smithhk
ቁርአንን የመቅራት ትሩፋት (ክፍል 1)

ቁርአንን ማንበብ የትክክለኛና እውነተኛ ሙእሚኖች መገለጫ መሆኑ ጥርጥር የለውም። የአላህንም እዝነት ተላብሰው የሚገኙት እነዚሁ ሰዎች ናቸው። በዚህ ፅሁፍ ቁርአን የመቅራትን ትሩፋት የሚዘረዝሩ ማስረጃዎቸችን ለማየት እንሞክራለን።

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መልእክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቁርአንን ያነቡ ዘንድ እንዲህ በማለት ያዛቸዋል፦

وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا

“ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡” (ሙዘሚል 4)

ሀሰን ይህን ሲፈስሩት ግልፅ የሆነን (የተብራራን) ማንበብ አንብብ ማለት ነው ይላሉ። (ተፍሲር ጠበሪ 23/680)

አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንን በመቅራት ተግባር ላይ የታተሩ ሰዎችን ሲያወድስ እንዲህ ይላል።

إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَّن تَبُورَ لِيُوَفِّيَهُمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضْلِهِ ۚ إِنَّهُ غَفُورٌ شَكُورٌ
“እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በምስጢርም ኾነ በግልጽ የለገሱ፣ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው፣ ከችሮታውም ሊጨምርላቸው (ተስፋ ያደርጋሉ)፡፡ እርሱ በጣም መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡” (ፋጢር 19-30)

በሀዲስም በተመሳሳይ መልኩ ቁርአንን በማንበብ የሚገኘውን ክብርና ጥቅም በተመለከተ በርከት ባሉ አጋጣሚዎች ተውስተዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሁሉም በፊት ሊታወቅ የሚገባ አንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ። እሱም ይህን ድንቅ መፅሀፍ ማንበብ ጥቅሙ የሚጎላው ውስጡ ባዘለው መልእክትና አስተምህሮ የሰራንበት እንደሆነ ነው፡፡

ቁርአንን የማንበብ ፍሬዎች
1- የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመጥፎ ተምሳሌትነት ከገለጽዋቸው ሰዎች ከመሆን ያድናል።

ኢብን አባስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ ያ በውስጡ ከቁርአን አንዳች ነገር የሌለው (ምሳሌው) እንደ ወና ቤት ነው፡፡›› ቲርሚዚ

አቢ ሙሳ አል አሽዓሪይ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉልን ዘገባ ተወዳጁ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምእንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ እንደ ትርንጎ ነው፡፡ ትርንጎ መዓዛውም መልካም ጣዕሙም መልካም ነው፡፡ ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ምሳሌው እንደ ቴምር ነው፡፡ ቴምር መዓዛ ባይኖረውም ጥፍጥናው ግን ልዩ ነው፡፡ ሙናፊቅ ሆኖ ቁርአንን የሚቀራ ሰው ምሳሌው እንደ አሪቲ ነው፡፡ አሪቲ መዓዛው መልካም ቢመስልም ጣዕሙ ግን መራራ ነው፡፡ እንዲሁም ሙናፊቅ ሆኖ ቁርአንን የማይቀራ ሰው ምሳሌው እንደ የቅል ፍሬ ነው፡፡ የቅል ፍሬ መዓዛም የለውም ጣዕሙም መራራ ነው፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም

2- ቁርአንን በመቅራት ላይ የዘወተረ ሰው ደጋግ ሰዎች ከሚቀኑባቸው ተርታ ይሰላፋል

ከኢብን ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በሁለት ነገሮች ካልሆነ በስተቀር ቅናት የለም (አይፈቀድም)፡፡ (እነሱም) አላህ የቁርአን እውቀትን ሰጥቶት ቀን ከሌት በሱ የቆመበት (ሰላት የሰገደበት) ግለሰብ እንዲሁም አላህ ገንዘብ ሰጥቶት ቀን ከሌት ከሚመፀውት›› ቡኻሪና ሙስሊም

እዚህ ቦታ ላይ የተጠቀሰው ‹‹ቅናት›› ወንድምህ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር ከሱ አንዳች ሳይቀነስ አልያም እንዲወገድበት ሳትከጅል ላንተም እንዲኖርህ መመኘት ማለት ነው፡፡

3- ቁርአንን መቅራት በዚህኛውም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ልቅናን የመጎናፀፊያ ምክንያት ነው፡፡

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል በማለት ዘግበዋል፡-

‹‹አላህ በዚህ መፅሀፍ ህዝቦችን ከፍ ያደርግበታል ሌሎቹን ደግሞ ያዋርድበታል፡፡›› ሙስሊም

4- ቁርአንን መቅራት መጀመርያውም መጨረሻውም በረከት ነው

አቡዘር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይለናል፡-

‹‹አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ምከሩኝ አልኳቸው፡፡ እንዲህም አሉኝ ‹አላህን በመፍራት ላይ አደራ እልሃለሁ ምክንየቱም አላህን መፍራት የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ነውና፡፡› እኔም አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ይጨምሩልኝ አልኳቸው፡፡ ‹ቁርአንን በመቅራት አደራ፤ እሱ በምድር ላይ ብርሀን በሰማይ ላይም መታወሻ ይሆንልሃልና፡፡› አሉኝ፡፡›› ኢብኑ ሂባን

‹‹በምድር ላይ ብርሀን ይሆንልሃል›› የሚለው ሀረግ ሁለት ትርጓሜዎች አሉት። አንደኛው ቁርአንን የሚያነብና በተግባር የሚያውል ሰው ከእንስሳዊ ማንነት ይላቀቃል ማለት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “መቀናት” ማለትም ወደቀጥተኛው መንገድ መመራት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አላህም እንዲህ ሲል ይህንን ሀሳብ ያፀናዋል፡-

قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ

“ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡” (አል ማዒዳ 15)

ኢብን ዓባስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹የቁርአንን ቅን መስመር የተከተለ ሰው በዚህ ዓለም እንደማይጠምና በመጪውም ዓለም እድለ ቢስ እንደማይሆን አላህ ቃል ገብቷል፡፡›› በማስከተልም ተከታዩን የቁርአን አንቀፅ አነበቡ፡-

فَمَنِ اتَّبَعَ هُدَايَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ

“መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡” (ጣሃ 123)

ኢብኑ አቢ ሸይባ ዘግበውታል፡፡

‹‹በሰማይ ላይ መታወሻ ይሆንሀል›› የሚለው ሀረግ ሀሳቡ በመጪው ዓለም የጌታችን እዝነት፣ ምልጃና ጀነትን መገጠም ሊሆን ይችላል። በሌላ መልኩ ደግሞ አል መናዊ አላህ ይዘንላቸውና እንዳሉት ‹‹የሰማይ ባልደረቦች መላእክት ናቸው፡፡ እነሱም እያነበብከው ባለኸው ቁርአን ላይ ፅናትንና ዘውታሪነትን ላንተ ይለግስህ ዘንድ እርስ በርስ አላህን ይለምናሉ፡፡›› የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በግልፅ እንደነገሩን አላህ ያስታውሳሀል።

5- ቁርአንን ማንበብ ከዝህች ዓለምና በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ ይበልጣል፡፡

ዑቅባ ቢን ዐሚር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላሉ፡-

‹‹የአላህ መልእክተኛሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምከእለታት በአንዱ ቀን ተሰብስበን ወደ ተቀመጥንበት መጡና እንዲህ አሉን፡- ‹ከናንተ ውስጥ ወደ ሜዳ ወጥቶ አልያም ወደ ኮረብታዎች ሄዶ በየእለቱ ባለሻኛ ግመል ቢሰጠውና ያለ አንዳች ወንጀልና ዝምድናን መቁረጥ ቢመለስ የሚወድ አለን;› ብለው ጠየቁ። እኛም ፡፡ ብለን መለስን፡፡ እሳቸውም ‹እንግዲያውስ አንዳችሁ ወደ መስጂድ ማልዶ በመሄድ ከአላህ ቃል ሁለት አንቀፆችን ቢያስተምር አልያም ቢቀራ ለሱ ከሁለት ግመሎች የበለጠ ነው፡፡ ሶስት አንቀፆችንም ቢያስተምር ከሶስት ይበልጥለታል፡፡ አራትም አንቀፅ ቢሆን እንደዛው፡፡ ባጠቃላይ ባስተማረውና በቀራው አንቀፅ ልክ ከግመሎቹ ይበልጣል፡፡› አሉን፡፡››ሙስሊም

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ሰለዋት እናብዛ‼️
🌴🌴🌴

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇

🌴💥🕋🌴💥🕋

قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"


"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"
#share
#Join
@smithhk
በ ጁምዐ ቀን ዱአ ተቀባይነት ሚሆንበት
ወቅት(ጊዜ) መኖርዋን አሽረፈል ኸልቅ
ነግረውናል:-« በ ጁምዐ ቀን አንዲት ጊዜ አለች በዚህች ወቅት አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀ የጠየቀው ነገር ሀራም እስካልሆነ ድረስ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል»ወቅቱም በሌላ ዘገባ«በቀኑ መጨረሻ» ማለታቸው ተዘግቧል።
🦋الهم صلى وسلم على نبينا محمد🦋

ከምንጠቀምበት ያድርገን🙏

መልካም ጁምዐ ተመኘን🌸

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
በአላህ ላይ ጥሩ ግምት መኖር

🍃ዩሱፍ አለይሂ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ስለነበረው አላህ አክብሮት ከታሰረበት አውጥቶ የግብፅ ንጉስ አደረገው ።

🍃ዩኑስ አለይሂ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ስለነበረው ከአሳ ነባሪው ሆድ ወጥቶ ሕይወቱን ቀጠለ።

🍃ሙሳ አለይሂ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ስለነበረው ከፊርአውንና ከበደሉ አላህ እሱንና ተከታዩቹን አዳናቸው ።

🍃መርየም አለይሀ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ሰለነበራት ከዘመኗ ከነበሩ ሴቶች ሁላ በላጭ ሁና በጥብቅነትና በመልካምነት ምሳሌ እንድትሆን አላህ አደረጋት ።

🍃ዘከሪያ አለይሂ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ስለነበረው ባለቤቱ የማትወልድ አሮጊት ሁና ነቢይ የሆነ ልጅ አላህ ሰጠው ።

🍃ኢብራሂም አለይሂ አሰላም በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ስለነበረው እንድታቃጥለው የተዘጋጀችው እሳት ለእሱ ሰላም ሆነችለት ።

🍃ነብያችን ﷺ በአላህ ጥሩ ግምት ስለነበራቸው ከፍጡራኖች በአጠቃላይ አላህ ዘንድ በላጭ ሊሆኑ ቻሉ።

🥀በአላህ ላይ መልካም ግምት ይኑረን … እሱም አላህ በገመትነው ቦታ ይገኝልናል ።

☆ በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ማሳደር ማለት መልካምን ነገር ከአላህ መጠበቅ ማለት ነው ። አላህ ለእነዚህ መልካም ባሪያዎቹ በገመቱት ልክ ተገኝቶላቸዋል ።

√ እኛስ በጌታችን አላህ ያለን ግምት ምንድን ነው ??! ይህን ጥያቄ በቁርዓን ላይ እናገኘዋለን …

{ فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ }

« በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?»

【 አል- ሳፋት 87】

⇢ ኢብኑ መስኡድ አላህ መልካም ስራውን ይውደድላትና እንዲህ ይላል ፦

" በአላህ እምላለሁ አንድ ሰው በአላህ ላይ የሆነ ግምትን አይገምትም ያ የገመተውን ነገር ቢሰጠው እንጂ "

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🌑የጀሀነም በሮች 7 ናቸው።
▰▰▰▰▰▰▰▰
1ኛው የጀሀነም በር (ሀነም) ይባላል፣
ሀነም ስያሜውን ያገኘው ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ ስለሚቃጠሉበት እና ስጋዎችን ስለሚትበላ ነው በሌሎች
የጀሀነም በሮች አንጻር አነስተኛ ቅጣት የሚስተናገድበት ነው።

2ኛው የጀሀነም በር (ለዛ) ይባላል፣
ለዛ ሁለት እጆችንና እግሮች በመብላት ትታወቃለች ለተውሂድ ጀርባ የሰጡ ሰዎችና የመልእክተኛውን ጥሪ
ያልተቀበሉ ሰዎች መኖሪያ ነች

3ኛው የጀሀነም በር (ሰቀር ) ይባላል፣ ሰቀር ያገኘውን ሁሉ አያስቀርም ወደ ብናኝ አመድነት ይቀይራል

4ኛው የጀሀነም በር (ሁጠማ ) ይባላል ።
ሁጥማ አጥንት፣ ከአጥንት በማጣበቅ ትታወቃለች ልብ ውስጥ
ዘልቆ የሚገባ ቅጣት የሚስተናገድባት የጀሀነም በር ነች በውስጧ የገቡ ይረዱ ዘንድ ደም፣በደም በሆነ እንባ የታጀበ
ለቅሶ ያለቅሳሉ ነገር ግን የሚረዳቸው አያገኙም።

5ኛው የጀሀነም በር ( ጀሂም) ይባላል፣
ጀሂም በትላልቅ የእሳት ፍሞች የተሞልቷል በጀሂም ውስጥ ያለው
አንዱፍም ትልቀቱ ብቻ ይቺን አለም ያክላል።

6ኛው የጀሀነም በር (ሰኢር) ይባላል፣
በሰኢር ውስጥ "300" ( ሶስት መቶ ) የእሳት ህንጻወች አሉ፣በያንዳዱ ህንጻዎች "300" (ሶስት መቶ) ቤቶች አሉ። በያንዳዱ ክፍል ውስጥ "300" (ሶስት መቶ) የቅጣት አይነቶች ይስተናገዱበታል
በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ እባቦችና ጊንጦች በብዛት ይገኙበታል።

7ኛው (ሀዊያ ይባላል)፣ ሀዊያ ውስጥ የገባ ዝንትአለም አይወጣም!!! ሀዊያ በውስጧ ሀባባ የተባለ እንደ ወንዝ ጅረት የሚፈስ እሳት የሆነ ወንዝ አለ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስድስትቱ የጀሀነም በሮች ሁሉ ሳይቀሩ ከዚህ ወንዝ አላህ ይጠብቃቸው ዘንድ ይማጸናሉ #ሰኡዳ የተባለ ተራራ በውስጧ የአላህ ጠላቶች እጆቻቸውና እግሮቻቸው ከፊቶቻቸው ጋር ታስሮ ከተራራው ጫፍ ላይ በአፍጡማቸው እንዲደፉ ይደረጋሉ !

የጀሀነም ዘበኞችም እነዚህን የአላህ ጠላቶች በከፍተኛ ሁኔታ ያሰቃዮቸዋል።

አላህ ከሁሉም የጀሀነም በሮች ቅጣት ይጠብቀን 🤲

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/05 20:11:34
Back to Top
HTML Embed Code: