Telegram Web Link
🔉 በነፃ

በቤትዎ ሆነው ኪታብ መቅራት ኢልምን መማር ይፈልጋሉ?
በ ሸህ ሰዒድ አሊ ሀቢብ ከ ሰኞ እስከ እሁድ ከ ጁመዐ ውጪ ኪታቦች በመቀራት ላይ ይገኛሉ ከእርስዎ የሚጠበቀው ቻናላችንን መቀላለቀል ብቻ ነው አሁኑኑ JOIN ብለው በ ቀጥታ ስርጭት ( LIVE ) ይከታተሉ
በ አካል መቅራት የምትፈልጉ አዲስ አበባ ቤተል መስጂድ
ሰአት ከ መግሪብ እስከ ኢሻ
📚 እስከ አሁን የተቀሩ ኪታቦች
📖አሱለል ፊቂህ
📖ሰፊና
📖ሹጅዐ
📖ባፈድል
📖ኡምደቱ ሳሊክ አሁን በመቀራት ላይ ያለ እና ሌሎችም
አሁኑኑ ይቀላቀሉ

https://www.tg-me.com/Al_Usmani
ሰለዋት እናብዛ‼️
🌴🌴🌴

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇

🌴💥🕋🌴💥🕋

قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"


"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"
#share
#Join
@smithhk
#የጁምአ_ቀን

ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም )እንዲህ ብለዋል ፡-
አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም

1) አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣

2) አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣

3) አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣

4) ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣

5) በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ።

የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:910)

[የጁምአ ቀን ሱናወች]

~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ

@smithhk
ተጨማሪ የቁርአን አንቀፆችን በቢላል ደርባሊ አቀራር ለማዳመጥ ከፈለጉ ከታች ያሉትን ሊንኮች በመንካት ያገኛሉ :: ሼር አድርገው ባንተ ምክንያት በሰሙት ሰዎች ቁጥር አጅር ታገኛለህ አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን ወንጀላችንንም ይማረን አሚንን

https://www.tg-me.com/BilalDarbali

https://www.tg-me.com/jgsrje

https://www.tg-me.com/belalaldrbale1

Https://www.tg-me.com/bilal_darbalii

🌼 اللهم بارك لنا في شعبان وبلغنا رمضان 🌼

#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
እርግጥ ነው የረመዳን ወር ሲገባ እመስጂዶች ላይ አዳዲስ ፊቶች ለጀመዐ ሰላተረ ይመጣሉ። ግና በአላህ! ረመዳን መጣላቹ እያልን አናሸማቅቃቸው። ሰንቀዋት የመጡትን ተስፋቸውን አንቀማቸው። አንግበው የመጡትን ሞራላቸውንም አንከሽክሽባቸው።

   መልካም ፈገግታ ሰደቃ ነውና ፈገግ ብለን እንቀበላቸው። አህለን ወመርሃበን ፤ እንኳን ደህና መጣቹልን የአላህ ቤት እናንተን ናፍቃ ነበር ብለን እንቀፋቸው። ከምን አይነት ኸይር ነገር እርቀን ነበር ብለው እስኪሰማቸው ድረስ እናቅርባቸው።

   በፍቅር ተንከባክበን መስጂድ ውስጥ ያለውን ሰላም፣ ፍቅር እና ደስታ እንዲያወቁ ያረግን ጊዜ ፤ መስጅድ ለመምጣት ረመዳንን አይጠባበቁም ፤ አወለ ሰፍ ሙአዚኑን ቀድመው የሚገኙ ቢሆን እንጂ።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
ረመዳን ሙባረክ


ይቅርታ!
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አሊያም በቸልተኝነት፣ በድርጊት ፣በምግባር ወይንም በቃላት ያስቀየምኳችሁ ካላችሁ ሁላችሁንም ይቅርታ እጠይቃለሁ። አፈይቱ' ሊላህ።
የአላህን ፀጋ ምህረትና በረከት የምናገኝበት የረመዳን የፆም ወር እንዲሆንልን እመኛለሁ

"ረመዳን ሙባረክ" 
رياض الصّالحين _1
الشيخ أول بن أحمد الخميسي
📌درس كتاب جــديـــد
📌 አዲስ የኪታብ ደርስ

📚 كتاب رياض الصّالحين للإمام أبي زكريا يحي بن شرف النووي الدّمشقي «رحمه الله تعالى»
📚ኪታብ ሪያዱ አስ-ሷሊሂን
የኢማም አቢ ዘከሪያ የህያ ቢን ሸረፍ አን-ነወዊይ አድ-ዲመሽቂይ «ረሒመሁሏህ»
الدرس الأول
ክፍል 1

🎙 الشيخ أول بن أحمد الخميسي «حفظه الله»

🎙 በሸይኽ አወል አህመድ አል ከሚሴ


#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
رياض الصّالحين _2
الشيخ أول بن أحمد الخميسي
📚 كتاب رياض الصّالحين للإمام أبي زكريا يحي بن شرف النووي الدّمشقي «رحمه الله تعالى»
📚ኪታብ ሪያዱ አስ-ሷሊሂን
የኢማም አቢ ዘከሪያ የህያ ቢን ሸረፍ አን-ነወዊይ አድ-ዲመሽቂይ «ረሒመሁሏህ»
الدرس الثّاني
ክፍል 2

🎙 الشيخ أول بن أحمد الخميسي «حفظه الله»

🎙 በሸይኽ አወል አህመድ አል ከሚሴ «ሐፊዘሁሏህ»


#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ተወዳጁ ቃሪዕ ዓፊፍ ሙሀመድ ታጅ ዛሬ(08/08/15) በተቅዋ መስጂድ የተራዊህ ሰላትን ያሰግዳል።
"አቧራ የነካው ልብሴ አላህ ዘንድ ምስክር ይሆነኝ ዘንድ ሳላራግፍ አጣጥፌ ከቁምሳጥኔ አኖረዋለሁ"

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

ስካቫተሩ በፀጥታ ኃይሎች ታጅቦ ከመስጂዱ ፊት ለፊት ቆሟል። ህዝቡ ጥጋ ጥጉን ይዞ ይታዘባል። መዳፋቸውን አፋቸው ላይ በሻርብ ሸፍነው በሀዘን የምፀት ድምፃቸውን የሚያሰሙ እናቶች ይስተዋላሉ። "አይ ጊዜ ...." እያሉ ያላዝናሉ። ብሶት፣ ቁጭት፣ መገፋት፣ ህመምና ብቸኝነት ከፊቶች ላይ ይነበባሉ። ክስተቱን በዓይን መመልከት በእጅጉ ያማል ውስጥን እየናጠ ሐዘንን ያላብሳል። በስሜት አጡዞ የሚሆኑትን ያሳጣል ይህን የውርደት ጥግ ከማየት ፊትን ዘወር አሊያም በለቅሶ ቦታውን ለቆ መሄድ ይሻላል ብዬ ብዞር ከኋላዬ ከዘራቸውን ተደግፈው የቆሙት አዛውንት በድንገት ትኩረቴን ሳቡት። ፀጉራቸው ሸብቶ ግንባራቸው ተሸብሽቧል። ከአንድ ፖሊስ ጋር ግብ ግብ ፈጥረው ሲገፈትራቸው ወድቀው ልብሳቸው አቧራ ቅሟል። ከዓይናቸው ዕንባ ኩልል ብሎ ይፈሳል።

ድክም ባለ ጉልበታቸው ከዘራቸውን ተደግፈው ከፍርስራሹ ጥግ አረፍ አሉ። እኔም ከጎናቸው ተቀመጥኩ። በተሰበረ ልብ አንገታቸውን ወደመሬት አቀረቀሩ። ዓይናችን እንባ እንዳቀረረ እርስ በርስ ተያየን "ሙስሊሞች ከአንደሉስ ተባረው መስጂዶች ወደ ቤተክርስቲያንነት የመቀየራቸውን ታሪክ ሰምተህ ይሆን?" አሉኝና ወደሰማዩ አንጋጠጡ።

እንባ ባደበዘዘው እይታ ሰማዩን እየቃኘሁ የተሰማኝን ሁሉ አወራሁ። ታሪኮችን ከወቅቱ ጋር እያዋጀሁ የሙስሊሞችን ሁኔታ አወጋሁ። ከእስልምናው ስንርቅ አላህ ፍርሀትን በልባችን አንግሶ በተታሮች እንዴት እንደቀጣን አስታወስኩ
"በወቅቱ የዓባሲያው ኸሊፋ የሙስሊሙን ኡማ ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በጥቅማጥቅም ተጠምደው የየራሳቸውን ስልጣን ኃብትና ዝና ክብርና ስም ለማስጠበቅ እርስ በርስ የሚናቆሩ ስለነበሩ የሙስሊሙን ኡማ ኃይልና ክብር አዳክመው በሆድ ውስጥ ያለ ሽል ሳይቀር በጩቤ እየተሞሸለቀ ሲገደል ግድ አይሰጣቸውም ነበር ልክ እንደዛሬው" አልኳቸው።

እንግዲያውስ አንድ ታሪክ ልጨምርልህ በማለት ንግግራቸውን ጀመሩ። በዕንባ የራሰውን ዓይናቸውን እየጠረጉ ታላቁ ሙአሪኽ ኢብኑ ከሲር አልቢዳያ ወንኒሀያ በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ትርክቱን እንዲህ ዘግበውታል
"የኢስላም ጠላቶች ባግዳድን ከበው በቀስት እያስወነጨፉ ባለበት ወቅት አንድ ቀስት በመስኮት በኩል ሾልኮ እየደነሰች ኸሊፋውን በማዝናናት ላይ የነበረችን ዐረፋ የተባለች ሴት ባሪያን ገደለ" አሉኝና ተከዙ። ከዚያም አስከትለው ለምን እንደመጣሁ ልንገርህ አሉኝ። ለማወቅ በእጅጉ እየጓጓሁ አይኖቼን አፈጠጥኩ።

"ወደዚህ ቦታ ያመጣኝን ታሪክ ላካፍልህ አሉኝ አቀማመጣቸውን እያስተካከሉ
"ከቀድሞ ደጋግ ሰዎች መካከል አንዱ በግዞት ተጠፍረው በታሰሩበት እስር ቤት ውስጥ የአዛንን ድምፅ ሲሰሙ ወደ እስር ቤቱ በር ይራመዳሉ። ጠባቂው በያዘው ዱላ ቸብ አድርጎ ሲመልሳቸው ጌታዬ ሆይ! ለአዛን ጥሪህ ምላሽ ሰጥቼ ከጀመዓ ሰላት መሐል እንዳልጣድ በአንባገነኖች ተከልክያለሁ። ከቤትህ ለመገኘት የአቅሜን ጥሬያለሁ የቻልኩትን አድርጌያለሁ ምስክር ሁነኝ እያሉ ክፍላቸው ገብተው ለብቻቸው ይሰግዳሉ። ይህ የሁልጊዜ ተግባራቸው ነው። እኔም ዛሬ እዚህ ተገኝቼ ለምን ታፈርሳላችሁ መስጂዳችን ህልውናችን ናቸው ብዬ ስጠይቅ በያዙት ዱላ እየገረፉ ገና ምን አይተህ እያሉ ሲገፈትሩም ከመሬቱ ወደቅኩ ጌታዬ ሆይ! መስጂድህ እንዳይፈርስ የአቅሜን ታግያለሁ ምስክር ሁነኝ እያልኩ ለአላህ ተናገርኩ። አቧራ የነካው ልብሴ አላህ ዘንድ ምስክር ይሆነኝ ዘንድ ሳላራግፍ አጣጥፌ ከቁምሳጥኔ አኖረዋለሁ" አሉኝና እጃቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው "ያፈረሱትን ሁሉ አፍርሳቸው" እያሉ ዱዓ ሲያደርጉ እኔም በሁኔታው እየተገረምኩ "አሚን" እልኩ.....

እንደ ሁኔታው ይቀጥላል
የመስጂድ ሚንበሮች ስለኛ ተርገፈገፉ። ዓለም ዓቀፍ ዳዒዎች ደም ስራቸው ተገታትሮ በቁጭት ስለሐበሻ ሙስሊሞች ለፈፉ። ከታዋቂው ዳዒ መህሙድ አልሀሰናት እስከ ጀምስ ሁሉም ልሳናቸው ስለኢትዮጵያ ሆነ።

"ወንድሞቻችሁ መስጂዶቻቸው ፈርሰውባቸው በመርዛማ ኬሚካል ጥይት ተመተው ከመሬት ተዘረሩ" እያሉ እንባ ተናነቃቸው። ጅማታቸው ተገታትሮ ንዴትና ቁጭት ልባቸውን ደለቃቸው። ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ያሉ ታዋቂ ሰዎች በአካልም ሆነ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ለማያውቁን ለኛ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ስለመደፈራችን አነቡልን።

አዎ ከጀሰዲን ዋሂድ ይሉሀል ይህ ነው። አንደኛው አካል ሲታመም መላው የሰውነት ክፍል በትኩሳትና በእንቅልፍ እጦት ይሰቃያል። የሆነውም ይህ ነው።

በአስፈሪ ጥይት እሩምታ መሀል በሞት አፋፍ ላይ አይተውት ጥለውት ሳይሸሹ ከወደቀበት አንስተው ሸሃዳ በል እያሉ የሚያስታውሱ ወንድሞች የጀሰዲን ዋሂድ አስኳሎች ነበሩ። አላህ አንድነታችንን ያጠንክርልን

Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ከጠቢባን አንደበት


🔜 « የአንተ መስተካከያና መታነጫ ዛሬ እንጅ ነገማ የፍፃሜህ ዕለት ሊሆን ይችላል ። »

🔜 « ራስህን ድል ሳታደርግ በሌላው ላይ አትዝመት ።»

🔜 « መታገስ ለራስ ጊዜ መስጠት ነው ። »


🔜 « ንደት ለችግሮች መፍትሔ ሳይሆን መንስኤ ነው ። »

🔜 « የውሸት እየኖርን የእውነት እንሞታለን ። »

🔜 « ደስታ ዱርዬ አይደለም ፤ ሰዎች ግን ዱርዬ እየመሰላቸው በየ መጠጥ ቤቱ ይፈልጉታል ። »

🔜 « ጠላቶችህን ባትወዳቸው እንኳን አድንቃቸው ፤ ስህተትህን ለመመልከት የመጀመሪያዎቹ ናቸውና ። »

🔜 « ጠላቶችህ ወደ አንተ ቢገሰግሱ ወደ ኋላ አታፈግፍግ ወደነሱም አትንደርደር ባለህበት ሆነህ ተዘጋጅና ጠብቃቸው ። »

🔜 « ብዙ ሰዎች ከአድማስ ማዶ የማይታያቸውን ቀን ይናፍቃሉ ። ዛሬን የሚንቋት በእጃቸው ስለገባች ነው ። »

🔜 « ዘልዓለም ለመኖር ዕድሉ ለሌላት ህይወትህ ሰላምን አትንፈጋት ። »

🔜 « ለሌሎች ይቅርታ የማያደርግ እራሱ የሚሸጋገርበትን ድልድይ የሚያፈርስ ነው ። »

🔜 « ቁጠኛ ጓደኛ የተረጋጋ ጠላት ነው ። »

🔜 « የቁጣ መድሀኒት ዝምታ ነው ። »

🔜 « ከመዝለልህ በፊት አስተውል ። »

🔜 « ገንዘብ መናገር ሲጀምር እውነት ዝም ትላለች ። »

🔜 « ትዕግስት ማለት ችግርህን ለአሏህ መንገር ማለት ነው ። »

🔜 « እምነት ማለት ግማሹ ትዕግስት ሲሆን ግማሹ ምስጋና ነው ።

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

በደልን አሜን ብላችሁ በመቀበል የበታችነትን አትለማመዱ
ታላቁ ሊቢያዊው ሙጃሂድ/ዑመር አል ሙኽታር


ወደ ሱዳን ከሚሄደው ቅፍለት ጋር አብረው ታላቁ ሊቢያዊው ሙጃሂድ/ዑመር አል ሙኽታር አየተጎዙ ሳለ በተለምዶ አንበሳ መንገደኞችን የሚያድንበት ቦታ ደረሱ ። አካባቢውን ጠንቅቀው የሚያውቁት:- " ከግመሎቻችን አንደኛውን አርደን ለአንበሳው ካልገበርን ተበልተን ማለቃችን ነው! " በማለት አንዱን ግመል እንረድ የሚል ሃሳብ አቀረቡ። ዑመር አል ሙኽታር ግን አልተዋጠላቸውም ፤በጽኑ ተቃወሙ። " በእኛ ላይ ድንበር አልፎ ለመጣ በሙሉ ማባበያ ማቅረብ የበታችነትን የሚያለማምድ ክፉ በሽታ ነው። በደልን አሜን ብላችሁ በመቀበል የበታችነትን አትለማመዱ። አንበሳውን ገድለን ማለፍ አለብን!" አሉ በጀግንነት።

እንደተለመደው አንበሳው ድንገት ብቅ አለ። መንገደኞች ብርክ ብርክ አላቸው። "የኔን ግመል ለመሰዋት ዝግጁ ነኝ። አንበሳውን አትተናኮሉት። ዋናው መትረፋችን ነው!" አለ አንዱ መንገደኛ ። ዑመር አልሙኽታር የሰውየውን ተማጽኖ ከቁብ ሳይቆጥሩ መሳሪያቸውን ወደ አንበሳው አነጣጥረው ተኮሱ። አንበሳው ግን አልሞተም ፤ ወልገድ ወልገድ እያለ ወደ መንገደኞች መገስገሱን ቀጠለ። ሰዉ በፍርሀት ተውጧል ዑመር ግን እጅ አልሰጡም። አንበሳውን ሲደግሙት ተዘረገፈ ። ሞተም። ዑመር አል ሙኽታር የአንበሳውን ቆዳ በመግፈፍ መንገደኞችን ከፍርሀት ቆፈን አላቀቋቸው!።

በዘመኑ ይህ ታላቅ ገድል የየመጃሊሱ መነጋገርያ ሆኖ ነበር። ሙሐመድ አል ጠይብ አል አሽሀብ ዑመርን "እንዴት ድፍረቱ መጣልህ?" ብሎ ለሰነዘረው ጥያቄ ከዑመር የተሰጠው ምላሽ ይህችን የቁርአን አንቀጽ በመጥቀስ ነበር :-

"فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمْ ۚ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ ۚ "
/ الأنفال:١٩/

"አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ "
/አል አንፋል:19/

ዑመር አልሙኽታር ጀግንነት ሲደመር ጽኑ ኢማን እና ተወኩል የእውነተኛ ሙስሊም መገለጫ መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከሩ ተላቅ ሰው ነበሩ።-ረሂመሁላህ-

ምንጭ: -
1- الأشهب ،عمر المختار
2- الصلابي، عمر المختار نشأته أعماله واستشهاده

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
Forwarded from Khalid Abu abdurahman
¶ሉቅማን የቁርአንና የተጅዊድ ማእከል

     ማእከላችን በኦን- ላይን ከ አሊፍ ጀምሮ እስከ
ተጅዊድ ትምህርት ድረስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል። እርሶም ፈጥነው ይመዝገቡና ትልቁን የቁርዐን እውቀት ይሸምቱ።

    ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች
    
    ነዝር ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር
    
     የተሟላ የተጅዊድ ትምህርት
    
    ቁርዐን ሂፍዝ (ፈተና አለው)

  𒊹︎︎︎ የቁርዐን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ

አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝ ጋር

↪️በቴሌግራም

↪️በዙም አፕልኬሽን እንዲሁም

↪️በዋትሳፕ

  𒊹︎︎︎ የቁርአን ቂረአት የሚሰጥበት ጊዜ

↪️ በሳምንት 5 ቀን

↪️ ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ ለሚመቻቸው ሰፋ ያለ
       ሰዓት በመስጠት እናስቀራለን።

📜 ለመመዝገብ እነዚህን መንገዶች ይጠቀሙ
                                 ☞︎︎︎  +251922094434
                                
  እንዲሁም በቴሌግራም መመዝገብ ለምትፈልጉ
     @Luqmanmemzgebiya2
     @Luqmanmemzgebiya3
 
©ሉቅማን የቁርአንና የተጅዊድ ማዕከል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/luqman1111111
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ሶላት የፍቅር ቦታ !
❥❥❥❥❥❥❥❥❥❥
    አይጥ ግመልን ወደደ ። ጓደኝነትም መሠረቱ ። አይጥም የግመሉን ልጓም በመያዝ በእንግድነት ወደ ቤቱ ወሰደው ።  አይጥ መኖርያው ግመሉን ሊያስገባ እንደማይችል ሲረዳ አዘነ፣ እፍረትም ተሰማው...
ግመልም እንዲህ አለው ...
" በልክህ ውደድ ።
አሊያም በወደድከው ልክ ቤትህን አዘጋጅ !!
    ኢብኑል ቀይም ይህን አንስተው አለቀሱና እንዲህ አሉ ...
" አንተ ሰጋጅ ሆይ !
ሰላትህን የምትሰግድለትን ጌታ የሚመጥን አድርገህ ስገድ   ወይም በሰላትህ ልክ ምትገዛውን ጌታ ፈልግ  !"
ኢብኑል ጀውዚ ...
" አንዲት አሮጊት ከዙህር ወቅት በፊት ዉዱእ ስታደርግ ያዩአት ሰዎች ዙህር አላዘነም ቢሏት...
" እኔኮ ሳይጠራኝ ነው ወደሱ ምሄደው አለች " አሉ !
#ፍቅር ጥሪ አይጠብቅም!
ጁምዐ
ሱረቱል ከህፍ
ሰሉ አለ ነቢ
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢዪና ሙሀመድ

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/04 15:46:48
Back to Top
HTML Embed Code: