Telegram Web Link
#ተውሂድን ማጥራት ድግምትንና እና ምቀኝነትን መመከት ከሚቻልባቸዉ መንገዶች ታላቁና ዋነኛው ነው!
==================================
ታላቁ አሊም ኢብኑልቀይም “በዳዒእ አሰናዒእ” በተሰኘው መጽሀፋቸው የምቀኛን “ሀሲድ” ጉዳት መመከት የሚቻልባቸዉ አስር መንገዶች እንዳሉ በመጥቀስ ዘጥኙን ካብራሩ በኋላ እንዲህ አሉ፡-

አስረኛው መንገድ፡- ይህ ሌሎቹን መንገዶች ሁሉ የሚያካትት ሲሆን የሁሉም መከላከያ መንገዶች መሽከርከሪያ ዛቢያ ነው። ይኸዉም የአላህን ብቸኝነት ተውሂድን ማጥራት እንዲሁም ሰበቦችን አስመልክቶ፤ ሰበቦችን ወዳስገኘው አሸናፊና ጥበበኛ ፈጣሪ በሀሳብ መንጎድ ነው። እነዚህ መዳረሻዎች ልክ እንደንፋስ ጎዞ መሆናቸዉን ልናውቅ ይገባል። ንፋስ በፈጠረዉና በሚያንቀሳቅሰው ፈጣሪው እጅ ነው። በእርሱ ፍቃድ ቢሆን እንጂ ሊጠቅምም ሊጎዳም አይችልም። ባሪያውን በንፋስ ተጠቃሚ የሚያደርገው ከእርሱም የንፋስን ጉዳት የሚያስወግደው አላህ ብቻ ነው። ከእርሱ ሌላ ማንም ይህንን ሊያደርግ አይችልም፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-
قال تعالى : ( وإن يمسسك الله بضر فلا كاشف له إلا هو وإن يردك بخير فلا راد لفضله) يونس 107

‹‹አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፤ በጐንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡›› (ዩኑስ 1ዐ7)

وقال النبي صلى الله عليه وسلم لعبد الله بن عباس رضي الله عنهما : ( واعلم أن الأمة لو اجتمعوا على أن ينفعوك لم ينفعوك إلا بشيء كتبه الله لك ، ولو اجتمعوا على أن يضروك لم يضروك إلا بشيء كتبه الله عليك ) . صحيح

ነብያችን (صلى الله عليه وسلم) ለአብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ አሉ፡- “ሰዎች ሁሉ አንተን በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ፈልገው ቢሰባሰቡ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር እንጂ ሊጠቅሙህ እንደማይችሉ እወቅ፤ ሁላቸውም በአንድ ነገር ሊጐዱህ አስበው ቢሰባሰቡ አላህ በአንተ ላይ በፃፈው ነገር እንጂ ሊጐዱህ እንደማይችሉ እወቅ፡፡”

فإذا جرد العبد التوحيد فقد خرج من قلبه خوف ما سواه وكان عدوه أهون عليه من أن يخافه مع الله تعالى، بل يفرد الله بالمخافة وقد أمنه منه وخرج من قلبه اهتمامه به واشتغاله به وفكره فيه وتجرد الله محبة وخشية وإنابة وتوكلا واشتغالا به عن غيره فيرى أن إعماله فكره في أمر عدوه وخوفه منه واشتغاله به من نقص توحيده.

አንድ የአላህን ባሪያ የአላህን ብቸኝነት “ተዉሂድ” ያጠራ ሰው ከእርሱ ውጪ ያለ ፍራቻ ከልቡ ይወገዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ጠላቱ ከአላህ ጋር መፍራት እጅጉን እንደማይገባው ይረዳል፡፡ እርሱን ከአላህ ጋር ተጋሪ አድርጐ ከመፍራት ይልቅ አላህን ብቻ ይፈራል፡፡ አላህም ከጠላቱ ሰላም ያደርገዋል፡፡ ከልቡ ውስጥ ስለ ጠላቱ ማሰብና መጠበብ ስለ እሱም ማስተንተን ሁሉ ይወገድበታል፡፡ በዚህም ጊዜ አላህን በብቸኝነት በማክበር፣ በመፍራት፣ ወደእርሱ በመመለስ እና በእርሱ በመመካት ከሌላውን ሁሉ ትቶ በእርሱ ብቻ ይጠመዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ሃሳቡን በጠላቱ ጉዳይ፤ እርሱን በመፍራትና በእርሱ በመጠመዱም ኢማኑ ጉድለት እንዳሳየ ለራሱ የሰማዋል ፡፡

ይህ ካልሆነ ግን... ልቡን ለተውሂድ ያጠራ ቢሆንማ፤ ሌላን ነገር ሁሉ ባስረሳው ነበር፡፡ አላህ እርሱን ይጠብቀዉ፣ ከእርሱም መጥፎ ነገርን ይከላከልለት ነበር። አላህ ከአማኞች ላይ መጥፎ ነገር ይከላከላል፤ እዉነተኛ አማኝ ከሆነ አላህ እንደሚከላከልለት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በእምነቱ ጥንካሬ ልክ የአላህን መከታ ያገኛል፡፡ እምነቱ የተሟላ ከሆነ ሙሉ የሆነ መከታ ከአላህ ያገኛል፡፡ የተቀላቀለ ከሆነም እንደዛው ይቀላቀልለታል፡፡ አልፎ አልፎም ከሆነ አላህም አልፎ አልፎ መከታ ይሆነዋል፡፡

كما قال بعض السلف "من أقبل على الله بكليته أقبل الله عليه جملة ومن أعرض عن الله بكليته أعرض الله عنه جملة ومن كان مرة ومرة فالله له مرة ومرة" .

ከቀደምቶቹ አንዱ እንዳለው፡- “ወደ አላህ በሁለመናው የዞረ የሆነ አላህ ሙሉ በሙሉ ወደ እርሱ ይዞራል፡፡ በሁለመናው አላህን የዘነጋ ደግሞ አላህ ሙሉ በሙሉ ችላ ይለዋል፤ አልፎ አልፎ ዝንጉ ለሆነው ደግሞ አላህ አልፎ አልፎ ቸል ይሆነዋል፡፡”

የአላህን አንድነት ማረጋገጥ ታልቁ መጠበቂያ ምሽግ ነው። ወደ እርሱ የገባ ጥብቅ ይሆናል፡፡ ከቀደምቶቹ አንዱ እንዲህ ይላል፡- “አላህን የፈራ ሁሉም ነገር እርሱን ይፈራዋል። አላህን የማይፈራ ግን ሁሉንም ነገር እንዲፈራ ያደርገዋል”

فهذه عشرة أسباب يندفع بها شر الحاسد والعائن والساحر وليس له أنفع من التوجه إلى الله وإقباله عليه وتوكله عليه وثقته به وأن لا يخاف معه غيره بل يكون خوفه منه وحده ولا يرجوا سواه بل يرجوه وحده فلا يعلق قلبه بغيره ولا يستغيث بسواه ولا يرجو إلا إياه ومتى علق قلبه بغيره ورجاه وخافه وكل إليه وخذل من جهته فمن خاف شيئا غير الله سُلط عليه ومن رجا شيئا سوى الله خذل من جهته وحرم خيره هذه سنة الله في خلقه ( ولن تجد لسنة الله تبديلا) الأحزاب 62 .

እነዚህ "አስር" መንገዶች የምቀኛ ተንኮልን፤ የሰው አይንን እንዲሁም የደጋሚን ጉዳት የምንከላከልባቸው መንገዶች ሲሆኑ፤ ወደ አላህ እንደመዞረ፣ በእርሱ እንደ መመካትና እንደ መተማመን ጠቃሚ የሆነ መንገድ የለም። ይኸውም፤ ፍራቻን ለአላህ ብቻ በማድረግ ከእርሱ ጋር ሌላን አካል አለመፍራት፤ እርሱን ብቻ በመከጀል ከእርሱ ሌላ ከማንም አለመፈለግ ነው። ልብን ከእርሱ ውጪ ባለ ነገር አለማንጠልጠል፣ከአላህ ዉጪ ከማንም እገዛን አለመለመን ናቸው። ከእርሱ ውጪ ባለ ነገር ልቡን ያንጠለጠለ፣ የከጀለና የፈራ ወደዛው ወደፈራው አካል ይተዋል፡፡ በርሱም በኩል ይዋረዳል፤ ከአላህ ውጪ ያለን አካል የፈራ በእርሱ ላይ ይሾምበታል፡፡ ከአላህ ሌላን የከጀለ በእርሱ በራሱ እርዳታን ይነፈጋል፡፡ ከጥሩ ነገሩም ይታገዳል። ይህ አላህ በፍጥረታቱ ላይ የጻፈው የማይለወጥ መንገዱ ነው፡፡
( ولن تجد لسنة الله تبديلا) الأحزاب 62
“የአላህን መንገድ ማንም ሊለውጠው አይችልም”፡፡ አል አህዛብ 62

አል ኢማም ኢብኑልቀይምን አላህ ይማራቸው። ስራቸውንም ይቀበላቸው። ወንድም እህቶች ሁሉ ተውሂድን በመማርና በአላህ ላይ ያላቸውን መመካት (ተወኩል) በማጠናከር ከሲህር ጉዳቶች እራሳቸውን ሊከላከሉ ይገባል። በተለይም በሸይኽ ሙሀመድ ቢን አብዱልወሀብ የተዘጋጀው #ኪታቡ_ተውሂድ የሽርክ መንገዶችን ግልፅ አድርጎ በማሳየትና የጥንቃቄ መስመሮችን በማመላከት ለችግሩ ፍቱን መድሀኒትነቱን አስመስክሯል። እባክዎን ጊዜ ሳይወስዱ ተውሂድን መማር ይጀምሩ።

አላህ ሁሉን አዋቂ ነው

ወንድማችሁ አቡ ጁነይድ 1432

© ሺፋእ
🔊የሙሐደራ ግብዣ 📀

ርዕስ ፦ ሲህር ምንድን ነው?

🎙 በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

ርዝመት፦ 16:03 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው (64kbps)
7.44 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚ ትምህርት!
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
🔊የሙሐደራ ግብዣ 📀

ርዕስ ፦ ሲህር የመስራት ሸሪዓዊ ብይን!

🎙 በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

ርዝመት፦ 25:14 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው (64kbps)
11.6 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚ ትምህርት!
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

📲 #ነሲሀ_ሙሐደራ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
🔊የሙሐደራ ግብዣ 📀

ርዕስ ፦ የድግምተኛ ሰው ቅጣት እና የሲሕር ጉዳት!

🎙 በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

ርዝመት፦ 10:50 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው (64kbps)
5.06 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚ ትምህርት!
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

📲 #ነሲሀ_ሙሐደራ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
🔊የሙሐደራ ግብዣ 📀

ርዕስ ፦ የድግምት መድሐኒት!

🎙 በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

ርዝመት፦ 18:25 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው (64kbps)
8.54 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚ ትምህርት!
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

📲 #ነሲሀ_ሙሐደራ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
🔊የሙሐደራ ግብዣ 📀

ርዕስ ፦ የድግምተኛ ምልክቶች!

🎙 በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

ርዝመት፦ 8:32 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው (64kbps)
4.01 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚ ትምህርት!
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

📲 #ነሲሀ_ሙሐደራ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
ጥያቄ፦ጂኖች አጋንንት በሰዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላሉን? ከነሱ የምንጠበቅበት መንገድስ ምንድነው?

መልስ፦ ጂኖች እስከመግደል ድረስ በሰዎች ላይ የተለያዩ አደጋዎችን እንደሚያደርሱ ጥርጥር የለውም። ድንጋይ ሊወረውሩበት ይችላሉ። ሊያስፈራሩት ይችላሉ። ሌሎች ችግሮችንም ሊያደርሱበት እንደሚችሉ በሀዲስም በተጨባጭ ተረጋግጧል። ነቢዩ (‏ﷺ) በአንድ ዘመቻ ላይ እያሉ (በኽንደቅ ዘመቻ ይመስለኛል) ለአንድ ሰሃባቸው ወደ ሚስቱ እንዲሄድ ፈቀዱለት። ወጣትና ሙሽራ ነበርና። እቤቱ ሲደርስ ሚስቱ ደጃፍ ላይ ቆማ ነበር። ደጃፍ ላይ በመቆሟ ተቆጣት። ግባና ታያለህ አለችው። ወደ ውስጥ ሲገባ እባብ ተጠቅልሎ ፍራሹ ላይ ተቀምጧል። ጦር በእጁ ይዞ ነበርና በጦሩ ወጋው። እባቡ ሞተ። ወዲያው ሰውየውም ሞተ። ማን ቀድሞ እንደሞተ እባቡ ወይስ ሰውየው አይታወቅም። ጉዳዩ ለነቢዩ (‏ﷺ) ሲነገራቸው አብተርና ዙጡፈተይን የተባሉ እባቦች ሲቀሩ በቤት ውስጥ የሚቀመጡ ጂንናን (የጂን እባቦች) እንዳይገደሉ ከለከሉ። [ቡኻሪ]

ጂኖች በሰዎች ላይ ድንበር እንደሚያልፉና አደጋ እንደሚያደርሱባቸው ይህ ማስረጃ ይሆናል። ተጨባጩ ሁኔታም ይህንኑ ያረጋግጣል። ሰው ወና ወደ ሆነ ቦታ ሄዶ ምንም ሰው ሳይኖር ድንጋይ እንደሚወረወርበት በሰፊው ይነገራል። እሱን የሚያስፈራራ ድምፅና ኳኳታም ይሰማል። እንደዚሁም ጂን ወደ ሰው አካልም ይገባል። አንድም አፍቅሮት ወይም ደግሞ ሊያሰቃየው ወይም በሌላ ምክንያት።

የሚከተለው የአላህ ቃል ይህንኑ ያመለክታል፦
الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسَِّ
“እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ነክቶት የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጅ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡”
[አል-በቀራህ - 275]

ወደ ሰው አካል የገባው ጂን ከሰውየው ውስጥ ይናገራል። ሰውየው ላይ ቁርአን የሚቀራበትን ሰው ያናግራል። ቁርአን የሚቀራው ሰው ጂኑ ወደ ሰውየው እንዳይመለስም ቃል ያስገባዋል። እነዚህ ሁኔታዎች በሰዎች ዘንድ በስፋት ታውቀዋል። ስለዚህ እንደ አየተል ኩርሲ ያሉና በሐዲስ የተዘገቡ ዚክሮችን በመቅራት ሰው ከጂን ክፋት ሊጠበቅ ይችላል። አየተልኩርሲን በማታ የቀራን ሰው አላህ ጠባቂ ያደርግለታል። እስከሚነጋ ድረስም ሸይጣን አይቀርበውም አላህ ይጠብቀን።

[ሸይኽ መሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ]

http://www.facebook.com/nosihr
2025/07/13 12:03:40
Back to Top
HTML Embed Code: