Telegram Web Link
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የትራምፕ የምክር ቤት ንግግር በግራ ዘመም የእስራኤል ፓርላማ አባል መስተጓጎል ገጥሞት ነበር ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ብዙም ሳይቆይ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ትራምፕ ለእስራኤል ፓርላማ ባደረጉት ንግግር የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 በመካከለኛው ምስራቅ የሽብርና የሞት ዘመን አብቅቷል፣ ቀጣናውም “አዲስና ታሪካዊ ዘመን” እያየ ነው።

🟠 ያለ ልዩ ተደራዳሪው ዊትኮፍ፤ “ዓለም ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ሊገጥማት ይችል ነበር።”

🟠 ዊትኮፍ ሞስኮን ከጎበኘ በኋላ ከፑቲን ጋር “ብዙ አስደሳች ነገሮችን” እንደተወያየ ሪፖርት አድርጓል።

🟠 በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ከማምጣት የዩክሬንን ግጭት መፍታት ቀላል ነው።

🟠 ራሳቸውን ተፈጥሯዊ ሰላም ፈጣሪ ሲሉ በመግለፅ፤ ጦርነቶችን በማስቆም እንደሚሳካላቸው አንስተዋል።

🟠 አሜሪካ ጦርነቶችን ለመጀመር ፍላጎት የላትም፤ ነገር ግን አስፈላጊ ከሆነ “ማንም አሸንፎ በማያውቀው ልክ” ታሸንፋለች።

🟠 የጋዛ ግጭት መቆም፤ “የፍልስጤማውያን የረዥም ጊዜ ቅዠት” እንዲያበቃ አድርጓል።

🟠 የኢራን የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋማት ሳይወድሙ የጋዛ የሰላም ስምምነት እውን አይሆንም ነበር፡፡

🟠 ኢራን ከአሜሪካ ጋር “ስምምነት ላይ በመድረስ” ግንኙነቷን መደበኛ ለማድረግ ፈቃደኛነት እያሳየች ነው።

🟠 ከጋዛ ስምምነት በኋላ በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ ትኩረት ለማድረግ አቅደዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🙏109😁7👍2👏1
🇪🇹 ኢትዮጵያዊቷ ሃዊ ፈይሳ በታሪክ አምስተኛዋ ፈጣን ሴት አትሌት መሆን ቻለች

የ2025 የቺካጎ ማራቶን የሴቶች ውድድርን በአስደናቂ ብቃት 2:14:56 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የምንግዜም አምስተኛዋ ፈጣን ሴት ሯጭ በመሆን አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሃዊ ውድድሩን ተቆጣጥራ የመራችበት መንገድ፣ ከ30 ኪሎ ሜትር በኋላ በብቸኘነትና በበለጠ ፍጥነት መምራቷ ርቀቱን ከጨረሱ ሴቶች ሁሉ ፈጣኗ እንድትሆን አድርጓታል።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:17:18 በመግባት 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በወንዶች ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አትሌት ሁሰዲን መሀመድ እና አትሌት ሰይፉ ቱራ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃን በቅደም ተከተል ይዘዋል። ኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ በ2:02:23 ውድድሩን አሸንፏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍119😁1
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በአልሻርም ኤል-ሼክህ የሰላም ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት ልዑካንን እየተቀበሉ ይገኛሉ

ዶናልድ ትራምፕና የግብፁ አቻቸው በጋራ ባዘጋጁት የጋዛ የሰላም ጉባዔ ላይ ከ20 በላይ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ልዑካን ይሳተፋሉ፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የካሜሩንን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ በኮትዲቯር አቢጃን በሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ውጥረት ተቀሰቀሰ

የምርጫ ድምጽ ቆጠራውን እንዳይመለከቱ ተከልክለናል ያሉ በርካታ የዳያስፖራ አባላት ቁጣ በተቀላቀለ ጩኸት ግልጸኝነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል፡፡

📍ኮትዲቯር

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ማመን መጀመር አለብን - የዘርፉ ባለሙያ

የአፍሪካ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቁልፍ ተግዳሮት የክህሎት ክፍተት ሳይሆን፤ ዕድሎችን የማስፋት ውስንነት መሆኑን የኮንቬክስ ቴክኖሎጂስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኖርማን ኦንደጎ ይናገራሉ።

📌 ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አኅጉሪቱ ለተቀረው የዓለም ማሻገር የምትችላቸው በርካታ የፈጠራ ውጤቶች ባለቤት መሆኗን አንስተዋል።

💬 "ለምሳሌ አንደ ኤም-ፔሳ እና ቴሌብር ያሉ ፈጠራዎችን ተመልከት። በትራንስፖርት ዘርፉም ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ራይድ ያሉ ከተቀረው የዓለም ክፍል ጋር የሚስተካከሉ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አሉ" ብለዋል።


ሁሉን አቀፍ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ሁነት የሆነው ''እንቆጳ ጉባኤ'' ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች የተፈቱ ዘመዶቻቸውን እየተቀበሉ ነው በራማላህ ፍልስጤም የደስታ የአደባባይ አቀባበሎች በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ታይተዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🇵🇸 የደስታ እንባዎች፣ የናፍቆት እቅፎች፣ ዳግም ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት ጥልቅ ስሜቶች

ከረጅም ጊዜ ጥበቃ በኋላ በእስራኤል ተይዘው የነበሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲገናኙ ያለውን ድባብ የሚያሳዩ ተጨማሪ ምሥሎች፡፡

በእስራኤል-ሃማስ የልውውጥ ስምምነት መሠረት፤ 1 ሺህ 986 ፍልስጤማውያን እስረኞች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ሲል የእስራኤል እስር ቤት አገልግሎት አስታውቋል።

ከፍልስጤም ራማላህ፤ በስፑትኒክ የተወሰዱ ምሥሎች

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍7🥰3👎21
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌍 ለአኅጉሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠናን ማስፋት ቁልፍ ጉዳይ ነው - የዘርፉ ምሑር

📌 የአፍሪካን የተፈጥሮ ሐብት ወደ ልማት ለመቀየር የወጣቶችን የሙያ ክህሎት ማሳደግ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የናሚቢያ የሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክተር ዳሊያ መዊያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"በዘርፉ ያሉንን አቅሞች ለይተን ማወቅ ይኖርብናል። የተፈጥሮ ሐብታችንን ለልማታችን ለማዋልም ቴክኖሎጂን እና ፈጠራን የሚያልቁ የሰው ኃይል ሥልጠናዎችን ማስፋት የግድ ነው" ብለዋል።


ከጥቅምት 3 እስከ 7 የሚካሄደው የአፍሪካ የክህሎት ሳምንት ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍1
ግብፅ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሊሻን ለዶናልድ ትራምፕ ልታበረክት ነው

ሽልማቱ ትራምፕ የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ባደረጉት ወሳኝ ሚና እና ለሰላም ጥረቶችና ግጭት አፈታት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት የሚበረከትላቸው እንደሆነ የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ትራምፕ በጥቅምት ወር መጀመሪያ እስራኤል እና የፍልስጤም ቡድን ሃማስ በጋዛ ሰርጥ ያለውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ዕቅዱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

በሌላ በኩል የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳቅ ሄርዞግ ለትራምፕ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሲቪል ክብር፤ የፕሬዝዳንታዊ የክብር ሜዳሊያ፤ ለመሸለም መወሰናቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁29👏72👻2
2025/10/22 21:04:04
Back to Top
HTML Embed Code: