Telegram Web Link
🇿🇦🇲🇦 ኬፕ ታውን እና ማራኬሽ በዓለም 20 ደስተኛ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

ታይም አውት መጽሔት 18ሺህ የከተማ ነዋሪዎች ላይ ባደረገው ጥናት ተመስርቶ ባወጣው ደረጃ ኬፕ ታውን ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ ማራኬሽ ደግሞ 15ኛ ላይ መቀመጥ ችላለች።

የደቡብ አፍሪካ እና የሞሮኮ ከተሞች በዚህ ቀዳሚ 20 ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ጎልተው የወጡባቸው መስፈርቶች፦

🟠 የጉርበትና ስሜት፣
🟠 የአረንጓዴ ቦታዎች፣
🟠 የጥበብ እና የባሕል ተደራሽነት፣
🟠 የአካባቢ ውበት፣
🟠 የሌሊት ህይወት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የጉዞ ቀላልነት፣
🟠 ተመጣጣኝ ዋጋ፣
🟠 የኑሮ ጥራት።

የደስታ መጠኑ ከተማዋ ነዋሪዎቿን ደስተኛ እንደምታደርግ፣ አስደሳች የዕለት ተዕለት ልምዶችን እንደምትሰጥ እና የደስታ ስሜት በቅርቡ መጨመሩን በመገምገም በአምስት መግለጫዎች መሠረት የተለካ ነው።

የደቡብ አፍሪካዋ የባሕር ዳርቻ ከተማ
97 በመቶ ነዋሪዎች በከተማቸው ደስተኛ እንደሆኑ ሲናገሩ፤ አቡ ዳቢ በ99 በመቶ የነዋሪዎች እርካታ የቀዳሚነት ሥፍራውን ይዛለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
18👍3
ፑቲን ዛሬ ከሶሪያ ፕሬዝዳንት አል-ሻራ ጋር ይገናኛሉ

መሪዎቹ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በሰብዓዊ መስኮች የሩሲያ እና የሶሪያን ግንኙነት ስለማጠናከር እንደሚወያዩ እና ወቅታዊ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮችን እንደሚገመግሙ ይጠበቃል፡፡

✍️ ስለ ሶሪያው ፕሬዝዳንት የሚታወቁ ጉዳዮች፦

ቀደም ሲል አቡ መሀመድ አል-ጁላኒ በመባል የሚታወቁት አህመድ አል-ሻራ፤ በ2024 መጨረሻ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ መንግሥት መወደቅን ተከትሎ ከጥር ወር ጀምሮ የሶሪያ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ይገኛል።

በ1982 በሪያድ የተወለዱት አል-ሻራ፤ ወላጆቻቸው ከጎላን ኮረብታ የመጡ ሶሪያውያን ናቸው። አባታቸው ሁሴን አሊ አል-ሻራ በሳዑዲ አረቢያ የአረብ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ እና አስተማሪ ነበሩ።

በብሄርተኝነት መንፈስ ያደጉ ቢሆንም በጂሃዳዊ አስተሳሰብ ተማርከው በ2003 የአሜሪካን ኃይሎች ለመዋጋት በኢራቅ ከሚገኘው አል-ቃይዳ* ጋር በአንድ ተሰለፉ። ከ2006 እስከ 2011 በካምፕ ቡካ እስር ላይ ቆይተውም ነበር።

በ2016 አል-ሻራ ከአል-ቃይዳ* ጋር ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠው ሃያት ታህሪር አል-ሻምን መስርተዋል፤ በኋላም በሹራ እና በእስላማዊ ፍትሕ መርሆዎች ላይ የተመሠረተውን "ሳልቬሽን መንግሥት" በኢድሊብ አቋቋሙ።

በታህሳስ 2017 የሶሪያ ተቃዋሚ ቡድኖችን ፈጣን ጥቃት በመምራት ደማስቆን እንዲቆጣጠሩ አስችለዋቸዋል።

ጥር 21 ቀን አህመድ አል-ሻራ በተስፋፋው የትጥቅ ትግል ተቃዋሚ ቡድኖች ስብሰባ ላይ የሶሪያ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። በዚያው ቀን ሀገሪቱን ከ60 ዓመታት በላይ ሲገዛ የነበረው የባዝ ፓርቲ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)፣ ጦር ሠራዊቱ እና ሁሉም የጸጥታ ኃይሎች ፈረሱ።

መጋቢት 4 ቀን አል-ሻራ የአምስት ዓመት የሽግግር ወቅት የሚያቋቁም ሕገ መንግስታዊ አዋጅን ፈርመው አጽቀዋል።

አል-ሻራ የመንግሥት መሪነት ሥራውን ተረክበው በደማስቆ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ያካሄዱ ሲሆን ቱርክን እና ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ በርካታ የቀጣናው አጋር ሀገራትን ጎብኝተዋል። በኋላም ወደ ኒውዮርክ በመጓዝ ከ1967 ወዲህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ንግግር ያደረጉ የመጀመሪያው የሶሪያ ፕሬዝዳንት መሆን ችለዋል።

ታይም መጽሔት አህመድ አል-ሻራን በ2025 በዓለም 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካቷቸዋል።

ቀደም ሲል መስከረም 2 ቀን አል-ሻራ "ሶሪያ እና ሩሲያ ሊጠበቁ የሚገባቸው ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነቶች አሏቸው" ሲሉ ተናግረዋል። "የሶሪያ እና ሩሲያን የተቀራረበ ግንኙነት ወርሰናል፤ እናም ልንጠብቃቸው ይገባል" ያሉት አል-ሻራ፤ ሩሲያ "ወሳኝ የዓለም ኃይል" እና የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አባል መሆኗን አክለው ገልፀዋል።

* በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍6👎1
⚡️🇷🇺 እንዳያመልጥዎ፦ የ2025 የሩሲያ ኢነርጂ ሳምንት ዛሬ በሞስኮ መካሄድ ይጀመራል

የሩሲያ ኢነርጂ ሳምንት ዓለም አቀፍ መድረክ ከጥቅምት 5-7 በሞስኮ የሚካሄድ ሲሆን ስለ ዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የኢነርጂ ኢንዱስትሪ የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት ከዓለም ዐቢይ መድረኮች አንዱ ነው።

የውጭ ተሳታፊዎች፦


🇰🇵 ኪም ዩ ኢል፡ የሰሜን ኮሪያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ሚኒስትር፣
🇭🇺 ፒተር ሲያሪቶ፡ የሀንጋሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣
🇦🇫 አብዱል ላፍ ማንሱር፡ የአፍጋኒስታን የኢነርጂ እና የውሃ ሚኒስትር፣
🇻🇪 ዴልሲ ሮድሪጌዝ፡ የቬንዙዌላ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፔትሮሊየም ሚኒስትር በበየነ መረብ ይሳተፋሉ።

🌍 የኢነርጂ ሳምንቱ ከ70 በላይ ሁነቶች የሚስተናገዱበት ሲሆን በባለብዙ ወገን የኢነርጂ ትብብር እንዲሁም በባለብዙ ዋልታ ዓለም የሩሲያ የነዳጅ እና የኢነርጂ ዘርፍ ላይ ያተኩራል።

📌 ስፑትኒክ የ2025 ኢነርጂ ሳምንት ይፋዊ የመረጃ አጋር በመሆን ልዩ ዜናዎችን፣ ምልከታዎችን እና ቃለመጠይቆችን በቀጥታ ከመድረኩ ወደ እናንተ ያደርሳል። ይጠብቁን!

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍75
የማዳጋስካር ማዕከላዊ መንግሥት በፈረንሳይ ሥር ነው - የሀገሪቱ ባለሥልጣን

"በማዳጋስካር ውስጥ ብዙ የፈረንሳይ ጥቅሞች አሉ። 70 በመቶ የሚሆነው የማዳጋስካር ኢኮኖሚ በፈረንሣይ ተይዟል" ሲሉ የሀገሪቱ ገለልተኛ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ተቀዳሚ ጄኔራል ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል።


ፕሬዝዳንት ራጆሊና በፈረንሳይ አውሮፕላን ሀገሪቱን ለቀው ስለመውጣታቸው የሚናፈሱ ወሬዎችን አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጡ፤ በፓሪስ እይታ "የፈረንሳይ ጣልቃ ገብነት ዋነኛ ግብ ደቀመዝሙሯን ለመጠበቅ ነው" ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

🌍 የአፍሪካ ኅብረት አህጉራዊ ሽምግልናን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የሰጠው መግለጫ፤ ማዳጋስካር የድርጅቱ አባል ከመሆኗ አኳያ ከ "ግዴታነት" የዘለለ አይደለም ብለዋል።

ያም ሆነ ይህ ወደ “ብሔራዊ ውይይት” ከማቅናት በፊት “ማስታረቅ” ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3😡2👍1🔥1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
⚡️🇷🇺 እንዳያመልጥዎ፦ የ2025 የሩሲያ ኢነርጂ ሳምንት ዛሬ በሞስኮ መካሄድ ይጀመራል የሩሲያ ኢነርጂ ሳምንት ዓለም አቀፍ መድረክ ከጥቅምት 5-7 በሞስኮ የሚካሄድ ሲሆን ስለ ዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የኢነርጂ ኢንዱስትሪ የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት ከዓለም ዐቢይ መድረኮች አንዱ ነው። የውጭ ተሳታፊዎች፦ 🇰🇵 ኪም ዩ ኢል፡ የሰሜን ኮሪያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ሚኒስትር፣ 🇭🇺 ፒተር ሲያሪቶ፡ የሀንጋሪ…
የሩሲያ ኢነርጂ ሳምንት የመጀመሪያ ምሥሎች በስፑትኒክ ዘጋቢ

ዝግጅቱ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ባህሬንን ጨምሮ 85 ሀገራትን አንድ ላይ ያሰባስባል።

👉 ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ በሚካሄደውና ከዓለማችን ግንባር ቀደም የኃይል መድረኮች አንዱ በሆነው በዚህ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏64
የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት 2025 በአዲስ አበባ ተከፈተ

ዝግጅቱ "በአፍሪካ አካታች እና ዘላቂ ትራንስፖርት ማፋጠን" በሚል መሪ ቃል በፖሊሲ፣ በፋይናንስ እና በአህጉሪቱ ዜሮ ልቀት ትራንስፖርት ትግበራ ዙሪያ ያተኩራል።

የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ አሊያንስ ዋና ዳይሬክተር ዋረን ኦንዳንጄ ባደረጉት ንግግር የአህጉሪቱን የነዳጅ ጥገኝነት በማንሳት፤ “ኢ-ሞቢሊቲ አፍሪካ ያሏትን ታዳሽ የኃይል ምንጮች ለልማት ጥረቶቿ እንድትጠቀም እድል ይፈጥራል” ብለዋል።

“የአዲስ አበባ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ውጥኖች፤ ራዕይ ወደ ተግባር ሲቀየር የሚቻለውን ያሳየናል፤ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚቻል የሚያስገነዝብ ነው” ያሉት ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የአዲስ አበባ የግንኙነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርግሬት ኦዱክ ናቸው።


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍73
አራት የአፍሪካ ሀገራት ከጥር 1 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን በአባልነት እንዲቀላቀሉ ተመረጡ

የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የሶስት ዓመት የሥራ ዘመን እንዲያገለግሉ የመረጣቸው ሀገራት፦

አንጎላ፣
ግብፅ፣
ሞሪሺየስ፣
ደቡብ አፍሪካ፣
ቺሊ፣
ኢኳዶር፣
ኢስቶኒያ፣
ህንድ፣
ኢራቅ፣
ጣሊያን፣
ፓኪስታን፣
ስሎቬኒያ፣
ዩናይትድ ኪንግደም፣
ቬትናም።

ጄኔቫ መቀመጫውን ያደረገውና 47 አባላት ያሉት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብቶችን የማስተዋውቅ እና የመጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ከአባላቱ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት በየዓመቱ በተከፋፈሉ የሶስት ዓመት የሥራ ዘመኖች ይተካካሉ።

👉የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መቀመጫዎች ጂኦግራፊያዊ ውክልናን ለማረጋገጥ በክልላዊ ቡድኖች መሠረት የሚመደቡ ሲሆን አፍሪካ እና እስያ-ፓሲፊክ እያንዳንዳቸው 13፣ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ስምንት፣ ምዕራብ አውሮፓ እና ሌሎች ግዛቶች ሰባት፣ ምስራቅ አውሮፓ ደግሞ ስድስት ወንበሮች ይኖራቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7👎2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪኖች በጋዛ ሰርጥ ድንበር ደረሱ

በእስራኤል ቁጥጥር ስር ባሉ ማቋረጫዎች ለመግባት ፍቃድ እየተጠባበቁ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍94🙏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚔️ የኔቶ ኃላፊ ለዩክሬን አዲስ የጦር መሳሪያ ሊቀርብ እንደሚችል ጠቆሙ

ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩተ የህብረቱ መከላከያ ሚኒስትሮች ዛሬ የሚያደርጉትን ስብሰባ ተከትሎ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ጨምሮ ወደ ዩክሬን ስለሚላኩ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች ሊገለፅ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

💬 “ምናልባት በሁለቱ የጀርመን እና የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስትሮች መሪነት ለዩክሬን ድጋፍን ስለማሳደግ ልንወያይ እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።


በነሀሴ ወር በጀመረው እና በምዕራባውያን አጋሮች በገንዘብ በሚደገፈው አዲስ መርሃ-ግብር ስር ዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ የገዳይ እና ኢ-ገዳይ መሣሪያዎች ድጋፍ ለዩክሬን እንደምታቀርብ አንስተዋል፡፡ ከሰኔ ወር ጀምሮ 2 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ ተገዝቷል ያሉት የኔቶ ዋና ፀሃፊ፤ ሌሎች ሀገራትም እንደሚቀላቀሉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

💬 "እነዚህ የአየር መከላከያ ስርዓቶች በተለይም የሲቪል ሕዝባቸው፣ ወሳኝ መሠረተ ልማታቸው በተቻለ መጠን የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ለዩክሬን አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ ሩተ ተናግረዋል፡፡


በኔቶ የአሜሪካ አምባሳደር ማቲው ዊትከር በአውሮፓ ሀገራት ፐርል ፕሮግራም አማካኝነት ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ግዢን ለማሳደግ ዛሬ በሚደረጉት ስብሰባ "ትልቅ መግለጫ" ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል።

ተነሳሽነቱ የአውሮፓ የገንዘብ ድጋፍ ለዩክሬን መሣሪያ ለሚያቀርቡ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ አምራቾች በቀጥታ እንዲፈስ ያስችላል።

ሩሲያ እነዚህ የጦር መሣሪያዎች ግጭቱን የሚያራዝሙ እና ኔቶን ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሚያደርጉ ስትገልጽ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሁሉም የጦር መሣሪያዎች ሕጋዊ ኢላማዎች እንደሚሆኑ አስጠንቅቀዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤬73👎3
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ መተግበሪያን አሁን በአንድሮይድ ማውረድ ይችላሉ።

ለአጠቃቀም በጣም ቀላል በሆነው መተግበሪያ የሚከተሉትን ያገኛሉ፦

🟠ቀላል አሰሳ
🟠ትኩስ የኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች
🟠ልዩ ቃለመጠይቆች
🟠ምስላዊ መረጃዎች እና ቪዲዮዎች
🟠የወደዱትን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ማጋራት

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡-

👉 APK ፋይል ሊንክ

👉
Galaxy Store

👉
GetApps

👉 AppGallery

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia

#social
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6
ኪዬቭ ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን እንደምታገኝ ተስፋ በማድረግ በሩሲያ ላይ ለምትፈፅመው የሽብር ጥቃት በግልፅ እየተዘጋጀች ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናገሩ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍721👎1
❗️በሶሪያ የሚገኙ የሩሲያ ጦር ሠፈሮች ጉዳይ የፑቲን እና አል-ሻራ የመወያያ አጀንዳ ነው - ክሬምሊን

"ይህ ቀን ለሩሲያ-ሶሪያ ግንኙነት በጣም ወሳኝ ቀን ነው" ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍75
2025/10/23 17:32:11
Back to Top
HTML Embed Code: