ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ሩሲያ የሶሪያን የመሠረተ ልማት ዳግም ግንባታ ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቫክ ተናገሩ ባለሥልጣኑ ይህን ያሉት ፑቲን እና የሶሪያ ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው፡፡ በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የቀድሞ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሮማኖ ፕሮዲ እና ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ የመካከለኛው ምስራቅ አማካሪ የነበሩት አምባሳደር ማርኮ ካርኔሎስ እንዳሉት፣ አዲሱ የሶሪያ መንግሥት ከሩሲያ ጋር ወዳጃዊ ግንኙነት እና ትብብር ለመፍጠር ያደረገው ውሳኔ ተግባራዊ እርምጃ ነው።
የሶሪያ አመራር “ከምዕራባውያን ኃይሎች ጋር ከመጠን በላይ ከመለጠፍ” ይልቅ “በተቻለ መጠን እጆቹን ነጻ እንዲሆኑ” ሊመርጥ ይችላል።
💬 “አሜሪካ እና እስራኤል በሩሲያ ወታደራዊ ሰፈሮች ምክንያት በዚያ አካባቢ በቸልተኝነት ከመስራታቸው በፊት ሁለት ጊዜ ሊያስቡ ይችላሉ” ሲሉ ካርኔሎስ ለስፑትኒክ አብራርተዋል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6❤5🤣2🙏1
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በሚሊዮኖች የሚገመት ጉዳት አስከትሏል
መንስኤው ያልታወቀው አደጋ በሆስፒታሉ ዋና የመድኃኒት መጋዝን ውስጥ የነበሩ የሕክምና መሣርያዎችንና ግብዓቶችን ማውደሙን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ከዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተገኙ ምስሎች
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
መንስኤው ያልታወቀው አደጋ በሆስፒታሉ ዋና የመድኃኒት መጋዝን ውስጥ የነበሩ የሕክምና መሣርያዎችንና ግብዓቶችን ማውደሙን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ከዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተገኙ ምስሎች
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏3😢3❤1🙏1
🇪🇹 🇸🇩 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን ዳግም በረራ መጀመሩን አስታወቀ
🛫 አየር መንገዱ ከትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ጀምሮ በየቀኑ ወደ ፖርት ሱዳን (PZU) እንደሚበር ይፋ አድርጓል፡፡
ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ጀምሮ ደግሞ ዕለታዊ በረራውን በእጥፍ እንደሚያሳድግ ገልጿል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🛫 አየር መንገዱ ከትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ጀምሮ በየቀኑ ወደ ፖርት ሱዳን (PZU) እንደሚበር ይፋ አድርጓል፡፡
ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ጀምሮ ደግሞ ዕለታዊ በረራውን በእጥፍ እንደሚያሳድግ ገልጿል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4❤1
ፑቲን በሩሲያ እና ቶጎ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነትን የሚያፀድቅ ሕግ ፈረሙ
ይህ አጋርነት፣ በመጋቢትና ሚያዝያ 2025 በሎሜ እና በኋላም በሞስኮ ፊርማዎች የታተመ ሲሆን፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው።
ስምምነቱ የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታል፦
🟠 የገንዘብ ድጋፍ ሂደቶች፣
🟠 የመረጃ ጥበቃ ሁኔታዎች እና እርምጃዎች፣
🟠 የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት፣
🟠 የዳኝነት ሥልጣን እና
🟠 የሕጋዊ ጥበቃ።
ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆየው ስምምነቱ፣ ሁለቱ አገራት የውስጥ አሰራራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ይህ አጋርነት፣ በመጋቢትና ሚያዝያ 2025 በሎሜ እና በኋላም በሞስኮ ፊርማዎች የታተመ ሲሆን፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው።
ስምምነቱ የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታል፦
ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆየው ስምምነቱ፣ ሁለቱ አገራት የውስጥ አሰራራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7❤2
ፑቲን በዛሬው የሩሲያ የኢነርጂ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ
🌐 ከ60 በላይ የንግድ ዝግጅቶችን ያካተተው ዓለም አቀፉ ስብሰባ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የኢነርጂ ኩባንያ መሪዎችን፣ ባለሙያዎችን እና የሳይንስ ማኅበረሰብ ተወካዮችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሞስኮ አገናኝቷል።
👉 በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሁነቱን ይከታተሉ!
በእንግሊዝኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🌐 ከ60 በላይ የንግድ ዝግጅቶችን ያካተተው ዓለም አቀፉ ስብሰባ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የኢነርጂ ኩባንያ መሪዎችን፣ ባለሙያዎችን እና የሳይንስ ማኅበረሰብ ተወካዮችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሞስኮ አገናኝቷል።
👉 በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሁነቱን ይከታተሉ!
በእንግሊዝኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤4👍3
🚨የእንግሊዝ እና የዩክሬን የስለላ አገልግሎቶች የቱርክ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ለማደናቀፍ እየተዘጋጁ ነው - የሩስያ ደህንነት አገልግሎት
በተጨማሪም የእንግሊዝ ጦር ኤስኤኤስ እና ኤምአይ6 አዛዦች በካስፒያን የማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ጥምር ድርጅቶች ላይ ተከታታይ የድሮን ጥቃቶችን ለማድረግ ማቀዳቸው ተዘግቧል።
የጥምር ድርጅቱ ባለድርሻዎች ከሩሲያ፣ ከካዛኪስታን እና ከአሜሪካ የተወጣጡ ኩባንያዎች መሆናቸውን ቦርትኒኮቭ አክለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
“እንግሊዞች ከዩክሬን የስለላ ድርጅት ጋር በመሆን በቱርክ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ላይ ብልሽት ለመፍጠር እየተዘጋጁ እንደሆነ መረጃ አለን" ሲሉ የፌደራል ደህንነት አገልግሎቱ ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የእንግሊዝ ጦር ኤስኤኤስ እና ኤምአይ6 አዛዦች በካስፒያን የማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ጥምር ድርጅቶች ላይ ተከታታይ የድሮን ጥቃቶችን ለማድረግ ማቀዳቸው ተዘግቧል።
የጥምር ድርጅቱ ባለድርሻዎች ከሩሲያ፣ ከካዛኪስታን እና ከአሜሪካ የተወጣጡ ኩባንያዎች መሆናቸውን ቦርትኒኮቭ አክለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤7👏2🤯1😈1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የማስፋት ቁርጠኝነት አብነት ማድረግ ይገባል - የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ጥምረት 📌 ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሥርዓት ለመሸጋገር መሠረተ ልማት ሥራ ላይ በትኩረት እየሠራች እንደምትገኝ የጥምረቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዋረን ኦንዳንጄ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። "የኢትዮ ቴሌኮምን የሕዝብ የመኪና መሙያ ማዕከላት ተመልክቻለሁ። በሥፍራዎቹ ቻርጅ ለማድረግ የተሰለፉ…
🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ50 - 120 ኪሜ ርቀት ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን እንደምትተክል አስታወቀች
🔌 በዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚተከሉት ጣቢያዎቹ በከተሞች መካከል የኤሌክትሪክ ጉዞን ለማሳለጥ ያለሙ መሆናቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።
🚘 በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ መሻገሩን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🔌 በዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚተከሉት ጣቢያዎቹ በከተሞች መካከል የኤሌክትሪክ ጉዞን ለማሳለጥ ያለሙ መሆናቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ሥሜ፣ መንግሥት በ2030 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን በመግለጽ፣ በዚህ ረገድ በመንግሥትና የግል አጋርነት የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አፅንኦት ሰጥተዋል።
🚘 በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ መሻገሩን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4😁4❤2🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“በእርግጥም አፍሪካውያን ሁለተኛ፣ ሦስተኛ ዕይታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አንድ ወገንን ብቻ ስታዳምጡ፣ ያ የተዛባ አመለካከት ይሆናል፤ ነገር ግን የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን እና የአንድን ክስተት የተለያዩ ትንታኔዎችን ስታዳምጡ፣ ስለሚፈጠረው ነገር ሰፋ ያለ ግንዛቤ ይኖራችኋል” ሲሉ የሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ዶ/ር ጂብሪል ኢብራሂም መሐመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ በአኅጉሪቱ ዕይታዎችን በማስፋት ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ አድናቆት እንዳለቸውም ገልፀዋል፡፡
“የስፑትኒክ ሥራ ግንዛቤያችንን እያበለጸገ፣ የአፍሪካ ህዝቦች የተለየ ዕይታ እንዲኖራቸው እየረዳ እንደሆነ እናምናለን።” ብለዋል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6❤5
🇪🇹🇷🇺 ኢትዮጵያ የሩሲያ-አፍሪካ ፎረምን የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ እያዋለችው መሆኑ ተገለፀ
ጥቅምት 5 እና 6 በሞስኮ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ፎረም እና ኤክስፖ ላይ አገሪቱ የኤክስፖርት ምርቶቿን፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎቿን እና የቱሪዝም መስህቦቿን ተደራሽነት ለማስፋት እያስተዋወቀች መሆኑን በሩስያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡
በሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የሚዘጋጀው ፎረም፣ በሎጂስቲክስና ባንኪንግ ላይ የሚደረገውን ዋነኛ የጋራ ስብሰባ ጨምሮ በርካታ የፓናል ውይይቶችን ያካትታል። ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎችም በመድረኩ ተገኝተዋል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ጥቅምት 5 እና 6 በሞስኮ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ፎረም እና ኤክስፖ ላይ አገሪቱ የኤክስፖርት ምርቶቿን፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎቿን እና የቱሪዝም መስህቦቿን ተደራሽነት ለማስፋት እያስተዋወቀች መሆኑን በሩስያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡
ኤምባሲው፣ "በኤክስፖው ላይ ከዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማት ጋር ለመገናኘት እና የአገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ለጉባኤው ተሳታፊዎችና ባለሀብቶች ለማስረዳት እየሠራ" መሆኑን ጠቁሟል።
በሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የሚዘጋጀው ፎረም፣ በሎጂስቲክስና ባንኪንግ ላይ የሚደረገውን ዋነኛ የጋራ ስብሰባ ጨምሮ በርካታ የፓናል ውይይቶችን ያካትታል። ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎችም በመድረኩ ተገኝተዋል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤5👍5