Telegram Web Link
❗️በዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተጎዱ የውጭ የኃይል አቅርቦት መስመሮችን የመጠገን ሥራ በአካባቢው የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ መጀመሩን ግሮሲ አስታወቁ

የዓለም አቀፉ የኑክሌር ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በኤክስ አካውነታቸው ላይ በሰጡት መግለጫ፣ "ከአራት ሳምንት መቋረጥ በኋላ የዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተጎዱትን የውጭ የኃይል መስመሮች የመጠገን ሥራ እንዲቀጥል በአካባቢው የተኩስ አቁም ቀጣናዎች ተቋቁመዋል" ብለዋል።


የውጭ ኃይልን ወደ ነበረበት መመለስ ለኒውክሌር ደህንነት ወሳኝ ነው ሲል ኤጀንሲው ገልጿል።

"ሁለቱም ወገኖች ውስብስብ የሆነውን የጥገና ዕቅድ ለማስፈጸም ከኤጀንሲው ጋር ገንቢ በሆነ መንገድ ተሳትፈዋል" ሲሉ ግሮሲ አክለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5🙏3
🇮🇷⚛️ ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ

🔊  የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2231 ጊዜው አልፏል፤ ይህም በኢራን ላይ ተጥለው የነበሩትን ሁሉንም የፀጥታው ምክር ቤት ገደቦች ያቋርጣል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አባስ አራግቺ "ኢራን የኒውክሌር መስፋፋት መከላከያ ስምምነት ፈራሚ እንደመሆኗ፣ በቀጥታ በስምምነቱ ስር መሠረት ባሉ መብቶቿና ግዴታዎቿ ብቻ ትገደዳለች" ብለዋል።

አክለውም "ይህም በኒውክሌር መርሃ ግብሯ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አለመኖሩን፤ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚደረግ ትብብርም በአጠቃላይ የጥበቃ ስምምነት ማዕቀፍ ውስጥና በኢራን ፓርላማ በቅርቡ በፀደቀው ሕግ መሠረት ብቻ መሆኑን ያጠቃልላል" ብለዋል።


👉 እ.ኤ.አ. በ2015 የፀደቀው የተመድ የፀጥታው ምክር-ቤት ውሳኔ 2231፣ የጋራ ሁሉን አቀፍ የድርጊት መርሃ ግብር የኒውክሌር ስምምነት በዛሬው ዕለት ከጥቅም ውጭ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7😁1
❗️የሩሲያ ኃይሎች በዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፑብሊክ የፕሌሽቼየቭካ መንደር ተቆጣጠሩ

👉 ከቅርብ ወራት ወዲህ የሩሲያ ጦር ኃይሎች በዶንባስ ክልል እና ባሻገር በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ መንደሮችን ተራ በተራ ነጻ እያወጣ በከፍተኛ ፍጥነት ወደፊት እየገሰገሰ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
10👍6👏2
ሩሲያ-አላስካ መተላለፊያ መስመር የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደ ነው ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ

ሩሲያን ከአላስካ የሚያገናኝመተላለፊያ (መሿለኪያ) መስመር ለመገንባት የሚያስችል የአዋጭነት ጥናት ከስድስት ወራት በፊት መጀመሩን የፕሬዝዳንት ፑቲን ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪቭ በኤክስ ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዲሚትሪቭ በተጨማሪም የሩሲያና የቻይና የባቡር ድልድይ ስኬትን አጉልተው አሳይተዋል፤ በዚህም የጭነት መስመሮችን ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ በማሳጠር እንደ ስኬታማ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ምሳሌነት አቅርበውታል።

የመጀመሪያው ምስል በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ነው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5
በአፍሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ ፈጠራ 'ታላቅ ዕድል' ነው ሲሉ ደቡብ አፍሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ

"አፍሪካ እጅግ ብዙ ታሪኮች አሏት። ማንነታችን ውስጥ ያሉትን ውስብስብ እና ድንቅ ታሪኮቻችንን የምንናገርበት ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ የ"ፍሪ ውመን ፊልምስ" ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ጁዲ ንዎከዲ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።


🎬🇷🇺 ንዎከዲ በሩሲያ እና በደቡብ አፍሪካ ፊልም ሰሪዎች መካከል ስላለው  'የእኔ አፍሪካ' የትብብር ፕሮጀክት ሲናገሩ፣ የሩሲያዊቷን ዳይሬክተር ኦልጋ አካቲየቫን  “ሩሲያውያን የሚወዷት፣ ዘመናዊና ወቅታዊ የሆነች አፍሪካን የማስተዋወቅ” ራዕይ አድንቀዋል።

"ከአፍሪካ ጋር ወደፊት " በተሰኘው የአፍሪካ የባህል እና ሲኒማ ቀናት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ጎን ለጎን በሁለቱ ቀጣናዎች መካከል እየጎለበተ የመጣውን የፈጠራ ትብብር አጉልተው አሳይተዋል።

"ሩሲያ-አፍሪካዊ እና አፍሪካ-ሩሲያዊ በሆኑ ታሪኮች ላይ በጋራ ፈጠራ እና በጋራ ስራ ላይ አብረን እንሰራለን። ይህ እኛ ልንመረምረው የሚገባ ታላቅ ዕድል ነው ብዬ አስባለሁ።"


☝🏽ንዎከዲ በተጨማሪም የትክክለኛ ውክልና አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል፦

"አፍሪካን በተመለከተ ያለውን ነገር ማረም እና በጥንቃቄ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው... ዓለም አፍሪካን እንደ ድሃ ወይም ሙሰኛ አድርጎ ማየት ይወዳል። ብዙ ማኅበረሰቦች ግን ተመሳሳይ ተግዳሮቶች አሏቸው።"


💫 ፍላጎት ላላቸው ፊልም ሰሪዎች ያላቸው መልዕክት አስመልክቶም፤

"ጥሩ ታሪኮችን እየፈለጋችሁ ከሆነ መገኘት ያለባችሁ አፍሪካ ውስጥ ነው" ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11
🇪🇹 አይኤምኤፍ በዚህ የ2025 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.2 በመቶ ያድጋል ሲል ተነበየ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ትንበያ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ከሚያድጉ ኢኮኖሚዎች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ የእድገት ትሩፋቶችን ለማስጠበቅ እና ማክሮ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማስቀጠል የአገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብን እና የዕዳ አስተዳደርን ማጠናከር እንደሚገባትም አሳስቧል፡፡

እነዚህ እርምጃዎች፣ የብድር ወጪን ለመቀነስ፣ ግልጽነትን ለማሻሻል እና ለአስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች በቂ የገንዘብ ድጋፍን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው።

ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ያቀረበቻቸው ምርቶች፣ ከውጭ የሚገኘው ዕርዳታ በመቀነሱና ዓለም አቀፍ የንግድ መስተጓጎል በመፈጠሩ ምክንያት የሚመጡትን አንዳንድ ጫናዎች ለማካካስ እገዛ ማድረጉንም ጨምሮ አመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁10🔥65👍4
🇪🇹 ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ተማሪዎች የምታቀርባቸው የነፃ ትምህርት ዕድሎች ቀጣናዊ ትስስርን ያጠናክራሉ ተባለ

በተለይም በሕክምና ዘርፍ ዕድሉን ያገኙ ከጎረቤት አገራት የመጡ ተማሪዎች  እንደገለጹት፤ በመውሰድ ላይ ያሉት ትምህርት እና ሥልጠና የየአገራቸውን የጤና ሥርዓት በማሻሻል ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

በስፔሻሊቲ እና በንዑስ-ስፔሻሊቲ የሕክምና የትምህርት ዕድሎችን ከሚጠቀሙ የጎረቤት አገራት ዶክተሮችን ውስጥ የሚከተልሉት አገራት ዜጎች ይጠቀሳሉ፦

🇸🇸 ደቡብ ሱዳን፣ 
🇸🇴 ሶማሊያ እና
🇷🇼 ሩዋንዳን ይጠቀሳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ430 በላይ የሚሆኑ የሕክምና ዶክተሮች በኢትዮጵያ በሚገኙ 19 የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ 105 የሚሆኑ የዕድሉ ተጠቃሚዎች መርሃ ግብሩን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍10😁92
#viral | ከሀንግዡ ወደ ሴኡል ሲበር በነበረ የኤር ቻይና አውሮፕላን ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

🔋 እሳቱ የተነሳው በአንድ ተሳፋሪ ሻንጣ ውስጥ በነበረ ሊቲየም ባትሪ ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል።

የአውሮፕላኑ ሠራተኞች እሳቱን በፍጥነት የተቆጣጠሩ ሲሆን አውሮፕላኑ ወደ ሻንጋይ ፑዶንግ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲዛወር ተደርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👏3🙏3
🇪🇹 የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ

ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያን የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መልክ ይጎድለዋል ሲሉ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

"ቀጥታ የውጭውን ዓለም የሥርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያውያን ሕይወት ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም፤ ልጆችን የማያሸጋግር፣ አካባቢውን የማይለውጥ፣ አካባቢውን ያልተገነዘበ ሥርዓተ ትምህርት ... ኢትዮጵያ አምጥተህ ስታስቀምጠው ግን አይገጣጠምም" ብለዋል።


የትምህርት አስተዳደር ባለሙያው አክለውም፣ የኢትዮጵያ ልጆች የራሳቸው የሆነ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሥነ ልቦና እና ባሕል ስላላቸው በሌላ አገር ዐውድ ውስጥ የተጻፈ ሥርዓተ ትምህርት አምጥቶ መጫን ልክ አለመሆኑን አስረድተዋል።

"ቋንቋ ትልቁ እና በግልጽ የሚታየው የግንኙነታችን መስመር ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ቋንቋ ስትወለድ ጀምሮ ያደክበት፣ የምታስብብበትና የምትናገረው ቋንቋ ተረስቶ በሌላ በባዕድ ቋንቋ መማር እና ማስተማራችን ሁሌም ይገርመኛል" በማለት ለአገር ውሰጥ ቋንቋ የተሰጠው ቦታ ማነሱን አስረድተዋል።


በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍19👏97💔1
2025/10/25 04:58:35
Back to Top
HTML Embed Code: